Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/ Biyya Lallaba Magaalaa Shaggar irraa kan darbu "ከሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሚተላለፍ Broadcasted from the Sheger City Diocese.
(1)

Follow the EOTC Shegercitydiocese page to get all the latest news about the EOTC in Afaan Oromoo and Amharic.

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕሥ...
10/09/2026

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፤

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣

በየዓመቱ የይቅርታ እጁን እየዘረጋ የሚመግበን እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ወደ ዘመነ ሉቃስ ሁለት ሺሕ ዓሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
“ወይእዜኒ ነስሑ ወተጠመቁ፤ ወይደመሰስ ለክሙ ኃጢኣትክሙ፤ ወይመጽእ ለክሙ መዋዕለ ሣህል እምቅድመ ገጹ ለእግዚአብሔር፤ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላችሁ፣ ኃጢአታችሁም እንዲደመሰስ አሁንም ንስሐ ግቡ ተመለሱም” (የሐ.ሥራ ፫፡፲፱)

የሰው ልጅ በስሑት ስራውና አእምሮው ምክንያት የኃጢአት ማዕበል በሚያናውጠው ባሕረ ዓለም እንደሚኖር ይታወቃል፤ የዓለሙ ባሕር በማዕበሉ በተናጠ ቁጥር በመርከቡ ተሳፍረው የሚጓዙ ሁሉ ጭንቀት ላይ መውደቃቸው የማይቀር ነው፤ በዚህ ጊዜ የሚያጽናና የቊርጥ ቀን ረዳትና ኃይል ያስፈልጋቸዋል፤ ሆኖም ረዳት በፍጥነት እንዲደርስላቸው መጮኽና መጣራት ከነሱ ያስፈልጋል፤ የምንኖርባት ዓለም ወይም ፕላኔት የክፋትና የጭካኔ ማዕበል በእጅጉ እየበረታባት መጥቶአል፤ ዓለማችን በስጋትና በፍርሓት፣ በራስ ወዳድነትና ባለመተማመን ተከባለች፣ በመሆኑም ዓለማችን ከምን ጊዜውም በላይ የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላት ትሻለች፤ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ የሰጠ አምላክ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ነው፤ ይሁንና እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልጋቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ በማያሻማ ሁኔታ አሳውቆአል፤ ከእነሱም መካከል በእውነተኛው መንፈስ ንስሐ መግባት፤ መጸጸትና መመለስ ናቸው፤ የዓለምን ሕዝብ በወሳኝነት ማጽናናት የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እኛ ራሳችንን በራሳችን ለማጽናናት እንኳ በቂና ዘላቂ ዓቅም የሌለን ውሱኖች ነን፤ ይህንን እውነት ዓውቀን የእርሱን ርዳታ እንድንሻ እግዚአብሔር ይፈልጋል፤ ይህንንም ከልብ በመጸጸትና ከቀደመው ስሑት ተግባራችን በመመለስ በፊቱ ተንበርክከን መታዘዛችንን በተጨባጭ እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት!

እግዚአብሔር ከታላቅ ቸርነቱ የተነሣ የመታደስ ዘመንን በየዓመቱ ከመስጠት አልተቈጠበም፤ እንደ ሁሉጊዜ አሁንም አዲሱን ዘመን ባርኮ ሰጥቶናል፤ ሆኖም አዲሱ ዘመን የመጽናናት ዓመት እንዲሆንልን የእኛ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው መዘንጋት የለብንም፤ ከሁሉ በፊት ያለፈውን ዓመት እንደ ግልም፣ እንደ ማኅበረ ሰብም፣ እንደ ሃገርም፤ እንደ ሃይማኖትም በኅሊናችን ልናስበውና ልንገመግመው ይገባል፤ ያለፈውን ዓመት በንጹህ ኅሊናችን በጥልቀት ስንገመግመው፤ የመጣንበትና ያለፍንበት ስለሆነ ኮለል ብሎ በፊታችን ይታያል፤ ጥቅሙም ሆነ ጉዳቱ በሙሉ ከኛ የራቀ ስለማይሆን ዳኝነት ለመስጠትና ውሳኔ ለመወሰን አንቸገርም፤ በመሆኑም ለፈጸምነው ስሕተት ይቅርታን ከመጠየቅ ባሻገር ድጋሚ ላንደግመው መወሰንና ለተግባራዊነቱ በጽናት መቆም አለብን፤ እኛ በዚህ ደረጃ ከቀደመው ስሕተታችን ተጸጽተን ንስሐ ከገባን እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልገውን አግኝቶአል ማለት ነው፤ በመካከላችንም ትክክለኛ መግባባት ተፈጥሮአል ማለት ነው፤ በዚህ ጊዜ እሱም ዘላቂ የሆነ የመጽናናት ዘመን ለኛ ይሰጣል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት!

በዓለሙ እንዳለው ሁሉ እኛም ወዲያና ወዲህ ከሚያወዛውዝ ፈተና አላመለጥንም ያለፈውን ዓመት በንጹሁ አእምሮአችን ስንመዝነው፤ ጥሩ የሚባል አልነበረም፤ በየአካባቢው ግጭቶች የቀጠሉበት፣ የሰው ደም የፈሰሰበት፣ ዕገታዎች የተፈጸሙበት፣ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የተቃጠሉበት፣ ምእመናን የተገደሉበትና የተፈናቀሉበት፣ ስጋት ያየለበት፣ ኑሮም የተወደደበት፣ ሌላም ሌላም ለሰው ልጅ የማይበጁ ነገሮች የተከሠቱበት ዓመት አሳልፈናል፤ ታዲያ አዲሱን ዘመን ስንቀበል እነዚህን ሁሉ እንዳሉ ይዘናቸው እንቀጥል ይሆን? ይህስ ከሆነ ‹‹እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሳችሁ›› መባባሉ ትርጉም ይኖረው ይሆን? እንዲህስ ልንሆን ፈጽሞ አይገባም፤ ይልቁንም ባለፈው ዓመት የሆኑትን ሁሉ ላንደግማቸው ሁላችንም እንወስን፤ እነሱንም ማስቀረት እንችላለን፤ ምክንያቱም ችግሮቻችን በሙሉ ሰው ሰራሽ እንጂ የተፈጥሮ አይደሉም፤ ሰው ሰራሽ ችግሮች ደግሞ በሰው እንደመጡ ሁሉ በሰው ሊቀሩ የሚችሉ ናቸውና እናስቀራቸው፤ ጦርነቱን፣ ዕገታውን፣ ጥላቻውን፣ ፉክክሩን፣ እልከኝነቱን፣ ጭካኔውን ራስ ወዳድነቱን ግድያውን፣ አብያተ ሃይማኖት ማቃጠሉንና ማፍረሱን እኛው እንዳመጣነው እኛው ማስቀረት እንችላለን፤ ስንተወው እኮ ይቀራል፡፡

ስለሆነም ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን እንዳለች የጋራ ዕድልና ሃብት አድርጋችሁ ተቀበሉ፤ ሌላውን ረጅም ጊዜ ሰጥታችሁም ቢሆን በውይይትና በመግባባት እየፈታችሁ በአንድነት ቀጥሉ፤ በይቅርታመንፈስ በአንድነት ተቃቅፎ ከመቀጠል ውጭ ሌላ የተሻለ ዕድል እንደሌለ በውል ተገንዘቡ፤ ለዚህ ሁላችሁም የበኩላችሁን ልባዊ ጥረት ከማድረግ አትቈጠቡ ብለን ከልብ እንመክራለን፡፡

በመጨረሻም፤

ለሁሉም መድኃኒቱ ቀና አእምሮ ነውና በአዲሱ ዓመት እግዚአብሔር ቅንና በጎ አሳቢ አእምሮ እንዲሰጠን በሱም ያሉብንን ጉድለቶች አርመንና አስተካክለን ሰላም የሰፈነበትን የመጽናናት ዘመን ማየት እንችል ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችንን እንለምን፤ እኛም በንስሐ እንመለስ እያልን በድጋሚ እንኳን ለአዲሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ በማለት አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን ፡፡
እግዚአብሔር መልካም አዲስ ዘመን ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኣምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኣሜን!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
መስከረም ፩ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ለሚያገለግሉ አንዳንድ ሠራተኞች ለአዲሱ ዓመት መዋያ የሚሆን ሥጦታ አበረከተ፡፡  ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ...
10/09/2026

ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ለሚያገለግሉ አንዳንድ ሠራተኞች ለአዲሱ ዓመት መዋያ የሚሆን ሥጦታ አበረከተ፡፡


ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ለሚያገለግሉ ሠራተኞች ለአዲሱ ዓመት መዋያ የሚሆን ሥጦታ አበረከተ፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዳሽን ባንክ በአበረከተው ስጦታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ክቡር አቶ አየለ ተሾመ የዳሽን ባንክ የስትራቴጂ ምክትል ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት “ዳሽን ባንክን በመወከል እንኳን ለ፳፻፲፱ ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ፤ ዳሽን ባንክ ከተቋቋመበት አንዱ ዕሴቱ መካከል ኅብረተሰቡን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማገዝ ነው” ብለዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ አክለውም “ለአዲስ ዓመት በኑሮ አነስተኛ ደረጃ ላሉ የኅብረተሰብ ወገኖቻችን የተለያዩ ድጋፎችን ስናደርግ ቆይተናል፤ ዛሬም እዚህ የተገኘነው በመንበረ ፓትርያርክ ለሚገኙ ወገኖቻችን ለበዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለትና መጠነኛ ስጦታ ለማበርከት ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ወደፊትም ይኸው ድጋፍ የሚቀጥል መሆኑን የገለጹት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያኗ ጎን ሆነን በሚያስፈልገው ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ ነን” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ “እንኳን ለ፳፻፲፱ ዓ.ም አዲሱ ዘመን በሰላምና በጤና አደረሰን፣ አደረሳችሁ፤ ዳሽን ባንክ ለወገኖቻችን መደገፍ አለብን ብላችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡ብፁዕነታቸውም አያይዘውም “ለወገኖቻችን ያደረጋችሁት ድጋፍ ቤተክርስቲያን ታመሰግናችኋለች እግዚአብሔር አምላክ ሥራችሁን ያቃናላችሁ፤ ከዚህ በበለጠ እንድታገለግሉ ያድርግልን፤ ዘመኑንም የሰላም፣ የበረከት፣ የአንድነት ያድርግልን” ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
“ዳሽን ባንክ በሁሉም ሥፍራዎች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፤ ዛሬ እዚህ ስንመጣ ደስ ብሎናል” ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ክቡር አቶ አየለ ተሾመ “በግቢው ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን አይተናል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊት፣ ታሪካዊት ብቻ ሳትሆን በጣም ብዙ የልማት ሥራዎችንም እንደምትሠራ፣ ኅብረተሰቡንም በብዙ ነገሮች እያገለገለች እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ይህን የልማት ሥራ ደግሞ ከፍ አድርጎ ለመሥራት ድጋፍ ያስፈልጋል፤ ዳሽን ባንክ በማንኛውም የባንክ አገልግሎት ለማገዝ ዝግጁ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ብፁዕነታቸውም “መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ራስ ዋናው መሥሪያ ቤት መቀመጫ ግቢውን እያስዋብን የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየሠራን እንገኛለን፤ ይህን ስንሠራ እንደናንተ ያሉ ሌሎችም እየረዱን፣ እያገዙን ነው፡፡ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ገዳም ቤተክርስቲን አጥር ሠርተውልናል፣ በመንበረ ፓትርያርክ ቅጽር ግቢ ለ50 ዓመታት በሌሎች ተይዞ የነበረውን ቦታ አስመልሰውልናል፤ የኮሪደር ልማት በሚሠራባቸው አብያተ ክርስቲያናት አካባቢም ርዳታ እያደረጉልን በመሆኑ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡” ብለዋል፡፡
በቅርቡም አዲሱ አዳራሽ ይመረቃል፤ በቀጣይ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ከዚህ በበለጠ ስለምንሠራ እንድታግዙን፤ ዛሬ በዚህ ተገኝታችሁ ላደረጋችሁልን ድጋፍ እናመሰግናለን ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

"አፍሪካ መጠበቅ አትችልም" በሚል  ርዕስ ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን አህጉር አቀፍ የአየር ንብረት ዘመቻ በይፋ አስጀመረች ።ጳጉሜን ፬/፳፻፲...
09/09/2026

"አፍሪካ መጠበቅ አትችልም" በሚል ርዕስ ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን አህጉር አቀፍ የአየር ንብረት ዘመቻ በይፋ አስጀመረች ።

ጳጉሜን ፬/፳፻፲፰ ዓ/ም Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን፣ ከ'ACT Alliance'
እና በአየር ንብረት ላይ በትብብር ከሚሠሩ የአፍሪካ የእምነት ተቋማትና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር "አፍሪካ መጠበቅ አትችልም ከቃል ኪዳን ወደ ፍትሐዊ ትግበራ" (Africa Can't Wait: From Pledges to Just Implementation) የተሰኘ የአየር ንብረት ዘመቻን በይፋ አስጀመረች።

ይህ ዘመቻ አዲስ አበባ ላይ ከሚካሄደው የኮፕ32 (COP32) ጉባኤ አስቀድሞ፣ በመላው አፍሪካ ጠንካራ የፓን-አፍሪካ የአየር
ንብረት እንቅስቃሴ ለመገንባት እና የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖች በፍትሃዊነትና በሰብአዊ መብት ላይ በተመሠረተ መልኩ እንዲተገበሩ ለመጠየቅ አንድ ሚሊዮን ፊርማዎችን ለማሰባሰብ ያለመ ነው።
ከ14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥና ልማት ጉባኤ (CCDA-XIV) ጎን ለጎን በተካሄደውና ከመላው አፍሪካ የመጡ ከ100 በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት በዚህ መርሐ ግብር ላይ፤ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ የቤተክርስቲያኒቱን አቋም የሚያንጸባርቅ ሰፋ ያለ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ለእኛ ለእምነት ተከታዮች፣ ለፍጥረት እንክብካቤ ማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊነት ብቻ አይደለም። መንፈሳዊ እና ሞራላዊ ጥሪ ጭምር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት 2፥15 ላይ የሰው ልጅ ኤደን ገነትን እንዲያለማትና እንዲጠብቃት እንደተቀመጠ ያስታውሰናል። ስለዚህ ምድርን የመጠበቅ እና ለመጪው ትውልድ የማቆየት ኃላፊነት የተሰጠን የእግዚአብሔር ፍጥረት ጠባቂዎች (stewards) ነን በማለት ገልፀዋል።
አክለውም ጠባቂነት ሁልጊዜም ከፍትሕ ጋር አብሮ መጓዝ አለበት። በትንቢተ ኢሳይያስ 1፥17 ላይ፣ ቅዱስ ቃሉ "መልካም ማድረግን ተማሩ፥ ፍርድን [ፍትሕን] ፈልጉ፥ የተገፋውንም አድኑ" በማለት ጥሪ ያቀርብልናል። ይህ ዛሬ ላለው የአየር ንብረት ፍትሕ ኃይለኛ መልእክት ነው። ፍትሕን መፈለግ ማለት፣ ለአየር ንብረት ቀውሱ አነስተኛ አስተዋጽኦ አድርገው ነገር ግን እጅግ የከፋ መዘዝ እየደረሰባቸው ያሉትን ማኅበረሰቦች ማዳመጥ እና ከጎናቸው መቆም ማለት ነው። ይህም የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ማላመድ (adaptation)፣ ጉዳት እና ኪሳራ (loss and damage)፣ መልሶ ማቋቋም እና ወደ ንጹሕ ኃይል የሚደረገው ሽግግር የሰውን ልጅ ክብር የሚያስጠብቅ እና ይበልጥ ለሚፈልጉት የሚደርስ መሆኑን ማረጋገጥ ማለት ነው በማለት ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለትውልዶች የዘለቀ የጠባቂነት (stewardship) ትውፊት አላት። የተቀደሱ የቤተ ክርስቲያን ደኖቻችን (አድባራትና ገዳማት ደኖች) እምነት፣ መንፈሳዊነት እና ለፍጥረት የሚደረግ እንክብካቤ አብረው ሊጓዙ
እንደሚችሉ ሕያው ምስክሮች ናቸው። ፍጥረትን መጠበቅ ለአፍሪካ አዲስ ኃላፊነት እንዳልሆነ፤ በታሪካችን፣ በባህላችን እና በእሴቶቻችን ውስጥ ጠልቆ የገባ መሆኑን ያስታውሱናል በማለት ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ በንግግራቸው ወደ ፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ ያመጣናል። የአየር ንብረት ለውጥ የሀገር ድንበሮችን፣ የእምነት ተቋማትን ወይም የሃይማኖት ወጎችን አያከብርም። የእኛም ምላሽ በእነዚህ ሊከፋፈል አይገባም። የፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ፣ አፍሪካ ጠንካራ የምትሆነው ሕዝቦቿ በአንድ የጋራ ዓላማ ዙሪያ አብረው ሲቆሙ መሆኑን ያስታውሰናል በማለት ተናግረዋል ።
የሲ.ሲ.አር.ዲ.ኤ (CCRDA) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ንጉሡ ለገሠ በበኩላቸው ሕዝባችን ቀድሞውንም ከተለዋዋጭ የአየር ንብረት መዘዞች ጋር እየኖሩ ባሉበት በዚህ ወቅት አፍሪካ ሌላ አዋጅ መጠበቅ አትችልም። ድርቅ ሰብልን ሲያጠፋ፣ ጎርፍ ቤትን ሲያፈርስ፣ የመሬት መራቆት የኑሮ መሰረትን ሲያናጋ፣ እና ቤተሰቦች ለትውልድ መኖሪያቸው ብለው ከጠሩት ቦታ ሲፈናቀሉ አፍሪካ መጠበቅ አትችልም። ወጣቶች እነሱ ያልወሰኑትን ውሳኔ መዘዝ ብቻ ሳይሆን እነሱ ያልፈጠሩትን ሥርዓት የመጠገን ሸክም ሲወርሱ አፍሪካ መጠበቅ አትችልም በማለት ተናግረዋል።
አፍሪካ መጠበቅ አትችልም ነገር ግን አፍሪካ መምራት ትችላለች። እናም አፍሪካ መምራት እንዳለባት አምናለሁ። በቁጣ ብቻ አይደለም። በጥገኝነት አይደለም። ዓለም ተጋላጭነታችንን እንዲገነዘብ በመጠየቅ ብቻ አይደለም። እኛ በሞራል ልዕልና፣ በአፍሪካዊ ጥበብ፣ በሳይንሳዊ እውቀት፣ በእምነት፣ በፈጠራ፣ በአንድነት እና በተግባራዊ መፍትሄዎች መምራት አለብን በማለት ገልጸዋል።የእምነት ማኅበረሰቡ በተለይ ጠቃሚ ሚና ያለው እዚህ ላይ ነው ብዬ አምናለሁ ። አማኙ ሕዝባችን የአፍሪካ የልማት ታሪክ ተመልካቾች አይደሉም። እኛ የታሪኩ አካል ነን። በመንደሮች ውስጥ እንገኛለን። በከተሞች ውስጥ እንገኛለን። በአርሶ አደሮች፣ በሴቶች፣ በወጣቶች፣ በተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች እና በችግሩ ግንባር ቀደም ተጋላጭ በሆኑ ቤተሰቦች መሐል እንገኛለን በማለት ተናግረዋል።
ዶ/ር ንጉሡ ለገሠ በንግግራቸው ሰዎችን በደስታቸው ጊዜ ብቻ ሳይሆን በመከራቸው ጊዜም አብረናቸው እንሆናለን። ስለዚህ፣ ስለ አየር ንብረት ፍትህ ስንነጋገር፣ ከተልዕኳችን ውጭ ስለሆነ ጉዳይ እየተነጋገርን አይደለም። እየተነጋገርን ያለነው ስለ ጥሪያችን/ተልዕኳችን ነው። የዚህ ዘመቻ ርዕስ ላይ “ፍትሕ” የሚለውን ቃል የተቀበልኩትም ለዚህ ነው። ምክንያቱም የአየር ንብረት ቀውሱ ስለ ሙቀት መጠን፣ ልቀት እና ካርቦን ብቻ አይደለም። ከእያንዳንዱ ስታስቲክስ ጀርባ የሰው ሕይወት አለ። ከእያንዳንዱ ድርቅ ጀርባ ቤተሰብ አለ። ከእያንዳንዱ ጎርፍ ጀርባ ማኅበረሰብ አለ። ከእያንዳንዱ የተፈናቀለ ቤተሰብ ጀርባ ታሪክ አለ። እናም ከእያንዳንዱ የጠፋ የኑሮ መሰረት ጀርባ የፍትህ ጥያቄ አለ። አየሩ የጋራችን ነው። ውቅያኖሶቹ የጋራ ናቸው። የመሬት እና የውሃ ስርዓቶች የተሳሰሩ ናቸው። የልጆቻችንም የወደፊት እጣ ፈንታ የጋራ ነው። ስለዚህ፣ ኃላፊነታችንም የጋራ መሆን አለበት በማለት ገልጸዋል ።
©EOTCTV

09/09/2026
    Faarfattoota Obboloota Shamaarraanii
08/09/2026

Faarfattoota Obboloota Shamaarraanii

Kabajni Ayyaana Waggaa Angafa Ergamoota Qulqulluu Ruufa'eel Mana Kiristaanaa Tulluu Eedoom Qulqulluu Ruufa'eel Sabbataat...
08/09/2026

Kabajni Ayyaana Waggaa Angafa Ergamoota Qulqulluu Ruufa'eel Mana Kiristaanaa Tulluu Eedoom Qulqulluu Ruufa'eel Sabbataatti haala ho'aan Kabajame Oole.
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ‎ሰበታ ደብረ ኤዶም ቅዱስ ሩፋኤል ቤ/ክ በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል  እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል  ዓመታዊ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!!!በወርኀ ጳጉሜን በድምቀት የሚከበረው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል ነው፡፡ ...
08/09/2026

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!!!

በወርኀ ጳጉሜን በድምቀት የሚከበረው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲኾን ስሙም ከቅዱስ ሚካኤል እና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ በሦስተኛ ደረጃ ይቀመጣል፡፡ “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል (ጦቢት ፲፪÷፲፭)፡፡
ወርኀ ጳጉሜን
ወርኀ ጳጉሜን እንደሌሎቹ ወራት ፴ ቀናት ሳይሆን በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ስድስት ቀናት ሲኖራት በዘመነ ማርቆስ፣ በዘመነ ሉቃስና በዘመነ በማቴዎስ ደግሞ አምስት ቀናት ብቻ ይኖራታል፤ ነገር ግን የዓመቱ ዐሥራ ሦስተኛ ወር ተደርጋ ትቆጠራለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ (Thirty months of sunshine) በመባል ትታወቃች፣ ትለያለች፡፡ Enclopedia of Aethiopica. Vol II.
ጳጉሜ የሚለው ስያሜ ‹‹ኤፓጉሜኔ›› ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲኾን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው፡፡ /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(፲፱፻፵፰)፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት ሐዲስ፡፡ ገጽ ፱፻፭/፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ወርኃ ጳጕሜን የዓለም ፍጻሜ መታሰቢያ ተደርጋ ትታሰባለች፡፡ ይህም ጳጉሜ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከክረምት ወቅት ወደ ጸደይ መሸጋገሪያ እንደኾነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ፣ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ፣ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነትና ነው፡፡ ጳጉሜ የክረምቱ ማብቂያ እንደኾነች ሁሉ፤ ምጽአትም በመጨረሻው ዘመን መከራ የሚበዛበት የዚህ ዓለም ማብቂያ ናት፡፡ ወርኃ ጳጉሜ አዲሱን ዓመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ጻድቃን አዲሲቷን ምድር (መንግሥተ ሰማያትን) ለመውረስ ተዘጋጅተው “ኑ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” የሚባሉባት ናት፡፡
በዚህም የተነሣ ብዙ ምእመናን በጾምና በጸሎት (በሱባዔ) ያሳልፏታል፡፡ የጳጉሜ ጾም ከሌሎቹ የዓመቱ አጽዋማታችን መካከልና የዓመቱ መደምደሚያ ጾማችን በመኾኗ ብዙዎች በዚህ ወቅት ሱባኤ ይገባሉ (ማቴ.፳፭÷፴፬)፡፡
ርኅወተ ሰማይ
ከዚህም ጋር ተያይዞ በቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል በጳጉሜን ሦስት ሰማያት የሚከፈቱበት (ርኅዎተ ሰማይ) በመሆኑ በዚህች በተከበረችው ዕለት ምእመናን ጸሎታቸው ያርግላቸው ዘንድ ከምን ጊዜውም በበለጠ ተግተው ይጸልያሉ፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን የእኛም ጸሎታችንን በምልጃቸው የሚያሳርጉልን ቅዱሳን መላእክትም መሥዋዕቱን የሚያሳርጉበትና የአምላካችንን ምሕረት ቸርነት ለሰው ልጆች የሚያወርዱበት ዕለት ነው፡፡
ርኅወተ ሰማይ የስሙ ትርጉም የሰማይ መከፈት ማለት ሲሆን በክርስቶስ ክርስቲያን የተባሉ ሁሉ ጸሎት፣ ልመናቸው ምልጃቸው የሚያርግበት ዕለት ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት የምእመናንን ልመና መሥዋዕቱን የሚያሳርጉበት እና የአምላካችንን ምሕረት፣ ቸርነት ለሰው ልጆች የሚያወርዱበት ዕለት ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ውኆች እንደሚባረኩ በሚረዳ ጽኑ እምነት ምእመናን ወደ ወንዞች በመሔድና በሚዘንበው ዝናብ ይጠመቃሉ፡፡
ቅዱስ ሩፋኤል

በወርኀ ጳጉሜን ከሚከበሩ በዓላት መካከል በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሚከበረው የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅነቱ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዐት ይከበራል፡፡ “ሩፋኤል” የሚለው የስሙ ትርጓሜ “ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ” ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲኾን ስሙም ከሚካኤልና ከገብርኤል ቀጥሎ በሦስተኛ ደረጃ ይቀመጣል፡፡ “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል (ጦቢት ፲፪÷፲፭)፡፡ ይህ መልአክ እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን ይጠብቃቸዋል (ዳን.፬÷፲፫፤ ዘፀ. ፳፫÷፳ መዝ. ፺÷፲፩-፲፫ )፤ ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል (ሉቃ. ፲፫÷፮-፱፣ ዘካ.፩÷፲፪)፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያለ ማቋረጥ ፈጣሪያቸው ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት አንዱ ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት አድርገው ቅዱስ ሩፋኤልን በአደረገው ተአምር መሠረት እንደሚከተለው ይገልጹታል፡፡
ፈታሔ ማኅፀን፡ ማኅፀንን የሚፈታ
በብሉያና በአዲስ ኪዳን ብዙ እናቶች ከመካንነት የተነሣ ኀዘን ጸንቶባቸው ቢቆይም፤ ምንም የማይሳነው አምላክ እጅግ ድንቅን ያደረጉ የተባረኩ ልጆችን ሰጥቷቸዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የይስሐቅ እናት ሣራ፣ የያዕቆብ እናት ርብቃ፣ የዮሴፍ እናት ራሄል፣ የነቢዩ ሳሙኤል እናት ሐና፣ የመጥምቀ መለኮት የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ፣ የድንግል ማርያም እናት ሐና ይገኙበታል፡፡ እግዚአብሔር የመካኒቱን ማኅፀን ፈትቶ የተባረከ ልጅን የሚሰጥ አምላክ ነው፡፡ ይህንንም ጸጋ ለቅዱሳን መላእክት ሰጥቷል፡፡ ይህም ስልጣን ከተሰጣቸው ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አንዱ ነው፡፡
ሴቶች በምጥ የመልአኩን መልክዕ አንግተው “ማርያም ማርያም” ይላሉ ማየ ጸሎቱን ጠጥተው ቶሎ ፈጥነው ይወልዳሉ፡፡ የይስሐቅን እናት ሣራን፣ የሶምሶንን እናት (እንትኩይን) ምክነታቸውን የቆረጠ ወልዶ ለመሳም ያበቃቸው ይኸው ፈታሔ ማኅፀን የልዑል እግዚአብሔር መልአክተኛ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ለነፍሰጡር ሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ (ኗ) በማኅፀን እያለ (ች) ተሥዕሎተ መልክዕ (በሥላሴ አርአያ መልኩ /ኳ/ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል በጥበቃው አይለያቸውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀልላቸዋል፡፡ ሕጻናትን በእናታቸው ማኅፀን የሚጠብቃቸው እናቶችንም ከመፅነስ እስከ መውለድ የሚራዳቸው፣ የመካኖችንንም ማኅፀን የመፍታት ጸጋ የተሰጠው መልአክ ነው፡፡
ፈዋሴ ዱያን፡ ሕሙማንን የሚፈውስ
ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኃጢአት ቍስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የሚረዳ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ዅሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል (ሄኖክ ፲÷፲፫)፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” እንዳለ ሄኖክ (ሄኖክ ፮÷፫)፡፡ ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው መልአክ ነው፡፡ ዛሬም ሁላችንን በአማላጅነቱ ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ ይፈውሰናል፣ ይጠብቀናልም፡፡
መልአከ ከብካብ: ጋብቻን የሚባርክ መልአክ
በድርሳነ ሩፋኤል መጽሐፍ እንደተገለጸው፡- የራጉኤል ልጅ ሣራ ሰባት ሰዎች አግብተዋት ሰባቱም ባገቧት ሌሊት ሞተው አድረዋል፡፡ ይህንንም ከነነዌ ወደ ራጌስ የመጣው የጦቢት ልጅ ጦቢያ ያውቅ ነበር፡፡ ለአዛርያስም “ስለዚህ እኔ ለአባቴና ለእናቴ አንድ ልጅ ነኝ እርስዋን አግብቼ ከዚህ በፊት እንዳገቧት ሰዎች እኔም የሞትኩ እንደኾነ አባቴንና እናቴን የሚረዳቸው የለም ቢሞቱም የሚቀብራቸው አያገኙምና እፈራለሁ” አለው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ግን “አባትህ ከዘመዶችህ ወገን ካልሆኑ በስተቀር ሌላ ሴት እንዳታገባ ሲል የነገረህን ረሳኸውን? በል ሰባት ባሎቿ ሙተውባታል ስለምትለው እኔ መድኃኒቱን አሳይሃለሁ፤ አይዞህ አትፍራ አትሞትም የዓሣውን ሐሞትና ጉበቱን ያዘው ያልኩህ ለምን ይመስልሃል? እንግዲህ ሐሞቱንና ጉበቱን ከዕጣን ጋር ጨምረህ ስታጤስበት በሣራ አድሮ የነበረው አስማንድዮስ የተባለው ጋኔን ወጥቶ ይሄዳል ፈጽሞም ወደ እርሷ በገባህም ጊዜ ሁለታችሁ ይቅር ባይ ወደ ሆነው እግዚአብሔር ጸልዩ እርሷም የተዘጋጀች ናት፡፡ ከእኛ ጋርም ወደ ሀገርህ ይዘናት እንሄዳለን” አለው፡፡ ጦብያም ይህንን ቃል በሰማ ጊዜ ደስ አለውና ከእርሷ በስተቀር ሌላ እንዳያገባ በሙሉ አሳቡ ወሰነ፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ራጉኤል ቤት እንደ ደረሱ ሣራ በደስታ ተቀበለቻቸው የሣራ አባትም ጦብያን ገና እንዳየው ሚስቱ አድናን “ይህ ልጅ የእኔ ዘመድ ጦቢትን ይመስላል” አላት ከዚያም ጋር አያይዞ “ልጆች ከየት ሀገር መጣችሁ?” አላቸው፡፡ እነሱም “ከነነዌ ሀገር ነው የመጣን” አሉት፡፡ “ከዚያም ሀገር ጦቢት የሚባል ወንድም ነበረኝ ታውቁት ይሆን?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ጦቢያ አባቱን ሲጠራለት “እናውቀዋለን፡፡ እኔም ራሴ የጦቢት ልጅ ነኝ” አለው፡፡ ከዚያ በኋላ ራጉኤል “የወንድሜ ልጅ ነህን?” ብሎ እቅፍ አድርጐ ሳመው፡፡ አድናም ሳመችውና ሁሉም ተያይዘው የናፍቆት ልቅሶ ተላቀሱ፡፡ ከወንድሙ እንደ መጡም ሲገነዘብ በግ አርዶ በጥሩ ሁኔታ ጋበዛቸው፡፡ እራትም ከበሉ በኋላ ጦብያ ቅዱስ ሩፋኤል በመንገድ የነገረውን በልቡ ሲያወጣ ሲያወርድ ስለ ዋለ ቅዱስ ሩፋኤልን ያንን በመንገድ የነገርከኝን አሁን ፈጽምልኝ ሲለው ሰምቶ ስለ ልጅቷ መሆኑን ስለ ገባው ራጉኤል ጦብያን “ልጄ ይህች ልጅ ላንተ የምትገባ ናት ሰጥቸሃለሁ አይዞህ አትጠራጠር አሁንም ብላ ጠጣ ለዛሬም ደስ ይበልህ” አለውና ሣራ ካለችበት የጫጉላ ቤት አግብተው ዘጉት፡፡ ጦብያም ሣራን “በይ እኅቴ ኑሮዋችን እንዲቃናልንና ጋብቻችን እንዲባረክልን አስቀድመን ወደ ፈጣሪያችን ጸሎት እናድርግ” አላትና አብረው ጸሎት ካደረጉ በኋላ ያንን የያዘውንና የዓሣ ጉበትና ሐሞት ከዕጣን ጋር ጨምሮ ቢያጤስበት በሣራ አድሮ ባሎችዋን ይገድልባት የነበረው አስማንድዮስ የተባለው ጋኔን ከሣራ ለቆ ወጥቶ ሄደ ሁለተኛም ሊመለስ አልቻለም፡፡ እነርሱም በሰላምና በጤና አደሩ፡፡
ቅዱሳንም ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ ጋብቻን በጸሎታቸው ይባርካሉ፡፡ የጦብያንና የሣራን ጋብቻ የባረከ ቅዱስ ሩፋኤል ስለኾነ “መልአከ ከብካብ” ይባላል፡፡ ዛሬም በምልጃው ላመኑት ጋብቻን ይባርካል፣ ትዳርንም ያጸናል፡፡
ሰዳዴ አጋንንት፡ አጋንንትን የሚያሳድድ
ቅዱስ ሩፋኤልም በተሰጠው ሥልጣን አጋንንትን የሚያሳድድ መልአክ ነው፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በሣራ (ወለተ ራጉኤል) ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል (ጦቢት ፫÷፰-፲፯)፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል “ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ተብሎ እንደ ተጻፈ (ሄኖክ ፫÷፭-፯)፡፡ ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው (ሄኖክ ፪÷፲፰)፡፡ ዛሬም ከእግዚአብሔር ተልኮ ለሰው ልጆች የተንኮልን፣ የጥላቻን፣ የመገዳደልን ሐሳብ እንዲያፈልቁ የሚያደርገውን የመልካም ነገር ጠላት የኾነውን ጠላታችንን አስጨንቆ የሚያባርር መልአክ ነው፡፡
እንደ ማጠቃለያ
በወርኀ ጳጉሜ በገናንነት የሚከበረው የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል በዓል፤ የአሮጌው ዘመን በዓላት መዝጊያ ለአዲሱ ዘመን ርዕሰ ዐውደ ዓመት ለቅዱስ ዮሐንስ በዓልም መሸጋገሪያ ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲኾን በመጽሐፈ ጦቢት፣ በመጽሐፈ ሄኖክ፣ በመጽሐፈ አክሲማሮስ እና በድርሳኑ ላይ እንደተገለጠው ከእግዚአብሔር በተሰጠው ጸጋ የሚካኒቱን ማኅፀን የሚያለመልም፣ ሕፃናትንም በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ የሚጠብቃቸው፣ ድውያነ ሥጋንና ድውያነ ነፍስን የሚፈውስ፣ ምሕረትን ለሚሹ ፈጥኖ የሚደርስ፣ የክፋት አባት የኾነውን ጠላት ሰይጣንን የሚያሳድድ፣ በጋብቻና በትዳር የሚፈተኑትን የሚረዳ፣ በመንገድ ያሉትን የሚመራ መልአክ ነው፡፡
የሊቀ መልአክ የቅዱስ ሩፋኤል ጸሎቱና አማላጅነቱ አይለየን፡፡አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ ድርሳነ ቅዱስ ሩፋኤል የወርኀ ጳጉሜን
✍️ መጽሐፈ ስንክሳር ጳጉሜን ሦስት
✍️ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት
✍️ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ
✍️ Enclopedia of Aethiopica. Vol II.
©EOTC tv

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አ...
07/09/2026

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች «የእንኳን አደረሳችሁ» ስጦታ አበረከተ።

ጳጉሜ ፪ ቀን ፪፻ ፲ወ፰

ስጦታው ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም የበላይ ኀላፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅርሳ ቅርስ ወመዘክርና የማኅበራት ክትትል መምሪያዎች የበላይ ኃላፊ ለብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማት ኮምሽንና የድርጅቱ የበላይ ሊቀ ጳጳስ የቀረበ ሲሆን፤ ተቋሙ ለቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎችና አባቶች ያለውን ጥልቅ አክብሮት፣ ፍቅርና የመታዘዝ መንፈስ የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል።

ስጦታው ድርጅቱ የቤተ ክርስቲያኗን ሀብትና ንብረት በጥንቃቄ የመጠበቅና የማልማት ኃላፊነቱን በሚወጣበት እንቅስቃሴ ውስጥ አባቶች ላደረጉለት ያልተለየ ድጋፍ፣ አባታዊ መመሪያና ጸሎት የታላቅ ምስጋና መግለጫ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የበዓል እንኳን አደረሳችሁ ስጦታ የማበርከትና ከአባቶች ቡራኬ የመቀበል ሥነ ሥርዓት ድርጅቱ አምናም ሲፈጽመው የቆየና እንደ መልካም ተቋማዊ ባህል አጠናክሮ የያዘው ተግባር ነው። በየዓመቱ በበዓላት ወቅት አባቶችን ማሰብ፣ ማክበርና መንፈሳዊ ቡራኬያቸውን መቀበል የተቋሙ ጽኑ እምነት እንደሆነና ይህ በጎ ልማድ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቅሷል።

በስጦታ ማበርከቱ ሥነ-ሥርዓት ወቅት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እስከአሁን ድርጅቱ ያደረገውን በጎ አፈጻጸም አድንቀው አዲስ ዓመት አዲስ የሚሆነው አዲስ ነገር ሲሠራበትና ቤተክርስቲያንን ከፍከፍ ስናደርግበት ነውና በአዲሱ ዓመት ይህንኑ አድርገን እስከ አሁን ከምናውቀው በተሻለ አፈጻጸም እንደምትመጡ አምናለሁ ብለዋል።

በመቀጠልም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራአስኪያጁ ባለፈው አንድ ዓመት ድርጅቱ ያሳየው ትጋት እጅግ የሚያስደንቅ መሆኑን ገልጸው ወደፊትም ቢሆን እኛን ያሰባሰበችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማስቀደም ግድ ስለሆን እርሷን አስቀድመን ጠንክረን መሥራት ይገባናል ብለዋል።

ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በበኩላቸው የድርጅቱ መነቃቃትና ትጋት በዚሁ እንዲቀጥል አሳስበው ለተደረገው የመልካም ምኞት ስጦታን አመስግነዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሸማኔ መወርወሪያ በሚፈጥነው ጊዜ ውስጥ እየኖርን ለሥራ አለመፍጠን አይቻልምና ልክ እንደ 2018ዓ.ም ቀጣዩን ዓመትም በዚሁ ልክ እየሠራን ልናሳልፍ ይገባል ያሉት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የድርጅቱ የበላይ ሊቀ ጳጳስ ናቸው።

በመጨረሻም አባቶች በደርጅቱ የተበረከተላቸውን ስጦታ በደስታ የተቀበሉ ሲሆን፤ ድርጅቱ የቤተ ክርስቲያኗን ንብረቶች በማልማትና ገቢዋን በማሳደግ በኩል እያከናወነ ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀዋል። አባቶች አክለውም ተቋሙ በቀጣይ በዘመናዊ አሠራርና በግልጽነት የታገዘ የልማት ሥራ በማከናወን የድርሻውን እንዲወጣ አባታዊ መመሪያና ቡራኬያቸውን አስተላልፈዋል።
© ኢኦተቤክ_ቤሕአልድ

ፍኖተ ሎዛ ሰንበት ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምረቃና የበጀት ዓመቱ የመዝጊያ መርሐ ግብር ተከናወነጳጉሜን 02 ቀን 2018 ዓ/ም  Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀ...
07/09/2026

ፍኖተ ሎዛ ሰንበት ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምረቃና የበጀት ዓመቱ የመዝጊያ መርሐ ግብር ተከናወነ
ጳጉሜን 02 ቀን 2018 ዓ/ም Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣ በሰበታ ገላን ጉዳና ፉሪ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር በሚገኘው የዓለምገና ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሎዛ ሰንበት ትምህርት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመዝጊያና የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሄደ።

ሰንበት ትምህርት ቤቱ በበጀት ዓመቱ በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን፤ ትምህርታቸውን ላጠናቀቁት የምስክር ወረቀት ሰርተፊኬት፣ እንዲሁም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ኮከብ ተማሪዎች በሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ ክፍል ኃላፊ እና በደብሩ አስተዳዳሪ እጅ ልዩ ልዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል።

የዕለቱ መርሐ ግብር በሊቃውንቱና በአበው ካህናት ጸሎትና ቡራኬ ተጀምሮ የዕለቱ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። "የምእመናን ድርሻ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቱ፣ የደብሩ አስተዳደር እና የስብከተ ጉባኤ ኃላፊነት" በሚል ርዕስ በሰንበት ትምህርት ቤቱ ሰብሳቢ ዲያቆን ዝናቡ ግዛው አቅራቢነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የሸገር ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ ክፍል ኃላፊ መጋቤ ወንጌል ሄኖክ ታዬ፤ "ለነገይቱ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ እንሥራ፤ ትውልዱንም በሃይማኖት እናጽና" ሲሉ አሳስበዋል። ኃላፊው አያይዘውም፤ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ማኅበራትን አስተባብሮ በሥርዓተ ትምህርት መሠረት አስተምሮ ማስመረቁ ለአበው አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸው፣ ለሥራው መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉት የደብሩ አስተዳዳሪ ክቡር መልአከ ገነት ልዑል ስብሐት፣ ለደብሩ ሠራተኞች፣ ለሰበካ ጉባኤ አባላትና ለመምህራን ምስጋና አቅርበዋል።

በዕለቱ የታደሙት ምእመናንም በመርሐ ግብሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ወደፊትም ከደብሩና ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ጎን በመቆም የድርሻቸውን ለማበርከትና ለወንጌል አገልግሎት መስፋፋት ተጋግዘው ለመሥራት ቃል ገብተዋል።

የበጀት ዓመቱ የመዝጊያና የምረቃ መርሐ ግብር በደብሩ አስተዳዳሪ በክቡር መልአከ ገነት ልዑል ስብሐት አባታዊ መልእክትና የጸሎት ቡራኬ ፍጻሜ አግኝቷል።

ምንጭ፦ የክ/ከተማ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት /

ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/ በጮሎ ባቦ መ/መ/ቅ/ዮሐንስ  ቤተ ክርስቲያን ወርሃዊ የቅዱስ ዮሐንስ በዓል በማ...
06/09/2026

ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

በጮሎ ባቦ መ/መ/ቅ/ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ወርሃዊ የቅዱስ ዮሐንስ በዓል በማስመልከት በርካታ ምዕመናን በተገኙበት የወንጌል መርሐ ግብር ተከናወነ።

ምንጭ፦ መጋቤ ወንጌል ሄኖክ ታዬ

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Miidiyaa Biyya Lallabaa Shaggar/የሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share