19/02/2024
------ የወንጌል ባላደራነት ----
የወንጌል ባላደራነትን ለመወጣት በመጀመሪያ ማንነታችንን ማወቅ ያስፈልጋል። ማወቅ መሰረታዊ ነገር ነው። ሰው የሚያምነው የሚያውቀን ያህል ነው። ሮሜ 10:14
ከየት መጥሁ? ለምን መጣሁ? ወዴት እሄዳለሁ? ብልን እንጠይቅ
ማን ነበርኩ?
በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ከአግዚአብሔር የተለየሁ (ኤፌ 2:1) ፣ አጢአተኛ ነበርኩ (ሮሜ 3:23፣) የሰይጣን ልጅ ነበርኩ (ዮሐ 8:44)
በዚህ ምክንያት የነበረኝ States ወይም ቦታ፥-
1) የሰይጣን ባሪያ ነበርኩ ዮሐ 8:44
2) ጣዖትን አምላኪ ነበርኩ መንፈሳዊ ችግር (ዘጸ 20:4-5)
3) የአእምሮ ችግር ያለበት ሰው ነበርኩ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ስጋት ወዘተ (ማቴ 11:21)
4) አካላዊ ችግር የነበረብኝ ነበርኩ-ቤተሰብ ችግር፣ ከአጋንንት የሚላክ በሽታ (ሐዋ 8: 4-8)
5) ከሞት በኋላ የዘላለም ሞት የተገባኝ የተፈረደብኝ ነበርኩ ሉቃ 16: 19-31 ዕብ 9:27
6) ከዘር የሚተላለፍ መንፈስ ወይም መርገም ወስጥ ነበርኩ (ማቴ 27:25)
ሰው ከዚህ ችግር ለመውጣት የራሱን ዘዴ ሞክሯል ግን አልሆነም። የሞከራቸው ነገሮች በጥቂቱ
1) ሀይማኖት፥- የሰው ሰርዓት፣ ደንብ፣ ወግ፣ ህግ (ማቴ 12:43-45)
2) መልካም ስራ (ኢሳ 64:6)
3) ፍልስፍና (ቆላ 2:8)
ይሄ ሁሉ ግን ሰውን ሊያድን አልቻለም ስለዚህም እግዚአብሔር ለእኛ የተገለጠው የድነት መንገድ፥-
1) ወደደን (ዮሐ 3:16)
2) ክርስቶስ ስለ እኛ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞተ (ሮሜ 5:8)
3) መንገድ እውነት ሕይወት ሆነልን (ዮሐ 14:6)
4) ደም አፍስሶ አስታረቀን (ሮሚር 8:2)
5) ከሰይጣን እስራት አውጥቶ ስልጣን ሰጠን (1ዮሐ 3:8)
6) ይህ ሁሉ መስዋእትነት የተከፈለበት ቢሆንም እንዲሁ በጸጋውና በእምነት መዳን ሆነልን (ኤፌ 2:8-9)
አሁን እኛ ጌታ ያደረገልንን ያመንን
1) መንፈስ ቅዱስን ተቀበልን (1ቆሮ 2:12)
2) የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ቤተመቅደስ ሆንን 1ቆሮ 3:16
3) በመንፈስ ቅዱስ መመራትን አገኘን ዮሐ 14: 16-17
4) በመንፈስ ቅዱስ ተሞላን ሐዋ 1:8
5) የልጅነት ስልጣን አገኘን ዮሐ 1:12
6) የሰይጣንን ስራ የማፍረስ ስልጣን አገኘን ሉቃ 10:19
7) የመልአክቶች ጥበቃ አገኘን ዕብ 1:14
8) የሰማዊ ዜግነትን አገኘን ፊልጵ 3:20
9) ታላቁ ተልዕኮን በመፈጸም ዓለምን የማሸነፍ የመማረክ መብት አገኘን ማቴ 28: 18-20
10) ለጸሎታችን ምላሽ የማግኘት ስልጣን አገኝን ዮሐ 14:14, ማቴ 7:7-11, ኤር 33:3, ሉቃ 18:1-8
11) የአጢአት ይቅርታ አገኘን ሮሜ 8:1-2, 1ዮሐ 1:9
12) በየቀኑ በድል የመመላልስ የአሸናፊነት መብት አገኘን 1ቆሮ 10:13,
------ የፍቅር ዕዳ አለብን -----
ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ ያለው ጳውሎስ ይህ ገብቶት ነው። እውነተኛ ወንጌል ሲገባን ብቻ በረከታችንን እና ማንነታችንን እናውቃለን። በዚህ ጊዜ እንደ ጳውሎስ እውነተኛ ወንጌልን ለመስበክ የሕይወታችን ዋና እሴት እናደርገዋለን።
እግዚአብሔር ጸጋና ሀይሉን የልብ አይኖቻችንን የልብ ጆሮዋችንን ይክፈትልን። እኛ ያገኝነውን ሌሎቹም እንዲያገኙ ወንጌልን መስበክ ስራችን ይሁን።
“ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም።”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥5
ብሩካን ናችሁ!