ምስጋና ቲዩብ - Praise Tube

ምስጋና ቲዩብ - Praise Tube እኔ እና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን!!

በህግ ጥላ ውስጥ ያለ ህገወጥነት ፍትህ ሆይ ወዴት ነሽ?በወር ከ60,000 ብር ወደ 320,000 ብ ር የሚያስጨምር  ኢፍትሀዊነት ! በምን ስሌት ይሆን???!!! በቅዱሳን ሀብት እና ጉልበት ...
04/04/2026

በህግ ጥላ ውስጥ ያለ ህገወጥነት
ፍትህ ሆይ ወዴት ነሽ?
በወር ከ60,000 ብር ወደ 320,000 ብ ር የሚያስጨምር ኢፍትሀዊነት ! በምን ስሌት ይሆን???!!!

በቅዱሳን ሀብት እና ጉልበት የተገነባውን የቤተክርስትያን ንብረት እንዲሁም የህዝብ ንብረት የሆነውን ዘመናዊ የአምልኮ አዳራሻችንን መንግስት እና ፍትህ ባለበት ሀገር በጠራራ ፀሀይ ፍትህን በማጣመም አጭበርብረው መነጠቃችን ሳያንስ በሥራ አፈጻጸማቸውና በሥነ-ምግባር ችግር አንቱታን ያገኙን በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ የተሰገሰጉን ጥቂት ግለሰቦችን በተለያየ ነገር በመደለል ጭምር በወር 60 ሺህ ብር እንከፍልበት የነበረውን ቦታ 400% ጨምረው በወር 320 ሺህ ብር ሒሳብ ተሰልቶ እንድንከፍል በግፍ ተበይኖብናል። የትኛው የአዲስ አበባ ወይም የሀገራችን ክፍል 400% የኪራይ ጭማሪ የተደረገበት ቦታ እንዳለ እኛ አይገባንም ይሁንና አሁን ቤተ ክርስቲያን ላይ ግን ይህ ግፍ ተሰርቷል ያውም እራሷ በሰራችው አዳራሽ እና ቢሮዎች ማለት ነው።

ይህ አዳራሽ በሚገኝበት በተለምዶ ለም ሆቴል በመባል በሚታወቀው በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 4 አካባቢ የሚገኙ እጅግ ቅንጡ የሆኑ የመኖሪያ አፖርትመንቶች እንዲሁም ቢሮዎች እንኳን ባለፉት 4 እና 5 አመታቶች ውስጥ ከ10% እና 30% በላይ የኪራይ ጭማሪ አለማድረጋቸው እሙን ሆኖ ሳለ፤ እኛ እራሳችን አዘምነን በገነባነው አዳራሽ ላይ ከአካባቢው ዋጋ እጅግ በተጋነነ መልኩ 60 ሺህ ብር እንከፍልበት የነበረውን ቦታ 400% ጨምረው በወር 320 ሺህ ብር ሒሳብ ክፈሉ መባላችን በፍትህ መንበር የተሰየሙት ዳኞች ከጥቅም ባለፈ ለእምነቱ ያላቸውን ጥላቻ ያንፀባረቁበት የበቀል በትር መሆኑን በገሀድ ያሳያል።

ምን ግዜም ለህግ ተገዢ የሆነችው የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያንም የአገሪቱን ህግ እና የፍትህ ስርዓት ተማምና ይህን ሁኔታ በሕግ አግባብ በመከላከል ከመቆየት ውጪ ሌላ መንገድም ሆነ አማራጭ ሳትከተል ቆይታለች።
ሆኖም ይህ ሕጋዊ ሒደት እልህን አስከትሎ ሃሰተኛ የሰው እና የሰነድ ምስክር በማደራጀት በቅዱሳን ጉልበት እና ንብረት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የተሰራን አዳራሽ ምንም አዲስ ግንባታ አልተደረገም የሚል ብያኔን በመስጠት ያለምንም ካሳ በግፍ ከቤተክርስቲያኗ እንዲነጠቅ ከማድረጋቸው ባሻገር 60 ሺህ ብር እንከፍልበት የነበረውን ቦታ 400% ጨምረው በወር 320 ሺህ ብር ሒሳብ እንድንከፍል እስከመወሰን አድርሷቸዋል

አሁንም እኛ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን ልጆች እና የወንጌል አማኞች

ፍትህ ሆይ ወዴት ነሽ?
የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 27 ሆይ ወዴት ነሽ? እያልን

እግዚአብሔርን ለሚፈሩ እና ፍትህን ለሚያከብሩ በመላው አገሪቱ ለሚገኙ ወገኖቻችን ነግ በእኔ ነውና ዘር ቀለም ሳንለይ የኃይማኖት ድንበር ሳይነጥለን ለእውነት እና ለፍትሕ ድምፅ እንድንሆን እንጠይቃለን!!!

ፍትህ እንፈልጋለን???

በዚህ ጉዳይ ከሰሞኑን በሚዲያና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በተመለከትነዉ ልክ እዉነታዉ ይህ ይሆናል ብለን ፈጽሞ አልጠበቅንም አልገመትንም ነበር። (ከስር የተለጠፉትን እያንዳንዱን ፎቶዎች ከፍ...
01/04/2026

በዚህ ጉዳይ ከሰሞኑን በሚዲያና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በተመለከትነዉ ልክ እዉነታዉ ይህ ይሆናል ብለን ፈጽሞ አልጠበቅንም አልገመትንም ነበር።

(ከስር የተለጠፉትን እያንዳንዱን ፎቶዎች ከፍተዉ ይመልከቱ! የቪዲዮ ሊንክም ከስር አስቀምጠናል!)

የክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተች ከጥቂት ጊዜ በኋላ ማስፋፊያ በማስፈለጉ በ2013 ከአከራዮች ጋር የሶስት ዓመት ኮንትራት ዉል በመግባት ተጨማሪ የአዳራሽና ሌሎች ግንባታዎችን ለማድረግ በስምምነት ኦና የነበረዉንና ከአገዳ በማይሻል ነገር የተሰሩ ቀድሞ የነበሩ የፈራረሱ ዝናብና ፀሐይ የሚያፈስባቸዉ ቤቶች እነሱን የሚፈርሰዉን በማፍረስ የሚታደሰዉን በማደስ ከ10 ሚሊየን በላይ በሆነ ወጭ አድሰዉ ሲያጠናቅቁ አከራዮች ነን ያሉት በመምጣት አመድ የመሰለ ጊቢዉ ዉሎ አድሮ ተዉቦና ደምቆ ሲመለከቱ ከ2 እጥፍ በላይ ጭማሪ አድርጉ ካልሆነ አንዳች ንብረታችሁን ሳትይዙ ለቃችሁ ዉጡ!” በማለት ፍ/ቤት ክስ መስርተዉ ላም እሳት ወለደች.. አይነት ነገር ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ወጪ አዉጥታ ያረገችዉን ግንባታ ለቀዉ እንዳይወጡ ከፍተኛ ገንዘብ፤ የምዕመኑ ጉልበትና ጊዜ የፈሰሰበት መሆኑ፤ እንዳይቀጥሉ ቀድሞ ከተደረገዉ ስምምነት ዉጪ ሁለት እጥፍ ጭማሪ ክፍያ በመጠየቅ ለሰሚም ለተመልካችም ጆሮን ጭዉ የሚያደርግ የክህደት ጥግ በማድረግ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንድትፈናቀል አድርገዋት ሳያበቁ በሚዲያ ላይ እኛም እናንተም ሲጮህ የነበረዉ ጩኸት ሌላ ሆኖ ከራረመ። በቲክቶክ ያሉ ጎሮምሶችንና የኃይማኖቱ ተከታይ ባልሆኑ ሰዎች ጭምር ክርስትናን በሚያስነቅፍ መልኩ የቤተ ክርስቲያኒቷን ባለራዕይ ዶክተሩን ጭምር ሲሰድቡ ሲያብጠለጥሉ ወንጀለኛ አርገዉ ሲፈርጁ ሲያጠለሹ በሁሉ እምነት ሲያሳጡት መሰንበትን ስራዬ ብለዉ ተያይዘዉ ሰነበቱ። በዚህም ሳይበቃ ቤቱን የኪራይ ጊዜዉ ሳይደርስ ከነግንባታዉ ወስደዉ፤ ለግንባታ ያወጣቸዉን ሚሊየን ብሮች እንኳ መክፈል ይቅር ጭራሽ በሀሰት የዓመታት እዳ አለበት ብለዉ እንዲፈጽም ተብሎ ሰማን። የእዉር ድንብር የሆነ ፍርድ!

በተራ የመንደር ቲከቶከርና ፌስቡከር እያስጮሁ በዚህ ልክ የዜጎችን የአልጋዮችን መብት መግፋት ምን ማለት ነዉ? ያዉም የቤተ እምነታችንን ወንጌል የሚሰራበትን!

አልፎ ተርፎ ካስረከብናችሁ ውጪ ባነርና ስቲከሮችን ከመለጣጠፍ ባለፈ ምንም ግንባታ አላከናወናችሁም የሚል የፍርድ ቤት ክስ በማምጣት ክርክሩን የመሬት ልቀቅ አልለቅም። ግብግብ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ የራሷን ንብረት ይዛ ልትወጣ የጠየቀችበት ጥያቄ ነበር። ሆኖም ጉዳዩ በሚዲያዎች ጩኸት ተጣመመ፤ እውነት ተደበቀ፤ ስም ለማጠልሸት የተሰሩ ትርኢቶች ተቀናበሩ ዋና መጋቢውም በቀጥታ ኢላማ ተደረጉ።

እዉነት ለመናገር በዚህ ልክ እኛም እናንተም ሌላዉም ዜጋ በጉዳዩ ላይ የዚህን ዓይነት እዉነት ይኖረዋል ብሎ የገመተ አይኖርም። እኛም አልነበረንም። ነገር ግን ጉዱ ሌላ የተነገረዉ ሌላ መሆኑ በጉዳዩ ላይ ምርመራችንን እንደናሰፋ አድርጎን እዉነታዉን ከዉጭም ከራሳቸዉ ከከሳሽ ወገን በኩል በተለያየ ሁኔታ በሚገባ ማረጋገጥ እንድንችል ሆነናል።

በአጠቃላይ በየክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ላይ ለአመታት በተለያዩ የሚዲያ አዉታሮች በግለሰቦች ሲነገር የነበረዉ ነገር እንዲህ ባለ መልኩ የተፈጸመ በእዉነት ያልተገባ የማጭበርበር ተግባር ጭምር ነዉ። እስቲ ለመረዳት ከታች ያሉትን አስረጂ ፎቶዎች ቀድሞ ገና ሲከራዩና ከክራይ በኋላ የነበረዉን የጊቢዉን ገጽታ የግንባታዎች ሁኔታ እያንዳንዱን ተመልከቱ!

ሊንኮቹንም ይመልከቱ👇
https://youtu.be/I0k74f96JVs?si=ERHHTGD2QTp8iIyE

https://youtu.be/1vPA79xyi8Q?si=t51lEP_bk_sgdpBd

በክፍል 2 እንመጣለን

Address

Hailegebresilase
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምስጋና ቲዩብ - Praise Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ምስጋና ቲዩብ - Praise Tube:

Shortcuts

Share