አንጉላላ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

አንጉላላ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት ሰሚነሽ ኪዳነምህረት ገዳም የምትገኘው ከአዲስ አበባ 125km በአንጎለላ ቀበሌ ሲሆን ከ ደብረብርሃን ወደ ጅሩ በሚወስደው መንገድ 10km ርቀት ላይ ነው፡፡
(1)

አሳዛኝ ዜና እና ጥሪ ለፍትህ! ተወዳጁ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ በተለይም ገጠራማ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ግድያና ስጋት በተመ...
04/11/2025

አሳዛኝ ዜና እና ጥሪ ለፍትህ!

ተወዳጁ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ በተለይም ገጠራማ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ግድያና ስጋት በተመለከተ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፏል።

በመልእክቱም

"ይኼንን ጽሑፍ ቁጭ ብለህ እያነበብህ ያለኸው በዚህ ሰዓት ምሥራቅ አርሲ ገጠር ውስጥ ስላልተገኘህ ብቻ ነው:: በዚህች ቅጽበት በሥጋት ውስጥ ሆነው "ከአሁን አሁን ምን ይመጣብን ይሆን?" እያሉ ያሉ የኦሮሚያ ምእመናን ቁጥራቸው ብዙ ነው::"

ከቀናት በፊት የተገደሉትን እየተናገርን ሳለ አሁን ደግሞ ሌላ ቦታ አምስት ሰዎች እንደተገደሉ እየሰማን ነው ብሏል።

ከሰይፍ ልጅዋን ማስጣል ያልቻለች የአርሲዋን እናትስ እንዴት ዝም እንበላት? ይህንን የማያቆም ሞት ዜና ሰምተን ወደ ጉሮሮአችን የሚወርድ ምግብና መጠጥ የምንተኛውም እንቅልፍ የለም::

የእነርሱ ሞት የእኛ ሞት ነው:: የእነርሱ መቁሰል የእኛ ቁስል ነው::" በማለት የችግሩን አስከፊነት ገልጿል።

1. ምሕላ እንዲታወጅ፣
ለተሠዉት ተገቢው ክብር እና ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግላቸው ጠይቋል።

2. ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደራዊ መዋቅሯ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ በሙሉ ትኩረት እንድትሠራበት ጊዜው አሁን መሆኑን አሳስቧል።

3. ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ዓይነት ጊዜ የሚያሳየው ምላሽ ከሌለ... ቤተ ክርስቲያን አልባ ክርስቲያን በራሱ ላይ ይፈጥራል::" በማለት የኃላፊነት ስሜት እንዲሰማው አሳስቧል።

ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ይህን ጊዜ ለመካሰስ፣ አባቶችን ለመሳደብ፣ አንዱ ሌላውን ለማስጠቆርና ለመናቆር ሳይሆን፦

* ለጸሎት፣
* ለምሕላ፣
* ለሰብአዊ ሥራ፣ እና
* ችግሮችን የሚፈቱ ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ምክንያት እንዲያደርጉት ጥሪ አቅርቧል።

ጉዳዩን "በኦርቶዶክሳውያን ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣ ጥቃት" ብለው ያወገዙ የሌላ እምነት ተከታዮችን አክብሯል።

በክፉ ቀን ክፋታቸውን ላሳዩ ደግሞ "ለሰማያዊው ዳኛ ሠጥተናቸዋል::" ብሏል።





Via ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

29/10/2025

ምህረት አለው ደጅሽ
ኪዳነምህረት ቤትሽ
🙏🙏🙏

➥ ዕለተ ሰኑይ /ሰኞ/ 🔔ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ /የቤተ መቅደስ መንጻት/ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ /ማር.11-11፣ ማቴ.21-18-22 ሉቃ.13-6-9/፡፡ ወን...
29/04/2024

➥ ዕለተ ሰኑይ /ሰኞ/ 🔔
ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ /የቤተ መቅደስ መንጻት/ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ /ማር.11-11፣ ማቴ.21-18-22 ሉቃ.13-6-9/፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ «ወመሰለ ሎሙ ወይቤሎሙ አሐዱ ብእሲ በለሰ ቦቱ ውስተ አጸደ ወይኑ ወየሐውር ይንሣእ ፍሬሃ ወኢይረክብ ...»፤ ይህንም ምሳሌ አለ ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡ በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባርን ነው፡፡ ሁላችን ቤተ እስራኤላውያን ፍሬ ሃይማኖት ወምግባር አስተባብረን ይዘን መገኘት ይገባናል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኑይ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡

💠 አሸናፊ አለማየሁ

[በዓለ ሆሣዕና]✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)♥ ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ “ሆሻአና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕ...
27/04/2024

[በዓለ ሆሣዕና]
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)
♥ ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ “ሆሻአና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕና ከ9ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት ውስጥ ሲኾን ክንፋቸው ትእምርተ መስቀል የሚሠራው ኪሩቤል ሱራፌል በፍርሀት በረዐድ ኹነው ዘፋኑን የሚሸከሙት ጌታ በትሕትና ኾኖ ጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ባለባት በአህያና በውርንጫይቱ ተቀምጦ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት፣ የዘካርያስ ትንቢት የተፈጸመበት፣ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት፣ ሕፃናት በንጹሕ አንደበታቸው ሆሣዕና ብለው ያመሰገኑበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

♥ ይኽም ታሪክ በ4ቱ ወንጌላት ላይ ሲጻፍ በማቴ 21፡1 ላይ “ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ” ይላል፡፡

♥ ቤተ ፋጌ ማለት የበለስ ቤት ማለት ሲኾን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በሚወስደው መንገድ አቅራቢያ ያለች ትንሽ መንደር ናት፤ ኹሉን ዐዋቂ የኾነው ጌታም ጴጥሮስንና ዮሐንስን “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ” በማለት እንደ ማዕምረ ኅቡአትነቱ (የተሰወረውን ዐዋቂነቱ) በመንደሯ ውስጥ ስለታሰሩት አህያና ውርንጫ አስቀድሞ ይነግራቸዋል፡፡

♥ በተናቀች ግርግም በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ላምና አህያ ትንፋሻቸውን እንደገበሩለት፤ አኹንም በሰዎች በተናቀች አህያ በጌትነት ተቀምጦ እንዲመሰገንባት መርጧታል፡፡

❤ በልደቱ ማንም ያልገባባት የማይገባባት የሕዝቅኤል የታተመች መቅደስ የተባለች ዘላለማዊት ድንግል እመቤታችንን እንደመረጠ ዛሬም በሆሣዕና ማንም ሰው ያልተቀመጠበት ውርንጫ እንዲያመጡ አዘዘ።

♦ ከዚያም “ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል” በማለት የኹሉ ጌታ ርሱ መኾኑን አመለከታቸው፤ በተሰጣቸው ሥልጣነ ክህነት የሕዝቡንም የአሕዛቡን ኀጢአት የማሰር የመፍታት ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው ሐዋርያትን የሕዝብ ምሳሌ የኾነችውን አህያይቱንና የአሕዛብ ምሳሌ የኾነችው ውርንጫዋንም እንዲያመጡ አዟቸዋልና።

♥ ሊቁ ጀሮምም፡- “ደቀ መዛሙርቱ አህያይቱንና ውርንጫይቱን ለመፍታት ኹለት ኾነው መላካቸው ለሕዝብም ለአሕዛብም መላካቸው ያመለክታል፡፡” ይላል።

♥ ሊቁ አምብሮስ፡- “አህያየቱን ለመፍታት ማንም አይከለክላችኁም ብሎ መላኩ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሰማያዊ መኾኑን ያመለክታል፡፡” በማለት ልዩ ምስጢርን አስተላፎበታል።

♥ አምጥተው “ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ”፤ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ኮርቻ ሳይኾን ልብስ ማድረጋቸው ኮርቻ ይቈረቊራል ልብስ ግን አይቈረቊርምና የማትቈረቊር ሕግ ሠራኽልን ሲሉ። ዳግመኛም ልብስ በአካል ያለውን ኀፍረት እንዲሰውር አንተም በደላችንን የምትሰውርልን ይቅር ባይ ነኽ ሲሉ በማለት መተርጉማን ይተነትናሉ፡፡ በተጨማሪም ልብስ በልጅነት ይመሰላልና የተገፈፍነውን የጸጋ ልብሳችን (ልጅነትን) ትመልስልናለህ ሲሉ ነው፨

♥ ቅዱስ ኤፍሬም ይኽነን ሲተረጉም "ልብሳቸውን አውልቀው ያነጠፉለት ሰዎች አሮጌውን ማንነታቸውን ትተው ዐዲሱን ልብስ ክርስቶስን መልበሳቸውን ያስረዳል። ሐዋርያ ጳውሎስ “አሮጌውን ሰውነት አስወግዳችሁ አዲሱን ሰው ልበሱት” እንዳለው (ኤፌ.4፣23) ይኸውም ጥምቀት ነው" ይላል።

♥ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲኾን መተርጒማነ ሐዲስ በትርጓሜ ወንጌል ላይ እንደሚገልጹት 14ቱን ጌታ በእግሩ ሲኼድ 2ቱን በአህያዋ፤ በውርንጫዋ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሷን ዞሯ

“ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” ማቴ. 21:9ታሪክ!የእስራኤል መንግስት የእግዚአብሔር መንግስት ነበረች ፤ የሰው ሁሉ ገዥ እግዚአብሔር ስለሆነ ፥ ከአዳም እስከ ሳሙኤል ሕዝቡን የሚመራ የሚያዝ በተስፋ...
27/04/2024

“ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” ማቴ. 21:9

ታሪክ!
የእስራኤል መንግስት የእግዚአብሔር መንግስት ነበረች ፤ የሰው ሁሉ ገዥ እግዚአብሔር ስለሆነ ፥ ከአዳም እስከ ሳሙኤል ሕዝቡን የሚመራ የሚያዝ በተስፋው የዘር ሐረግ ውስጥ ባለቤቱ እግዚአብሔር በመሆኑ ንጉሥ አልነበረም። በሳሙኤል ጊዜ ግን ሕዝበ እስራኤል እንደ አሕዛብ ንጉሥ ፈለጉና ንጉሥ አንግስልን ብለው ሳሙኤልን ጠየቁት ፣ ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት አንተን ሳይሆን እኔን ነውና የናቁት አንግስላቸው አለው። ሳሙኤልም ንጉሣችን እግዚአብሔር ስለሆነ ይቅርባችሁ ቢላቸው እምቢ ስላሉት አህያ ጠባቂውን ሳኦልን ሾመላቸው። እግዚአብሔር እንዲገዛው ያልወደደ ሕዝብ የአህያ እረኛ ይገዛዋል።

የሳኦልም መንግስት ተሻረና እግዚአብሔር ሳኦል እያለ እንደ ፈቃዱ ሕዝቡን የሚመራበትን የእሱ መንግስት የምትገለጥበትን ዳዊትን እንዲቀባ አደረገ ፤ የዳዊት መንግስት የእግዚአብሔር መንግስት ነበረች ፣ ለዳዊትም ከአብራክህ የሚከፈለው ልጅህ በዙፋንህ ላይ ይቀመጣል ብሎ ለጊዜው ሰሎሞን ሲሆን ፍጻሜው ግን ጌታ ከእርሱ እንደሚወለድ ቃል ገብቶለት ነበር። መበሥር መልዓክ ቅዱስ ገብርኤልም ይህንኑ ተናግሯል። ሉቃ. 1:33

ስለዚህ በስውር ይተላለፍ የነበረው የእግዚአብሔር መንግስት በእግዚአብሔር ልጅ መወለድ ስለተገለጠች ፥ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በማለት ዘመሩ። በዚህ ሁኔታ ወደ ኢየሩሳሌም መሲሕ ሲገባ መላው ከተማ “ይህ ማን ነው?” ብሎ ተናወጠ ፤ ሕዝቡም “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣው ነቢዩ ኢየሱስ ነው” አሉ። ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የንግድ ማዕከል የነበረውን ቤተ መቅደስ ከንግድ እና በንግድ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች አጸዳ።
“ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና በአርያም” ማቴ. 21:9

አምላከ ቅዱሳን መዋዕለ ጾሙን በሽልም አስፈጽሞ ለብርሃነ ትንሣኤው ያድርሰን።
እንኳን አደረሰን!

➥ደብረ ዘይት ..◆ ስያሜው የተወሰደውም ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፫-24፥3 ካለው ትምህርት ነው። ደብረ ዘይት ከእየሩሳሌም በስተምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ በወይራ ዛፎች የተሸፈነ ትልቅ ተ...
07/04/2024

➥ደብረ ዘይት ..
◆ ስያሜው የተወሰደውም ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፫-24፥3 ካለው ትምህርት ነው። ደብረ ዘይት ከእየሩሳሌም በስተምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ በወይራ ዛፎች የተሸፈነ ትልቅ ተራራ ነው። ጌታችን አምላካችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢራትን በተለያየ ቦታ ገልጧል።
ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴሴማኒ፣
ምሥጢረ መንግሥቱን በደብረ ታቦር፣
ምሥጢረ ቁርባንን በቤተ አልዓዛር፣
ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታንን በቤተ ኤያኢሮስ፣
ምሥጢረ ምጽአቱን ደግሞ በደብረ ዘይት ገልጧል።

🥰እሁድ ²⁹'2016✍

➠የክብር ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር
⪨ ዕለተ ሰንበትን
⪨ ዕለተ ደብረ ዘይትን
⪨ ዕለተ ቀኑን ባርኮ ያውለን፣ ያሳድረን ያሰንብተን።
ለዘለዓለሙ አሜን

💠 አሸናፊ አለማየሁ

ሁሉን የያዘውን ያዙት ሁሉን የሚገዛውን አሰሩት የህያው አምላክን ልጅ አሰሩት በቁጣ ጎተቱት በፍቅር ተከተላቸው በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኀላቸው እየተከተለ ወሰዱት፡፡ ...
05/04/2024

ሁሉን የያዘውን ያዙት ሁሉን የሚገዛውን አሰሩት የህያው አምላክን ልጅ አሰሩት በቁጣ ጎተቱት በፍቅር ተከተላቸው በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኀላቸው እየተከተለ ወሰዱት፡፡ ሊቃነ መላእክት በመንቀጥቀጥ በፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት ኀጥያተን ይቅር የሚለውን ኀጥያተኛ አሉት በፈራጆች ላይ በሚፈርደው በእርሱ ላይ ፈረዱበት፡፡ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾህ ዘውድ አቀዳጁት፡ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ቀይ ግምጃ አለበሱት፡፡ የመላእክት ሰራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡ ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትነናነው? ይህን ያህል ትዕግስት እንደምን ያለ ትዕግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነወ? የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳቀው እስከ ሞትም አደረሰወ፡፡

 መምህሩ ተማሪዎችን ሊፈትን በአንድ ሰዓት ውስጥ የሚመለሱ ሁለት ጥያቄዎችን አዘጋጀ። ተማሪዎች ራሳቸውን አዘጋጅተው ወደ ፈተና ክፍል ገበተው ወንበር ወንበራቸውን ይዘው ይጠብቃሉ። መምህሩ የፈ...
03/04/2024



መምህሩ ተማሪዎችን ሊፈትን በአንድ ሰዓት ውስጥ የሚመለሱ ሁለት ጥያቄዎችን አዘጋጀ። ተማሪዎች ራሳቸውን አዘጋጅተው ወደ ፈተና ክፍል ገበተው ወንበር ወንበራቸውን ይዘው ይጠብቃሉ። መምህሩ የፈተና ወረቀቱን ይዞ ገባ። የፈተናውን መመሪያ ተናግሮ የፈተና ወረቀቱን አደለና ሰዓት ይዞ "መጀመር ትችላላችሁ" አላቸው።

የመጀመሪያው ጥያቄ ስለ እግዚአብሔር የምታውቀውን ጻፍ የሚል ነው። ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ ስለ ሰይጣን የምታውቀውን ጻፍ ይላል፡፡ "ለአንዱ ጥያቄ 30 ደቂቃ ነው የተሰጠው ማለት ነው" ብለው ሰዓት ሳያልቅባቸው ሁለቱንም ጥያቄዎች ለመጨረስ ተሎ ተሎ ይጽፋሉ። ፈተና ከተጀመረ 30 ደቂቃ መሙላቱ ሰዓት ያዩ ተማሪዎች ከአንደኛው ጥያቄ ወደ ሁለተኛው አልፈው መስራት ጀምረዋል፡፡ በአእምሮአቸው የመጣላቸውን ሐሳብ በቻሉት ፍጥነት ይጽፋሉ፡፡ መምህሩም ሁሉም ተማሪ የየራሱ መስራቱን እየዞረ ይከታተላል።

"ለማጠናቀቅ አስር ደቂቃ ይቀራችኋል" አለ መምህሩ። መልሰን ጨርሰናል ብለው ያሰቡ ተማሪዎች ግማሾቹ ፈተና ወረቀቱን ለመምህሩ ሰጥተው ሲወጡ፥ ሌሎቹም የመለሱትን ደግመው ያነባሉ፡፡ ያልጨረሱም የቀረችውን ደቂቃ ለመጠቀም ይጣደፋሉ። ከአስር ደቂቃ በኋላ "ሰዓት አልቋል ሁላችሁም መስራት አቁሙ" አለ መምህሩ፡፡ እየዞረም ፈተና ወረቀቱን መሰብሰብ ጀመረ፡፡ አንድ ተማሪ ጋር ሲደርስ ግን አሁንም መልስ እየጻፈ ያገኘውና "ሰዓት አልቋል ሲባል አትሰማም እንዴ?" ብሎ ወረቁትን ተቀበለው፡፡

ሁሉም ተማሪዎች ለሁለቱም ጥያቄ የሚያውቁትን የመለሱ ሲሆን አንዱ ተማሪ ግን ለጥያቄ ቍጥር አንድ (ስለ እግዚአብሔር የምታውቁትን ጻፉ ለሚለው) ብቻ ነው መልስ የሰጠው። መምህሩ በዚህ ተማሪ መልስ ተገርሞ "ለምንድ ነው ለሁለቱንም ጥያቄዎች መልስ ያልጻፍከው?" ብሎ ጠየቀው። እርሱም " " ስለ እግዚአብሔር ራሱ የማያልቅ ቢሆን እኮ ነው የተሰጠን ሰዓት አልቆ ገና እየጻፍኩ ያስቆምከኝ" አለው ይባላል፡፡

እውነት ነው ነገረ እግዚአብሔር ቢጽፉት፣ ቢናገሩት፣ ቢሰሙትና ቢያዜሙት የማያልቅና የማይሰለች ጥልቅ ምሥጢር ነው። የፈለግነው ያህል ጊዜ ብንሰጠው እንኳን በጅምር እያለን ጊዜው ያልቃል። በቃሉ ፍቅር፥ በምሥጢሩ ተመስጦ ውስጥ ሆነን ወደማያልፈው ዓለም እንሻገራለን፡፡

ይህንን ገንዘብ ለማድረግ ግን ለሰይጣንና ለጉዳዮቹ የሚሆን ጊዜ የለኝም ማለት ይገባል፡፡ ከጊዜ ውጭ የሚሰራ ነገር የለምና ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን ከኃጢአት ሁሉ መራቃችን አይደል? ለሰይጣን ጊዜ ላለመስጠት ደግሞ ከእርሱ ጋር መጣላት ነው። መቼም ሰው ለጠላው ነገር የሚሆን ጊዜ አይኖረውም። ምንም ስራ ባይኖረውም እንኳ ከጠላው ጋር ላለመገናኘት ምክንያት ፈጥሮ ይርቅ የለ? ስለዚህ ለሰይጣን ጊዜ እንዳይኖርህ ከእርሱ ጋር ተጣላ። የሚገርመው ከሰይጣን ጋር ስትጣላ ደግሞ ከሰው እና ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር መኖር ትችላለህ፡፡ ከ24ቱ ሰዓት ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን መቼም ቢሆን ኃጢአት ሊያሰራን የሚችልበት ዕድል ወይም አጋጣሚ አይኖርም። የተሰጠን ጊዜ ለሰጪው አምላክ መልሰን እንሰጠው ዘንድ ማስተዋሉን ያድለን።

03/04/2024

ምስክር

ሰላም ለእናተ ይሁን የእግዚአብሄር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ 🙏 ስሜ አፀደ ማርያም እባላለሁ እናቴ እመቤቴ አማላጄ የሰሚነሽ ኪዳነምህረት ያደረገችልኝን ድንቅ ተአምር እናገራለሁ ከዛሬ 16 አመት በፊት ጀምሮ ከማህፀኔ በጣም መጥፎ ሽታ( ጠረን) ያለው ፈሳሽ ይወጣ ነበር እሰው አጠገብ ስቀመጥ ሽታዬ ይረብሻቸው ነበር እኔ ላይ ሰው ደገፍ ብሎ መቀመጥም ሆነ መተኛት አይታሰብም እኔም ከሰው ሸሽቼ ነበር የምኖረው ሀኪም ቤት ስሄድ የሚሰጡኝ መድሀኒት ለሦስት ወር ብቻ ነው የሚያስታግሰው ከዛ ተመልሶ ይመጣል ብዙ ጊዜ አረብ ሀገር ነው ያሳለፍኩት ብዙ ፈተና አይቻለሁ ከሰውጋ መተኛት አልችልም ልጆቹም እፍፍፍ ትሸቻለሽ ይሉኛል ግን ምን ላድርግ በቀን 30 ጊዜ እታጠባለሁ ግን ሽታው እኔንም ይረብሸኛል እራሴን እጠላዋለሁ ከሰው ራቅ ብዬ እቀመጣለሁ ሰው በአጠገቤ ሲያልፍ እሳቀቃለሁ ሁሌ በራሴ አዝናለሁ አገሬ ስገባ እህቴ ታማ ነበር የሰሚነሽን ፀበል አምጭላት አሉኝ ሰዎች ቦታውን ጠቆሙኝ እኔም የማር ፀበሉ በሚሰጥበት ቀን ሄጄ የማር ፀበሌን ጠጥቼ ለእህቴ የማር እምነት ይዥ ተመለስሁ ይኸው ከዛወዲህ ማለትም ከ16 የስቃይ አመት በኋላ ምንም ጠረን የተባለ የለብኝም እናቴ ኪዳነምህረት ነቅላ ጣለችልኝ እኔ ፈልጌ ሳይሆን እናቴ ፈልጋ በቃሽ ብላ አዳነችኝ ለኔ የደረሰች ኪዳነምህረት ለእናተም ትድረስላችሁ እልልልልል ብላችሁ አመስግኑልኝ🙏🙏🙏

➥ ነፍስ በዝምታ ወደ ጤና ትመለሳለች።  ስለዚህ እራስን ዝምታን ማሰልጠን አስፈላጊ ነው - እና ይህ ወደ ልብ ጣፋጭነት የሚያመጣ የጉልበት ሥራ ነው.  ሰው ከማይፈለጉ ሀሳቦች ሰላም የሚደርሰ...
03/04/2024

➥ ነፍስ በዝምታ ወደ ጤና ትመለሳለች። ስለዚህ እራስን ዝምታን ማሰልጠን አስፈላጊ ነው - እና ይህ ወደ ልብ ጣፋጭነት የሚያመጣ የጉልበት ሥራ ነው. ሰው ከማይፈለጉ ሀሳቦች ሰላም የሚደርሰው በዝምታ ነው።

◆ ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251923668841

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አንጉላላ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to አንጉላላ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት:

Share