Yene tiwulid - የኔ ትውልድ

Yene tiwulid - የኔ ትውልድ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16

13/11/2025
13/11/2025

✅ያገባ መፍታት ይፈልጋል ወይም በትዳሩ ደስተኛ አይደለም

✅ያላገባዉ መፈቀር መወደድ ጥሩ ትዳር ይፈልጋል

✅ተራ የሚባሉ ሰዎች መፈመስ መታወቅ ይፈልጋሉ

✅ታዋቂዎቹ ነፃነታቸዉን ይፈልጋሉ

✅ህፃናት ትልቅ ለመሆን ይመኛሉ

✅ትልልቅ ሰዎች ልጅነታቸዉ ያ ደግ ዘመን ይናፍቃቸዋል

✅ስራ ያላቸዉ ሰዎች እረፍት ቀናቸዉን በጉጉት ይጠብቃሉ

✅ስራ አጡ ሰርቶ ራሱን ለማኖር ያልማል

✅ወጣት ስትሆን ከወላጆችህ ጋር ግዜ ማሳለፍ ይደብርሀል

✅ስታረጅ “ምናለ ቤተሰቦቼ በኖሩና ይሄንን ባዩልኝ” ትላለህ!!

ዞሮ ዞሮ ህይወት ትንሽ ደስታ ብዙ ጭንቅ ያለባት ናት ግዜያችሁን ተጠቀሙ ተደሰቱ እና እለፉ!!!

12/11/2025

መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ ከሰማይ ሰማያት የወረደው ከድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

 ?==================🎯"ክርስትና ጥሩ ነው፤ ግን በጣም አታክርር!" ሰው ብሏችሁ ያውቃል? ታዲያ ምን ላክርር እሺ? ንገረኝ? ምን ላክርር? ይህን ዓለም ላክርረው? አሁን ገንዘብ የ...
12/11/2025

?
==================

🎯"ክርስትና ጥሩ ነው፤ ግን በጣም አታክርር!" ሰው ብሏችሁ ያውቃል? ታዲያ ምን ላክርር እሺ? ንገረኝ? ምን ላክርር? ይህን ዓለም ላክርረው? አሁን ገንዘብ የምር ነው? ላጥብቀው? ባንድ ጊዜ "ወደቀ" የሚባል!
እኛ አገር እንኳ ይኸው ስንቴ ወደቀ። በቀደም በነበረው ዋጋ ዛሬ እሱን ላጥብቅ? አብሬው ልውደቅ?

🎯 ውበትን ላጥብቀው? ክርር አድርጌ ዋናዬ አንተ ነህ ልበለዉ? እየወረደ ያለን ነገር ላክርረው? ይሄን ዓለም ላክርረው? ሥልጣንን ላክርረው? ዋና አድርጌ ልያዘው? ነገ ጠዋት የሚሄድ ውበትና ክብር የዚህ ዓለም ኃብትና ብልጥግናን ዋና ላድርገው? እንዴት አድርጌ? ገና እንደገዛሁት ዋጋዉ የሚቀንስን ነገር እንዴት አድርጌ ዋና ላድርገው?

🎯 ካከረርኩ አይቀር የማይቀንሰውን፤ የዘላለም የሆነውን በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔር የሰጠንን እርሱን ነው!! እሱ ነው ዋና!!

Follow me

መሐመድ አበባዉ ከእስልምና ወደ ክርስቶስ ፍቅር የመጣ እጅግ የምንወደዉና የምናከብረዉ የወንጌል መልዕክተኛ ወንድማችን መፅሐፍ ፅፎ እንሆ ታህሳስ 5 በፖስተሩ ላይ ባለዉ አድራሻ ይመረቃል ። እ...
12/11/2025

መሐመድ አበባዉ ከእስልምና ወደ ክርስቶስ ፍቅር የመጣ እጅግ የምንወደዉና የምናከብረዉ የወንጌል መልዕክተኛ ወንድማችን መፅሐፍ ፅፎ እንሆ ታህሳስ 5 በፖስተሩ ላይ ባለዉ አድራሻ ይመረቃል ። እርስዎም ተጋብዘዋል!

 ፈጣሪ የወንድ እና የሴትን ግንኙነት ብቻ ነው የፈቀደው!ጤናማ የሆነውም እሱ ብቻ ነው!  #ሰውነት
11/08/2025



ፈጣሪ የወንድ እና የሴትን ግንኙነት ብቻ ነው የፈቀደው!

ጤናማ የሆነውም እሱ ብቻ ነው!


#ሰውነት

"1K መግባት አለበት ይለኛል የእግዚአብሔር መንፈስ..." 😁ከስሟ በፊት "ፕሮፌት" ከሚል ቅጥያና፣ "መዲ" ከሚል ቁልምጫ   ጋር የምትጠራ መድኃኒት ታደሰ የምትባል ልጅ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ...
08/02/2025

"1K መግባት አለበት ይለኛል የእግዚአብሔር መንፈስ..." 😁

ከስሟ በፊት "ፕሮፌት" ከሚል ቅጥያና፣ "መዲ" ከሚል ቁልምጫ ጋር የምትጠራ መድኃኒት ታደሰ የምትባል ልጅ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ሞልታ የተረፈች ስለሆነች ስለ እርሷ ብዙ ማለት አይጠበቅብኝም። ከጥቂት ዓመት በፊት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የራሷን ቸርች የተከለችቱ ይህቺ እህታችን ባለፈው ሰሞን አፍሪካዊ ቅላጼና የሙዚቃ ስልተምት ባለው ዝምሬ መቀመጫዋን ለጉልህ ዕይታ በሚሆን መልኩ እያወዛወዘች፣ በቪዲዮ ቀርጻ ለለቀቀችው ግለ ክሊፕ ከሕዝብ ያገኘችው አሉታዊ ግብረ መልስ ከበድ ያለ ነበር።

ዘመኑ መቀመጫን በማወዛወዝ የመደሰትም ዓይደል? እሷም ልሞክረው ብላ ነበር አልሆነም። እናም ይኼ ተቃውሞ ጫና የፈጠረባት መዲ በሌላ ቅጂ ብቅ ብላ እየተፍለቀለቀች ምን ብትል ጥሩ ነው? "ሕዝቡ በኃይለኛው ተቃወመኝ፣ ጌታ ግን አይዞሽ በኢንተርናሽናል ደረጃ ታዋቂ ላደርግሽ ነው አለኝ!" 😁

ያው ልጅቱ "ነቢይ" ስለሆነች ምን አልልም እንጂ ቅጥፈቷ እኮ ልክ የለውም። ይኸው ዛሬ ጠዋት ደግሞ ወዳጄ፣ መጋቢ መራዊ ንጉሤ በሰደደልኝ የቲክ ቶክ ቅጂ ላይ፣ መዲ ዐይኗ ተጎልጉሎ ሊወጣ እስኪመስል ድረስ በስሜት አፍጥጣ፣ "በታላቅ መንፈሳዊ ኃይል" እንደተሞላች ይታወቅላት ዘንድም "ልሳኗን" እያንበለበለችና የፈረደበትን የጌታ ኢየሱስን ስም እየጠራች እንዲህ ስትል አደመጥኳት፦

"ዋው... ዋው... ዛሬ ማታ በኢየሱስ ደም ሸፈንኳችሁ... [ረጅም ልሳን] ሼር አድርጉ ባካችሁ፣ አሁን ልመታው ነው። እዚህ ላይ ግን 1k መምጣት አለበት። አንድ ሺህ ኬ መግባት አለበት። ቶሎ በሉና ሼር አድርጉ። በኢየሱስ ደም ሸፍኜ... አያያያያ... ዛሬ ማታ...አገኘሁት...አገኘሁት ... አይገርምም ይመታል! ...በኢየሱስ ስም ይመታል! .... "

"በዚህ ፕሮግራም ላይ ራሱ መናፍስቶች ገብተዋል። እንዲጽፉ አዛላሁ። ምን እንደምታደርግባቸው እንድትጽፍ አዛለሁ። ግባ...ግባ...በኢየሱስ ስም አዝሃለሁ ግባ! ...አዎ ገባ! መናፍስት እየገቡ ነው አሁን። በሰዎች ላይ የተቀመጡ መናፍስቶች... ስልካቸውን እንዳትዘጋ አዛለሁ...አንድ ቁጥር ንኩልኝ ...1K መግባት አለበት ይለኛል የእግዚአብሔር መንፈስ።.... [ዘለግ ያለ ልሳን]... ኦርቶዶክሶች፣ ሙስሊሞች፣ ጴንጤዎች፣ እምነት የሌላችሁም ብትሆኑ... ሼር አድርጉ! ባካችሁ ቶሎ በሉ። ልመታው ነው አሁን..." እያለች መዲ የቲክ ቶክ ገበያዋን ማድራቷን ትቀጥላለች። እንደተመኘችው 1k ሞልቶላት መናፍስቱን ረፍርፋቸው ይሆን? 😁

እንግዲህ እንዲህ ዓይነት ከባድ ፈተና ነው የገጠመን። ነገሩ ለወሬም ባይመች ነገር ግን በዚህ መልኩ በኢየሱስና በመንፈሱ እየተቀለደም እንደ ፍጥርሩ ይሁን ብሎ ዝም ማለትንም ስላልቻልኩበት በሳቄ ላቃለው ብዬ ነው ወዲህ ያመጣሁት። መቅለልም አለበት!

ሰናይ ቅዳሜ!

©ሽመልስ ይፍሩ

ስሜ ወንድማገኝ ከበደ ይባላል።በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ  ያደግኩ ቢሆንም፣ ሲደረግ ያየሁትን ልማድ ከማድረግ ባለፈ በተደጋጋሚ ስሰማው የነበረውን፣ ኢየሱስ የተባለውን ጌታ ከእኔ የግል ሕይወት...
05/02/2025

ስሜ ወንድማገኝ ከበደ ይባላል።
በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ያደግኩ ቢሆንም፣ ሲደረግ ያየሁትን ልማድ ከማድረግ ባለፈ በተደጋጋሚ ስሰማው የነበረውን፣ ኢየሱስ የተባለውን ጌታ ከእኔ የግል ሕይወት ጋራ የነበረውን ቀጥተኛ ግንኙነት አልገነዘብም ነበር። ነገር ግን ሁልጊዜ ሲነገሩኝ የነበሩትን አስደሳች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች እውነተኛነት እጠራጠር ነበር።

ምንም የክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ያለው ቢሆንም የክርስትና ትርጉም በሕይወቴ ምንም አይታይም ነበር ከዚህም የተነሳ ምንም አባቴን በመፍራት ወደ ቤተክርስቲያን የምሄድ ቢሆንም በተግባር የአመጻ ተባባሪ የሆንኩ ተደባዳቢና ሌባ በመሆኔ ነበር ሰዎች የሚያውቁኝ ለመስረቅ ከግለሰብ እስከ አጋዚ ፖሊስ እንዲሁም ከነጮች ሳይቀር መስረቅን የተለማመድኩ ከዛም አልፎ ከቤተክርስቲያን ሰው ለማምለክ ስገባ ቦርሳ ከፍቼ እሰርቅ የነበርኩ ነበርኩ😭

ምንም አስጠሊታ ሕይወት ያለኝ ቢሆንም እህቴ 2000 ዓ/ም የገና በዓል አጠቃላይ የአዳር ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳተፉኩ ሌሊቱን ሙሉ በዘማሪ አገኘሁ ይደግ "ውለታው x4 በዛብኝ" የሚለውን ዝማሬ እየሰማው እያለቀስኩ አደርኩኝ።
ኢየሱስ ለኔ ያለውን ፍቅር ተረዳው ሆኖም ከተወሰነ ወራት በኃላ ተመልሼ የቀድሞ ሕይወት ማሳለፍ ጀመርኩ።

በግል ፀባይ ምክንያት የትም ት/ቤት እንዳልማር ተደርጌ ብዙ ት/ቤቶች እያፈላለኩ ወደ አንድ ት/ቤት ሄርኩኝ bright future የሚባል በየግቢው የተባረሩ ተማሪዎች ያሉበት አጫሽ ቃሚ ተደባዳቢ የበዙበት ት/ቤት ነው ባለቤቶች እና አስተዳደሮች ራስታዎች (ጀማይካዎች) ናቸው በዚህ ት/ቤት በብዙ ልመና ከገባው በኃላ ለተወሰነ ወር በቀድሞ ሕይወቴ የቀጠልኩ ቢሆንም 2001 የገና በዓል ዕለት ለሕይወት ለውጥ ያመጣ አንድ ሕልም አለምኩ
ምንም መጥፎ ሕይወት ላይ ብሆንም
በጎዳና ላይ ወንጌል እንዲህ እያልኩ ስሰበክ አየሁ

" መንግስተ ሰማይ ቀርባለችና ንስሃ ግቡ"

እያልኩ ይሄን ያየሁትን ሕልም ወደ ቤተክርስቲያን በግድና በልመና ይወስደኝ ለነበረው ወንድም ነገርኩት እሱም ደስ ብሎት እግዚአብሔር ለወንጌል ይፈልግሃል እና እንኳን ደስ አለህ በማለት ፀለየልኝ ከዛን ዕለት ጀምሮ ይሄው የመስቀሉ መስካሪ እና አፍቃሪ ሆኜ ቀረው ይሄን መሲሁን እንመሰክራለን።

ምስክር ነኝ ኢየሱስ የዘላለም አምላክ ነው

"እግዚአብሔር የተባልከው አምላክ ሆይ፥ ስለ አንተ ብዙ የተነገረኝን ብቻ ሳይሆን በግሌ እንዳውቅህ እፈልጋለሁ፤ እንዴት አንተን ማመን እንዳለብኝ አስተምረኝ" ብዬ እጸልይ ነበር።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና ከዘላለም ሞት ማዳን የሚችል ብቸኛ መንገድ መሆኑን እኔም አይቻለሁ።

#እኔምስክርነኝ

በረከት ለማ እባላለሁ፡፡ ገና የ 8ተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ በትምህርት ቤታችን የሚዲያ ክበብ ስብሰባ ላይ ተሳታፊ ነበርኩና በዚያን ጊዜ ባዮሎጂ መምህራችን መምህር ሰለሞን "ወደፊት ምን መሆን...
04/02/2025

በረከት ለማ እባላለሁ፡፡ ገና የ 8ተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ በትምህርት ቤታችን የሚዲያ ክበብ ስብሰባ ላይ ተሳታፊ ነበርኩና በዚያን ጊዜ ባዮሎጂ መምህራችን መምህር ሰለሞን "ወደፊት ምን መሆን ትፈልጋላችሁ?'' እያለ ሁሉንም ተማሪ መጠየቅ ጀመረና ሁሉም ተማሪ እንደየፍላጎቱ ብቻ ሳይሆን እንደየ ትምህርት አቀባበሉ መሆን የሚፈልፖትን ተናገሩና ተራው እኔ ጋር ደርሶ ተጠየኩኝ፡፡ ያው ሰነፍና አስቸጋሪ ተማሪ በመሆኔ ምን እንደምል ለመስማት የሰው ሁሉ ዓይን ወዷ እኔ አፈጠጠ ከዚያን መምህር ሰለሞን "በረከት ወደፊት ምን ምትሆን ይመስልሃል?'' አለኝ እኔም ቆምኩኝና ኮስተር ብዬ "ማጅራት መቺ!'' አልኩት፡፡ ተማሪ ሁሉ ሳቀብኝ እኔ ግን ለቀልድ ሳይሆን የምሬን እየተናገርኩ ነበር ከዚያን መምህራችን ቀጠለና ፈገግ ብሎ ታዲያ ለምን ትማራለህ? አለኝ እኔም "ቢያንስ ማጅራት የት እንደሆነ ማወቅ አለብኛ" ብዬ የልቤን ባወራ ክፍሉ በሳቅ ተረበሸ፡፡ ወዳጆቼ ገና በልጅነቴ ለክፏ የተሰጠው በፍጹም ተስፋ የማይታየኝ 7ና በልጅነት አመፅ ልቤን ያሳወረው ብላቴና ነበርኩኝ ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ራራልኝና ጠልቄ ሳልጠፋበት የህይወትን መንገድ አሳየኝ፡፡

ቀድሞ ኢየሱስ ሳያገኘኝ በፊት ተስፋ አልነበረኝም ፣ አመጸኛም ነበርኩ ፣ ደህንነትም አይሰማኝም ነበር ነገር ግን የናዝሬቱ ኢየሱስ የበራልኝ ቀን እንዷ አዲስ ተወለድኩ ፣ ምንም እንኳን ባለማወቄ ባልወዷውም ከዘላለም አውቆኝ ሳይሰስት ወዷዷኝና የዘላለም ህይወትን በነፃ አገኘው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ስለ እኔ በዷልና መተላለፍ ከሰማያት ወርዶ ሰው እንደሆነ ፣ እንደተሰቀለና እንደሞተ ፣ በ 3ተኛውም ቀን ከሙታን እንደተነሳና እንዳረገ ደግሞም ተመልሶ እንደሚመጣና እንደሚወስዷኝ በማመኔ ነፍሴ አረፈች፡፡ ኢየሱስ ብቸኛ የመዳኛ መንገድ እንደሆነና ነፍስን እንደሚያሳርፍ እኔም ምስክር ነኝ፡፡ አሁን በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነውንና የሚያኮራውን ስራ በትህትና እሰራለሁ ይህም የእግዚአብሔር መንግስት ነው፡፡

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደኾነና ከዘላለም ሞት ማዳን የሚችል ብቸኛ መንገድ መኾኑን እኔም አይቻለሁ።

#እኔምስክርነኝ

ስሜ መስከረም ጌቱ ይባላል። በክርስቲያን ቤተ ሰብ ውስጥ እና በቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ባህል ውስጥ ያደግኹ ቢኾንም፣ ሲደረግ ያየኹትን ልማድ ከማድረግ ባለፈ በተደጋጋሚ ስሰማው የነበረውን፣ ...
04/02/2025

ስሜ መስከረም ጌቱ ይባላል። በክርስቲያን ቤተ ሰብ ውስጥ እና በቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ባህል ውስጥ ያደግኹ ቢኾንም፣ ሲደረግ ያየኹትን ልማድ ከማድረግ ባለፈ በተደጋጋሚ ስሰማው የነበረውን፣ ኢየሱስ የተባለውን ጌታ ከእኔ የግል ሕይወት ጋራ የነበረውን ቀጥተኛ ግንኙነት አልገነዘብም ነበር። ነገር ግን ሁልጊዜ ሲነገሩኝ የነበሩትን አስደሳች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች እውነተኛነት እጠራጠር ነበር። አባቴ ጸሎት ስለመጸለይ ባስተማረኝ መሠረት ያኔ ትንሽ ልጅ እያለኹ “እግዚአብሔር የተባልኸው አምላክ ሆይ፥ ስለአንተ ብዙ የተነገረኝን ብቻ ሳይኾን በግሌ እንዳውቅኽ እፈልጋለኹ፤ እንዴት አንተን ማመን እንዳለብኝ አስተምረኝ” ብዬ እጸልይ ነበር። በጊዜ ኺደት ርሱ ኢየሱስ ራሱ ማን እንደኾነ ያስተምረኝ ጀመር። እንዲሁም የመስቀሉ ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ የመጣ አፈ ታሪክ ሳይኾን ከዛሬ ኹለት ሺሕ ዓመታት በፊት ፈጣሪ የፈጠራቸውን ፍለጋ ሰው ኾኖ መጥቶ በመስቀል በመሞት በኀጢአተኛ ሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን ጥል አስወግዶ እንድንታረቅ ማድረጉ ሐቅና እውነተኛ ክሥተት መኾኑን ለትንሿ ልቤ አስረዳኝ። ይህ እውነተኛ መለኮታዊ ብርሃን በውስጤ መረጃ ኾኖ ከመቀመጥ ዐልፎ ሕይወት በመዝራት መላ እኔነቴን ቀይሮ ዐዲስ ሰው አደረገኝ። ይህ መገለጥ ከእግዚአብሔር ጋራ ያለኝን ግንኙነት ለወጠው። ርሱ የሚሰጠውን ጸጋና ዐላማ እንድቀበል፣ በሙሉ ልቤ ርሱን ለመከተል ኅሊናዊ ምርጫ እንዳደርግ በመንፈሱ መራኝ። ከዚያም “ጌታ ሆይ ስላንተ ብዙ ሰምቼ ነበር አኹን ግን ዐይኔ አየችኽ” በማለት የሕይወቴ ጌታና አዳኝ አድርጌ ተቀበልኹት።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደኾነና ከዘላለም ሞት ማዳን የሚችል ብቸኛ መንገድ መኾኑን እኔም አይቻለሁ።

#እኔምስክርነኝ

ሰላም ይብዛላቹ እኔ ሄለን ጌታቸው እባላለሁ የተወለድኩት በአርሲ ክፍለሀገር  ትንሽዬ የገጠር መንደር ውስጥ ከሙስሊም ቤተስብ ነው። እኔ በተውለድኩበት ቤተስብ ውስጥ ከፍተኛ የባዕድ አምልኮ ይ...
04/02/2025

ሰላም ይብዛላቹ እኔ ሄለን ጌታቸው እባላለሁ የተወለድኩት በአርሲ ክፍለሀገር ትንሽዬ የገጠር መንደር ውስጥ ከሙስሊም ቤተስብ ነው። እኔ በተውለድኩበት ቤተስብ ውስጥ ከፍተኛ የባዕድ አምልኮ ይደርግ የነበር ስሆን ከዚህም የተነሳ ከኔ በፊት የተወለዱ እህትና ወንድሞቼ በሞት ተወስደዋል ። እኔም የዚው መንፈስ ሰለባ የሆንኩት ገና በሶሰት አመቴ ነበር ከውላጅ እናቴ እንደሰማውት መንፍሱ ለእናቴ ተእዛዝ የሰጣት እና ያልታዘዘች እንደሆነ እኔን እንደሚገልባት ያስጠነቃታል።

በንጋተውም ከልጆች ጋር ስንጫወት የግራ እግሬን የአጋም እሾህ ወጋኝ በዚያው የጀመር በአራት አመቴ ከቤተሰብ ለየኝ አንድ እግሬን አሳጣኝ ። በህፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ለብቻዬ በብዙ ስቃይ አለፍኩ ልናገርው ከሚችለው በላይ በብዙ ስቃይ አደኩ ። ከዛም በአስራ ስድስት አመቴ ካለጥፈቴ ከማደጎ ተባረርኩ ብቻዬን ቀርው እራሴን ሳላድግ የልጅ እናት ሆንኩ መካራው እየባሰ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም ። ብዙም ሳይቆይ የሳንባ ታማሚ በመሆኔ በሞት አፋፍ ላይ ሳለሁ ባደኩበት ማደጎ እንደ ልጅ ሳይሆን እንደበሽተኛ ተቀብለው የሞቴን ቀን እጠባበቅ ነበር ። በሽታውም ከተለመደው ሳንባ አልፎ (ኤም ድ አር) ወደተባለ በሽታ ተቀይራል ብዙም ተስፋ የለውም አሉኝ ።

በዛ ላይ መድሀኒቱም እኔ ለይ ብዙም ሊሰራ አልቻለም ኪሎየም ከሰላሳ አምስት አልጨምርም አለ። በዚህ መልኩ ለሁለት አመታት ህመምኛ ሆኜ ሳለው ሁሌ አንድ ጥያቄ ውስጤ ይመላለሳል እኔን የፍጠርኝ ማነው? ለምንድነው በዚህ አይነት ውጣ ውርድ ማልፈው? ልጅነት ምን እንደሆነ አላውቅም፣ የቤተስብ ፍቅር አላውቅም ፣ አንድ ምሽት ቀኑ አስራ ስድስት ነው ልጄን የወለድኩበት ቀን ኪደነምህርት ሻማ አብርቼ አንድ ፀሎት ፀለይኩ ቀን ልጄ ልሞት እንደሆነ ኒሞኒያ እና ኩፍኝ ይዞታል በኦክስጅን ነው ሚተነፍሰው ብለው ነግርውኛል አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ የሆነ የሚያድን አካል የስፈልገኛል ለራሴ ሳይሆን ለልጄ ግን አላውቅም በዚያን ቀን አንድ ህልም አየው እሱም በብዙ ህዝብ መሀል ተገኝቼ ስፀልዩልኝ ከዚያ ቦሀላ እንደሌላ ሰው ተቀይሬ አየው ።

በንጋተውም ከአንድ እህቴ ጋር ጉባዬ እግዚአብሔር ስድስት ኪሎ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ወስኜ ይዛኝ ሄደች ። በህልሜ እንዳየሁት እንደዛው ሆነልኝ ከረዥም ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ደስታ ተመለሰልኝ ታስፋ አገኛው አዘኔን አስረሳኝ አባት አገኛው ልጄ ዳነልኝ መንፈሱ ከኔ ሲወጣ ከልጄም ከእናቴም ከዘርማንዘሬ ውሉ ወጣ ። ከሀያ አመት ቦሀላ ወላጆቼን አገኘው ።

ዛሬ እኔም ቤተሰቤም ጌታን እናገለግላለን ጌታ ርድቶኝ በተውለድኩበት አካባቢ እንደ እኔ አካል ጉዳት ላለባቸው እና ልጆቻቸውን ያለ አባት የሚይሳድጉትን እናቶች ሚርዳ ሚንስትሪ አቋቁሜለው ከባለቤቴ ጋርም ውንጌሉን እንመስክራለን በዝማሬም አዳኜን አመስግናለው አገለግላለው ልጄ ዛሬ አስራ አምስት አመት ሆኖታል አልሞትኩም። ይኸው ድኜ ቀረው አስራ ሶስት አመት ጌታ ይክበር አሜን ዛሬም በእንዲህ አይነት ውጣ ውርድ እያለፋቹ ከሆነ እመኑኝ እግዚአብሔር በቀኑ ይመጣል እየሱስ እውነተኛ የአለም መድኃኒት ነው እኔ ምስክር ነኝ

ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም::
ዮሐንስ ወንጌል 1:4

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደኾነና ከዘላለም ሞት ማዳን የሚችል ብቸኛ መንገድ መኾኑን እኔም አይቻለሁ።

#እኔምስክርነኝ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yene tiwulid - የኔ ትውልድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share