19/12/2025
የአእላፋት ዝማሬ በዚህ ዓመት በመስቀል አደባባይ እንደሚደረግ ተገልፆል::
በጌታችን በመድሐኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ገና ዋዜማ ለሶስተኛ ጊዜ የሚከበረው መንፈሳዊ ማዕድ ከዚህ በፊት ከሚደረግበት ቦሌ መድሐኒዓለም ቤተ-ክርስትያን ተቀይሮ በመስቀል አደባባይ እንደሚከበር የኢጃት ስራ አመራሮች እንዲሁም የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል፡፡
የአእላፋት ዝማሬ ከዚህ ቀደም ከሰማንያ ሺ እስከ ዘጠና ሺ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ሲሳተፉበት በአሁኑ በመቶ ሺዎቸ እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል፡፡
ታህሳስ 28 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ፣ በድሬደዋ ለገሐር አደባባይ ከ10:00 ሠዓት ጀምሮ መንፈሳዊ ፕሮግራሙ ይከናወናል::
"ከዚህ ታላቅ ማዕድ እንዳልሳተፍ የሚከለክለኝ ምንድነው"
አምላካችን እግዚአብሔር ሐገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ