አላማጣ ኪዳነ ምህረት Alamata Kidane Mhret

አላማጣ ኪዳነ ምህረት Alamata Kidane Mhret ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው

04/07/2024

«ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ»/መዝ. 88÷3/



«ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ» ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደ ፊትም ያደርጋል፡፡ /መዝ. 88÷3/ ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡ በቅዱሳን አበውና በቅዱሳት እማት/እናቶች/ ታሪክ፣ ገድልና ድርሳን እንደምናነበው እግዚአብሔር ለቅዱሳን ከመሞታቸው አስቀድሞ ይገለጥላቸዋል፤ የምሕረት ቃል ኪዳንም ይሰጣቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን በቅዱሳኑ ሕይወት ዙሪያ ብቻ የሚያተኩር አይደለም፡፡ ለስማቸው፣ ለመስቀላቸው፣ ለልብሳቸው ገድላቸውን ለያዘ መጽሐፍ፣ አልፎ ተርፎም ለረገጡት አፈርና ለተጋደሉበት ቦታ ሁሉ ተርፎላቸዋል፡፡ ስለዚህ ልዩ ልዩ ቃል ኪዳን የተገባላቸው ቅዱሳት መካናት ሞልተዉናል፡፡

'ኪዳን' የሚባለው ቃል «ቃል» ከሚለው ጋር እየተቀናጀ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ከ33 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ «ኪዳን» ቃሉ «ተካየደ» ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡
«ምሕረት» የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡
፡፡«ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ» ባለው መሠረት ጌታ ከእመቤታችን ጋር ብዙ ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ እርሷ የተመረጠች ብቻ ሳትሆን ከተመረጡትም ሁሉ የተመረጠች ናትና፡፡ ከቅዱሳን ሁሉ እመቤታችን ድንግል ማርያም በሁሉም ረገድ ስለምትበልጥ ከተሰጣቸውም የምሕረት ቃል ኪዳን ለሷ የተሰጣት ኪዳን ኪዳነ ምሕረት ተብሎ ተለይቶ ይታወቃል፤ ማለትም ትጠራበታለች፤ ኪዳነ ምሕረት ትባላለች፡፡ ስለዚህ የኃጥአን ሁሉ ዓይን የእርሷን የምሕረት ቃል ኪዳን ተስፋ ያደርጋል፡፡ የሚገባቸውን ሁሉ አድርገው ላወቁትና ላላወቁት ጉድለቶቻቸው ሁሉ ስሟን ለሚጠሩ ቃል ኪዳንን ለመቀበል ያበቃትን ለሰው ልጆች ነጻነት ልጇ ለሰጠው ፍፁም መድኃኒት ምክንያት የሆነችበት ጸጋዋ ሁሉ በሥላሴ ፊት ይታሰብላቸዋል፡፡
ቅድስት ድንግል ማርያም በቃል ኪዳኗ አትለየን 🙏🙏🙏

Address

Alamata And All Over The World
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አላማጣ ኪዳነ ምህረት Alamata Kidane Mhret posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share