30/06/2012
ስለ አማላጅነት መማለድ ማለት ይቅርታ በስው ፈንታ መጠየቅ ማለት ነው ሁሉ ህይወት ያለው ሰው ፡ እግዚአብሄር የሚያውቅ በእግዚአብሀር ፊት በንስሃ መቅረብ የሚችል ሁሉ መጽለይ ይቅርታ መጠየቅ ይችላል እየሱስ ግን ስላልሞተ ወይም ሞትን ድል አድርጎ ስለተነሳ አሁንም መጠየቅ ይችላል። ሰውም አምላክም ስለሆነ በሰውነቱ ይማልዳል በአምላክነቱ ደግሞ ሃጥያትን ይቅር ይላል ሁላችንም ህያውን አንዳችን ለአንዳችን ልንጸልይ ልንማልድ ታዘናል ኢንማልድማለን ።
[*]ያዕ.5:16:...ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤
ከሞትን በሁዋላ ግን አንችልም
[*] መክ.9:5:- ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም።
በጌታችን ዘር ሃርግ ውስን የገቡ ሃጥያትን ያላደረጉ ማንም የለም:: ሃጥያትን የሰራ ደገሞ የስጋ ሞት ይምታል።ከሞትን በሁዋላ ግን አንችልም:: ጻድቅ ጌታችን መድሃኔታችን ክርስቶስ እየሱስ ብቻ ነው። ከጌታችን መድሃኔታችን ክርስቶስ እየሱስ የተነሳ እኛም ጻድቆች ነን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:24 በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
1. ስለ ዘላለማዊ ድንግልና ግን ዮሰፍ ኢንደሚያገባት መላኩ ቃል ገብቶለታል ዮስፍ ሚስትም ሳያገባ ወይም አልወሰዳትም ለማለት ግን አይቻልም
[*]ማቴ.1:20:...እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
በግብረ ስጋ ግንኙነት አሆን ያረገዘችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና አትፍራ ውሰዳት አለው ወሰዳት ቢያንስ 12 አመት አብረው ኖረዋል
2. የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ ---- ሲል ሁለት ትልልቅ ነገሮች እናገኛለን
2.1. የበኩር ልጅ
የበኩር ልጅ ማለት በራሱ ከሌሎች ልጆች የመጀመርያ ማለት ነው ስለዚህ ኢየሱስ አንድያ ልጇ ሳይሆን የበኩር ልጇ ነው
2.2. ድረስ
ድረስ የሚለው ቃል በሚገባ ስለሚቀጥለው ነገር እንድናስብ ይረዳናል ስለዚህ የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ሲል ከዛ በኋላ ምንእንደተፈጠረ ማሰብ የኛ ፋንታ ነው
2.3. ከዚህ በላይ ደግሞ ማርያም እህት አላት ብለህ አስበህ ታውቃለህ
የዮሐንስ ወንጌል 19 ፡25 ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር።
አየህ ኢየሱስ አክስት ነበረችው ማለት ነው ያብቻ ሳይሆን አያት እና ሌሎች ዘመዶች ነበሩት ስለዚህ ወንድም እና እህት ቢኖረው ክብሩን ማንነቱን አይቀይረውም ማሪያም ሌላ ለጆች ቢኖሯት ምን ያስገርማል
ቤተሰብ አልባ አይደለችም ኢየሱስም እንደዛው
ሌሎች ጥቅሶችን እስኪ ተመልከት
1. ማርያምና ወንድሞቹ
የሐዋርያት ሥራ 1 ፡13 በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፥ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም።እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።
2 እናቱና ወንድሞቹም
የማርቆስ ወንጌል3፥31 እናቱና ወንድሞቹም መጡ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት።
2. የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም
የማርቆስ ወንጌል 15፥40-41
ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የወጡ ሌሎች ብዙዎች ሴቶች ነበሩ።
3. እኅቶቹስ
የማቴዎስ ወንጌል 13:55
ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?
56
እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።
ማርያም ሰው ናት ቤተሰብ መስርታ መኖሯ አያረክሳትም ከቅድስናዋ አያጎድላትም ብጽህናዋን አታጣም
ማሪያም ሌላ ልጅ ኖራት አልኖራት በኛ መንፈሳዊ ህይወት የሚጨምርልን ወይም የሚቀንስብን ነገር የለም ፡፡ በበኩር ልጇ ከመንን እንድናለን እውነተኛው መንፈሳዊው አለም ውስጥ በቀላሉ እንቀላቀላለን ካልሆነ ግን የማሪያም ቲፎዞ ከመሆን የዘለለ ማንነት አየኖረንም ቆም ብለን ተሸዉደው ያሸወዱንን የዱሮ አባቶች ትምህርት ተረተረት አሉባልታ ታሪክ ብንመረምርና
ጥርት አድርገን የእግዚያብሄርን ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን ብናውቅ እኛም እናንተም አንድ እንሆናለን፡፡ለሃይማኖታችሁ ለምታሳዩት ትጋት ጌታይባርካችሁ እወዳቸሁዋለሁ!!!!!! ልጅ ወልዶ ለዘላለም ድንግልና የለም። በድንግልና ጸነስች እንጂ ከወለድች ቦሃላ ድንግል ሆና ቀረች የሚል ትምህርት የለም።
ተባረኩ