Gods Childrens Page/የእግዚአብሔር ልጆች ገጽታን

Gods Childrens Page/የእግዚአብሔር ልጆች ገጽታን Jesus Christ yesterday today and Forever Lord

ሁል ጊዜ ያሉበትን መንሳዊ ህይወት ሁኔታ                   መመርመር ከመናቅ  ያስመልጣል"እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል!"ሁል ጊዜ የንጉስ ሳኦልን ታሪክ ሳ...
18/05/2026

ሁል ጊዜ ያሉበትን መንሳዊ ህይወት ሁኔታ
መመርመር ከመናቅ ያስመልጣል

"እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል!"

ሁል ጊዜ የንጉስ ሳኦልን ታሪክ ሳስብ የሚገርመኝ ትልቅ እውነት አለ። ሰውየው የወጣው የጠፉትን አህዮች ፍለጋ ነበር፤ ነገር ግን ሳይዘጋጅበትና ሳይጠብቀው ንግስና በትከሻው ላይ ወደቀ።

ሳኦል አህያ ለመፈለግ እንጂ ለንግስና አልተዘጋጀም ነበር። በመጨረሻም ይህ የዝግጅት ማነስና አለመታዘዝ ዋጋ አስከፈለው። አንድ ቀን አድርግ የተባለውን ባለማድረጉ፣ ነቢዩ ሳሙኤል "የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል" አለው።

ለመሆኑ እግዚአብሔር መሪን ሲንቅና ስልጣኑን ሲወስድ ምን እንደሚያደርግ አስተውላችኋል?እግዚአብሔር ንጉስን ሲንቅ የሚያደርገው ግዑዙን የቤተ-መንግስት ወንበር መውሰድ ብቻ አይደለም፤ ከዛ በባሰ ሁኔታ ከህዝቡ የልብ ዙፋን ላይ ያወርደዋል።


በፌስ ቡክ መንደር የሚነበብ መንፈሳዊ ፅሁፍ

18/05/2026
18/05/2026

ባንኮች እባካችሁን አታንገላቱን ያላስፈላጊ ወጪ አታስወጡን በአግባቡ ፉይዳችንን አስተሳስሩልን አካውንታችንን አትዝጉ ለምናችሁ ታስከፍቱን እና ታሰቃዩናላችሁ🤔የኑሮ ውድነቱ አይበቃም???

ሰው እረፍት ለማግኘት ብዙ ርቀት ይሄዳል። የምትደርስበት ነገር ላይ አይደለም እረፍት ያለው። የምትደርስበት ነገር፤ እስከምትደርስበት ነው እንጂ ሚያጓጓህ እንጂ ያገኘኸው ሰዓት ደግሞ፤ ከመጀመ...
18/05/2026

ሰው እረፍት ለማግኘት ብዙ ርቀት ይሄዳል። የምትደርስበት ነገር ላይ አይደለም እረፍት ያለው። የምትደርስበት ነገር፤ እስከምትደርስበት ነው እንጂ ሚያጓጓህ እንጂ ያገኘኸው ሰዓት ደግሞ፤ ከመጀመሪያው ይልቅ የባሰ ሌላ ስቃይ ነው ልብህ ላይ የሚያስቀምጥብህ። እየሱስ ጋር ስትመጣ ግን፤ “ወደ እኔ የመጡትን መልሼ አላስወጣቸውም” አለ።

እውነተኛ እረፍት ከእየሱስ ጋር ብቻ ነው ያለው። እውነተኛ ሰላም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ብቻ ነው ያለው። አለምን አትችለውም፣ ሰይጣንን አትችለውም፣ የዚህን አለም ነገር አትችለውም። እየሱስ አንተ ጋር ሲገባ ድል ታደርገዋለህ። ና ወደ እየሱስ... በነፃ! ምንም ነገር አለም በነፃ አትሰጥህም። ስትቀበላት ታስከፍልሃለች፣ መጨረሻ ላይ ደግሞ የሰጠችህንም ከነ ህይወትህ መልሳ ትወስደዋለች።

እየሱስስ ምላሽ አይፈልግም፣ እንዲሁ ነው የሚሰጥህ። በመጥራቱ የማይፀፀት አምላክ፣ ለምን አዳንኩት የማይል አምላክ። ድነትን የዘላለምን ህይወት በነፃ ጴጥሮስ እንዳለው በእኛ ላይ አፈሰሰው። ይሄን ለማድረግ ታዲያ ምን ላድርግ? ምንም አታድርግ። እጅህን አንስተህ ና ወደ ልቤ ግባ በለው፣ ህይወትህን ይቀይረዋል።
አሜን🙏❤️

07/05/2026

✝️💖ዛሬም ርዕስ አልቀየርንም ኢየሱስ ይሰበካል✝️💖
የአጋንንት ሰንሰለት ይበጠሳል‼️
ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት ሌላው ሁሉ ከዚህ ስም በታች ነው ማለት ነው።

30/04/2026

እስቲ ባርኳቸው🙏

18/04/2026

📍አንድን ጨለማ ምንም አይነት ከዚያ የከፋ ጨለማ ብታመጡ አታስወጡትም፡፡ አንድ ድቅድቅ ጨለማ ስፍራውን እንዲለቅ ግን ትንሽ ብርሃን በቂው ነው፡፡ የሰዎች ጥላቻም እንዲሁ ነው፡፡ የሰዎችን ጥላቻ ምንም አይነት የከፋ ጥላቻ በእነሱ ላይ ይዛችሁ ብትነሱ አታስወግዱትም፡፡ የሰዎችን ጥላቻ የምታሸንፉት እናንተም እንደነሱ ከመሆን ራስን በመጠበቅ፣ ሁኔታውን አልፎ በመሄድ ዓላማ ላይ በማተኮር፣ የፍቅርና የአብሮነት ነገር የገባቸውን ሰዎች በማቅረብ አፍቃሪነታችሁንና አጋርነታችሁን ለእነሱ በመግለጥ ነው፡፡ #🤌🏽🤌🏽

#💚💛❤️

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gods Childrens Page/የእግዚአብሔር ልጆች ገጽታን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category