02/08/2026
በሰንበት ትምህርት ቤታችን የእቅድ ግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ከመደበኛ አባላት ጋር ተደረገ።
በሰንበት ት/ቤታችን አዲስ የተመረጠው ስራ አመራር በቀጣይ ሊሰራቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ጥቆማ እና ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ ጉባኤ በዛሬው እለት ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም በሰ/ት/ቤታችን አዳራሽ አካሂዷል።
በዚህም ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ዐበይት ርዕሶች እና የውይይት መነሻ ሃሳቦች ላይ በመመስረት በቀጣይ አመታት ሊሰሩ የሚገባቸው እና ሊታረሙ የሚገባቸው ችግሮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በተለያዩ ቡድኖች በመከፋፈል የተደረጉ ውይይቶች ማጠቃለያዎችም ለጠቅላላ ተሰብሳቢዎች ከቀረቡ በኋላ ያልተነሱ የተባሉ ተጨማሪ ሃሳቦችን ከጉባኤው የማሰባሰብ ሂደት ተከናውኗል።
ከዚህ በኋላ የሰንብት ት/ቤታችን ሊቀመንበርነቱን መ/ር ዘውዱ ኃ/ገብርኤል በሰጡት ማጠቃለያ የተሰጡትን ግብአቶች ወደ እቅድ አውርዶ ለመተግበር እንዲቻል በሐዋርያት ስራ ም 2 ቁ 46 ላይ እንደተመለከቱት የመጀመሪዎቹ ክርስቲያኖች የሚያስፈልግ መሆኑን በመጥቀስ በግብዓቶቹ መሰረት ለሚወጡ እቅዶች ትግበራ አባላት ቀና ትብብራቸውን እንዲያደርጉ በማሳሰብ ጉባኤው ተጠናቋል።
በቀጣይ ሳምንታት መሰል ውይይቶች ከነባር እና ጎልማሳ አባላት እንዲሁም ከማዕከላውያን ክፍል (ታዳጊ) አባላት ጋር የሚቀጥል ይሆናል።