Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

Miidiyaa  Shaggar/ሸገር  ሀገረ ስብከት ሚዲያ/ Biyya Lallaba Magaalaa Shaggar irraa kan darbu "ከሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሚተላለፍ Broadcasted from the Sheger City Diocese.
(1)

Follow the EOTC Shegercitydiocese page to get all the latest news about the EOTC in Afaan Oromoo and Amharic.

በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተመራ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ልዑክ የተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጎበኘ።ሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም. Miidiyaa  Shaggar/ሸገር  ሀገረ ስብከት ...
08/06/2026

በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተመራ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ልዑክ የተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ጎበኘ።

ሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም. Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የተመራ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን፤ በፒያሳ ልዩ ስሙ አሮጌ ቄራ እና በጠቅላይ ቤተ ክህነት አካባቢ በግንባታ ላይ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዘመናዊ ሕንጻዎች ጎበኘ።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የሕንጻዎቹ የግንባታ ሂደት አፈጻጸም ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለመገምገምና እያጋጠሙ ያሉ ማነቆዎችን በመለየት መፍትሔ ለመስጠት መሆኑ ተገልጿል። ብፁዕነታቸው በሁሉም የግንባታ ቦታዎች በአካል በመገኘት የሥራውን ሂደትና ጥራት በጥንቃቄ የተመለከቱ ሲሆን፣ የየፕሮጀክቶቹ ተቋራጮችም (ኮንትራክተሮች) እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትንና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ አድርገውላቸዋል።

የግንባታው ተቋራጮች በገለጻቸው ወቅት፤ ብፁዕነታቸው በተደጋጋሚ እስከ ሳይቶቹ ድረስ በመገኘት የሚያደርጉት ቀጣይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ ለሥራው መፋጠንና ለጥራቱ መጠበቅ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ መሆኑን ገልጸው፣ እያጋጠሟቸው ያሉ ወቅታዊ ችግሮች እንዲቀረፉላቸው ጠይቀዋል።

ብፁዕነታቸውም ከተቋራጮቹ የተነሱትን አበይት ችግሮች ካደመጡ በኋላ፣ የግንባታው ሂደት ሊከተለው ስለሚገባው ሥርዓትና መስተካከል ስለሚገባቸው ጉዳዮች አባታዊ የሥራ መመሪያና ምክር ሰጥተዋል። አክለውም፣ እየተገነቡ ያሉት ሕንጻዎች የቤተ ክርስቲያኒቱ የልማትና የዕድገት አካል በመሆናቸው ተቋራጮቹ ሥራውን እንደ ራሳቸው ንብረትና ኃላፊነት ሊቆጥሩት እንደሚገባ አሳስበዋል። በግንባታው ሂደት ላይ የሚገጥሙ ፈተናዎችን በጽናትና በብልሃት በማለፍ፣ የሕንጻዎቹ ግንባታ ጥራታቸውን ጠብቀውና በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁም ብፁዕነታቸው አሳስበዋል።

"አገልግሎታችን ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት ዓምድ ነው!" የቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር 5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን አከበረ።ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. Miidiyaa  Shaggar/...
07/06/2026

"አገልግሎታችን ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት ዓምድ ነው!" የቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር 5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን አከበረ።

ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

የቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር (ወልዳ ዱበሮ ማርያም) "አገልግሎታችን ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት ዓምድ ነው!" በሚል መሪ ቃል 5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን በዛሬው ዕለት በአራት ኪሎ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው በቅዱስ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን የመሰብሰቢያ አዳራሽ የማኅበሩ አባላት በተገኙበት አክብሯል።

ማኅበሩ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች (ፕላትፎርሞች) የመጀመሪያ አገልግሎቱን የጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ምእመናን በቋንቋቸው የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ ለማድረግ በሀገር ውስጥ 10፣ በውጭ ሀገር ደግሞ 4 ቅርንጫፎችን ማፍራት መቻሉ ተገልጿል።

ይህ መንፈሳዊ ማኅበር በኢሉ አባ ቦራ ሀገረ ስብከት አንድ አዲስ ቤተ ክርስቲያን አሳንጾ ለምርቃት ያበቃ ሲሆን፤ በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት በጊዳ አያና ወረዳ ተዘግቶ የነበረውን ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማስከፈትና አገልግሎት እንዲጀምር ለማድረግ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝም በማጠቃለያው አስታውቋል።


ማኅበራዊ ሚዲያን ለመንፈሳዊ አገልግሎት የመጠቀም ፋይዳ
በዜናው ላይ እንደተጠቀሰው ማኅበሩ መጀመሪያ የተቋቋመውና ሥራውን የጀመረው በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሆን ይህ እውነታ ቴክኖሎጂው ለሐዋርያዊ አገልግሎትና ለወንጌል ማስፋፊያ ያለውን ከፍተኛ ሚና በግልጽ ያሳያል።

ማኅበራዊ ሚዲያን ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት መጠቀም የሚከተሉት ዓበይት ፋይዳዎች አሉት

ርቀትን ማጥበብና ዓለም አቀፍ ተደራሽነት፦ ወንጌል በጂኦግራፊያዊ ድንበር ሳይወሰን በአንድ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ምእመናን በፍጥነት እንዲደርስ ያደርጋል። በውጭ ሀገር የሚኖሩ ወገኖችም ከእናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ከሃይማኖታቸው ጋር በቀላሉ እንዲገናኙ ይረዳል።

በቋንቋ የመድረስ ዕድል፦ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ምእመናን በቀላሉ በገዛ ቋንቋቸው የወንጌልን ትምህርት እንዲሰሙና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነታቸውን እንዲረዱ ሰፊ ዕድል ይፈጥራል።

ሀብትና የሰው ኃይል ማስተባበር፦ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ለመሥራትና የተዘጉትን መልሶ ለማስከፈት የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከምእመናን ለማሰባሰብ ማኅበራዊ ሚዲያ ትልቅ የመገናኛ አቅም ይፈጥራል።

ለወጣቱ ትውልድ መድረስ፦ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ወጣት ጊዜውን የሚያሳልፈው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በመሆኑ፣ ክፉ አስተሳሰቦችንና የሞራል መውደቅን ለመከላከል፤ መንፈሳዊና ገንቢ የሆኑ መልእክቶችን ወደ ወጣቱ ዘንድ ለማድረስ ከሁሉ የተሻለ መሣሪያ ነው። ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር።

Waggaa 5ffaan Hundeeffama Waldaa Dubroo Maariyaamii Mata-duree "Tajaajilli Keenya Utubaa Manneen Kiristaana Baadiyyaati!...
07/06/2026

Waggaa 5ffaan Hundeeffama Waldaa Dubroo Maariyaamii Mata-duree "Tajaajilli Keenya Utubaa Manneen Kiristaana Baadiyyaati!" Jedhuun Kabajame.

Caamsaa 30, 2018 B.A. | Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

Waldaan Dubroo Maariyaamii hundeeffama isaa waggaa 5ffaa guyyaa har'aa Kaatedraala Teessoo Waaqummaa Qulqulluu Sillaasee Kiiloo 4, Galma Mana Kiristaanaa Qulqulluu Baalawalditti mata-duree "Tajaajilli keenya Utubaa Manneen Kiristaana Baadiyyaati!" jedhuun kabajateera.

Waldaan kun jalqaba irratti karaa miidiyaalee hawaasummaa hojii kan jalqabe yoo ta'u, yeroo ammaa kanatti amantoonni afaan isaaniitiin wangeela akka dhaga'aniif biyya keessatti dameewwan 10, biyya alaatti ammoo dameewwan 4 horachuu danda'eera.

Godina Iluu Abbaa Booraatti Mana Kiristaanaa Abune Gabra Manfas Qiddus ijaarsisee eebbaaf qaqqabsiiseera.

Biyya Lallabaa Wallagga Bahaatti Aanaa Giddaa Ayyaanatti mana kiristaanaa cufamee ture deebisee bansiisuuf sochii irra akka jiru beeksiseera.

Dabalataanis, Kiristaanota Biyya Lallaba Arsii Bahaa keessatti miidhaan irra deddeebiin qaqqabaa jiruuf gaddi guddaan akka itti dhaga'ame ibsuun, nagaa fi jajjabina hawwera.
Maddi:- EOTC Afaan Oromoo

Mana Kiristaanaa Qulqulluu Mikaa’el Garmeentitti Amantoonni Haaraan Cuuphaman.Caamsaa 30, 2018 B.A Miidiyaa  Shaggar/ሸገር...
07/06/2026

Mana Kiristaanaa Qulqulluu Mikaa’el Garmeentitti Amantoonni Haaraan Cuuphaman.

Caamsaa 30, 2018 B.A Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

Biyya Lallaba Magaalaa Shaggar, Kutaa Mana Lubummaa Magaalaa Sabbataa, Galaan Guddaa fi Fuuriitti kan argamu, Mana Kiristaanaa Tulluu Araaraa Qulqulluu Mikaa’el Garmeentiitti amantoonni haaraan lama cuuphamuun mucummaa Sillaasee argatanii jiru.

Milkaa'inni kun bu'aa tajaajila wangeelaa qindoomina Kutaa Lallaba Wangeelaa fi Yaa'ii Sabakaa Gubaa'ee mana kiristaanichaa gidduutti taasifame irraa kan argamedha jechuun, manni kiristaanichaa miidiyaa keenyaaf ibsa kenneera.

Mana kiristaanaa kanaatti amantii biraa hordofaa kan turan ja'a (6) kanaan dura barsiifamanii cuuphamuun gara mana Qulqulleetti Kiristaanaatti makamuun isaanii ni yaadatama.

Yeroo ammaattis Amantoonni haaraan cuuphamanii mucummaa Waaqayyoo argachuuf, gargaarsa Kutaa Lallaba Wangeelaatiin barnoota isaanii kan duraa hordofaa akka jiran beekameera.

በሸገር ከተማ በጋርመንት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ አማንያን ተጠመቁ።ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም | Miidiyaa  Shaggar/ሸገር  ሀገረ ስብከት ሚዲያ/ በሸገር ከተማ ሀገ...
07/06/2026

በሸገር ከተማ በጋርመንት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ አማንያን ተጠመቁ።

ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም | Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣ በሰበታ ገላን ጉዳ እና ፉሪ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በጋርመንት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሁለት እህቶች በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል። ይህ ስኬት የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት እና የስብከተ ወንጌል ክፍል በጋራ ባከናወኑት የተቀናጀ የወንጌል አገልግሎት የተገኘ ፍሬ መሆኑን ከደብሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ደብሩ ቀደም ሲል የሌላ እምነት ተከታይ የነበሩትን እነዚህን አዲስ አማንያን ጨምሮ፣ ባለፉት ወራት በተመሳሳይ መልኩ ስድስት ሰዎችን አስተምሮ ማጥመቁ ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅትም በጥምቀተ ክርስትና የእግዚአብሔርን ልጅነት ለማግኘት፣በደብሩ ስብከተ ወንጌል ክፍል አማካኝነት የቅድመ ጥምቀት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።

ምንጭ፦ ደብሩ

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የጉልላት መስቀል በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ በጉልላቱ ላይ ተቀመጠ፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቁነ ሕርያቆስ  የአዲስ አበባና ...
07/06/2026

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የጉልላት መስቀል በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ በጉልላቱ ላይ ተቀመጠ፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቁነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ስብሐት ዐቢይ ዘለቀ የብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ልዩ ጸሐፊ ፣ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ታደለ የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ሥራአስኪያጅ ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል፡፡

የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከተቆረቆረ 130 ዓመታትን ያስቆጠረ በሥነ ሕንጻ ቅርጹ ለየት ያለ ታሪካዊ ድንቅ ቤተክርስቲያን ነው።

📷 EOTC TV

የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

Maqaa Abbaa Kan Ilmaa Kan Afuura Qulqulluu Waaqa Tokko Ameen  Waamicha Yaa'ii Afuurawaa AddaaMana Kiristaanaa Tulluu Ifa...
05/06/2026

Maqaa Abbaa Kan Ilmaa Kan Afuura Qulqulluu Waaqa Tokko Ameen
Waamicha Yaa'ii Afuurawaa Addaa
Mana Kiristaanaa Tulluu Ifaa Qulqulleettii Kakuu Araaraa Awaashiitti, Yaa'iin Addaa Afuuraa Tokkummaa Waldaaleen Caamsaa 30/2018 B.A. ni gaggeeffama.

Isinis yaa'ii kana irratti argamuun eebba argamu qooddachuu fi hirmaattota akka taataniif affeeramtaniittu.

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜ።

#ልዩ መንፈሳዊ የጉባኤ ጥሪ
በአዋሽ ደብረ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ልዩ የማኅበራት የአንድነት ጉባኤ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ስለሚካሄድ፣ እናንተም በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል።

ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዓን አባቶችን መደበግንቦት   28 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ  በምሥራቅ አርሲ ሀ...
05/06/2026

ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዓን አባቶችን መደበ

ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተገኝተው ጉዳት የደረሰባቸውን ኦርቶዶክሳዊያን የሚያጽናኑ ብፁዓን አባቶችን መደበ።

የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሺርካ፣ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በዛሬው ዕለት ባካሔደው መደበኛ ስብሰባው በችግሩ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ፣ በብፁዓን አባቶች የሚመራ የቤተ ክርስቲያናችን ልዑካን ቡድን ችግሩ ወደ ተፈጠረበት ቦታ በመሄድ ተጎጂዎችን እንዲጎበኝ፣ እንዲያጽናና እና አስፈላጊውን ጊዜያዊ ድጋፍ አንዲያደርግ ወስኗል።

ቋሚ ሲኖዶስ በጠቅላይ ቤተክህነት በኩል በሚቋቋም ኮሚቴ አስተባባሪነትም በተፈጠረው ችግር ምከንያት የመቃጠል አደጋ የደረሰበት ጥንታዊው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲያሰራ፣ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች በቋሚነት ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ፣ በሀገረ ስብከቱ ዳግመኛ መሰል ችግሮች እንዳይፈጠርሩ ጥናት አካሒዶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር የሚያቀርብ ዐቢይ ኮሚቴ ተሰይሞ በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል።

በትላንትናው ዕለት በምሥራቅ አርሲ አንዳንድ ወረዳዎች የተከሰተውን ችግር ተከትሎ ፦

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
ብፁ አቡነ ዲዮስቆሮስ
ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ከፌዴራል ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተከሰተው ችግር ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።
tv

በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስዋና ጸሐፊው የተመራ የቤተክርስቲያናችን የልኡክከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተ...
05/06/2026

በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ
ዋና ጸሐፊው የተመራ የቤተክርስቲያናችን የልኡክ
ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።
(ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት አንዳንድ ወረዳዎች በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ሕልፈተ ሕይወትና የቤተ ክርስቲያን መቃጠልን በማስመልከት የተሰማትን ጥልቅ ኀዘን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አማካኝነት ከገለጸች በኋላ ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመራ ከፍተኛ የቤተክርስቲያናችን የልዑካን ቡድን ከሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ፣
ከሚኒስትር ዲኤታው ከዶ/ር ኸይረዲን ተዘራና ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስሮስ በምሥራቅ አርሲ በአሰኮ፣ በሺርካ፣ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ በደረሰው የሕይወት ጉዳት እና በጥንታዊው ቤተ ክርስቲያን መቃጠል እጅግ ማዘናቸውን ገልጸው መንግሥት የችግሩን ምንጭ አጣርቶ ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግና በአካባቢውም አስተማማኝ ሰላምን እንዲያሰፍን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

አያይዘውም በአሁኑ ወቅት በችግሩ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትና መልሰው የሚቋቋሙበት ሥራ እንዲሠራ፣ ወንጀሉን የፈጸሙ ሰዎችም ለፍርድ ቀርበው
ቅጣታቸውን እንዲያገኙ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የምሥራቅ አርሲና የጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሀገረ ስብከታቸው የተከሰተውን ችግር በማስመልከት ዝርዝር መረጃዎችን በቊጥራዊ ማስረጃዎች አስደግፈው አቅርበዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው
በተፈጠረው ችግር እጅግ በጣም ማዘናቸውን ገልጸው በመንግሥት በኩል በአስቸኳይ አጣሪ ቡድን ተቋቁም ወደ ስፍራው ተልኳል ካሉ በኋላ የአጣሪ ቡድኑን ሪፖርት መሠረት በማድረግም አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ብፁዓን አባቶቻችን በኦሮሚያ ፕ/ት ጽ/ቤት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ከብልጽግና ፓርቲ ድ/ ቤት አመራሮች ጋር ዝርዝር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ወቅት የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንደገለጹት የክልሉ መንግሥት በሥፍራው የተከሰተውን ችግር ለመቆጣጠርና ሊከሰት ይችል የነበረውን ተጨማሪ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጉን፣ በአሁኑ ወቅትም ወደ ሥፍራው አጣሪ ቡድን መላኩንና የማጣራት ውጤቱን ተከትሎም አጥፊዎችን ለሕግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው ቤተክርስቲያኗ ምዕመናንን ለማጽናናትና ድጋፍ ለማድረግ በምታደርገው ጥረት ሁሉ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግላት ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ፣ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንዲሁም የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለመገንባት እና በአካባቢው ዳግመኛ መሰል ችግር እንዳይፈጠር ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በተጠናከረ መልኩ እንደሚያከናውኑ ከልዑካን ቡድኑ ጋር ባደረጉት የማጠቃለያ ውይይት ገልጸዋል።
©ኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የራሺያ ቤተክርስቲያን ልኡካን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጉብኝት አደረጉ። ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ምልኡካኑ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳ...
03/06/2026

የራሺያ ቤተክርስቲያን ልኡካን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጉብኝት አደረጉ።
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

ልኡካኑ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ከብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፣ የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ከብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል ።
ከልኡካኑ መካከል የሞስኮ ፓትርያርክ የውጭ አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት መምሪያ ሊቀመንበር የሆኑት የቮሎኮላምስክ ሜትሮፖሊታን አንቶኒ የራሺያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር ያላትን መንፈሳዊ አና ታሪካዊ ግንኙነት አንስተው በቀጣይም የጋራ ሥራዎች እንዳሏቸው ገልጸዋል ።
አያይዘውም በሩሲያ የቲዎሎጂ አካዳሚዎች ከፍተኛ ትምህርታቸውን ለመከታተል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ወደ ራሺያ ማቅናታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር መቻሉን ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፣የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በበኩላቸው የራሺያ ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያለፋበት መንገድ ተመሣሣይነት ያለው መሆኑን አንስተው በበርካታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት መወያየታቸውን ተናግረዋል ።
©EOTC TV

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share