Yaredawi midea ያሬዳዊ ሚዲያ

Yaredawi midea ያሬዳዊ  ሚዲያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yaredawi midea ያሬዳዊ ሚዲያ, Christian church, Addis Ababa.

የአመት ሰው ይበለን
26/07/2024

የአመት ሰው ይበለን

ደጓ እናቴ    እንኳን  ለእዚህ  ለተባረከች ቀን በሰላም አደረሳችሁ
28/06/2024

ደጓ እናቴ እንኳን ለእዚህ ለተባረከች ቀን በሰላም አደረሳችሁ

አው ማርያም ልደትሽ ልደታችን ነው
08/05/2024

አው ማርያም ልደትሽ ልደታችን ነው

 እለተ አርብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት ቀን ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው ስቃይና መከራ ለዓይን የሚዘግንኑ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ከባድ ቀንን ለእኔና ለእና...
03/05/2024


እለተ አርብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት ቀን ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው ስቃይና መከራ ለዓይን የሚዘግንኑ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ከባድ ቀንን ለእኔና ለእናንተ ፍቅር ሲል አሳልፏል፡፡
" ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። " ኢሳ. 53 : 7
13ቱ ህማማተ መስቀል
1 እራሱን በዘንግ ተመታ ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው እራሱን መቱት ። (ማቴ 27÷30)
2 በጥፊ ተመታ ፦ በጥፊም ይመቱት ነበር። «የሀ 19÷4)
3 ምራቅ ተፉበት ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው እራሱን መቱት። " ማቴ 27÷30)
4 የሾክ አክሊል ጎንጉነው በእራሱላይ አቀዳጁት
«ማቴ.27፥29 »
5 መራራ ሀሞት አጠጡት ፦ በሀሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም ። «ማቴ 27÷34)
6 ጀርባውን መገረፉ ፦ በዚያን ጊዜም ጲላጦስ እየሱስን ይዞ
ገረፈው ። «ዩሀ 19÷1)
7 ጎኑን በጦር መውጋት፦ ነገር ግን ከጭፈራዎቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ወድያውም ደምና ውሃ ወጣ። «የሀ 19÷34 »
8 ወደ ኃላ መታሰሩ
የሾለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም
ሌሎችም እየሱስን ይዘው አሰሩት። "ዩሀ.18÷12 »
9 ሳዶር
10 አላዶር
11 ዳናት
12 አዴራ
13 ሮዳስ
5ቱ ቅንዋተ መስቀል ችንክሮች ሳዶር ፣ አላዶር ፣ ዳናት
፣ አዴራ እና ሮዳስ ይባላሉ።
1ሳዶር ፦ ማለት ቀኝ እጁ የተቸነከረበት
2አላዶር፦ ማለት ግራ እጁ የተቸነከረበት
3 ዳናት ፦ ማለት እግሮቹ የተቸነከረበት
4 አዴራ ፦ ማለት ደረቱን የተቸነከረበት
5 ሮዳስ ፦ ማለት ከወገቡ (እብርቱ) አጣብቆ እንዲይዝ የተቸነከረበት
መከራን ታገሰ
ሁሉን የያዘውን እርሱን ያዙት
ሁሉን የሚገዛውን እርሱን
የአምላካችንን እጅ አሰሩት
ሀጥያትን የሚያስተሰርይ እርሱን ሀጢያተኛ አሉት
የማይገረፍ አምላክ እርሱን የሰውን ስጋ በመልበሱ ገረፉት
እንደ መብረቅ የሚያንፀባርቀውን ነጭ ልብስ
የሚያለብስውን አምላክ እርሱን ቀይ ግምጃ አለበሱት።
በእሳት በተጋረዱ ዙፋን ላይ የሚቀመጥ እርሱን
በመዘባበቻ
ወንበር ላይ አስቀመጡት።
እንደ ድንኳን ሰማይን የዘረጋ እርሱን በመስቀል ላይ ሰቀሉት::
የመላአክት አለቆች በፊቱ በመፍራት የሚቆሙለት እርሱን
በጲላጦስ ፊት አቆሙት ፡፡
በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈርድ እርሱን እንደበደለኛ ተፈረደበት
አለምን ሁሉ በቅፅበት የፈጠረ እርሱ በስጋው ሞተ በመለኮት ህያው ሆነ
▣ ጌታችን_መድኃኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ ከ6-9 ስአት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር ቃላት
ኤሉሄ ኤሉሄ ለማስበቅታኒ (አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ) ማቴ 27÷46
እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ። ሉቃ.23÷43
አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ሉቃ 23÷43
አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው። ሉቃ.23÷34
እናትህ እንኋት እንሆ ልጅሽ:: ዩሀ 19÷26-27
ተጠማሁ። ዮሀ 19÷28
ተፈፀመ። ዮሀ 19÷30
ጌታችን
መድኃኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ በመስቀል ላይ
ሳለ የተፈፀሙ 7ቱ ተዓምራት
1ፅሀይ ጨለመች
2 ጨረቃ ደም ለበሰች
3 ከዋከብት ብርሃናቸውን ነሱ
4የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከሁለት ተከፈለ
5 አለቶች ተሰነጣጠቁ
6 መቃብራን ተከፈቱ
7 የሞቱት ተነሱ
ክብርና ምስጋና አምልኮት ውዳሴ ስግደት ዝማሪ ይድረሰ ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ
አቤቱ አምላካችን ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ
አስበን

የሕማማት ሐሙስ1. ሕጽበተ እግር ይባላልይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአትለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው ይህን...
02/05/2024

የሕማማት ሐሙስ

1. ሕጽበተ እግር ይባላል

ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት
ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡንብ ኃጢአት እጠብ ሲሉ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን
እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ / ዮሐ.13:4-15/

2. የጸሎት ሐሙስ ይባላል

የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍፁም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴሴማኒ ሲጸልይ በመቆየቱ ነው /ማቴ26:36 ዮሐ 17:1/

3. የምስጢር ቀንም ይባላል

ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመስርቷል ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ስጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ
በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው

በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል የሚቀደሰውን በለሆሳስ /በዝግታ/ ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው ይህም
አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው

በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም። ሥርአተ ቁርባን ግን.ይፈጸምበታል ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሀ ታጥቦ
ተዘጋጅቶ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል

4. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል
ምክንያቱም መስዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንሰሳ ደም የሚቀርበው መስዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኀነቱ ዓለም ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው /ሉቃ 22:18-20/
ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው

ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም
የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን

5. የነጻነት ሐሙስ ይባላል
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው ራሱም
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነፃነት ሲናገር ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን
አያውቅምና ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ /ዮሐ 15:15/ ከባርነት ነፃ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ.ያስረዳል። ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ
ከእግዚአብሔር ሕይወቱን በቅድስና መምራት ይኖርበታል። እርሱ
ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል /ማቴ 26:17-19/
6 አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአትክልት ቦታ ስለ ጸለየ። ዝቅ ብሎ ትትናንና አክብሮትን ያስተማረን ጌታ ልባችንን ይስበርልን አሜን

መልካም በዓል

አው አራዳ ያከፍላል💪💪💪
30/04/2024

አው አራዳ ያከፍላል💪💪💪

https://youtu.be/WK1C4Z5PvTI ኪራላይሶ ኪራላይሶ ኪራላይሶ
30/04/2024

https://youtu.be/WK1C4Z5PvTI ኪራላይሶ ኪራላይሶ ኪራላይሶ

ዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ እንድታጠነክሩን እንድታበረቱን ስንል በድንግል ማርያም ስም እንጠይቅወታለንYoutubeቅዱስ​ ​ ​ ​ ...

https://youtu.be/WK1C4Z5PvTIኪራላይሶ ኪራላይሶ ኪራላይሶ
28/04/2024

https://youtu.be/WK1C4Z5PvTIኪራላይሶ ኪራላይሶ ኪራላይሶ

ዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ እንድታጠነክሩን እንድታበረቱን ስንል በድንግል ማርያም ስም እንጠይቅወታለንYoutubeቅዱስ​ ​ ​ ​ ...

27/04/2024
ዕድሜ ጠገቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ቤተክርስትያን! ቱሉ ዲምቱ (ቀዩዋ ተራራ)  ቱሉ ዲምቱ ቃል አፋን ኦሮሞ ሲሆን ቱሉ ማለት ከፍታ ኮረብታ ተራራ ወደሚለው ይቀርባል ዲምቱ ደግሞ ለእንስት ጾታ የሚ...
23/04/2024

ዕድሜ ጠገቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን! ቱሉ ዲምቱ (ቀዩዋ ተራራ)


ቱሉ ዲምቱ ቃል አፋን ኦሮሞ ሲሆን ቱሉ ማለት ከፍታ ኮረብታ ተራራ ወደሚለው ይቀርባል ዲምቱ ደግሞ ለእንስት ጾታ የሚሰጥ የቀይ ቀለምነት ስያሜ ነው። በዚህም ቱሉ ዲምቱ የሚለው ቀዩዋ ተራራ ወደሚለው አቻ የአማርኛ ትርጉም ይቀርባል።

ቱሉ ዲምቱን እንደኔ ላለ የቱሪዝም ባለሙያ ቶሎ ወደ አእምሮ የሚመጣው ባሌ ተራራ ብሔራዊ ፖርክ ውስጥ የሚገኘው በከፍታዉ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ያለው ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ዙርያ በስተምስራቅ ለሚገኙት ኮንደምንየም አልያም የአዲስ-አዳማ ፈጣን መንገድ መግብያ በር ጋርም ተያይዞ ይነሳል።

በመሰረቱ በፊት ቱሉ ዲምቱ እየተባለ የሚታወቀው አቃቂ ኬላ አካባቢ ወይም ዩኒሳ ፊት ለፊት የሚገኘው የቀይ አሸዋ ኮረብታማ ስፍራ ሲሆን; አሁን ላይ መተላለፍያ ሆኖ ከሚያገለግለው የአቃቂ መጨረሻ አደባባይ ወይም ከገላን ኮንደሚኒየም መስመር ወደ ቱሉ ዲምቱ ፈጣን መንገድ መግቢያ በስተቀኝ ተከምሮ የሚታየው የቀይ አሸዋ ተራራ ነው።

ተራራው በላዩ ትልቁ ታሪክ ይገኝበታል ይሁን እንጂ
አቃቂ ከተማ ላይ የሚኖር ሰው ቱሉ ዲምቱ እንሂድ ብሎ አንዱ ሌላውን ቢጠይቅ 'ምነው ማን ሞተ' በማለት ቦታውን አንዳንድ ጊዜ ከቀብር ቦታ ጋር የሚያያዝ ሲሆን በርግጥም በርካታ በተዋህዶ ክርስትና እምነት ኖረው የሞተ ሰውች የተቀበረበት ቦታ ሲሆን ቦታው ላይ ሲደረስም ግራና ቀኙ መግቢያ በሩ በመቃብር ስፍራ የተሞላ ነው።

ቱሉዲምቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕድሜ ጠገብ ታሪክ ባለቤት ሲሆን በቦታው ለመሳለም ሄጄ የተረዳሁትን በዛም ያሉ አባቶች ያወጉኝን እና ከታተመው መጽሄት ያገኘሁትን ላካፍላቸሁ!

ምስረታውን በተመለከተ ከአዲስ አበባ 4ኛ በ1862 ዓ.ም. የሚል መረጃ ያገኘሁ ቢሆንም በቦታው ያሉ አባቶችና የታተመ መጽሄታቸው 1881 ዓ. ም. ጀምሮ እንደሆነ እንዲህ ይገልጹታል።

በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት የሸዋው ገዥ የመንዙ ተወላጅ ፊታውራሪ ጠንፉ በዘመናቸው ካስተከላቸው 5 አብያተ ክርስትያናት አንዱ ይህ ሲሆን ጽላቱንም ከመንዝ ከአንጋቻ ቅ/ጊዮርጊስ ታላቅ ደብር እንዳስመጡት ይገለጻል።

አመጣጡ ብዙ ውጣ ውረድ የነበረው ሲሆን በ1868 ዓ.ም. ከመነሻው ቦታ ጉዞ ጀምሮ በአንድ ወር ተኩል ጊዜ ቡልጋ ንብጌ ማርያም ደርሶ ሁለት ዓመት በመቆየት በመቀጠልም ጉዞ ቀጥሎ ዱከም በሚገኘው ጥንታዊው ዳሎታ ቅዱስ ገብርኤል ለ10 ዓመታት የአሁን ቦታ እስኪመቻች ተቀምጣል። በኃላም በወቅቱ የነበሩት አባቶች አለቃ ወልደ ህይወትና ርዕሰ ደብር ደስታ ፊታውራሪውን በመወትወት አሁን ያለቦት ቦታ ላይ እንዲተከል አስድርገዋል።

በዚህም በስተምስራቅ ዋሻው ካለበት ዋርካ አካባቢ ድንካን ተተክሎ ጽላቱ በዋሻው ውስጥ እየተጠበቀ ከ1881 - 1886ዓ.ም. የቆየ ቢሆንም የፊታውራሪው የልጅ ልጅ ደጃዝማች በየነ ግድግዳው የጭቃ ጣራው የሳር የሆነ ቤተክርስትያን በማሰራት ጽላቱ ከዋሻ ወጥቶ ከ1886-1906 ዓ.ም. ሲገለገል ቆይቷል። በኃላ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ የተሰራውን መቃኞ ጣራ ገንጥሎ በአቅራብያው ሁለት ክፍል ያለው ዋሻ አጠገብ አሁን ቤተክርስትያኑ ካለበት ደልዳላ ቦታ ላይ ወደሚገኘው ጥሎታል።

በዚህም በወቅቱ የነበሩ አባቶች ፈጣሪን በሱባኤ ጠይቀው በተገለጸላቸው መሰረት አሁን ያለበት ቦታ ላይ ቤተክርስትያኑን ሊሰሩት የቻሉ ሲሆን አጠገቡ የነበረን ዋሻም በቀከፊል ቅኔ ማህሌት መቅደስና ቤተልሄም ከ1906- 1914 ዓ.ም. አድርገው ተገልግለውበታል።

በዚህ ስፍራ ተጠናቆ የተሰራው ባለ ሳር ክዳን ቤተክርስትያን ለ33 ዓመት ካገለገለ በኃላ አቶ ሞገስ ደስታ የተባሉ

እናቴ ቀኑን የበረከት ቀን አድርጊልን
23/04/2024

እናቴ ቀኑን የበረከት ቀን አድርጊልን

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yaredawi midea ያሬዳዊ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share