Ethiopian Addis Kidan Baptist Church Semen-Local

Ethiopian Addis Kidan Baptist Church Semen-Local Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Addis Kidan Baptist Church Semen-Local, Religious organisation, Addis Ababa, Addisu Gebysa/, , Kechena, Addis Ababa.

25/05/2026
02/05/2021
04/11/2018

በራስህ ፈርደሃል ?
ስለራሳችን ማንነት በሚገባ እያወቅን በጥፋታችን በራሳችን ላይ ለመፍረድ ድፍረቱ ያለን ስንቶቻችን ነን ?
ለዚህ ጥያቄ እውነተኛ ማሳያ የሚሆኑን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረው የተሰቀሉት ሁለቱ ክፉ አድራጊዎች ግራና - ቀኝ የተሰቀሉትን ስንመለከት አንደኛው በእራሱ ላይ ፈርዶ ጥፋቱን ኃጢያት ፥ በደሉን ሲያምን ፤ ሁለተኛው ግን በእራሱ ላይ መፍረድ አቅቶት ነፍሱ ከስጋው ልትለይ ጥቂት ደቂቃዎች ቀርተውት እንኳን ስለ ኃጢያቱ መፀፀት እና መናዘዝ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር ማሰብ አልፈለገም ።
ዛሬም የብዙዎቻችን ሕይወት ቢፈተሸ ለእግዚአብሔር አምላካችን የምንሰጠው ምላሸ በቃልም - በተግባርም ከዚህ የተለየ አይደለም ። ልብ - በሉ ሁለቱም ግራና - ቀኝ የተሰቀሉት ክፉ አድራጊዎች በኢየሱስ ላይ የሚደረገውን ስድብ ፥
ፌዝ የሃሰት ቃል እያዳመጡ የሰጡት መልስ የተለያየ እንደሆነ ፤
ዛሬም ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት ፥ ፃድቅ ፈራጅ አምላክነቱን በመቀበል እና ባለመቀበል ዓለም በሁለት ተከፍላ የተለያዩ በጎ እና መጥፎ ምላሾች በየአቅጣጫው እንሰማለን ፤

ለመሆኑ እኛስ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት በግል የሰጠነው ምላሸ ምንድን ነው ??
ለኃጢያት ይቅርታ / ሰርየት / ብቸኛ መንገድ ፥ እውነት ፥ ሕይወት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ ገብቶን ፤ በእራሳችን የምንድንበት ምንም የፅድቅ ስራ እንደሌለን በመገንዘብ በራሳችን ላይ በመፍረድ በኃጢያታችን ተናዘን ከእርሱ ጋራ ታርቀናል ??
ሁለቱ ክፉ አድራጊዎች በተሰቀሉበት መስቀል ላይ ሆነው ፦

" ከተሰቀሉት ከክፉ አድራጊዎቹም አንዱ ። አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን ? ራስህንም እኛንም አድን ብሎ ሰደበው ።

ሁለተኛው ግን መልሶ ። አንተ እንደዚህ ባለ ፍርድ ሳለህ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን ?

ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው ፤ ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው ።

ኢየሱስንም ። ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ
በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው ። "
ሉቃ 23 : 39 - 42
የተሳዳቢው ክፉ አድራጊውን ንግግር ከአስተዋልነው ኢየሱስን ከመሳደብ አልፎ ፥ አስቀድሞ ከፈፀመው ኃጢያት ጋር ተባባሪ እንዲሆን እኛንም አድን ብሎ በትዕቢት በክፉ ስራው ሳይፀፀት በትዕቢት ተናገረ ።
ዛሬም እንደ ትዕቢተኛው ክፉ አድራጊው ሰው አንዳንዶች ነፍሳቸው ልትወጣ በጣር እያለ ፥ በብዙ ስቃይ ፥ ህመም ተይዘው ፥ ብዙ ነገራቸውን እያጡ ትክክል አለመሆናቸውን ሕሊናቸው እያወቀ ለምስራቹ የወንጌል ቃል ምላሸ የማይሰጡ ልባቸውን አደንድነው ፣ ጆሮአቸውን ደፍነው ወደገሃነመ እሳት ለመሄድ የሚጣደፉ በርካቶች ናቸው ።
በተቃራኒው ሁለተኛውን ክፉ አድራጊ ስንመለከት በእራሱ ላይ የፈረደ ፤ ስለ ፈፀመው ወንጀል የሚገባውን እንደተቀበለ ያመነ ፤ በምድራዊው የወንጀል ድርጊቱ ሕግ ከፈረደበት እውነተኛ በያኔ እንደማያመልጥ የተረዳ ፤ እነሱ የተከሰሱበትን ወንጀል የተቀበለ ፦
ጌታ ኢየሱስ ምንም ክፋት እንዳላደረገ የመሰከረ ሰው ፤ አልፎም ጓደኛውን በንግግሩ ትክክል አይደለህም ብሎ የገሰፀ እውነትን የተጠማ ፤
h ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው ሰዓት በመስቀል ላይ የተናገራቸውን ቃሎች ፥ እንዲሁም የሕዝቡን የካኽናት አለቆች እና የከሳሾቹን ተቃውሞ አስተውሎ ከመስማት በአለፈ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማያዊ መንግስት ከዚህ እንዳልሆነች ስለተረዳ " ጌታ ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው ። "
ብዙዎቻችን በራሳችን ላይ የሚያስፈርድብን ነገር አስቀድመን ብናውቅ እንኳን ፥ በእራሳችን ላይ አንፈርድም ፥ ጥፋታችንን አንቀበልም ። እግዚአብሔር አምላክ ፃድቅ ፈራጅ ስለሆነ ኃጢያት እና በደልን ሳይቀጣ ስለማያልፍ ፤ የሁላችንንም ኃጢያት እና በደል ለመደምሰስ ፤ ፈቅዶ በጌታችን ኢየሱሰ ክርስቶስ ላይ አኖረው ፦
" እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን ።

እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ ፤ "
ኢሳ 53 : 5 - 6
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁ የሁላችንንም / የዓለሙን / ኃጢያት እና በደል በመሸከሙ አስቀድሞ በእራሱ ላይ በመፍረድ የተናገረው ፦
" በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል ። "
ዮሐ 3 : 15 የሚል ነው ።
አንዳንድ ጊዜ የማንፈልገውን ነገር አድርገን የተፀፀትን አንጠፋም ፦

" በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና ፤ ፈቃድ አለኝና ፥ መልካሙን ግን
ማድረግ የለኝም ።

የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገር አላደርገውም ።

የማልወደውን የማደርግ ከሆንሁ ግን ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም ፥ በእኔ የሚኖር
ኃጢአት ነው እንጂ ። "
ሮሜ 7 : 18 - 20
እግዚአብሔር የስጋችንን ፈቃድ እያደረግን እንድንኖር አይፈልግም ። ምክኒያቱም የስጋ ስራ መጨረሻው ጥፋት እና ሞት መሆኑን ደጋግሞ ገልፆልናል ።
እያንዳዳችን በግል ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የእርሱን ጸጋ ስንቀበል የኃጢያት ዝንባሌ ያለው ተፈጥሮአችንን በመለወጥ እርሱን በመምስል እንድንኖር ያስችለናል ።

" አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል ፥

እርሱም ፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው ፤ ልዩነት የለምና ፤

ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል ፤

በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ ።

እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው ፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ
ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው ፥ "
ሮሜ 3 : 21 - 25
በራስ መፍረድ እግዚአብሔር ከኃጢያት ጋር እንደማይተባበር አውቆ ለጌታ የእረፍት እና የሠላም ጥሪ ምላሸ መስጠት ነው ።
ስው በራሱ ኃጢያተኛ ባህሪ ላይ አስቀድሞ ካልፈረደ የእግዚአብሔርን ምህረት ሊቀበል አይችልም ። ኃጢያተኝነትን ማመንና መናዘዝ እንዲሁም ፈፅሞ ከቀደመው የኃጢያት መንገድ መመለስ ያስፈልጋል ።
በራስህ ፈርደህ በጽድቅ መንገድ ለመመላለስ ወስነሃል ? ዛሬም በጌታ ጸጋ የተሰጠህ የአንተ ጊዜ መሆኑን እወቅ ።
ሰው እራሱን ለጌታ ማስገዛት ካልቻለ ለዓለም ፥ ለሥጋና ለሰይጣን መጠቀሚያ ሆኖ ከፍተኛ ወንጀል ሊፈፅም ይችላል ።
ወንጀል የሚስራ በምድራዊው ህግ እንደሚቀጣ ሁሉ እንዲሁ የእግዚአብሔርን ሕግ ከማንኛውም ክፉ የኃጢያት ስራ ጋር እንዳንተባበር ስለሚያዘን ቅጣቱ የከፋ የዘልዓለም ሕይወትን እስከማጣት ስለሚያደርስን ፤
ዛሬ ቀን ሳለልን ቅድሚያ የእግዚአብሔር መንግስት ወራሾች መሆናችንን አውቀን በመረዳት ፤ እርሱ በሰጠን እድሜ በምድራችን በጎ ተፅእኖ በማምጣት የሠላም ስው ለመሆን በራሳችን ላይ በመፍረድ በኃጢያታችን በመናዘዝ ምሕረትን ከእግዚአብሔር ዘንድ መቀበል ይገባናል ።
ዛሬ ትንሽ ሆነ ትልቅ ክፉ ስራ እንድትስራ በሚገፋፋህ ኃጢያተኛ ባህሪ ላይ በመፍረድ ወደ እግዚአብሔር ብትጠጋ በሕይወትህ ላይ የሚመጣውን መከራና ፈተና የምትቋቋምበትን ጸጋ ከማግኘትህም በላይ በነገር ሁሉ በጎ ተፅእኖ የምታመጣበትን ለተተኪው ትውልድ ምሳሌ ፥ በረከት የምትሆንበትን ኃይል ትቀበላለህ ።

01/11/2018

Abraham Esayas:

_
እ.ኤ.አ ሕዳር 10 ቀን 1483 ዓ.ም በሳክሶኒ ጀርመን በምትገኝ አይስሌበን በተባለች መንደር የተወለደውና የካቲት 18 ቀን 1546 ዓ.ም በ 63 አመቱ ያረፈው ማርቲን ሉተር በዘመኑ በአውሮጳየተቀጣጠለውን የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ መሪ ነበር:: አባቱ ሀንስ እና አናቱ ማርጋሬት ዚግለር ሉተር ድሆች ገበሬዎች ስለ ነበሩ ከችግሩ የተነሳ እየለመነ ትምህርቱን የተማረበት ጊዜ ነበር:: በትምህርቱ ጉብዝናን ስለ አሳየ በነበረበት ዩንቨርስቲ እጅግ በጣም ታዋቂነትን ካተረፉ ተማሪዎች አንዱ ለመሆን በቅቶ ነበር::

-
አንድ ቀን በኤርፉርት አቅራቢያ ሓይለኛ መብረቅ ወረደና የሞት ፍርሃት አሳደረበት:: ከዚያ ጊዜ አንስቶ ወደ አጉስቲኒያን ገዳም ገብቶ የምንኩስና ኑሮውን ተያያዘው:: እ.ኤ.አ በ 1510 ዓ.ም ለስራ ጉዳይ ወደ ሮማ ሔዶ እያለ በቤተ ክርስቲያን ይታይ በነበረው አስተዳደራዊና ስነ ምግባራዊ ጉድለት ልቡ አዘነ:: ከጥቂት አመታት በኋላ ሊቀ ጳጳሳት ሌዎ አስረኛ የቅዱስ ጴትሮስን ቤተ ክርስቲያን አሳድሶ ለማሰራት አንድ ዜደ አቅዶ በስራ ላይ አዋለ:: ይኸውም ገንዘብ ለሚሰጡ ሰዎች "የሀጥያት ይቅርታ ተስፋ የሚሰጥ የስርየት ጽሁፍ" በይፋ እንዲሸጥ አዘዘ:: ይህ ድርጊቱ ሉተርን ለተቃውሞ አነሳሳው:: ከዚያ በፊት በጥልቀት ያነበበውና ያጠናው በተለይም ሮሜ 1:17 የሚገኘው "ጻድቅ በእምነት ይኖራል" የሚለው ቃል ህይወቱን ሰለ ለወጠው የሊቀ ጳጳሳት ሌዎን ስህተት አይቶ በቸልታ ሊያልፈው አልቻለም::
-
በዚህም ምክኒያት እ.ኤ.አ በ 1517 ዓ.ም ዘጠና አምስት መከራከሪያ ነጥቦችን በዊተንበርግ ቤተ ክርስቲያን በር ላይ በመዶሻ ጠረቀ:: ዘጠና አምስቱ የመከራከሪያ ነጥቦች ሊቀ ጳጳሳቱ በስርየት ጽሁፍ አማካይነት የሓጥያት ይቅርታ ለማሰጠት ያደርገው የነበረውን ሙከራ የሚቃወሙ ነበሩ:: ሉተር በነዚህ ነጥቦች አማካኝነት ጽድቅ የሚገኘው በሌላ በምንኛውም መንገድ ሳይሆን በእምነት [ብቻ] መሆኑን አረጋገጠ:: ሀሳቡን እንዲለውጥ ቢነገረውም ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ ካልተሰጠው በቀር ከተነሳበት አላማ ንቅንቅ እንደማይልና እምነቱን እንደማይተው አብዝቶ ተናገረ::
-
ብዙ ክስ ብዙ ውጣ ውረድና እንግልት ቢደርስበትም ከጊዜ በኋላ ሉተር በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ተመስርቶ ያቀረበው ሃሳብ ተቀባይነትን በማግኘቱ ብዙ ተከታዮችን ሊያፈራ ቻለ:: ምኞቱና ፍላጎቱ ጥረቱም በሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መነፈሳዊ ተሐድሶ እንዲኖር ማድረግ እንጂ ለመገንጠል አልነበረም:: ከፍላጎቱ ውጪ በሆነ ምክኒያት ይህ ሃሳቡ ከግቡ ባይደርስም በእርሱ መሳሪያነት እግዚአብሐር ብዙዎችን ከጨለማ ወደ ወንጌል ብርሀን ሊያወጣ በመቻሉ ድካሙ ከንቱ ሆኖ አልቀረም::
-
ማርቲን ሉተር ለዘመናት ተዳፍኖ ለነበረው የወንጌል እሳት መቀጣጠልና ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ አራማጆች ቁጥር መጨመር ደግሞም ለፕሮተስታንት እምነት መመሥረት ምክኒያት በመሆኑ ስሙ በታሪክ ማህደር ውስጥ ጉልህ በሆነ ስፍራ ይዞ ይገኛል::

ምንጭ፦ [ደረሰ ብሩ እንደጻፈው - ዘጠና አምስቱ የሉተር መከራከሪያ ነጥቦች]

Address

Addis Ababa, Addisu Gebysa/, , Kechena
Addis Ababa
MARK'SWAREHOUSEONTHEWAYFROMTHEADDISUGEBYATOTHECREEKMARKSUPSTAIRS,DR.FISCHERACADE

Telephone

+251111554298

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Addis Kidan Baptist Church Semen-Local posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ethiopian Addis Kidan Baptist Church Semen-Local:

Share