Ldeta Mulu Wengel

Ldeta Mulu Wengel let us love one another for loves comes from God..........

“ከተራራው በወረደ ጊዜም ብዙ ሕዝብ ተከተለው። እነሆ፤ አንድ ለምጻም ሰው ወደ ኢየሱስ ቀረበና ከፊቱ ተንበርክኮ እየሰገደለት፣ “ጌታ ሆይ፤ ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” አለው። ኢየሱስም እ...
30/01/2022

“ከተራራው በወረደ ጊዜም ብዙ ሕዝብ ተከተለው። እነሆ፤ አንድ ለምጻም ሰው ወደ ኢየሱስ ቀረበና ከፊቱ ተንበርክኮ እየሰገደለት፣ “ጌታ ሆይ፤ ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” አለው። ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “ፈቃዴ ነው፤ ንጻ!” አለው። ሰውየውም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ። ከዚያም ኢየሱስ፣ “መፈወስህን ለማንም አታውራ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ሙሴ ያዘዘውንም መባ አቅርብ፤ ይህም ምስክር ይሆንላቸዋል” አለው።”
‭‭ማቴዎስ‬ ‭8:1-4‬ ‭
Paster Dawit kassahun

ከተራራው በወረደ ጊዜም ብዙ ሕዝብ ተከተለው። እነሆ፤ አንድ ለምጻም ሰው ወደ ኢየሱስ ቀረበና ከፊቱ ተንበርክኮ እየሰገደለት፣ “ጌታ ሆይ፤ ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” አለው። ኢየ.....

“እነርሱም፣ “ታዲያ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ምን ማድረግ አለብን?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው” ሲል መለሰላቸው።”‭‭ዮሐንስ‬ ‭6:2...
14/10/2021

“እነርሱም፣ “ታዲያ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ምን ማድረግ አለብን?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው” ሲል መለሰላቸው።”
‭‭ዮሐንስ‬ ‭6:28-29‬ ‭

እነርሱም፣ “ታዲያ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ምን ማድረግ አለብን?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው” ሲል መለሰላቸው።

19/09/2021
18/06/2020

ይህ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት በየሳምንቱ እየተዘጋጀ
የሚቀርብላችሁ መልእክት ነው፡፡

ኢሳስ 26፡4
ጌታ እግዚ አብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ፡፡
በእግዚአብሔር መታመን
1. መግቢያ
በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።
ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ፥ ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው።
ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ የኃጥኣን በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም።
አቤቱ፥ ለቸሮች ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።
ወደ ጠማማነት የሚመለሱትን ግን ዓመፃን ከሚሠሩት ጋር እግዚአብሔር ይወስዳቸዋል። ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን (መዝ 125)
እግዚአብሔር ባህሪይው ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን አዋቂ፣ በሁሉ ስፍራ የሚገኝ፣ አልሻዳይ አምላክ ነው፡፡ በችሎቱ መሳይ የለውም፡፡ ሁሉን ያደርጋል ይታደጋል፡፡
በመዝሙር 125 እንደተገለጸው በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሰዎች አይታወኩም፡፡ ምክንያቱም አስተማማኝ እጅ ውስጥ ናቸው፡፡

በእግዚአብሔር መታመን ያሉት በረከቶች

ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ




2. አምባ ማለት በአቀማመጡ ከፍ ያለ ገዥ መሬት ማለት ነው፡፡ አምባ
2.1. ከፍ ያለ ቦታ ስለሆነ ጠላት በቀላሉ ሊያጠቃው አይችልም፡፡ ሊደርስበትና ሊወጣበት አይችልም
2.2. ገዥ መሬት ስለሆነ አከባቢን ለመቆጣጠር ያመቻል፡፡ ከአራቱም አቅጠጫዎች የሚሆነውን ለማየትና ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡
2.3. አምባ ላይ ያለው ሰው ጠላቱን ወደ ታች ያያል፡፡ ጠላቱን በንቀት ወደ ታች ያያል ምክንያቱም ገዥ መሬት ይዞአልና

3. መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና በእግዚአብሔር ታመኑ ሲል

3.1. በእግዚአብሔር የታመነና እግዚአብሔር አምባ የሆነለት ሰው ጠላት በቀላል አያገኘውም፡ ማለቱ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት ስለሆነ ጠላት አይቀርበውም፡፡
በዘፍጥረት 49፡24 ላይ የዮሴፍ ቀስት ፀንታ እንደቀረች ይናገራል፡፡ በዚህ ስፍራ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዮሴፍ ሲናገር
 ዮሴፍ ፍሬያማ የወይን ተክል እንደሆነ
 በምንጭ ዳር የተተከለ የወይን ዛፍ እንደሆነ
 ፍሬው ቅጥርን የሚያለብስ እንደሆነ ይናገርና
 ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት ፣ በጥላቻም ነደፉት ይላል፡፡
ይህ ማለት ቀስተኞች አልራሩለትም፡፡ ሊያጠቁትና ሊነድፉት ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመዋል፡፡ ይሁን እንጂ በቁጥር 24 ላይ “ነግር ግን በያዕቆብ ሃያል አምላክ ክንድ፣ እረኛ በሆነው በእስራኤል ዐለት ቀስቱ ጸና፣ ጠንካራ ክንዱም ቀለጠፈ“ ይላል፡፡ እዚህ ላይ እንደምንረዳው የዮሴፍ ጠላቶች ቀስት የተመለሰው በዮሴፍ ችሎት አልነበረም፡፡ ከዮሴፍ ጋር የነበረው የአስራኤል አምላክ ክንድ ፣ እረኛው የሆነው የእግዚአብሔር ክንድ የጠላትን ቀስት ከእርሱ ላይ መለሰው፡፡ እግዚአብሔር የረዳው የጠላትን ቀስት በመመለስ ብቻ አልነበረም፡፡ የዮሴፍ ቀስት እንዲፀና በማድረግ ጭምር እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ተካላካይ ብቻ ሳይሆን አጥቂ ያደርጋል፡፡

ደዊት ከጎልያድ ጋር በተጋጠመ ጊዜ የእስራኤል አምላክ የደዊትን ጠጠሮች ጎልያድ ከታጠቀው የተሻለ የጦር መሰሪያ ይልቅ ብርቱና ውጤታማ አደረጋቸው፡፡ ደዊት የወረወረው ጠጠር ጠንካራ ሆኖ ሳይሆን ደዊት ጠጠሮቹን የወረወረበት ስምና እምነት ጠንካራ ስለነበረ ነው፡፡
ስለዚህ መዝሙር 62፡8 ላይ “ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ታመኑ ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፣ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና “ ይላል፡፡ እንዲሁም በኢሳያስ 12፡2 ላይ “ ጌታ እግዚአብሔር ድነቴ ነው፣ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም“ ይላል፡፡ ኢሳያስ 50፡ 10 ላይ ደግሞ ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ካለ በኋላ ያ ሰው በጨላማ የሚሄድ ከሆነና ብርሃንም ከሌለው በእግዚአብሔር ስም ይታመን፣ በአምላኩም ይደገፍ ይላል፡፡ ሰው ወደ ብዙ ነገር ሊጠጋ ይችላል ፡፡ ብርቱ መጠጊያና የዘላለም አምባ ግን እግዚአብሔር ብቻ እንደሆ መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጥልናል፡፡
ኤርሚያ 17፡5-8
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።
በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ይሆናል፥ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በሌለበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደርቅ ስፍራ ይቀመጣል።
በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።
በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።

ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመንና እግዚአብሔር የዘላለም አምባ የሆነለት ሰው ለጠላት አይገኝም፡፡ አምባ የሆነለት እግዚአብሔር በቀኝ እጁ ይጋርደዋል፣ ይከልለዋል፡፡ መጋረድና መከለል ብቻ ሳይሆን ጉልበት ይሆነዋል፡፡ በጠላት ጭንቅላት ላይ እንዲጫማ ያደርገዋል፡፡

ይቀጥላል…………..

ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ በአድራሻችን ላኩልን፡፡

ጌታ ይባርካችሁ፡፡

10/06/2020

የልደታ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ማስታወቂያ ዘወትር እሮብ እና አሁድ ከማለዳ 12:00-1:00 ድረስ ምእመናን በየቤቶቻችን ከታች በተዘረዘሩት ርእስ እንድንፀልይ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።
የጸሎት ርዕስ
1. በአሁኑ ጊዜ ቁጥሩ እጅግ እየጨመረ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ
ወረርሽኝ እግዚአብሔር እንያስወግድልን አጥብቀን እንጸልይ፡፡
2. ስለ ግብጽና ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ምክንያት ያለ አለመግባባት
በተመለከተ መጸለይ፡፡
3. ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ መጸለይ፡፡
4. ስለ ሀገራችን ኢኮኖሚ አጥብቆ መጸለይ፡፡
5. የአንበጣ መንጋና የርሃብ ሥጋት እንዲወገድ፡፡
6. ስለ ቤተ ክረስስቲያናችን ሁለንተናዊ እድገት መጸለይ
በፋይናንስ እግዚአብሔር እንዲባርከን
መንፈሳዊ ተሃድሶና መነቃቃት ጌታ እንዲሰጠን፡፡

07/06/2020

ይህ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት በየሳምንቱ እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ መልእክት ነው፡፡

የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ዕቅድ መረዳትና በዕቅዱ መመላለስ
/በእግዚአብሔር መንግስት ተለዋጭ መለኮታዊ ዕቅድ የለም፡፡/
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።
ኤፌ 2፡10
ክፍል- 3 ካፈው የቀጠለ የመጨረሻ ክፍል

4. የበደሉንን ይቅር ማለት አለብን፡-
በሕይወታችን ከምንቸገርባቸው ነገሮች ውስጥ ዋንኞቹ
4.1. ሃዘን፡- ባለፉት ዘመናት ካጣናቸው ነገሮች የተነሳ የሚያጋጥመን
4.2. በደለኝነት፡- ባለፉት ጊዜያት ከሰራነው ኃጢአት የተነሳ የምንጸጸትብት
- ንስሀ በመግባት ማደስ
4.3. መጎዳት፤- ሰዎች ካደረሱብን ነገር የተነሳ - የበደሉንን ይቅር በማለት
ማቴ 6፡14-15
 በህይወታችን መዘንጋት ከሌለብን ነገር መካከል ሁል ጊዜ
• ጸጋ/አገልግሎት - ከጌታ እንቀበላለን ለሌሎች ደግሞ የተቀበልንውን እንሰጣለን
• ይቅርታ - ለሌሎች እናደርጋለን ከእግዚአብሔር ይቅርታን እንቀበላለን፡፡
5. ከፊታችን ያለውን ነገር መጋፈጥ፡-
ኢዮብ 11፡13-18 እናንብበው ይህንን ከፍል ከላይ ያስቀመጥናቸው ነገሮችን ያብራራልናል እነርሱም፡- ያለፈውን ነገር ሃላፊነት መውሰድ፣ ንስሀ መግባት፣ የእግዚአብሔር ጸጋን መቀበል እና የበደሉንን ይቅር ማለት ይህንን ስናደርግ እግዚአብሔር እንደገና የተሀድሶና የመመለስ ዕድልን ይሰጠናል፡፡
በዕብ 11 የምንመለከታቸው የእምነት አባቶች
• አብርሀም - ሚስቱን እህቴናት ብሎ ዋሸ
• ሙሴ - ሰው ገደለ
• ዮናስ - ከእግዚአብሔር ፊት ሸሸ
• ኖህ - ሰከረ
• ዳዊት - የሰው ሚስት አስነወረ ባልዋንም አስገደለ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ሁለተኛ ዕድል የተሰጣቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ምናልባት ዛሬ በተለያየ ነገር ተይዘን ከሆነ እግዚአብሔር እንደገና ዕድልን ይሰጠናልና እንመለስ፡፡
ኢሳ43፡ 18-19 … የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ። እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ እናንተም አታውቁትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ።…
ማር 16፡7 … ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም፦ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው አላቸው።… ጌታ መሀሪ ስለሆነ አስቀድሞም ስለማለደ ጴጥሮስ ቢክደውም በትንሳኤው ጠዋት ለተገለጠላቸው ሴቶች ሄዳችሁ ለደቀመዛሙርቴ ለካደኝም ለጴጥሮስ መነሳቴን ንገሩልኝ አለ፡፡
ጴጥሮስ ጌታ ኢየሱስን 3 ጊዜ ስለካደው ደግሞም አስቀድሞ ስትመለስ ወንድሞችን አበርታ አለው በዮሐ 21፡ 15-17 … ከእነዚህ ይልቅ … ብሎ ሲጠይቀውና ሊሰራ የሚገባውን አስቀድሞ እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ዘለዓለማዊ ሃሳቡን ሲያሳውቀው እንመለከታለን፡፡
በእግዚአብሔር መንግስት ለአንተ ተለዋጭ መለኮታዊ ዕቅድ የለም፡፡
ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ በአድራሻችን ላኩልን፡፡

ጌታ ይባርካችሁ፡፡

25/05/2020

ይህ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት በየሳምንቱ እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ መልእክት ነው፡፡

የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ዕቅድ መረዳትና በዕቅዱ መመላለስ
/በእግዚአብሔር መንግስት ተለዋጭ መለኮታዊ ዕቅድ የለም፡፡/
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።
ኤፌ 2፡10
ክፍል፡ 1
ባለፉት ጊዜያት የሆኑብን ነገሮች ሁሉ አሁን ላለንበት ነገር ትክክል ያልሆነ ውሳኔዎቻችን እንድንወስን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ እንመለከታለን፡፡ በያዕ 3፡2 ያለው የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል እንደሚነግረን… ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና… ይህ ብዙዎቻችን ባፉት ጊዜያቶች በተለያየ መንገድ ስንሰናከል አንደነበረ ይግረናል፡፡ በመክ 7፡20 … ማንም ስህተት ሳይፈጽም ሁል ጊዜ መልካም ነገርን የሚሰራ ደግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም …. / አመት 1997/ በሮሜ 3፡23 …ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤… ይለናል፡፡
ሉቃ19፡10 … የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።… ባለፉት ጊዜያት በብዙ መንገድ ከጌታ ክብር የጎደልንበት ነገሮች ቢኖሩም ነገር ግን የጌታን ሃሳብ መረዳትና በዚህ ሀሳብ መመላለስ መቻል አለብን፡፡ አንግዲህ የእግዚአብሔር ሀሳብ በእኛ ማንነት የሚቀየር ስላልሆነ የእግዚብሔር ሀሳብ እንዲፈጸም እኛ የሚጠበቅብንን ማድረግ መቻል አለብን፡፡ ባለፉት የህይወት ጉዞዎቻችንና ጊዜያቶች የደረግናቸው ነገሮች ነገሮቻችንን እንዳይያበላሹብን ማድረግ ያለብን ነገር ምንድን ነው?
1. ስላለፈው ውድቀታችን ወይም ስህተቶቻችን ሀላፊነት መውሰድ፡-
በላፉት ጊዜያቶቻችን ለደረሱብን ነገሮች ብዙውን ጊዜ በሌላ ሰው ወይም በሰይጣን ስናሳብብ መኖራችን ይታወቃል፡፡ እውነት ነው ሰዎች ወይም ሰይጣን ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ወሳኙ እኛ ነን ምክንያቱም ያንን ከፊታችን የተጋረጠውን ነገር ማድረግ ወይም አለማድረግ ሃላፊነቱ ያለው በእኛ ስለሆነ፡፡ ሰይጣን ቢሆን መንገድ ስንከፍትለት ነው ስፍራን ሊያገኝ
የሚችለው፡፡ ኤፌ4፡27 የሚነግረን ሰይጣን አይፈትንም ሳይሆን ነገር ግን … ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።… ይህ ክፍል ከሰው ጋር ላለን ጉዳይም የተያያዘ እንደሆነ ያለመክተናል፡ ስለዚህ ዋናው ላለፈው ውድቀት ወይም መሰናክል ሃሳፊነትን መውሰድ ግድ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በተለይ የምንሰናከልባቸው አጋጣሚዎች በማር 14 ላይ ጌታ ኢየሱስ ሁላችሁም በእኔ ትሰናከላላችሁ ብሏል ለምሳሌ ጴጥሮስ የተሰናከለባቸውን አራት ምክንያቶች እንመለከት፡-
1.1. ትዕቢት፡- ትዕቢት ለብዙዎቻችን ድብቅ የሆነ ማንነት ነገር ግን ሰውን ወደከፋ ነገር የሚመራ ሂደት ነው፡፡ ቁ.29 …ጴጥሮስም፦ ሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም አለው… ጵጥሮስ ራሱን ከሁሉም እንደበለጠ አድርጎ በማየቱ ነው ይህንን ሊናገር የቻለው፡፡ ነገር ግን ጌታ ትሰናከላለህ ለዚያውም ዶሮ ሳይጮህ 3 ጊዜ ትክደኛለህ አለው፡፡ ነገር ግን የጴጥሮስ ትምክህት ወይም ትዕቢት ወደውድቀት መራው፡፡ … ትዕቢት ከመጣ ውርደት ይመጣል… ምሳ 11፡2 ይህንኑ ይነግረናል፡፡
1.2. ድካም ወይም መጨናነቅ፡- ማር 14 የተፈጸመበት ሁኔታ በጌቴሰማኒ ት እንደሆነ ስንመለከት በዚህ ስፍራ በተለይ ጌታ ኢየሱስ አልፎ ሊስጥበት ባለው ምሽት ነው፡፡ ወደዚህ ስፍራ ከመምጣታቸው በፊት አብረው እራት በልተዋል እግራቸው ታጥበዋል ይህንን ሁሉ ከሆነ በኃላ ነው ወደዚህ ስፍራ የመጡት ስለዚህ ድካም ድካም ብሎአቸው ነበር፡፡ … ደግሞም መጥቶ ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፥ የሚመልሱለትንም አላወቁም።.. ቁ.40 መጸለይ የማይቻል ሰዓት ነው፡፡ ወደፈተና እንዳይገቡ መጸለይ ነበረባቸው ነገር ግን አልቻሉም፡፡ ሁልጊዜ ድካም ሲይዘን መጸለይ ሲያቅተን ፈተናን መወጣት አንችልም፡፡ ብዙዎቻችን እንዲህ ባለ ሰዓት ነው የምንሰናከለው፡፡
1.3. ከርቀት መከተል፡- ከጌታ በራቅን ቁጥር ነገሮች አጥብቀው ይፈትኑናል፡፤ ጌታ ኢየሱስ እንደተናገረው ደቀመዛሙርቱ ወድያው ተበታተኑ ጵጥሮስ ጌታን እከተልሀለሁ እንዳለው ሳይሆን ነገር ግን ከሩቅ መከተል ጀመረ፡፡ አብዛኞቻችን በቤተክርስቲያንም ሆነ በአገልግሎታችን በደረሰብን ነገር የተነሳ ከሩቅ የምንከተል ከሆን ይህም ለመሰናከል ወይም እግዚአብሔር ላየልን ራዕይ እንዳንኖር ያደረገን ውሳኔ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ቁ.54 … ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ በሩቁ ተከተለው፥… ፡፡
1.4. ጊዜያዊ ደስታ ላይ ማተኮር፡- ጌታ ኢየሱስ እንደዛ እያነገላቱት እየገረፉት ጵጥሮስ ግን ራሱን ከህዝቡ ጋር አመሳስሎ ነበር ቁ.54… ከሎሌዎችም ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ነበር።… ከጠላት ጋር አብሮ ተቀምጦ ነበር ስለዚህም ጌታ እንደተናገረው ጴጥሮስ ጌታን ሲክደው እንመለከታለን፡፡
ጌታ የሚሆነውን ያውቅ ስለነበር ነው ጴጥሮስን አስቀድሞ የነገረው፡፡ የሚገርመው ነገር ግን በሉቃ 22፡31-32 ጌታ አስቀድሞ ጸልዮለት ነበር፡፡ …ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።… ሊቀካህን የሆነው ኢየሱስ ስለእኔና ስለአንተ ይማልዳል፡፡ ጌታ ከዚህ ውድቀት በኃላ ዳግመኛ ተሀድሶ እንዲሆን ነው የነገረው፡፡ ነገር ግን ስለውድቀቱ ብቻ ሳይሆን ከውድቀቱ መልስ ሊሆነው ስለሚገባ ነገር ሲነግረው እንመለከታለን፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የሚያጋጥሙን ውድቀቶች የህይወታችን ፍጻሜ አይደሉም ጌታ ባለፍንበት መንገድ ለሌሎች የመነሳት ምክንያት እንድንሆን ዳግመኛ እድል ይሰጠናል፡፡ 2ቆሮ 1፡4 -6
ስለዚህ ባለፉት ጊዜያት የሆነውን ሁሉ በተለይ ለሰራናቸው አስከፊ ነገሮች ወይም መሰናክሎች/ውድቀቶች/ ሃላፊነት መውሰድ ያለብን እኛ ነን፡፡
ይቀጥላል…………….
ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ በአድራሻችን ላኩልን፡፡

ጌታ ይባርካችሁ፡፡

Address

Hotel D’Africque
Addis Ababa

Telephone

+251910093349

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ldeta Mulu Wengel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ldeta Mulu Wengel:

Share