Righteous Manna Professionals Fellowship (RMPF)

Righteous Manna Professionals Fellowship (RMPF) RMPF is a fellowship of young professionals who dedicate their life to Glorify Christ in their PROFESSION.

11/12/2020

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:10

በደል ሁልጊዜ ተበዳዩን ያስቆጣል። በበዳዩም ላይ ፍርድን ያስከትላል። በበዳዩ ላይ የሚደርሰውን ፍርድ የሚወስነው ደግሞ የተበዳዩ ማንነት ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ግለሰብን ሰርቆ ቢያዝና ያው ሰው ደግሞ የመንግስትንና የሕዝብን ሀብት ዘርፎ ቢያዝ ፍርዱ አንድ አይደለም። ምንም እንኳን በሁለቱም ተግባር ተመሳሳይ ሌብነት ቢሆንም፤ አቅምና ጉልበቱ ዝቅተኛ የሆነ ሰው ሲቆጣና ሁሉን ማድረግ የሚችል ፈላጭ ቆራጭ የሆነ መንግስት ሲቆጣ አንድ አይደለም። የተበደለው አካል ማንነት በበዳይ ላይ ሊደርስበት የሚችለውን ፍርድ ይወስናል። የሰው ልጆች በሐጥያታችን የበደልነውና ያሳዘነው የሰማይንና የምድርን ፈጣሪ እግዚአብሔርን ነው። እርሱ ቅዱስ ነው። ብርሀን ነው በብርሀንም ውስጥ ይኖራል። በእርሱ ዘንድ ጨለማ ፈፅሞ የለም። እርሱ ሀጥያትን አያውቅም። ይህንን አምላክ መበደል ከሁሉ የባሰና የጠነከረን ቁጣ ያመጣል። መፅሐፍ ቅዱስ በሐጥያት ስለመጣው ማንነታችን ሲናገር “ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን” ይላል ኤፌሶን 2:3። በሐጥያታችን እግዚአብሔር ደስ አልተሰኘም። ይልቁንም ቁጣውን ገለፀ እንጂ። ሐጥያትና የሐጥያት መዘዙ አስከፊ የሆነው ይህንን ታላቅ አምላክ ስለበደልን ነው።

ከእግዚአብሔር ቁጣ ማን ሊያድነን ይችላል? ብለህ ልታስብ ትችላለህ። ለዚህ መልሱ አንድ ብቻ ነው። እርሱም በመስቀል ላይ ስለ ሰው ልጆች ብሎ ራሱን መስዋዕት ያደረገው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ስራ ለመስራት ብንሞክር መዳን አንችልም። ምክንያቱ ደግሞ የእኛ ስራ የእርሱን ፅድቅ ሊያሟላ ስለማይችል ነው። ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ስርዓቶችን ብንፈፅምም ደህንነትን ማግኘት አንችልም። ምክንያቱም ሐይማኖት የሰውን የውጫዊ ማንነት ይገራና ያስተካክል ይሆናል እንጂ ፍጥረታችንን ከሐጥያተኝነት ወደ ፃድቅነት ሊለውጥ አይችልም። ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው? መፍትሄው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ብቻ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የወጣው የአለምን ሁሉ ሐጥያት ተሸክሞ ነው። የእኔን፣ የአንተን፣ የአንቺን፣ የጥቁሩን፣ የነጩን፣ የድሀውን፣ የሐብታሙን፣ የተማረውን፣ ያልተማረውን፣ የሁሉንል ሐጥያት ይዞ በመስቀል ላይ ተሰዋ። ሐጥያት የማያውቀው እርሱ ስለ እኛ ሐጥያት ሆነ። የእግዚአብሔር ቁጣ በመስቀል ላይ ተገለጠበት። ስለ እኛ ሐጥያት እርሱ ደሙን አፈሰሰ። መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር “... እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።” ይላል ኢሳይያስ 53:6። በእርሱ መስዋዕትነት እኛ ሕይወት አገኘን። የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚያበርድ እውነተኛ መስዋዕት ሆነ።

ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ደሙን ሲያፈስ ስለ ሐጥያታችን ዋጋ እየከፈለ ነው። መስዋዕትነቱ እኛን ከሐጥያት ኩነኔ ለማዳን ነው። የእግዚአብሔርን ቁጣ እንዲነድ ያደረገውን ሐጥያት ከእኛ ላይ በደሙ ለመሸፈንና ለማጠብ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ደሙን ሲያፈስ መካከለኛ ሆኖ እኛን ከእግዚአብሔርን ጋር ለማስታረቅ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሐጥያት ሀይል ከሰይጣን እስራት ነፃ የሚያወጣ ብቸኛው የደህንነት መንገድ ነው።

ዛሬ ይህንን የደህንነት ጌታ አዳኝህና ጌታህ አድርገህ ሕይወትህን ብትሰጠው ለዘላልም ለዚህም አለም ዋስትና አለህ። የእግዚአብሔር ልጅ ትሆናልህ። ወዶሀል እንዳትጠፋ የሐጥያትና የሰይጣን ባሪያ ሆነህ ሕይወትህ እንዳያልቅ ኢየሱስ ዋጋውን ከፍሎሀል። ታዲያ ይህንን የእውነት ጌታ ተቀብላችሁ ወደ ሕይወታችሁ እንዲገባ ከፈቀዳችሁ፤ ይህንን ፀሎት ባላችሁበት ፀልዩ።

“የፍጥረት ሁሉ አባት እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ከታላቅ ፍቅርህ የተነሳ ልጅህን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ እኔ ሐጥያትና በደል በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ መስዋዕት ይሆን ዘንድ አሳልፈህ ስለሰጠሀው አመሰግንሀለሁ። አሁን ደግሞ ኢየሱስ የተሰቀለው፣ የሞተው እንዲሁም ከሞት የተነሳው እኔን ከአምላኬና ከአባቴ ከአንተ ጋር ለማስታረቅ መሆኑ ስለገባኝ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሐጥያቴን ሁሉ ይቅር እንድትለኝ እለምንሀልሁ። ብቸኛው የደህንነት መንገድ ኢየሱስ እንደሆነ ገብቶኛል። ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር መዳን በማንም እንደሌለ አምናለሁ። በልቤ የማምነውን የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት በአንደበቴ ‘ብቸኛው አዳኝ ኢየሱስ ነው’ ብዬ እመሰክራለሁ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ሐጥያቴንና በደሌን ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለተሰረዘ አመሰግንሃለሁ። አሁን የአንተ ልጅ ነኝ። ከዚህ በኋላ በእኔ ሕይወት ላይ ሰይጣን፣ አለም፣ ሐጥያት ማናቸውም ገዢ አይሆኑም። የሕይወቴ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ጌታ ሆይ ስላዳንከኝ አመሰግንሃለሁ። አሜን።”

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።” 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:10

This is the truth 👉🏿
15/09/2020

This is the truth 👉🏿

ለሰው ልጆች ጥያቄ ብቸኛው መልስ የእግዚአብሔር መንግስት ነው:: የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በሰውና በእግዚአብሔር መሀል: በሰውና በሰው መሀል ሰላምን ያመጣ ብቸኛው መፍትሄ ነው::
2013 ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር የምንራመድበት ዓመት አንዲሆን ፀሎቴ ነው::

Remembering welenchiti
28/07/2018

Remembering welenchiti

... we will continue to empower professionals to be agents of change!
05/12/2017

... we will continue to empower professionals to be agents of change!

Come and worship the King with Us- This saturday
05/11/2015

Come and worship the King with Us- This saturday

All professionals from any stream are kindly invited to this important Bible study program!
22/10/2015

All professionals from any stream are kindly invited to this important Bible study program!

What happens to Debre Zeit?I can say some visible and invisible things. Why do I say invisible? Oh... First I need to te...
26/03/2015

What happens to Debre Zeit?

I can say some visible and invisible things. Why do I say invisible? Oh... First I need to tell you the visible one. People has given their blood on the city main square for the blood bank so that any one who needs blood can get it at the right time and of course with the right type.

Fine. Now let me tell you about the invisible. If one person's blood can save the other one (visible) through donations, how much saving power will have the blood of Jesus Christ!? (Invisible) which has been donated by God the Father. This blood has the ability to save all human race. Everyone needs it and it is a type of blood that can match any type of your blood. Whether you are A, B, AB or O.

The invisible one that happens in Debre Zeit last Saturday is, people have taken this blood since all of them were hurt and damaged by sin. Now they are well, very well and guaranteed for ever and ever.

If your blood has the potential to save somebody, how much will be the saving power of blood of the Holy?!

Dears, I would like to share you some useful insights on the importance of Christian Professionals' Fellowship. 1. It is...
02/02/2015

Dears,

I would like to share you some useful insights on the importance of Christian Professionals' Fellowship.

1. It is a place where you can sharpen your grace (spiritual gifts) and natural talents. Keeping in mind also the sharing of experiences and ideas on your specific profession.

2. It is a spiritual family that will give you the conducive environment for your spiritual growth. I respect and accept that the Church is such a congregation for any person, that will let people to become a true disciples of Jesus Christ. But with the current Mega Church trends and strategies, I don't think it is feasible. When people sit in a small group they will have the opportunity to see each others back and mentor each other. So as any fellowship of believers, when Christian professionals sit together for a purpose God will use the opportunity to build Christ in them.

3. It is a place where you can find your inspiration and vision for the rest of your life, if don't have any. The vision of one person among the group may be an inspiration for the others to pursue theirs or even to share that vision. If we have open heart and mind we can take a lesson from others success and failure. For which such type of peer group setting or arrangement is very useful.

Finally, if anyone is curious about his/her spiritual development in Christ, then you need to think seriously about how you value fellowship. The spiritual fellowship that you should have. When you want to see your profession to be used by God for His Kingdom I recommend you to consider a fellowship of Christian Professionals who have the same zeal like you have. Then you put yourself in the path to become a useful and influential person who will glorify God in all his/her life.

Glorifying God in life
Yoftahe

Happy New year!
25/12/2014

Happy New year!

12/09/2012

Happy New Year

31/05/2012

To All Servants of RMPF; Saturday, Sene 2, @ 8:00 * Ethio.time; in GC main campus, we will be holding New Leadership Ordination Program. and we will be having our marvelous coffee and fellowship time at Crystal Dome. NEVER MISS IT!

20/02/2012

Righteous Manna Professionals' Fellowship (RMPF) is going to celebrate its Fourth year Anniversary on this Saturday at Pacific Hotel. All members are kindly invited to join us!!

Address

Meganagna GCM Campus
Addis Ababa
14813

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Righteous Manna Professionals Fellowship (RMPF) posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share