መርሐቤቴ ደብረ ገነት ጉናጉና ቅድሥት ማርያም ቤተክ/Merhabetie D.G.Gunaguna saint Mary church

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • መርሐቤቴ ደብረ ገነት ጉናጉና ቅድሥት ማርያም ቤተክ/Merhabetie D.G.Gunaguna saint Mary church

መርሐቤቴ ደብረ ገነት ጉናጉና ቅድሥት ማርያም ቤተክ/Merhabetie D.G.Gunaguna saint Mary church አምሳለ ኢየሩሣሌም ደ/ገ/ ጉናጉና ቅድሥት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን

"ዓመታትን በቸርነትህ ታቀዳጃለህ መዝ ፷፬÷፲፩" "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሥ።                አሀዱ አምላክ አሜን!!!"❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ "እንኳን ...
10/09/2025

"ዓመታትን በቸርነትህ ታቀዳጃለህ መዝ ፷፬÷፲፩"
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሥ።
አሀዱ አምላክ አሜን!!!"
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
"እንኳን ለ፪ሺ፲፰ ዓ.ም ዘመነ ቅዱስ ማቆስ በሰላም አደረሳችሁ።"
🌻~ ዓመታት በቸርነትህ ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። መዝ ፷፬፥፲፩
🌻~ ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የመሸጋገሪያው ዕለት በየዓመቱ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ የዘመን መለወጫ፣ እንቁጣጣሽ፣ ሌላም መጠሪያ ስሞቹ ናቸው፡፡ በግእዝ ርእሰ ዐውደ ዓመትም ይባላል፡፡
~☆☆☆~
🌻~ እግዚአብሔር በልግስናው በስጦታው ምድርን በልምላሜ ወንዝንም በውሃ ተራሮችንም በፅጌያት ሰማያትን በከዋክብት ያደምቃቸዋል፤ ከግዜ ውጭ የሆነ ጌታ ዘመናትንም እስረጅቶ አዝማናትን ይተካል።
~☆☆☆~
🌻~ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን ሲጽፍ “የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልእክተኛዬን በፊትህ
እልካለሁ፡፡ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፡፡ ጥርጊያውን አቅኑ” እያለ “በምድረ በዳ የሚጮኸ ሰው ድምፅ” ተብሎ በኢሳይያስ እንደተነገረ የነቢዩ ዘካርያስ ልጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘመነ ሐዲስ መጀመሪያ ላይ ተነስቶ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!” እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ መጣ ብሎ ለዘመነ ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፍ ትምህርትና ተግሳጽ እንዳደረገው ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ ይነግረናል፡፡ ማር.፩፥፲፬ ኢሳ. ፵፥፫-፬
~☆☆☆~
🌻~ የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ ሆኖ መገኘቱን በመረዳት የቤተ ክርስቲያን አበው የበዓላትን ድንጋጌ በወሰኑበት አንቀጽ የመጥምቁ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በሚከበርበት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር በየዓመቱ የዘመኑ መጀመሪያ በእርሱ ስም እንዲጠራ እንደወሰኑ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ ፩-፫
~☆☆☆~
🌻 ~ የዘመኑ መቀየር ከቁጥር በዘለለ የእኛውም አስተሳሰብ እንዲቀየር ነው፡፡ ለሥጋዊ ኑሮአችን መሳካት በእቅድ እንደምንመራው ሁሉ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን እናስብ፤ ቃለ እግዚአብሔር ለመማር፣ ንስሐ ለመግባት፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል መንፈሳዊ እቅድ እናውጣ! ተግባራዊ ለማድረግም ጥረት እናድርግ፡፡ አምላካችን ከእኛ ሕይወት ፍሬ ለማግኘት በልጅነታችን፣ በወጣትነትና በሽምግልና እድሜያችን ሦስት ጊዜ መጣ ፍሬ ሃይማኖትና ምግባር አጣብን አትክልተኞቹን ቅዱሳን መላእክትን “ ስለምን ደግሞ መሬቱን ታጎሳቁላለች?” ቢላቸው “ጌታ ሆይ ዙርያዋን እስክኮተኩትላትና ፋንድያ እስካፈስላት ድረስ በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት” እያሉ በለመኑት የብድር እድሜ ነው አዲስ ዓመቱን ለማየት የቻልነው። ሉቃ. ፲፫፥፲፯ በተሰጠን የብድር እድሜ መልካም ነገር ለመሥራት እንነሣ በስንፍና ያሳለፍነው ጊዜ ይብቃን! ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ እንዲህ ይለናል “የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት ጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና”። 1ኛ ጴጥ. ፬፥
☆☆☆
🌻 ~ ፪ሺ፲፰ ዓ.ም ብዙ ነገር ያየንበት የሰማንበት ያዘንበት እና የተጨነቅንበት ዘመን ነው። በተለይ ለኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች በአንድ በኩል ዓመቱን ሙሉ አሕዛብ እና መናፍቃን ዕረፍት በመንሳት አክራሪወቹ፦ በሰይፍ ሲያርዱን፤በድንጋይ ሲቀጠቅጡን፤ በእሳት ሲያቃጥሉን፤ መንግስት ሳይቀር አይቶ ፍትህን ሲነፍገን ፤ ጌታ በደሙ የሰጠንን የምህረት ዘመን ዓመተ ፍዳ አድርገውብን አልፈናል። ግን ፪ሺ፲፰ ዓ.ምህረትስ? ሥለሁሉም ነገር የዓለም መድኃኒት የድንግል ልጅ ይክበርና በቸርነቱ ጠብቆ ይኸው ለ ፪ሺ፲፰ ዓ.ም አደረሰን፤ በዕውነት በቸርነቱ ፪ሺ፲፫፰ ዘመነ ቅዱስ ማርቆስ የምህረት ዘመንን ያድርግልን።
"ፈሪ ልብ ላላቸው። እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው። ኢሳ ፴፭፥፬
☆☆☆
🌻 ~ በዘመናት የማያረጅ ዘመናትን የሚያስረጃቸው ዘመንን የፈጠረ ሰፍሮ ለሰው የሰጠ ልዑል እግዚአብሔር መጨው ፪ሺ፲፫፰ ዓመተ ምህረትን ባርኮ ለቤተክርስቲያን ይስጥልን፤ የመከራውን ዘመንም በቃ ይበለን፤ የእመአምላክ እናትነቷ ምልጃና ርህራሄ ሊመጣ ካለው መከራ ይጠብቀን ፤አስራት ሀገሯን ኢትዮጵያም በቀደመ ክብሯ ታስብልን አሜን!!!
_ዓመት #እንቁጣጣሽ

 #ሩፋኤል
09/09/2025

#ሩፋኤል

27/08/2025

20/05/2025

"እንኳን ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ!"

ከመላእክት ጋር የምንዘምርበትን ሰማያዊ ዜማ፣
የብሉይ እና ሐዲስ ምሥጢራትን ያስማማ።
የምስጋና ማዕድ ሥርዓትን የሠራ፣
ዕንዚራ ስብሐት ማሕሌታይ ቅዱስ ያሬድ፣

ዛሬ ምሽት 2፡00 ይጠብቁን፡፡

~ እግዚአብሔር በደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተክርስቲያን በዘር ደዌ ከወደቁ ምንደኞች ይጠብቅልን ። ~ እግዚአብሔር ወደ ቀልባችሁ ይመልሳችሁ ።
24/10/2024

~ እግዚአብሔር በደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተክርስቲያን በዘር ደዌ ከወደቁ ምንደኞች ይጠብቅልን ።
~ እግዚአብሔር ወደ ቀልባችሁ ይመልሳችሁ ።

 ++  የደመራው ምሥጢር   ++እግዚአብሔር አምላካችን የሠራቸው ታላላቅ ሥራዎች በምልክት የተገለጡ ናቸው፤ ለምሳሌ የሙሴ መስፍንነት፣ የአሮን ሊቀ ካህንነት የተረጋገጠው በአሮን በትር ምልክት...
26/09/2024



++ የደመራው ምሥጢር ++

እግዚአብሔር አምላካችን የሠራቸው ታላላቅ ሥራዎች በምልክት የተገለጡ ናቸው፤ ለምሳሌ የሙሴ መስፍንነት፣ የአሮን ሊቀ ካህንነት የተረጋገጠው በአሮን በትር ምልክትነት ነው፡፡ አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ሊሠዋ በታዘዘ ጊዜ የሞርያን ተራራ የመረጠው እግዚአብሔር በተራራው ላይ ካሳየው ብርሃን የተነሣ ነው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ መስቀልም የድኅነታችን ምልክቶች ናቸው፡፡ የአሮንና የሙሴ በትሮች፣ የይስሐቅ ቤዛ የሚኾን በግ የተገኘባት ዕፀ ሳቤቅ ደግሞ የእመቤታችንና የመስቀል ምልክቶች ነበሩ፡፡ ወደ ፊት የምንወርሰው መንግሥተ ሰማያት ክርስቶስ ነው፤ እርሱን ደግሞ ያገኘነው ከመስቀል ላይ ነው፡፡

ጥንተ ጠላት ሰይጣን ይህንን ስለሚያውቅ ቅዱስ መስቀሉን አጥብቆ ይቃወመዋል፤ ስለዚህም አይሁድን አነሳሥቶ ከ፫፻ ዓመታት በላይ ተቀብሮ እንዲቆይ አድርጓል፡፡ በመሠረቱ ለሰይጣን ምሥጢሩ ስለማይገባው ነው እንጂ የመስቀሉ ትክክለኛ መቀበሪያ ሥፍራ የምእመናን ልቡና ነው፡፡ ቀራንዮ ለመስቀሉ መትከያነት የተመረጠችውም ቀዳሜ ፍጥረት አዳም የተቀበረው በዚያ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቦታው ‹‹የራስ ቅል ሥፍራ›› /ማቴ.፳፯፥፴፪/ መባሉም የኹላችን ራስ አዳም ዓፅሙ በዚያ ስላረፈ ነው፡፡ መስቀሉ በአዳማውያን ፍጥረታት አእምሮ ውስጥ እንጂ ከዚያ ውጪ የሚኖር ባለመኾኑ ተቀብሮ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥም ፍቅሩ ከሰው ልጆች ልቡና አልወጣም፡፡

ጠላት በሠራው ተንኮል ተቀብሮ እንዳይቀር መስቀሉን እንድታወጣ መንፈስ ቅዱስ ንግሥት ዕሌኒን አስነሣት፡፡ ይህች ሴት ቤቷ በሀብት፣ በንብረት ሞልቶ በነበረበት ጊዜና በገረድ፣ በደንገጡር በምትንቀሳቀስበት ወቅት ምን እንደ ሠራች አልተመዘገበላትም ነበር፤ ከክብሯ ወርዳ በተጣለችበት ጊዜ ግን እግዚአብሔር ለሚፈልገው ሥራ ምቹ ኾና ተገኘች፡፡ እርሷ በተጣለችበት ባዕድ አገር ውስጥ ኾና የመስቀሉን ነገር ታስብ፤ ብርሃነ መስቀሉም ዘወትር በልቧ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ ሐሳቧን እንዲያሳካላት የለመነችው አምላክም ኪራኮስ የተባለውን አይሁዳዊ ሽማግሌ ልኮ አቅጣጫውን አመላከታት፤ ኪራኮስ የጀመረውን ምሥጢርም መልአኩ ‹‹ደመራ ደምረሽ፣ ሰንድሮስ የሚባል ነጭ ዕጣን ጨምረሽ አቃጥዪው›› ብሎ ተረጐመላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንደ ነገራት ብታደርግ ጢሱ ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ተመልሶ መስቀሉ ወደሚገኝበት ተራራ ሰገደ፡፡ በጢሱ ምልክትነት መስከረም ፲፯ ቀን የተጀመረው ቍፋሮ መጋቢት ፲ ቀን አልቆ ዕሌኒ መስቀሉን ከልበ ምድር ለማውጣት ችላለች፡፡

መስቀልና ደመራ እንዲህ ነበር የተገናኙት፡፡ ደመራው ለመስቀሉ መገኘት፣ መስቀሉም ለደመራው መሠራት ምክንያት ናቸው፡፡ በዚህ አንጻር መለኮትና ትስብእት በአንድነት መደመራቸው መስቀሉ እንዲሠራ ምክንያት ኾነዋል፡፡ አምላካችን ሥጋ ለብሶ ‹ክርስቶስ› በሚል የተዋሕዶ ስም ሲጠራ ለመከራ መዘጋጀቱን እንረዳለን፡፡ መስቀሉ የሥጋ ብቻ ነበረ፤ አሁን ግን መለኮትም በሥጋ ባሕርይ የመስቀሉ ተካፋይ ኾነ፡፡ ይህም የደመራው ውጤት ነው፡፡ መለኮት አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዘመን መስቀል የተሸከመ ሥጋን ሲዋሐድ መስቀሉን አስወግዶ አልነበረም፡፡ ይኸው በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከምነው መስቀል ነው፡፡ ሥጋ ዓቅም አጥቶ መስቀሉን ከትከሻው ላይ ሳያወርድ ለዘመናት የተጓዘውን ጕዞ መለኮት ኀይል ኾኖት ድካሙን ሳይለቅ ኀያል፤ ኀይሉን ሳይለቅ ደካማ ኾነ፡፡ መስቀል ትርጕሙ መከራ ቢኾነም ነገር ግን እግዚአብሔር ሲያመጣውና ሰው ሲያመጣው ግን ትርጕሙ ይለያያል፤ ሰው ያመጣው መስቀል ኹላችንን ለመከራ፣ ለሞት አሳልፎ ሰጥቶናል፡፡ የእግዚአብሔር መስቀል ግን መከራነቱ ለሰይጣን እንጂ ለእኛ ሕይወታችን ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ‹‹መስቀል ብሂል ዕፀ ሕይወት ብሂል፤ መስቀል ማለት የሕይወት ዛፍ ማለት ነው›› በማለት የመስቀልን ትርጕም ነግሮናል፡፡

አዳም ከገነት ሲወጣ በመላእክት እንዲጠበቅ የተደረገው የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መስቀል ነው፡፡ በዕፀ በለስ ምክንያት ኹላችንም እንደ ተጎዳን በዕፀ ሕይወቱም ተጠቃሚዎች ኾነናል፤ አስቀድመን በአዳም መከራ እንደ ተባበርን አሁን ደግሞ በደስታው እንተባበራለን፡፡ ሞትም ሕይወትም አንድ አድርጎናል፡፡ የክርስቶስ መስቀል ኹሉንም በሕይወት አስተባብሯልና፡፡ በአንጻሩ ሰውና ዲያብሎስን ለያይቷል፡፡ የኀጢአት ቁራኝነትን አጥፍቷል፡፡ ጌታችን በማኅፀን ሲፀነስ ጀምሮ የእኛን መስቀል መሸከም ሲጀምር የእርሱ የኾነውን ለእኛ ስለ ሰጠን ከሰይጣን ጋር መለያየታችን በመስቀሉ ተረጋግጧል፡፡ የአምላካችን መስቀል ምልክቱ ደመራ መኾኑ የእኛን ወደ እርሱ መሰብሰብና የጠላታችንን መበተን የሚያረግጥልን ነው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወብየ ካልዓትኒ አባግዕ እለ ኢኮና እምዝንቱ ዐፀድ ወኪያሆንሂ ሀለወኒ አምጽኦን ዝየ፤ ከዚህ በረት ያልኾኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ላመጣቸው ይገባኛል›› በማለት ሊሰበስበን እንደ መጣ ነግሮናል /ዮሐ.፲፥፲፮/፡፡ መስቀሉ ፍጥረት አንድ ደመራ ኾኖ የተሠራበት ስለ ኾነ በደመራ እንዲገለጥ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ኾነ፡፡

መስቀሉ አንድ ደመራ ያደረጋቸው ፍጥረታት

፩. ነቢያትና ሐዋርያት

ነቢያት የሚባሉት ከአዳም እስከ ዮሐንስ መጥምቅ ያሉ አባቶች ሲኾኑ፣ ከክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያን የወንጌልን የምሥራች እንዲነግሩ የተላኩ አባቶች ደግሞ ሐዋርያት ይባላሉ፡፡ በእርግጥ ሐዋርያ የኾነ ነቢይ የለም እንጂ ነቢይ የኾነ ሐዋርያ አለ፡፡ ነቢያትና ሐዋርያት በዘመን፣ በክብር እና በግብር የማይገናኙ ፍጥረታት ናቸው፡፡ መንፈሰ ረድኤት የተሰጣቸው ነቢያት ለሐዋርያት የተሰጠውን መንፈሰ ልደት ለማግኘት አልተቻላቸውም፡፡ ሐዋርያት ግን ኹሉንም አንድ አድርገው ይዘዋል፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ስለዚህ ሲመሰክር ‹‹በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጠን›› በማለት አጕልቶ የተናገረው /ዮሐ.፲፥፲፰/፡፡ ነቢያት በዚህ ምድር የእግዚአብሔርን መንግሥት በመፈለግ ብዙ ደክመዋል፡፡

ሊቃውንቱ ነቢያትን በክረምት፣ ሐዋርያትን በበጋ ገበሬ ይመስሏቸዋል፡፡ የክረምት ገበሬ ላዩ ውሃ፣ ታቹ ውሃ ኾኖበት በጭቃ ወጥቶ በጭቃ ይመለሳል፡፡ ወደ ቤቱ ሲገባም ሚስቱ ጨምቃ ያቆየችለትን ጐመን በልቶ ደስ ሳይለው ይተኛል፡፡ ነቢያትም በዚህ ዓለም በጣዖት አምላኪ ነገሥታት፣ በነቢያተ ሐሰት ስብከት ሲንገላቱ ኖረው ሲሞቱም ሲዖል ይገባሉ እንጂ ገነትን አይወርሱም ነበር፡፡ የበጋ ገበሬ በደረቅ ወጥቶ፣ እሸት በልቶ፣ ተደስቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ከቤቱ ሲገባም እንጀራው በሌማት፣ ጠላው በማቶት፣ ሲቀርብለት ደስ ብሎት ይበላል፤ ይጠጣል፡፡ ሐዋርያትም ልጅነትን አግኝተው ለማስተማር ተልከዋል፤ በሔዱበት ኹሉ ተአምራትን እንዲያደርጉ፣ ልጅነትንም እንዲሰጡ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሞታቸው ሲደርስም መንግሥተ ሰማያት ተከፍቶ ይጠብቃቸዋል፡፡

ቅዱስ ያሬድም ‹‹ኖትያት ነቢያት ራግናት ሐዋርያት›› በማለት ነቢያትን በዋናተኛ፣ ሐዋርያትን በጀልባ ቀዛፊ መስሎ ይናገራል፡፡ ከቀዛፊዎች ይልቅ ዋናተኞች ይደክማሉ፡፡ ዋናተኞች ውሃው አጥልቋቸው፣ መተንፈስ ተስኗቸው አንዳንዶቹ ከዳር ይደርሳሉ፤ አንዳንዶቹም በድካም በውሃ ውስጥ ሰጥመው ይቀራሉ፡፡ ቀዛፊዎች ግን ምናልባት ሞገድና ማዕበል ካላሰጋቸው በስተቀር ይህ ኹሉ ውጣ ውረድ የለባቸውም፤ በጀልባዋ የተመሰለችው ቤተ ክርስቲያን ለነቢያት በተስፋ እንጂ በአካላ አልተሰጠችም፡፡ ነቢያት ከእርሷ ሳይደርሱ ሞት ቀድሟቸዋል፡፡ ሐዋርያትም በነቢያት ድካም ገብተው ነቢያት የዘሩትን የትንቢት ዘር አጭደዋል፡፡ ወንጌል የነቢያት ዘር ናት፤ ዳሩ ግን ፍሬውን ለመብላት የታደሉት ሐዋርያት ናቸው፡፡ እሸቱ ሲደርስ የገበሬዎቹ የነቢያት ጌታ ክርስቶስ ዘሩን እንዲሰበስቡና እንዲያከማቹ ሐዋርያቱን በእርሻ መካከል ይዟቸው ገብቷል /ማቴ.፲፪፥፩/፡፡ በአበው ፋንታ ውሉድን ለመተካት የመጣው መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በመስቀሉ አንድ ማኅበር አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው መስቀሉን ‹‹ገባሬ ሰላም›› በማለት ይጠራዋል /ኤፌ.፪፥፲፫/፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን አንድ አድርጎ የእግዚአብሔርን መንግሥት ያወረሰ የክርስቶስ መስቀል ነውና፡፡

፪. ሙታንና ሕያዋን

አዳም በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከመው መስቀል ሞትን አምጥቶብናል፤ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ድኅነት ሲል የተሸከመው መስቀል ግን ሞትን ገድሎ ሕይወትን ሰጥቶናል፡፡ በዚህ ምክንያት የሞት መውጊያ ሲሰበር፣ የመቃብር ስቃይ ሲቋረጥ፣ የጨለማ ኀይል ሲሻር ከመስቀሉ ሥር ብዙ ሙታን እንደ አሸን ብቅ ብቅ አሉ፡፡ ምድር እስከዚያች ቀን ድረስ ሙታንን ትቀበል ነበር እንጂ ሕያዋንን ማስገኘት አትችልም ነበር፡፡ ሙታንና ሕያዋን የተፈላለጉበት መስቀል የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ በመስቀል ሙታን ሕያዋንን ፍለጋ ከመቃብር ወጥተው ወደ ከተማ ገቡ፡፡ ከታደለው የሕይወት ስጦታ የተነሣ ሞት አካባቢውን ለቆ ስለጠፋ በሩ እንደ ተከፈተለት እሥረኛ ሙታን ከመቃብር እየወጡ ከተማውን ሞልተውታል፡፡ ይህ ዕለት ሙታንን ከሕያዋን ጋር አፍ ለአፍ ያነጋገረ ዕለት ነው፡፡ ደመራው ሙታንን ከሕያዋን የሚለይ አይደለም፤ ታላቅነቱም እስከ ሲዖል ድረስ የሚታይ ነው፡፡

፫. ጻድቃንና ኀጥአን

የአዳም በደል በሕይወት የሚኖሩ ወንድማማቾችን በሁለት ሐሳብ ከፋፍሏቸው ነበር፡፡ የክርስቶስ የጽድቅ መስቀል ግን አንድ ሐሳብ ፈጠረላቸው፡፡ ጻድቁ አቤል ሳይበድል በደል የደረሰበት፣ ሳይገድል የተገደለ መኾኑ ከክርስቶስ ጋር ቢያመሳስለውም ሞቱ ግን ለሰው ልጆች ድኅነት አልጠቀመም፤ የፍጡር ደም ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀን አይችልምና ኹላችንም በመከራ ውስጥ ለመቆየት ተገደናል፡፡ የክርስቶስ ሞት ግን የድኅነታችን መሠረት ኾነልን፡፡ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መብራት ከፍ ብሎ ሲቀመጥ ኹሉን እንዲያሳይ ከምድር ከፍ ብሎ የተሰቀለው ክርስቶስም ጻድቃነ ብሊትንና ጻድቃነ ሐዲስን በዓይን እንዲተያዩ አድርጓቸዋል፡፡ በመስቀል ላይ የተፈጸመው ዕርቅ የኀጥአንን በደል ደምስሶላቸዋል፤ የጻድቃንን ጽድቅ አረጋግጦላቸዋል፡፡ ጻድቃንም ኀጥአንም አንድ ኾነው መንግሥቱን በጸጋው ወረሱ፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ እንዳደረገው አሞራውያን ወጥተው እስራኤል ብቻ ምድሪቱን የወረሷት አይደሉም፡፡ መስቀሉ ለኹሉም አንድ መንግሥትን አውርሷቸዋል፤ ጊዜው የደመራ ነውና፡፡ በምድር ደምቆ የታየው ይህ ደመራ እስከ መንግሥተ ሰማያት ድረስም ይቀጥላል፡፡

ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

   💠~"በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሥ               አሀዱ አምላክ አሜን!!!" ❖ ✝️~ ሰኔ ፳ በሀገረ ቂሣርያ፣ ኬልቄዶንያ አውራጃ የመጀመሪያዋ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማ...
27/06/2024


💠~"በሥመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሥ
አሀዱ አምላክ አሜን!!!" ❖
✝️~ ሰኔ ፳ በሀገረ ቂሣርያ፣ ኬልቄዶንያ አውራጃ የመጀመሪያዋ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የታነጸችበት ዕለት ነው ።
✝️~ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውኀ በሦስት ድንጋዮች ቤተ ክርስቲያኗን ያነጸበት ዕለት ነው፡፡

✝️~ ይኸውም ሐዋርያው ጳውሎስና በርናባስ አሕዛብን ሰብከውና ብዙዎችን አሳምነው ከመለሱ በኋላ ሕዝቡ ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያን ስላልነበረ በጸሎትና በሱባኤ ጌታችን ኢየሱስን እንዲማጸኑ ሕዝቡን አዘዙ፤ ጌታችንም በሱባኤው ፍጻሜ ላይ ለሐዋርያቱ ተገልጾ በመላው ሀገር እስከ ፊልጵስዩስ ድረስ በደመና ከሰበሰባቸው በኋላ ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ "ይህች ዕለት በእናቴ በማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነፁ የፈቀድኩባት ናት፡፡" ከዚያም ጌታችን የቤተ ክርስቲያኗን ቦታና መሠረት ወስኖ ንዋየ ቅዱሳቷ፣ አልባሳቷንና መሠዊያዋን ካዘጋጀ በኋላ በዚያ ሥፍራ የነበሩትን ሦስት ድንጋዮች የተራራቁትን አቀራርቦ፣ ጥቃቅኑን ታላላቅ አድርጎ ቁመቱን በ፳፬፣ ወርዱን በ፲፪ ክንድ ለክቶ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጣቸው፡፡

ከዚህም በኋላ እጁን በጴጥሮስ ራስ ላይ ጭኖ በአራቱ ማእዘነ ዓለም ውስጥ አርሳይሮስ (ሊቀ ጳጳሳት) ብሎ ሾመው፤ በዚያን ጊዜም ‹‹ለሐዋርያት አለቃ ጴጥሮስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የጳጳሳት አለቃ ይሆን ዘንድ ይገባዋል! ይገባዋል! ይባዋል! እያሉ መላእክትና ምድራውያን ሦስት ጊዜ ተናገሩ፡፡ ኅብስት ሰማያዊ፣ ጽዋዕ ሰማያዊ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወረደ፤ ጌታችንም፤ እመቤታችንን ታቦት፣ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ሆኖ ቀድሶ ካቈረባቸው በኋላም የቅዳሴን ሥርዓት እንዲያከናውኑና ለሕዝቡ ቅዱስ ቊርባንን እንዲያቀብሏቸው አዘዛቸው፤ በመቀጠልም ለሐዋርያቱ እንዲህ አላቸው፤ "በዚህች ቀን የእጃቸውን ሥራ እንዳይሠሩ ሕዝቡን ሁሉ እዘዙአቸው" ይህም የሆነው ሰኔ ፳፩ ቀን ነው፤ ጌታችንም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ በታላቅ ክብር ዐረገ፡፡

✝️~ ቅዱሳን ሐዋርያትም በመላው ዓለም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያንን በእጃቸውም አነጹ፤ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ቁመትም በነገሥታት ዘመን የነበሩ የ፳፬ቱ ነቢያትና የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ሲሆን ወርዱ ደግሞ የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው፡፡ ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴ አምሳል ሲሆኑ፣ ከታች አቀማመጣቸው ሦስት፣ ከላይ ሕንጻቸው አንድ መሆኑ የሥላሴን ሦስትነትና አንድነት ያመለክታል፡፡ የሠሩትም ሦስት ክፍል አድርገው ሲሆን ይህም የመጀመሪያው የታቦተ አዳም፣ ሁለተኛው የታቦተ ሙሴ፣ ሦስተኛው የታቦተ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ዳግመኛም የሦስቱ ዓለማት ማለትም የመጀመሪያው የጽርሐ አርያም፣ ሁለተኛው የኢዮር፣ ሦስተኛው የጠፈር ምሳሌ ነው፡፡ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራውም ጌታችን በዐረገ በ፲፱ኛው፣ እመቤታችን በዐረገች በ፬ኛው ዓመት ሰኔ ፳ ቀን ነው፡፡

✝️~ ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም በዘመኑ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በታነጸው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሥዕል ለማሳል በመሻቱ ሠሌዳ ፈለገ፤ ከአንድ ባለጠጋ ዘንድ እንዳለም ሰምቶ እንዲሰጠው ቢያስልከብትም ባለጠጋው ግን ለልጆቹ እንደሆነና ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ፤ በቅጽበትም ወድቆ ሞተ፤ በዚህን ጊዜ ልጆቹ በመፍራታቸው ሠሌዳውን ከብዙ ወርቅና ዕንቊ ጋር ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ወሰዱለት፤ እርሱም ሠሌዳውን ወደ ሠዓሊው ወስዶ እንዲስልበት ሰጠው፤ ሆኖም ግን እመቤታችን ድንግል ማርያም በራእይ ተገልጻ ሥዕሏን በሠሌዳው እንዳይሥል ከለከለችው፤ ከዐመጸኛ እጅ የተገኘ ነበርና፡፡ የአንዱ በቀኝ የአንዱ በግራ የተሣለ የእመቤታችን ሥዕል ቀይ ሠሌዳ ያለበትንም ሥፍራ ነገረቸው፡፡

✝️~ ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ወደ አመለከተችው ቦታ በመሄድ ሠሌዳውን አግኝቶ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ አምጥቶ ሁለት ምሰሶዎች ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ካቆመ በኋላ ሥዕሏን በዚያ አስቀመጠ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም በምሰሶዎቹ በታች የውኃ ምንጭ አፈለቀ፤ ድውያንም በእርሷ ይፈወሱ ነበር፡፡ ከእመቤታችንም ሥዕል በሽተኞች የሚፈውስ የዘይት ቅባት መፍሰስም ጀመረ፡፡
✝️~ ነገር ግን አንዲት ሴት በፈለቀው ምንጭ ውኃ ስትታጠብ መላ ሰውነቷ በለምጽ ተሸፈነ፤ በዚህን ጊዜም ቅዱስ ባስልዮስ አስጠርቶ ምን እንደሆነች ጠየቃት፤ እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባቸው ነገረቸው፤ ቅዱስ ባስልዮስም ታላላቅ ሦስት ኃጢአት በመሥራቷ ምንአልባት እግዚአብሔር ይቅር ይላት እንደሆነ ንስሓ እንድትገባ አዘዛት፤ ነገር ግን በዚያች ሰዓት ምድር ተሰንጥቃ ዋጠቻት፤ እርሷ ቤተ ክርስቲያንን ተዳፍራለችና፡፡
✝️~ እኛም የቤተ ክርስቲያን ልጆች ቤተ ክርስቲያንን በማክበርና ሥርዓቱን በመጠበቅ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ክብረ በዓል እናከብር ዘንድ ይገባል፡፡ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፤ አሜን።
✝️~ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ስለ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ሲል በጎውን ዘመን እናይ ዘንድ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ሰላሟን ይመልስልን አሜን።

ምንጭ፦

 #ኦርቶዶክስ እና  #ፕሮቴስታንት ስለ   ምን ይላሉ ?  #እኛ እና  #እነርሱ      ✝️~ የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምን ትላለች  ፦ ~ ኢየሱስ ክርስቶስን  ~  የባህሪ...
10/04/2024

#ኦርቶዶክስ እና #ፕሮቴስታንት ስለ ምን ይላሉ ? #እኛ እና #እነርሱ
✝️~ የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምን ትላለች ፦
~ ኢየሱስ ክርስቶስን ~ የባህሪ አምላክ ፈራጅ ትላለች
~ የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ነው
ትላለች።
~ ጥምቀት ~ የድኅነት ወይም ወደ መንግስተ
ሰማያት መግቢያ በር ነው ትላለች።
~ ቅዱስ ቁርባን ~ ክርስቶስ በዕለተ አርብ የሰጠን
አማናዊ ቅዱስ ስጋ እና ደም ነው ይኸውም
ዘላለማዊ ህይወት የሚያሰጥ ነው ትላለች።
~ በጎ ስራ ~ አንድ ሰው አምኖ ከተጠመቀ በኋላ በጎ
ምግባራትን መስራት አለበት። ይኽውም
መጾም ፥ መጸለይ፥ መስገድ፥ መመጽወት እና
የመሳሰሉትን ማድረግ አለበት ትላለች።
~ ዝክር ~ በባለቤቱ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር
ስም በወዳጆቹ በቅዱሳን ስም ማዘከር
ይገባል ትላለች።
~ ቅድስት ድንግል ማርያምን በተመለከት ተዋህዶ
የእግዚአብሔር እናት ወላዲተ አምላክ ብርሃን ክርስቶስን የወለደች እመብርሃን ፤ የውርስ ኃጢያት ያልነካት ዘላለማዊ ድንግል ናት ትላለች

ፕሮቴስታንቶች ምን ይላሉ፦
~ ኢየሱስ ክርስቶስን. × አማላጅ ነው ይላሉ
× የግል አዳኝ ይላሉ

~ ጥምቀት × መንግስተ ሰማያት ከመግባት ጋር
አንዳች የሚያገናኘው ነገር የለም ይላሉ
~ ቅዱስ ቁርባን × መታሰቢያ ነው ለድኅነትም
አስፈላጊ አይደሉም ይላሉ
~ በጎ ስራ × ክርስቶስ ሞቶልናልና አያስፈልግም ይላሉ
~ ዝክር × ይህ የሰዎች የፈጠራ ትምህርት ነው ይላሉ
~ ቅድስት ድንግል ማርያምን በተመለከ ፕሮዎች የእግዚአብሔር እናት መባል አይገባትም ለስም አጠራሯ ክብር ይግባትና ጥንተአብሶ ማለትም የውርስ ኃጢያት አለባት ከጌታም ውጭ ሌላ ልጅ አላት ይላሉ።

መጽሐፍቅዱስስ ምን ይላል ፦
መሆኑን በተመለከት

፩- '' " ዮሐ 3÷35
~ ''የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን እውነተኛም በሆነው በርሱ አለን፥ ክርስቶስ ነው። ነው።" 1ኛ ዮሐ 5 :20
~ '' በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በርሱ ተፈጥረዋልና፥ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው።ሁሉ በርሱና ለርሱ ተፈጥሯል።" ቆላ 1:16 በማን ከተባለ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
~ '' የተባረከውን ተስፋችንን ርሱም የታላቁን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ቲቶ 2:12

፪. ''ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ያላመነ ግን ይፈረድበታል።" ማር 16:16

፫.'' ፥እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለኹ።"" ዮሐ 6:54
''ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በርሱ እኖራለኹ።'' ዮሐ 6:16

፬.~ ''ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።'' ዮሐ 14:15
''ወንድሞቼ ሆይ፥እምነት አለኝ የሚል፥ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?'' ያዕ 2:12
'~ 'እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።' ያዕ 2:17
~ ''አንተ ከንቱ ሰው፥እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳ፟ለኽን?" ያዕ 2:20

፭. "ማንም ከነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ብቻ ፥እውነት እላችኋለሁ፥ ።" ማቴ 10:42
፮. ''ወዳጄ ሆይ ሁለተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም" መሓል 4:10

~ " የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር። ት.ኢሳ 1:9
"ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"ኢሳ ፱፥፮
~ እኛ እና እነሱ ልዩነታችን በዋናው በነገረ ክርስቶስ ትምህርት ላይ ነው እንጁ ፤ እነርሱ እንደሚሉት የነገረ ቅዱሳን የመስቀል የጠበል የጾም የጸሎት እና የመሳሰለት ጉዳይ አይደለም ፤ እነሱ ኢየሱስ ኢየሱስ ስላሉ ትክክል ናቸው ማለት አይደለም። ፕሮዎቹ ኢየሱስን የሚረዱበት መንገድ ፈፅሞ ስህትት ነው፤ እድስ እና እንግዳ ትምህርት ነው ፤ሐዋርያት ያልሰበኩት ሌላ ኢየሱስ ነው ፤ እናም አንቀበለውም ፤ ክርስቶስ ከነገረን ሐዋርያት ካስተማሩን ውጭ አንቀበልም።
~ እናም ወገኖቻችም ገና በአማነዊው ኢየሱስ እንዳላመኑ ልናሳውቃቸው ይገባል፤ ከ፲፯ኛው መቶ ክፍለዘመን የፈጠራ ትምህርት እንዲወጡ ልናግዛቸው ይገባል።
√ ሚዛኑን ለአንባብያን ተውኩት
!
በሚያቆለጳጵስም ንግግር ።

05/04/2024

26/04/2023

VidMeta is the best YouTube video downloader that can easily download YouTube videos 1080p, 4k, 8k on any Android, IOS & Windows device.

Address

መርሐቤቴ-አለምከተማ/Merhabetie Alemketema
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መርሐቤቴ ደብረ ገነት ጉናጉና ቅድሥት ማርያም ቤተክ/Merhabetie D.G.Gunaguna saint Mary church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to መርሐቤቴ ደብረ ገነት ጉናጉና ቅድሥት ማርያም ቤተክ/Merhabetie D.G.Gunaguna saint Mary church:

Share