God's Visitation Fire Ministry

God's Visitation Fire Ministry God's Visitation Fire Ministry will have a crusade in Sawla southern part of Ethiopia in the month of February. Please pray and support.

To Proclaim The God News of Jesus Christ

24/10/2020

በድፍረት እንስበክ!

“ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”” ሐዋርያት 1፥8

ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነው። በእርሱ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የምንደርስበት መንገድ የለም። ስለዚህ በዚህ እውነት በመተማመን የመስበክ ኃላፊነታችንን እንወጣ። የእርሱንም ስም በምናውጅበት ጊዜ ሊደርስብን የሚችለውን ስደት አንፍራ።

፪ጢሞ.3:12 እንዲህ ይላል፤ “በርግጥም በክርስቶስ ኢየሱስ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት መኖር የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።” የቀደሙት ሐዋሪያት የኢየሱስን ስም ፈጽመው እንዳያውጁ ተገርፈዋል፣ ዛቻና ማስፈራሪያም ደርሶባቸዋል። ነገር ግን እምነት ለሌላቸው ለኃይማኖታዊና ለመንግሥት ባለሥልጣናት እጅ ከመስጠት ይልቅ በላቀ ድፍረት ክርስቶስን ሰበኩ። መላ ኢየሩሳሌምንም በትምህርታቸው ሞልዋት (ሐዋ.5:28)።

የወንጌልን ስርጭት ለማክሸፍ የሚሠራ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ዛሬም በዓለም ላይ አለ። ነገር ግን ይህ ለእኛ ግድ ሊለን አይገባም። ምክንያቱም እኛ በክርስቶስ ቀድመን አሸንፈናል። “ልጆች ሆይ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፤ እነርሱንም አሸንፋችኋቸዋል፤ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል” (1ኛ ዮሐንስ 4፥4)።

ለክርስቶስ ካለው ፍቅርና ለወንጌል ካለው መሰጠት የተነሳ ለምንም ነገር ወደ ኋላ የማይለውን የሐዋርያው ጳውሎስን አርዓያ እንከተል። እርሱ በሐዋ.20:22-24 ላይ እንዲህ ብሏል፤“አሁንም እዚያ ስደርስ የሚደርስብኝን ባላውቅም፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው። ነገር ግን በምሄድባቸው ከተሞች ሁሉ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል። ይሁን እንጂ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት"።

እንዲህ ዓይነት ጽኑ እምነት ይኑረን። ይህ ለእኛ ታምኖ የተሰጠን ወንጌል ዋጋው እጅግ የከበረ ነው። ስለዚህ በሁሉም ሥፍራ በድፍረት እንስበከው።

20/10/2020

የክርስቶስን ርስት ተካፋይ መሆን

ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን።” ቆላስይስ 1፥12

አንድ ሰው ብቃት አለው ስንል መብቱ የተረጋገጠለት፣ የታወቀ፣ የተመረጠና የተለየ ሆነ ማለታችን ነው። ዳግም የተወለዱ፣ መንፈስ ቅዱስ የሞላባቸው የክርስቶስ አማኞች የርስቱ ተካፋይነት መብት ያላቸው ሲሆኑ በህጋዊነት ርስታቸው የእነርሱ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች ግን በህግ የእነርሱ የሆነውን ስለማያውቁ እምነታቸውን በማንቀሳቀስ መብታቸውን እየተጠቀሙ አይደለም።

ምድራዊ ወላጆች ዕድሜ ጠግበው ሲያልፉ ምድራዊ የሆነን ሀብትና ንብረት በህጋዊነት ተጽፎ ይናዘዛሉ።

በተመሳሳይ ተናዛዣችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወት በዚህ ምድር ላይ እስከነበረ ድረስ ኑዛዜው ወይም ኪዳኑ የጸና አልነበረም። ኪዳኑን የሚያጸናው የተናዛዡ ሞት ነውና (ዕብ.9:16-17)። በክርስቶስ የሆነ ማንም ሰው አሁን እንኳን ክርስቶስን ቢቀበልም በዚህ ርስት ተጠቃሚ ነው። ይህም ርስት የእግዚአብሔር ቃል ሲሆን ቃሉ በብዙ ተስፋዎች የተሞላና ለዘላለምም በኢየሱስ ደም ታትሞ የተጻፈልን ደብዳቤ ነው (2ቆሮ.1:20)።

አንተም ከቅዱሳን ጋር ከዚህ ርስት በብርሃን ለመካፈል የተጠራህ በመሆኑ ርስትህን ከመጽሐፍ ቅዱስ መርምረህ በማየት መብትህን አስጠብቅ። በሕይወትህ የምትፈልገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ማለትም በኪዳኑ ውስጥ መኖሩን አምነህ ልክ እንደ ዮሴፍ፣ ምናሴና ኤፍሬም ልጆች ርስትህን ተካፈል (ኢያሱ 16:4)።

በሚሊዮን ብር የሚያወጣ ስዕል ወርሳ ዋጋውን እንዳላወቀች መንፈሳዊ መሃይም አትሁን። ስዕሉ ምን ያደርግልኛል ብላ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ጣለችው። አንድ ጎዳና ተዳዳሪ ግን ስዕሉን አግኝቶ በመውሰድ ተባረከበት።

መጽሐፍ ቅዱስ "ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል” ይላል ሆሴዕ 4፥6። በእርግጥ መንፈሳዊ መሃይምነት ከፍተኛ መንፈሳዊ ኪሳራን ያስከትላል። በክርስቶስ ኢየሱስ መለኮታዊ ርስት ተዘጋጅቶልሃል። ገመድም ባማረ ሥፍራ ወድቃልሃለች፣ አሜን።

05/10/2020

ከመጨረሻው ጀምር

“በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እርሱ እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን ድረስ ከፍጻሜው እንደሚያደርሰው ርግጠኛ ነኝ” ፊልጵስዩስ 1፥6

ፊልጵስዩስ 1:3–11

"ስታድግ ምን መሆን ነው የምትፈልገው?" ልጅ ሳለሁ በተደጋጋሚ የምጠየቀው ጥያቄ ነበር። መልሴም እንደነፋስ ተለዋዋጭ ነበር። ፓይለት፣ ዶክተር፣ ኢንጂነር መንፈሳዊነት ሲሰማኝ ደግሞ መነኩሴ እል ነበር። ታናሽ ወንድሜ ግን "እናጢ መሆን" ይል ነበር። ዛሬ የፈርኒቸር ባለሙያ ሊሆን። አሁን ታዲያ ታደገና ተጎለመሰና የእግዜር አገልጋይ መሆን ተቻለ። አገልጋይም ሆኜ ወጣቶችን ሳገለግል የተፈጠሩበትን ዓላማ እንዲያውቁ አበረታታቸዋለሁ። ወላጆች ልጆች ያላዩትን አቅም በልጆቻቸው ውስጥ ማየት ይችላሉ።

ይህንን ምሳሌ ጳውሎስ ስለሚወዳቸውና ስለሚጸልይላቸው ለፊልጵስዩስ አምኞች ካደረገው ጋር ልናነጻጽረው እንችላለን። ምንም ይባል ምን መጨረሻቸውን ሊያይ ችሎአል። መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ መፈጸሚያ የሆነውን ታላቅ ራዕይ ይሰጠናል፣ ትንሣኤና የሁሉ ነገር አዲስ መሆን (1ቆሮ 15 እና ራእይ 21)። በተጨማሪም ታሪኩን ማን እንደጻፈውም ይነግረናል።

ጳውሎስ ለፊልጽስዩስ ቤተክርስቲያን የጻፈው ከእሥር ቤት ሆኖ ነበር። ሥራውን የጀመረው ኢየሱስ ከሆነ የሚፈጽመውም እርሱ ነው። መፈጸም የሚለው ቃል የተለየ ቃል ነው። እግዚአብሔር የጀመረውን ሳያጠናቅቅ የሚተው አምላክ ባለመሆኑ ታሪካችን አያበቃም።

ዛሬ በታሪካችን ውስጥ የት ላይ ደርሰን ይሆን? ኢየሱስ ታሪካችንን የምንጽፍበትን ብዕር ከእጆቻችን ይውሰድና ጽፎ ይፈጽምልን።

ኢየሱስ ሆይ የታሪኬ ባለቤት አንተ ነህ። እንዲሆን ማድረግ የምችለው እኔ አይደለሁም። ሕይወቴን ላንተ አስገዛለሁ። ባንተ እታመን ዘንድ እርዳኝ።

29/09/2020

የተከፈተ ዓይን

“ከሕግህ ድንቅ ነገርን እንዳይ፣ ዐይኖቼን ክፈት” መዝሙር 119፥18።

መዝሙር 119:97–104

የአናሞርፊክን አርት ማድነቅ የጀመርኩት ከቅርብ ጊዜ ወዱህ ነው። በመጀመሪያ በዘፈቀደ ተዘበራርቆ የተሰራ ቢመስልም የአናሞርፊክ ጥበብ ከትክክለኛ አቅጣጫ ትኩረት በመስጠት ካየነው ግን ትርጉም የሚሰጥ መልእክት ያለው ነው። በአንድ በኩል ብዙ ወደታች የተሰመሩ መስመሮች የምናይ ቢመስለንም ትኩረት ሰጥተን በትክክል ካየነው የአንድ ታዋቂ ሰው ምስል ሊሆን ይችላል። በሌላ ወገን ደግሞ ብዙ የሽቦ ውስብስብ የሚመስለን ነገር የዝሆን ምስል ሆኖ ይገኛል። ሌላው ደግሞ በብዙ ጠቃጠቆ ነጥቦች የተንቆጠቆጠ ስዕል ቢሆንም በትኩረት ካየነው የአንዲት ሴት ዓይን ምስል ሊሆን ይችላል። የአናሞርፊክ ጥበብ ዋና ቁልፉ ትርጉም እስኪሰጠን ድረስ ምስሉን ከተለያየ አቅጣጫ ማየት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስም በታሪክ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ና በሌላም ነገር የበለጸገ በመሆኑ አንዳ ንዴ ለመረዳት አዳጋች አናሞርፊክ ዓይነት ሊሆንብን ይችላል። ሆኖም የትርጓሜውንም ቁልፍ እንዴት ማግኘት እንደምንችልም ቃለ እግዚአብሔር ያስተምረናል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ አናሞርፊክ ምስል አድርገን በማሰብ ከተለያየ አቅጣጫ በማየትና በጥልቁ በማሰላሰል ለመረዳት እንሞክር።

የክርስቶስም ምሳሌዎች በዚህ ዓይነት የሚሠሩ ናቸው። በቃሉ ላይ አጥብቆ ለማሰብ ጊዜ የሚሰጡ ትርጓሜውን የሚረዱበት ዓይን ይከፈትላቸዋል (ማቴ.13:10-16)። ጳውሎስ ጢሞቴዎስን " “እኔ የምለውን ልብ በል፤ ጌታ በሁሉም ነገር ማስተዋልን ይሰጥሃልና” ይለዋል (2ጢሞ.2፥7)። መዝሙረኛውም የሚለን ቃሉን ለማሰላሰል ጊዜ ከሰጠነው ጥበብንና የውስጥ እይታን እንደሚያስገኝልን ነው። ዓይኖቻች ተከፍተው ትርጓሜውን መረዳት እንጀምራለን (መዝ 119:18, 97-99)።

ታዲያ አንድን ምሳሌ አንብበን ለአንድ ሳምንት ወይም ደግሞ አንድን የወንጌል ክፍል አንዴ ቁጭ ባልንበት በማንበብ አናሰላስልም? መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታ የሚገኘው በማንበብ ብቻ ሳይሆን የምናነበውን በማሰላሰል ስለሆነ ጠልቀን እንሂድ።

እግዚአብሔር ሆይ የሚያዩ ዓይኖችን ስጠን።

መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብና በማሰላሰል መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው ብለህ ታስባለህ። ዛሬ ባነበብከውስ ቃል ላይ ለማሰላሰል ጊዜ ወስደሃል ወይ?

እግዚአብሔር ሆይ ከቃልህ ተአምራትህን አይ ዘንድ ዓይኖቼን ክፈት። ቃልህ በሚመራኝ መንገድ ጋር አገናኘኝ።

27/09/2020

አትሳቱ

“ዲያብሎስ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት በመሆኑ ሐሰትን ሲናገር፣ የሚናገረው ከራሱ አፍልቆ ነው” ዮሐንስ 8፥44።

ዘፍጥረት 3:1–7

አብሪ የማሪያም ፈረስ የክንፎችዋ ውጫዊ ክፍል ጠቃጠቆ ያለበት በውስጠኛው ክንፏ ደግሞ ስትበር የሚያንጸባርቅ ብርሃን ያላት ውበትን የተላበሰች የተባይ ዝርያ ናት። ውበትዋ ግን አታላይ ነው። ይህች ተባይ በተለይ እንደ አሜሪካ ባሉ ሀገራት ለመጀመሪያ መታየት የጀመረችው በ2014 ዓ.ም ሲሆን በሰሜን አሜሪካ በብዛት ወረርሽኝ ሆና የተከሰተች ሲሆን ያ ማለት አካባቢን የማጥፋትና ኢኮኖሚውን የመጉዳት አቅም ነበራት። ይህች የምታበራ የማሪያም ፈረስ ያገኘችውን ዛፍ የሆድ ዕቃ ሁሉ በመብላት የታወቀች ሲሆን በተለይ በአሜሪካ የሚዘወተረውን የእንጆሪና እንዲሁም የሌሎች ፍራፍሬዎችን ዛፍ ታጠቃለች። ከበላችም በኋላ የሚያጣብቅ ሙጫ ስለምፈጥር ያ ተክሎችን በሙሉ እንዲመክኑ አልያም ከተገመተው ያነሰ ምርት እንዲሰጡ ያደርጋል።

በአዳምና በሄዋን ታሪክ ላይ ደግሞ አንድን ሌላ ጠንቅ እናያለን። እባብ ማለትም ሠይጣን ጥንዶቹ እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ የተከለከሉትን ፍሬ እግዚአብሔርን ለመሆን ብለው እንዲበሉ ሲፈትናቸው እናያለን (ዘፍ.3:1-7)። ይሁንና እባቢቱን ማዳመጥ ለምን አስፈለጋቸው? ለመሆኑ ንግግሩ ሔዋንን አማልሏት ይሆንን ወይስ አንዳች መስህብ ነበረው? በእርግጥ ሰይጣን ሲፈጠር የውበት መደምደሚያ እንደነበረ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል (ሕዝ.28:12)። ይሁንና ሰይጣን የወደቀው ሔዋንን ሊጥል በፈተነበት ፈተና እንደነበረ እናያለን፣ "በልዑልም እመሰላለሁ"።

ዛሬ ሰይጣን ያለው ውበት የመሸንገያ መሣሪያው ነው (ዘፍ.3:1፣ ዮሐ.8:44፣ 2ቆሮ.11:14)። ከወደቀ ጀምሮ ሌሎችን ይዞ መውደቅ አልያም እንዳያድጉ መከልከል ሥራው ሆነ። ሆኖም በአጠገባችን ያለው እጅግ ኃያል ነው። በመሆኑም ውበትን ወደተሞላውና አዳኛችን ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ መሮጥ እንችላለን።

መስህብ ያለበት በመሰለ ግለሰብ ወይም ቡድን ተስበህ ታውቃለህን? ሽንገላንስ እንዴት ነው ለይተህ የምታውቀው?

እግዚአብሔር ሆይ ለሰማሁትና ላየሁት ወንጌል ሚዛኔን እንድደፋ እርዳኝ። በመስቀሉ በኩል በክፉው ላይ ድልን ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ።

23/09/2020

ወሬን ማቆም

“የሐሰት ወሬ አትንዛ”
ዘጸአት 23፥1

ዘፀዓት 23:1–3

ከ1759-1836 ይኖር የነበረው ቻርለስ ሲሞን በእንግሊዝ ሀገር በካምሪጅ ያለችውን ቤተክርስቲያን ትሪኒቲ ቤተክርስቲያን ብሎ ከሰየመበት ጊዜ አንስቶ ለዓመታት ተቃውሞዎችን ተጋፍጦ ነበር። አብዛኛው የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ሲሞን ከሚያገለግል ረዳት አገልጋይ ለመሾም ፈልገው ነበር። ስለአገልግሎቱም ወሬ በመንዛት ከአገልግሎቱ ሊያባርሩት ቻሉ። ሲሞን ግን በእግዚአብሔር መንፈስ የመሞላት መሻት ያለው በመሆኑ አንድን የኑሮ ዘይቤ በመቅረጽ ከወሬኞች ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል ዘየደ። አንደኛው እውነት መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ምንም ዓይነት ወሬን ማመን እንደሌለበትና ሌላው በሌላ ወገን ያለው ተደማጭነቱ የሰፋ ከሆነ ለሁኔታው የተለየ ትኩረት ሰጥቶ መከታተል ነበር።

በዚህ መንገድ ሲሞን የእግዚአብሔርን መርህ በመከተሉ ምክንያት ህዝቡ እርስ በርሱ የነበረውን ፍቅር ከመሸርሸር በመታደግ ወሬዎችና ሃሜተኞች ጸጥ እንዲሉ አድርጎአል። ከአሥርቱ ትእዛዛት አንዱ እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን እውነተኛ አሳብ የሚያሳይ ነበር። “በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር” (ዘጸ.20፥16)። ሌላው በዘፀዓት ላይ ያለው መመሪያ ደግሞ ይህንኑ ያጠናክርልናል። "የሐሰት ወሬ አትንዛ" (ዘፀ.24:1)።

እኛ እያንዳንዳችን ሀሰተኛ ወሬንና ሀሰተኛ ምስክርነትን መንዛት ሆነ የሚነዙትንም መስማት ብናቆም ዓለማችን የተለየች ትሆን ነበር። እውነትን በፍቅር በመናገር እግዚአብሔርን ማክበር እንድንችል ይረዳን ዘንድ በሚችለው መንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ ይሁንልን።

ተቃውሞ ሲገጥማችሁ የሚረዳችሁ ምን ይሆን? ወሬ በሰማችሁስ ጊዜ ምላሻችሁ ምንድነው?

ኢየሱስ ሆይ የአንተን እውነት በፍቅር እናገር ዘንድ እርዳኝ። ሰላምን፣ ፀጋንና ብርታትን የሚያመጣውን ቃል ስጠኝ።

12/09/2020

በልባችን የታተመ

“በጣትህ ላይ እሰረው፤ በልብህ ጽላት ላይ ጻፈው” ምሳሌ 7፥3።

ምሳሌ 7:1–5

ዮሐንስ ጉተንበርግ የተባለው ሰው የህትመት ሥራን እንዲንቀሳቀስ ካደረገበት ከ1450 ዓ.ም ወዲህ በምዕራቡ ዓለም ባለው የሕዝብ ግንኙነት ላይ ፈጣን ለውጥን አምጥቶአል። ሥነ ጽሁፍ በዓለም ዙሪያ እያደገ ሲመጣ በሶሻልና በኃይማኖቱ ዓለም ላይ ፈጣን ለውጥ ሊመዘገብ ችሎአል። ጉተንበርግ የመጀመሪያውን የታተመ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ያዘጋጀ ሰው ነው። ከዛ በፊት ግን መጽሐፍ ቅዱስ ይጻፍ የነበረው በእጅ በመሆኑ ለጸሐፍቶች ዓመታት ይፈጅባቸው ነበር።

ከዛ ዘመን ወዲህ ግን የሕትመት ቴክኖሎጂው እንደ እኔና እንደ እናንተ ላለን ሰዎች ቃለ እግዚአብሔር እጃችን ላይ እንዲደርስ ረድቶናል። ሁላችንም የኤሌክትሮኒክስ መጽሐፍ ቅዱስ ቢኖረንም በዚህ ግኝት ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስን ከቤታችንና ከራስጌያችን አላጣንም። ከዚህ ቀደም እንደልብ የማይገኘውና ውድ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ አሁን አሁን በየእጆቻችን እንዲደርስ ተደርጎአል።

ወደ እግዚአብሔር እውነት ለመድረስ መቻል በእውነት ታላቅ ዕድል ነው። የምሳሌ ጸሐፊ የእግዚአብሔርን መመሪያ የሆነውን ቃል እንደ ዓይናችን ብሌን መንከባከብ እንዳለብን ይናገራል (ቁ.2)። ይህንንም የጥበብ ቃል በልባችን ጽላት ላይ መጻፍ እንዳለብን ያስተምረናል (ቁ.3)። መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳትና በውስጡ ባለው ጥበብም ለመኖር ስንወስን የጻፉልን ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ከእጆቻችን ባለፈ ወደልቦቻችን እንዳደረሱልን እንረዳለን።

ለመሆኑ በልብህ የእግዚአብሔርን ቃል ይዘህ እየተጠቀምክበት ነውን? የእግዚአብሔርን ጥበብ ይበልጥ ወደ ውስጥህ ለማስገባትስ ምን የወሰንከው ውሳኔ አለ?

ውዱ እግዚአብሔር፣ የአንተን መሻት መኖር የሚያስችለኝን ቃልህን እረዳ ዘንድ እርዳኝ።

31/08/2020

ባሪያህ ይሰማል

“እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፥ እንደ ቀድሞውም፦ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፦ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለው” (1ኛ ሳሙኤል 3፥10)።

1 ሳሙኤል 3:1–10

ገመድ የለሹ ራዲዮ ባይጠፋ ኖሮ ታይታኒክ ልትሰጥም መሆኑን ያውቁ ነበር። በሌላ መርከብ ላይ የነበረው ሲሪል ኢቫንስ የተባለው የሬዲዮ ኦፕሬተር በታይታኒክ ላይ ለነበረው ጃክ ፊሊፕስ ለተባለው የሬዲዮ ኦፕሬተር ታይታኒክ ከበረዶ ክምር ጋር ልትጋጭ መሆኑን የሚገልጽ መልእክት ለማስተላለፍ ሞክሮ ነበር። ሆኖም ግን ፊሊፕ መንገደኞችን በማስተናገድ ላይ ስለነበረ ኢቫንስ አፉን እንዲዘጋ ይናገረዋል። ስለዚህ ኢቫንስ ሬዲዮኑን አጥፍቶ በግትረኝነቱ ወደ መኝታው ይሄዳል። ከ10 ደቂቃዎች በኋላም ታይታኒክ ከበረዶው ክምር ጋር ልትላተም ችላለች። ማንም የሚሰማቸው አልነበረምና የድረሱልን ጥሪያቸው ሁሉ ከንቱ ሆነ።

በ1 ሳሙኤል ላይ የእስራኤል ካህናቶች ሙሰኞችና መንፈሳዊ ዕይታቸውን በማጣት የሳቱ ነበሩ። " “በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር” (1ኛ ሳሙኤል 3፥1)። እግዚአብሔር ግን በህዝቡ ተስፋ አልቆረጠም። እናም በካህናት ቤተሰብ ዘንድ ይኖር የነበረን ሳሙኤል የተባለ ታዳጊ ወጣትን ሊያናግር ጀመረ። ሳሙኤል ማለት እግዚአብሔር ሰማ ማለት ነው። ይህ ስም የተሰጠውም የእናቱን ጸሎት እግዚአብሔር እንደሰማ ለመመስከር ነው። ይሁንና ሳሙኤል እግዚአብሔርን እንዴት መስማት እንደሚችል ማወቅ ነበረበት።

"ባሪያህ ይሰማልና ተናገር" (ቁ.10)። ባሪያ መስማት አለበት። እኛም ብንሆን እግዚአብሔር በቃሉ ለገለጠልን ነገር መስማት ብቻ ሳይሆን መታዘዝ አለብን። ሬዲዮናችንን እንደከፈትን ትሁት አገልጋዩ በመሆን ሕይወታችንን ለእርሱ እናስገዛ።

እግዚአብሔር በቃሉ ለገለጠልን ነገር መታዘዝ ለምን አስፈለገን? ለድምጹ ሞገድ ጆሮአችንን አስተካክለን ማዳመጥ ያለብን እንዴት ነው?

ውዱ ኢየሱስ የምትናገረኝ አምላክ እንደመሆንህ አመሰግንሃለሁ። በመታዘዝ እንድከተልህ ስለተሰጠኝም ቃል አመሰግንሃለሁ። ተናገር ባሪያህም ይሰማል።

30/08/2020

የመጨረሻው ሞገድ

“ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በዓለም ዙሪያ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በእናንተም ዘንድ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው።” ቆላስይስ 1፥6

ቆላስይስ 1:1–8

ሰዎች ሞገድ መሥራት ይወዳሉ። በዓለም በስፖርትና ኮንሰርት በሚዘጋጅበት አካባቢ የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሰዎች እጃቸውን በማንሳት ይጀምራሉ። ከጥቂት ጊዜም በኋላ ካጠገባቸው የተቀመጡት ሰዎች ተመሳሳይ ነገር ያደርጋሉ። ዋናው ዓላም በእስታዲየሙ ዙሪያ በየተራ የሆነ የፍሰት እንቅስቃሴ መፍጠር ነው። አንዴ ወደ ፍጻሜው ሲደርስ እነዛ ከመጀመሪያው የጀመሩት ፋገግ ማለትና መደሰት ይታይባቸዋል። እንዲሁ በድጋሚ እንቅስቃሴውን ይደግሙታል።

የመጀመሪያው ሞገድ የመሥራት ሙከራ የተደረገው በ1981 ዓ.ም ሲሆን ኦክላንድ አትሌቲክስ ከኒው ዮርክ ያንኪስ ጋር በተጋጠመበት ጊዜ እንደነበረ ይነገራል። ደስ ስለሚል ይህንን ሞገድ መቀላቀል ያዝናናል። እንዲሁም ለእኔ ስናደርገው አብረን ደስታን የምንጋራበት በየሥፍራው አማኞችን አያይዞ የሚያቀራርበው የኢየሱስን ድነት አብሳሪው ወንጌል እንደሆነ እረዳለሁ። ይህ የመጨረሻው ሞገድ የተጀመረው ከሃያ ምእተ ዓመታት በፊት በኢየሩሳሌም ነው። ለቆላስይስ የቤተክርስቲያን አባላት ሲጽፍላቸው ጳውሎስ በዚህ መንገድ እንዲህ ብሎ ይገልጠዋል፡ " “ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በዓለም ዙሪያ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በእናንተም ዘንድ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው” (ቆላ.1:6)። የዚህ መልካም ዜና ውጤትም "በክርስቶስ ኢየሱስ ያለ እምነትና ለቅዱሳን ሁሉ ያላቸው ፍቅር ነው” (ቆላ.1፥4)።

እኛም በኢየሱስ እንደማመናችን በታሪክ የዚህ ታላቅ ሞገድ ባለድርሻ ነን። እንቀጥለው። ልክ ስናበቃ የጀመረውን የእርሱን ፈገግታ ማየት እንችላለን።

ለመሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢየሱስን መልካም ዜና የሰማችሁት ከማን ይሆን? በዚህ ሳምንትስ አጠገባችሁ ላለ ሰው ለማካፈል አቅዳችኋልን?

አባት ሆይ አስደናቂ ስለሆነው የመዳኔ ስጦታ አመሰግንሃለሁ። ዛሬ ያንተን መልካምነት መስማት ያለበትን ሰው ወደ እኔ ትልክልኝ ዘንድ እጠይቅሃለሁ!

24/08/2020

ዘመን ተሻጋሪ ደብዳቤ

“ሕይወት ተገለጠ፤ እኛም አይተነዋል፤ እንመሰክርለታለንም። በአብ ዘንድ የነበረውን፣ ለእኛም የተገለጠልንን የዘላለም ሕይወት እንነግራችኋለን፤” 1ኛ ዮሐንስ 1፥2

1 ዮሐንስ 1:1–8

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች በዓለም አቀፍ የደብዳቤ አጻጻፍ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ። በ2018 ዓ.ም የነበረው የመወዳደሪያ ርእስ "ዘመን ተሻግራችሁ የምትሄዱ ብትሆኑ ለአንባቢዎቻችሁ የምትተዉላቸው ደብዳቤ ምን ሊሆን ይችላል?" የሚል ነበር።

ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይግባውና ዘመናትን አቋርጠው እኛ ዘንድ የደረሱ የደብዳቤ ስብስቦች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ። የክርስቲያን ቤተክርስቲያን እያደገች ስትሄድ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት በአውሮጳና በትንሽዋ እስያ ላሉ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ሰዎች በክርስቶስ ያገኙትን አዲስ ሕይወት እንዲረዱ ለማድረግ የተጻፉ ደብዳቤዎች ዘመንን ተሻግረው ዛሬ በመጽሐፍ ቅዱስ መልክ ተሰባስበው እኛ እጅ ደርሰዋል።

እነዚህ ደብዳቤውን የጻፉት ሰዎች ለአንባብያን ማስተላለፍ የፈለጉት መልእክት ምን ነበር? ዮሐንስ በመጀመሪያው መልእክቱ "ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውን፣ የሰማነውን፣ በዐይኖቻችን ያየነውን፣ የተመለከትነውንና እጆቻችን የዳሰሱትን እንናገራለን” በማለት ይጽፋል (1ኛ ዮሐንስ 1፥1)። የጻፈውም አንባቢዎቹ እርስበርሳቸው፣ እንዱሁም ከአብና ከልጁ ከኢየሱስ ጋር ኅብረት ይኖራቸው ዘንድ ነው (ቁ.3)። እንደጻፈውም ኅብረት ሲኖረን ደስታችን ፍጹም ይሆናል (ቁ.4)። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው ደብዳቤ ዘመንን ከተሻገረ ማለትም ከዘላለማዊ እግዚአብሔር ጋር ወደሚገኝ ኅብረት አስገባን።

ዛሬ እግዚአብሔር ደብዳቤ ቢጽፍልህ ምን የሚልህ ይመስልሃል? ከሕያው እግዚአብሔር ጋር ስላለህ ግንኙነት ለአንድ ወዳጅህ መጻፍ ብትፈልግ ምን ልትል ትችላለህ?

አባት ሆይ ከአንተ ጋር ስላለኝ ኅብረት አመሰግንሃለሁ።

21/08/2020

ከእግዚአብሔር ጋር መሥራት

“እኛ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ዕርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥9

1 ቆሮንቶስ 3:1–9

በ1962 ዓም ቢል አሽ የተባለ ሰው ለጉብኝት ወደ ሜክሲኮ ሄዶ ነበርና በህጻናት ማሳደጊያ ድርጅት ውስጥ ተበላሽተው የነበሩትን የንፋስ ወፍጮዎችና ፓምፖች ጥገና ይጀምራል። ከ15 ዓመታት በኋላ ንጹህ ውኃ ለመንደርተኛው በማቅረብ እግዚአብሔርን ለማገልገል በመነሳሳት ቢል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ይመሠርታል። ሲናገርም "ሌሎችንም ጭምር ለዚህ በጎ ሥራ በማነሳሳት ለገጠርማው የሀገሪቱ ክፍል የሚጠጣ ንጹህ ውኃ እንዲያገኙ የማደርግበትን ተነሳሽነት እግዚአብሔር ሰጠኝ" ይላል። ቆይቶም ከመቶ በላይ ከሆኑ ሀገራት በሺህ በሚቆጠሩ መጋቢያንና ወንጌላውያን ጠያቂነት ቢል ሌሎች ይህንን አገልግሎት እንዲተባበሩ አድርጎአል።

እግዚአብሔር እርሱን ሆነ ሰውን ሁሉ በተለያዩ መንገዶች እንድናገለግል ወደሚያስችለን ጥምረት እየጠራን ነው። የቆሮንቶስ አማኞች በተሻሉ አገልግሎታቸው እየተከራከሩ ባሉበት ሰዓት ሐዋርያው ጳውሎስ እርሱና አጵሎስ ያላቸውን የጋራ ድርሻና የእግዚአብሔርን የማሳደግ ድርሻ ለይቶ ይናገር ነበር (1ቆሮ.3:1-7)። እግዚአብሔር የሰጠን ሥራ ሁሉ ዋጋ ያለው መሆኑን ያሳስበናል (ቁ.8)። እርሱን ስናገለግለው ከሌሎች ጋር በአጋርነት መሆኑን እንድናውቅ ጳውሎስ እርስ በርሳችን በመተናነጽ በፍቅር እንድናገለግል ያሳስበናል (ቁ. 9)።

ሁሉን ቻዩ አባታችን ሥራውን ለመፈጸም በእኛ እርዳት አይደገፍም። ይሁንና ከእርሱ ጋር አጋር እንሆን ዘንድ ያዘጋጀናል፣ ይጋብዘናል።

የማይቻለውን ዋጋ አስከፋይ ሥራ በመሥራት ውጤቱን ግን ለእግዚአብሔር መተው ያበረታናል። አንድን ሥራ እንድንሠራ ሲጋብዘን ከእርሱ እርዳታ ጋር ነው።

አባት ሆይ በእኔ ታላላቅ ሥራ ስትሠራ የሚያስፈልገኝን አቅርቦት ሁሉ እያደረክልኝ ስለሆነ አመሰግንሃለሁ።

19/08/2020

ታመን ብቻ

“በዚህ ሁኔታም ኤልያስ፣ መበለቲቱና ቤተ ሰቧ ብዙ ቀን ተመገቡ፤” 1ኛ ነገሥት 17፥15

1 ነገሥት 17:8–16

ሦስት መቶ የሚሆኑ ህጻናት ልብሳቸውን ለብሰው ለቁርስ እገበታው ፊት ከቀረቡ በኋላ ስለምግቡ ጸሎት ተደረገ። ይሁንና ገበታው ላይ የቀረበ ምንም ምግብ አልነበረም። እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ለዚህ ህጻናት ማሳደጊያ ዳይሬክተርና ሚሽነሪ ለጆርጅ ሙለር ያልተለመደ አልነበረም (1805- 1898)። እግዚአብሔር በእርግጥ አቅርቦትን እንደሚያደርግ እዚህ ላይ ጥሩ ምሳሌ ማግኘት እንችላለን። ሙለር ከጸለየ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ከዓይኑ ርቆት የነበረ ዳቦ ጋጋሪ ህጻናት ማሳደጊያው በር ከተፍ ይላል። ይህ የህጻናት ማሳደጊያ ሦስት ቅርጫት ሙሉ ዳቦ እንደሚያስፈልገው ተሰምቶት ነበር። ብዙም አልቆየም በከተማው በወተት አዳይነት የተሰማራው ሰው ደግሞ ብቅ አለ። ዝም ብሎ እንዳይመስላችሁ። ወተት የሚያመላልስበት ጋሪ ህጻናት ማሳደጊያው በር ላይ ተስብሮ ኖሮአል የመጣው። ወተቱ ከሚበላሽ ብሎ እንዳለ ለህጻናቱ ትቶት ሄደ።

ወገኖቼ ማዘናችን፣ መስጋታችን፣ ለድነታችን የሚያስፈልጉንን እንደ ምግብ፣ መጠለያና ጤና፣ ገንዘብና ወዳጅ ማጣታችን የተለመደ የሕይወት ግጥጥሞሽ ሊሆንብን ይችላል። አንደኛ ነገሥት 17:8-16 ያለው ቃል የሚያስተምረን ባልተጠበቀች ባልቴት እርዳታ ወደ እኛ ሊመጣ እንደሚችል ነው። " “እርሷም መልሳ፣ “አምላክህን ሕያው እግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ዕፍኝ ዱቄትና በማሰሮ ካለው ጥቂት ዘይት በቀር ምንም የለኝም" (12)። ቀደም ሲል ለኤልያስ አቅርቦት ሲያደርጉለት የነበሩት ቁራዎች ናቸው (4-6)። ለእኛ ፍላጎት መሟላት ግድ የሚለው አምላክ በመሆኑ በወደደው አቅጣጫ ወደ መሻታችን ይመጣል። እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን አቅርቦት የሚያሟላልን አምላክ እንደሆነ ግልጽ ዕይታ ካለን ነጻነት አለን። መፍትሄዎችን ከመፈለጋችን በፊት እርሱን ለመፈለግ ጠንቃቆች ልንሆን ይገባናል። ይህንን ማድረግ ጊዜያችንን፣ አቅማችንን በመቆጠብ ስጋት ይቀንስልናል።

ስለዚህ ስንጸልይ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ከማስቀደማችን በፊት አቅራቢውን እናስቀድም። በእግዚአብሔር ፊት ስለምናቀርበውም መሻት እንጠንቀቅ። ከስጦታው ሰጪው ይበልጣል።

አባት ሆይ አንተን የሁሉ ነገር አቅርቦቴ አድርጌ እንዳይህ የሰላ ዓይን ስጠኝ። አንተን ሳላስቀድም በከንቱ በራሴ ስለባከንኩባቸው ጊዜያት ይቅር በለኝ። በኢየሱስ ስም፣ አሜን!

Address

Gullele Subcity, 08/16, Hse No. 185/18
Addis Ababa
17669

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251911646418

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when God's Visitation Fire Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to God's Visitation Fire Ministry:

Share