Excellence Life Faith Church

Excellence Life Faith Church Excellence Life Faith Church

The vision of ELFC is to proclaim to all people the redemptive work accomplished by Jesus Christ, making known His love, sacrifice, and saving grace to every nation and generation.

ሀሙስ ነሀሴ.21 ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ በEXCELLENCE LIFE FAITH CHURCH /THE HOUSE OF FAITH/ አጥቢያ የኤፌሶን መፅሐፍ ተከታታይ የትምህርት ሴሚናር ስለሚቀጥል እን...
26/08/2026

ሀሙስ ነሀሴ.21 ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ በEXCELLENCE LIFE FAITH CHURCH /THE HOUSE OF FAITH/ አጥቢያ የኤፌሶን መፅሐፍ ተከታታይ የትምህርት ሴሚናር ስለሚቀጥል እንዲሁም የአምልኮ ጊዜ ስለሚኖረን እርስዎም በዕለቱ በቤተክርስቲያናችን በመገኘት አብራችሁን እንድታመልኩና እንድትማሩ በክብር ተጋብዛችዃል

:-መፅሀፍ ቅዱስ እና አጀንዳዎትን መያዝ አይዘንጉ!!

አድራሻ :- ጀሞ ሚካኤል መብራቱን ተሻግረው ወደ ጀሞ በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር እንደተጓዙ ብርሀን ባንክ ያለበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ

ቃሎቻችን ህያው ናቸውየእግዚአብሔር ቃል ስድስተኛ ሳምንት   ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5 ¹⁴ ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣ “አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ...
24/08/2026

ቃሎቻችን ህያው ናቸው
የእግዚአብሔር ቃል ስድስተኛ ሳምንት

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5
¹⁴ ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣ “አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሏል።
¹⁵ እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ።
¹⁶ ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ።
¹⁷ ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ።

እግዚአብሔር አባታችን በሰጠን ዘመንና ወቅት ላይ መንቃታችን ህይወታችንን የማሳመርና የማከናወን ሀይል አለው።
አለበለዚያ ግን በመፅሐፍ ቅዱሳችን እንደተፃፉልን ተኝታ ልጇን እንደገደለቺውና ተኝታ ልጇን እንዳስሰረቀችው ሴቶች መሆናችን የማይቀር ነው።

ቀኖቹ በራሳቸው ክፉዎች ስለሆኑ ለእኛ ለመልካም እንዲሰሩ የምንዋጃቸው እኛው እራሳችን ነን።

መዋጀት ማለት አስቀድሞ የእኛ የነበረ ነገር ግን በተለያየ መንገድ ከእኛ የተለየን ነገር መልሶ መግዛት ማለት ነው።
ይቺን የምንኖርባትን ክፉ እኛ ካልዋጀናት በስተቀር አለም ከክፋቷ ተለውጣ አታውቅም ክፋትም ቀንሶ አያውቅም ።

እንዴት ነው የምንዋጀው?

1 በምንናገረው ቃል /በአንደበታችን/

የተስፋን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለሆነ፣ አምነን የምንናገርለትን ተስፋ አጥብቀን እንያዝ።
ወደ ዕብራውያን 10:23

ለእኛ ለአማኞች መናገር ማለት የእግዚአብሔርን ቃል መልሰን መደጋገምና መናገር ማለት ነው።

ህይወታችን የሚወሰነው በንግግራችን ልክ ስለሆነ የምንናገረው እያንዳንዱ ነገር በህይወታችን ላይ መገለጡ የማይቀር ነው።

አንደበቱን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤ አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ግን ይጠፋል።
መጽሐፈ ምሳሌ 13:3

የምናስበውን ነገር የማያውቀው የተናገርነው ቃል ግን እንደሚሰራ የሚያውቀው ጠላታችንም የአንደበታችንን ቃል ማስቀየር የሚፈልገው ለዚህ ነው።

ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ የሆኑና በስሜታዊነት የምንናገራቸው ነገሮች ሁሉ ህይወታችንን የማበላሸትና እንደተናገርነው የማድረግ አቅም አላቸው በተመሳሳይ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆኑ መልካም ንግግሮች ሁሉ መገለጣቸው አይቀርም።

ምክንያቱም የምንናገረው ነገር ልክ እንደ ዘር ነው። የትኛውም ገበሬ በቆሎ ዘርቶ ስንዴ ለማጨድ እንደማይጠብቀው ከተናገርነው ውጪ መሆን አንችልም።

ስለዚህ፣ “ሕይወትን የሚወድድ፣ መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል። — 1ኛ የጴጥሮስ መልዕክት 3:10 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ይህቺ ምድር በቃል የምትተዳደር ስለሆነች መልካም የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል መናገር መልካሙን ህይወት እንድንኖር ያደርገናል

በመጨረሻም አንተ ወይም አንቺ ከየትኛው ወገን ነህ/ነሽ?
ባለማስተዋል የሞትን ንግግር ተናግሮ 21 ዓመት ሙሉ የተገዛላትን ራሄልን እንዳጣው እንደ ያዕቆብ

ወይስ ስለሞቱ ብቻ ሳይሆን ስለመነሳቱም በየጊዜው ሲናገር እንደነበረውና ልክ እንደተናገረውም እንደሆነለት እንደ ኢየሱስ

አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወድዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።
መጽሐፈ ምሳሌ 18:21


ፓስተር ካሴ ከበደ
እሁድ.ነሀሴ.17.2018
የመለኮታዊ ሞገስ አመታችን ነው

22/08/2026
እሁድ ነሀሴ.17 ከ 03:00 ሰዓት ጀምሮ በEXCELLENCE LIFE FAITH CHURCH /THE HOUSE OF FAITH/ አጥቢያ የእግዚአብሔር ቃል በሚል ርዕስ የተጀመረው ተከታታይ የትምህ...
22/08/2026

እሁድ ነሀሴ.17 ከ 03:00 ሰዓት ጀምሮ በEXCELLENCE LIFE FAITH CHURCH /THE HOUSE OF FAITH/ አጥቢያ የእግዚአብሔር ቃል በሚል ርዕስ የተጀመረው ተከታታይ የትምህርት ሴሚናር ስድስተኛ ቀን እንዲሁም የአምልኮ ጊዜ ስለሚኖረን እርስዎም በዕለቱ በቤተክርስቲያናችን በመገኘት አብራችሁን እንድታመልኩና እንድትማሩ በክብር ተጋብዛችዃል

:-መፅሀፍ ቅዱስ እና አጀንዳዎትን መያዝ አይዘንጉ!!

አድራሻ :- ጀሞ ሚካኤል መብራቱን ተሻግረው ወደ ጀሞ በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር እንደተጓዙ ብርሀን ባንክ ያለበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ

Address

Ayertena, China Camp 50m Away From The Bridge On The First Building
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Excellence Life Faith Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share