20/06/2026
የእናቱን አስክሬን ቤት አስቀምጦ
ሚኒስትሪ የተፈተነው የ14 ዓመቱ ካሊድ
በሸገር ከተማ ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ የሚኖረው የ14 ዓመቱ ታዳጊ ካሊድ፣ ለ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ሲዘጋጅ እናቱ በድንገት በጽኑ ይታመማሉ። እናቱ ከመሞታቸው ጥቂት ሰዓታት በፊት “እኔ ምንም ብሆን የለፋህበትን ፈተና እንዳታቋርጥ” በማለት ለካሊድ ቃል ያስገቡታል። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ፈተናው ሊጀመር ጥቂት ሰዓታት ሲቀረው የእናቱ ሕይወት ያልፋል። ካሊድ በደረሰበት ከባድ ሐዘን ሳይሰበር፣ ለእናቱ የገባውን ቃል ለማክበር ሲል የእናቱን አስክሬን ቤት ውስጥ አስቀምጦ የጠዋቱን ፈተና ለመፈተን ወደ ትምህርት ቤት ያመራል።
የጠዋቱን ፈተና አጠናቆ ከተመለሰ በኋላ፣ ከሰዓት በልጅነት ዕድሜው ሊሸከሙት የሚከብደውን የእናቱን ለቅሶና ቀብር ሥነ-ሥርዓት ያከናውናል። ይሁን እንጂ ሐዘኑን ውጦና እንባውን አብሶ፣ የእናቱን የመጨረሻ ምኞት ሙሉ በሙሉ ለመፈጸም በዚያው ዕለት ከሰዓት በኋላ ወደ ፈተናው አዳራሽ በመመለስ የቀረውን ፈተና ተፈትኗል። የዚህ ታዳጊ አስደናቂ ጥንካሬ፣ ጽናትና ለእናቱ የነበረው ታማኝነት የብዙዎችን ልብ የነካና ያስለቀሰ ታሪክ ሆኖ አልፏል።
Dagu journal-
#ኢትዮጵያ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas