Ye Ethiopia ye Hiwotkal Church channel

Ye Ethiopia ye Hiwotkal Church channel Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ye Ethiopia ye Hiwotkal Church channel, Church, Nifas Silk lafto kifleketema Woreda 01, Addis Ababa.

አቶ ኡፋይሳ ኡቃ  አዲስ ለሚትተከል ለቢሸፍቱ/ደብረዘይት / ከተማ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን 50 የኘላስቲክ ወንበሮችን ገዝተህ ገቢ ስላደረግህ አንተንና ቤተሰብህን እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ...
16/09/2026

አቶ ኡፋይሳ ኡቃ አዲስ ለሚትተከል ለቢሸፍቱ/ደብረዘይት / ከተማ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን 50 የኘላስቲክ ወንበሮችን ገዝተህ ገቢ ስላደረግህ አንተንና ቤተሰብህን እግዚአብሔር በመንፈሳዊ እና በምድራዊ በረከት ሁሉ ይባርካችሁ ! ሌሎችም እስቲ ለሚሽን ሳይት እጃችሁን ዘርጉ እግዚአብሔር ይባርካችኋል !

>  https://t.me/+zskl9tHAstQ3MjI0በጅግጅጋ ከተማ በሥራ, በንግድ, በትምህርት እና በትዳር ምክንያት ነዋሪ የሆናችሁ የቤተክርስቲያናችን አባላት የኢትዮጵያ የሕይወት ቃል ቤተ...
15/09/2026

> https://t.me/+zskl9tHAstQ3MjI0
በጅግጅጋ ከተማ በሥራ, በንግድ, በትምህርት እና በትዳር ምክንያት ነዋሪ የሆናችሁ የቤተክርስቲያናችን አባላት የኢትዮጵያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን እዛው እተተከለች ስለሆነ ከላይ ያለውን የቴሌግራም ሊንክ እየተጫናችሁ የራሳችሁን እና የሌሎችንም ስልክ አድ እንዳታደርጉ እናሳስባለን ። ተባረኩ!

መስከረም 3/2019 ቦዲቲ ከተማ የሕይወት ቃል እናት አጥቢያ ቤተክርስቲያን በዋናው ጽ/ቤት ታዝዘው የቢሾፍቱ/ደብረዘይት /ከተማ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያንን ከዋና ጽ/ቤት እጅ ተረክበው ሙሉ...
14/09/2026

መስከረም 3/2019 ቦዲቲ ከተማ የሕይወት ቃል እናት አጥቢያ ቤተክርስቲያን በዋናው ጽ/ቤት ታዝዘው የቢሾፍቱ/ደብረዘይት /ከተማ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያንን ከዋና ጽ/ቤት እጅ ተረክበው ሙሉ የሚሽኔሪው ደመወዝ እና የማምለኪያ አዳራሽ ኪራይ እንዲሁም ቤተክርስቲያኒቱን ለመረከብ የሄዱ መሪዎች በዕለቱም በተደረገው ገንዘብ ማሰባሰብ; አቶ ኡፋይሳ ኡቃ 50 ወንበር ለመግዛት , አቶ በለጠ በርገኔ 20,000 መጋቢ ኡፋይሳ ሶርሳ 5,000 እንዲሁም መጋቢ አስፋው ጡሜቦ ከኪሳቸው ለወንጌል በመስጠት እና እስከነሰነዶች ሙሉ አደረጃጀት አጠናቀው እና ተረክበው ተመልሰዋል ። እንደ አባት ታዛችሁ የወንጌልን ሥራ ለመሥራት የወሰናችሁ የቦዲቲ እናት አጥቢያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን አባላት እና መሪዎች እግዚአብሔር በወንጌል በረከት ይባርካችሁ ! እግዚአብሔር በመንፈሳዊ እና በምድራዊ ፍሬያማነት ያክብዳችሁ!
በጠቅላላ ጉባኤ እንደተወሰነ እና የቤተክርስቲያናችን ዋና ዓላማ በሆነው የወንጌል ሥራ ከዋናው ጽ/ቤት ደብዳቤ እስክደርስ ሌሎች አጥቢያዎችም ለሁለት ወር በያላችሁበት ለቤተክርስቲያን ተከላ እና ሚሽኔሪ ለመላክ እየተዘጋጃችሁ እንዲትቆዩ እናሳስባለን።

10/09/2026

እንኳን ለ2019 አዲሱ ዓ.ም በሠላም አደረሰን ! 2019 ወንጌል ላልሰሙ ወንጌልን የምናደርስበት, የሰሙ አምነው የምድኑበት , የወንጌል ባለአደራዎች የሚነሡበት እና ኃይላችን የሚታደስበት ዓመት ይሁንል!

10/09/2026

እንኳን ለ2019 ዋዜማ በሠላም አደረሳችሁ ! በዚህ የመጨረሻው የጸሎት ቀን በክርስቶስ አምኖ ያልዳኑ እንዲድኑ , ቤተክርስቲያን እንዲተከል, ተተኪ የወንጌል ባለአደራዎች ከጌታ እንሰጡን ጸልዩ !

የኢትዮጵያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን የ2018 ዓ.ም መደበኛ 2ኛ ጠቅላላ ጉባዔ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመሐል እናት አጥቢያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን ነሐሴ 29-30/2018 ዓ.ም በጌታ ...
07/09/2026

የኢትዮጵያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን የ2018 ዓ.ም መደበኛ 2ኛ ጠቅላላ ጉባዔ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመሐል እናት አጥቢያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን ነሐሴ 29-30/2018 ዓ.ም በጌታ አብሮነት ጀምራ በድል አጠናቃለች እግዚአብሔር ይመስገን ።
በዕለቱ ለጠቅላላ ጉባዔ ለውይይት የቀረቡ አጀንዳዎች :-
1ኛ , የ2018 የሥራ ክንውን እና የውጭ ኦዲት ማድመጥ እና ማጽደቅ
2ኛ, የ2019 የሥራ እና የበጀት ዕቅድ ማድመጥ እና ማጽደቅ
3ኛ, ለአገራችን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር በቂ ዝናብ እንዲሰጥ በጌታ ፊት ለ3 ቀናት ሁሉ አባላት በንስሃ እና በጸሎት የጌታን ፊት እንዲፈልጉ ማድረግ በሚሉ አጀንዳዎች ጉባኤው መክሮበት ሁሉን በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ጉባኤው በሠላም ተጠናቋል ጌታ ይመስገን ። ጥሪያችንን አክብራችሁ የመጣችሁ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት እና የጠቅላላ ጉባኤ የክብር አባላት እንዲሁም የጠቅላላ ጉባዔ ሰብሳቢዎች በሙሉ የወንጌል በርከት ያግኛችሁ። በመጨረሻም በአጭር ጊዜ ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤን እኛ እናስተናግደዋለን ብላችሁ በፍጹም ፍቅር የተቀበላችሁ የሶዶ መሐል እናት አጥቢያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን መሪዎች እና አባላት እግዚአብሔር በወንጌል በረከት ይባርካችሁ ! ከሁሉም በላይ ለቤተክርስቲያናችን ለአገራችን ሠላምን ለጉባዔውም ጥበቃና የሰላም የሰጠን ጀምሮ ላስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር ክብር ይሁንለት!

በአዲስ አበባ ጀሞ 1 አጥቢያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን ከነሐሴ 22-24/2018 የተካሄደው የወጣቶች ኮንፈረንስ የወንጌል እሳት እንድጨምርብን ምክንያት ሆኗል ጌታ ይባረክ! በሁሉ ስኬትን ...
01/09/2026

በአዲስ አበባ ጀሞ 1 አጥቢያ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን ከነሐሴ 22-24/2018 የተካሄደው የወጣቶች ኮንፈረንስ የወንጌል እሳት እንድጨምርብን ምክንያት ሆኗል ጌታ ይባረክ! በሁሉ ስኬትን የሰጠን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባረክ! በመቀጠል ይህንን ድንቅ ኘሮግራም ያዘጋጁ የወጣት አገልግሎት አስተባባሪዎች ተባረኩ ይቀጥልበት! የወጣት አገልግሎት እንደዚህ አይነት ኘሮግራም እንዲሠሩ ምቹ ሁኔታዎችን ያመቻቻችሁ የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ተባረኩ! በመጨረሻም ለሰማችሁት ወንጌል ለሰዎች መዳን ልባችሁ ተነክቶ ለወንጌል እጃችሁን የዘረጋችሁ እና የአንድ ሚሽኔሪ የአንድ ወር የቤት ኪራይ የከፈላችሁ እና ሚሽኔሪውንና ቤተሰቡን የዕለቱን ምሣ የጋበዛችሁ አባላት በሙሉ የወንጌል በረከት ያግኛችሁ !

29/08/2026

ነጌ እሁድ ጠዋት እና ከሰዓት ከሻክሾ ሾኔ የሕይወት ቃል ቤተክርስቲያን ኮንፈረንስ ቀጥታ ስርጭት በቲክታክ ይኖረናል ከታተሉ ። የቲክታክ ሊንክ እዚሁ ታገኛላችሁ ። የዳዊትን ድንኳን ኢየሱሰ ያነሣታል

27/08/2026
የወንጌል ባለአደራ የሆኑ ወ/ዊ ተዘራ ሎምባ ዛሬ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም ወዳገለገሉት አምላካቸው ሄደዋል።  የወንጌል ባለ አደራ ተዘራ ሎምባ  በምዕራብ ኢትዮጵያ  ክልል ቦንጋ ከተማ , በም...
22/08/2026

የወንጌል ባለአደራ የሆኑ ወ/ዊ ተዘራ ሎምባ ዛሬ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም ወዳገለገሉት አምላካቸው ሄደዋል።
የወንጌል ባለ አደራ ተዘራ ሎምባ በምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቦንጋ ከተማ , በምዕራብ አርሲ ዞን በሥራሮ ወረዳ በዓለም ጤና አጥቢያ እንድሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ካራት ከተማ አሁን ለተተከለች ቤተክርስቲያን ቦታ ያመቻቸልን የወንጌል ባለአደራ ነበሩ።እግዚአብሔር ለቤተሰባቸው መጽናናትን እንዲሰጣቸው እንጸልያለን!

Address

Nifas Silk Lafto Kifleketema Woreda 01
Addis Ababa

Telephone

+251911947868

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ye Ethiopia ye Hiwotkal Church channel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ye Ethiopia ye Hiwotkal Church channel:

Shortcuts

Share

Category