The Rock Was Christ

  • Home
  • The Rock Was Christ

The Rock Was Christ The Rock Christ Preach the Christ Crucified We Needed to Reveal the Way of Heaven ,He is Jesus.

09/04/2023

Religion does not Save anybody, Jesus is NOT religion, he is LIFE the eternal life and the Lamb of God, He took away the World reproach.
Jesus didn't taught RELIGION, he teaches about the Eternal life, through him ALL WOULD be saved .
:::::::::HAPPY PASSOVER ::::::::

"16 I will satisfy him with long life, and show him my salvation.(Psalms 91:16)
26/07/2022

"16 I will satisfy him with long life, and show him my salvation.
(Psalms 91:16)

Thank You Lord Jesus for taking away My Suffering and My Reproach ❤ጌታ ሆይ ሞቴን ስለሞትክልኝ አመሠግንሃለሁ። መልካም ፋሲካ❤
30/04/2021

Thank You Lord Jesus for taking away My Suffering and My Reproach ❤
ጌታ ሆይ ሞቴን ስለሞትክልኝ አመሠግንሃለሁ።
መልካም ፋሲካ❤

ይህ የእምነት መግለጫ የተደነገገው በ325 ዓ.ም በሮማው ነጉሦ በቆንጣስጥኖስ ዘመን በኒቂያ ጉባኤ ሲሆን እንደገና በ395 ዓ.ም በሮማው ንጉስ በታዲዮስ ዘመን በድጋሜ  በቆንጣስጢንያ ጉባኤ ፀ...
14/03/2021

ይህ የእምነት መግለጫ የተደነገገው በ325 ዓ.ም በሮማው ነጉሦ በቆንጣስጥኖስ ዘመን በኒቂያ ጉባኤ ሲሆን እንደገና በ395 ዓ.ም በሮማው ንጉስ በታዲዮስ ዘመን በድጋሜ በቆንጣስጢንያ ጉባኤ ፀድቋል። በዚያን ጊዜ ክርስቲያኖች በሀሰት ትምህርት ከእውነት ወንጌል በመራቃቸው ነው።
ዛሬ ኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ካውንስል ይህንን እውነት በትውልዱ ጆሮ ካላሰማ ትውልድ??????????

07/03/2021
ዮሐን ምዕ. 1142፤ ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።43፤ ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ። አልዓዛር ሆይ...
23/01/2021

ዮሐን ምዕ. 11
42፤ ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።43፤ ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ። አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ።

ስላወጣሔኝ ተራራስላሳለፍከኝ መከራስላሻገርከኝ ማዕበልተመስገን እንጂ ምን ልበል!!!
19/01/2021

ስላወጣሔኝ ተራራ
ስላሳለፍከኝ መከራ
ስላሻገርከኝ ማዕበል
ተመስገን እንጂ ምን ልበል!!!

አንብቡትና አስተያየታችሁን አስቀምጡልኝ።የሚጨመር ወንም የሚቀነስ ካለ እቀበላለሁ። ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የአድሱ ዓለም ሥርዓት ወይንም የኢሉሚናቲ (The New World Order o...
03/05/2020

አንብቡትና አስተያየታችሁን አስቀምጡልኝ።
የሚጨመር ወንም የሚቀነስ ካለ እቀበላለሁ።

ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የአድሱ ዓለም ሥርዓት ወይንም የኢሉሚናቲ (The New World Order or the Illuminati) ዋና ምልክት ነው።
ሥሙ ደግሞ BAPHOMET ይባላል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይም በግልፅ እንደተቀመጠው በመጨረሻው ዘመን የክርስቶስ ተቃዋሚ ሆኖ የሚነሣው ሀሤተኛው ክርስቶስ ከሚገለጥባቸው ምልክቶች አንዱ ነው።

ለምልክቱ ብዙ ትርጓሜዎች አሉት።
1ኛ. በመጀመሪያ የፍየል ፊት። የዚህ ትርጓሜ ክርስቶስ በበግ መመሰሉን ለመቃወምና የበግ ዘመን አልፎ የፍየል ዘመን እንደመጣ ለማመላከት ነው። " በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ። እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።"
(የዮሐንስ 1:29)። በግ ደግሞ የጻድቃን ተምሳሌት ነው በሌላ በኩል ፍየል ደግሞ የሐጢአተኞች ምሳሌና ለፍርድና ለቅጣት የሚቀርቡ ናቸው። " በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።" (የማቴ 5:33)። በአጠቃላይ ሰይጣን የክርስቶስን ሥራንና የደሙን ውጤት ዋጋ በማሳጣት ብዙዎችን ወደ ሲኦል ለማውረድ ነዉ።

2ኛ. በግምባሩ ላይ ያለው የኮከብ ምልክት።
በውስጡ የ666 ቁጥሮችን ይዟል።
(ምዕይ ምዕ. 13) የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ። 18፤ አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።

3ኛ. በደረቱ ላይ ያለው የሴት የጡት ምልክት።
ይህ ደግሞ ክርስቶስ አለምን ሊያድን ሲመጣ በአዳም ምሳሌ ሆኖ በወንድ መልክ ስለተገለጤ ይህንኑ የክርስቶስን የወንድ ባሕሪውን ለማርከስ ነው። " ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።" (ሮሜ 5:14)። በተጨማሪ ደግሞ ሄዋን አዳምን እንዳሳተች ሁሉ ይህ መንፈስ በሴት ተመስሎ አለምን አሳስቶ ከክርስቶስ ለመለየት ነው።

4ኛ. በወገቡ ላይ ያለው የተጠላለፈው የዘንዶ ምልክት። ይህ ደግሞ አለምን ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስ ነው።
" ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።" (ራእይ 12:9)

በዚህ የመጨረሻው መጨረሻ ላይ ሆነን የእግዚአብሔርን ቃል ካልያዝን ማምለጥ አንችልም። የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንድታነቡ እተውላችኋለሁ።

(ኤፌሶን ምዕ. 6)
10፤ በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረችሁ ሁኑ። 11፤ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። 12፤ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።

13፤ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። 14-15፤ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤

16፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ 17፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

በመጨረሻም በምስሉ ትርጓሜ ላይ የጨመርኩት ወይንም የቀነስኩት ካለ ኮመንት ስጡኝ።
አመሰግናለሁ!!!

በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንድምና እህት የሆናችሁ በተለያየ ምክንያት ዛሬ ጉልበት ያጣችሁ ከገባችሁበት መውጣት እስከማይመስል ድረስ ግራ የተጋባችሁ። ከችግሩ ክብደት የተነሣ የእግዚአብሔርን...
01/05/2020

በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንድምና እህት የሆናችሁ በተለያየ ምክንያት ዛሬ ጉልበት ያጣችሁ ከገባችሁበት መውጣት እስከማይመስል ድረስ ግራ የተጋባችሁ። ከችግሩ ክብደት የተነሣ የእግዚአብሔርን መኖር የተጠረጠራችሁ፣ ነገር ግን በዛ ሁኔታም ሆናችሁ የእግዚአብሔርን ማዳን የሚትጠባበቁ!!

አንድ እውነት ልንገራችሁ እሱም የእግዚአብሔር ማስተዋልና እውቀት ነው። እሱም አይመረመርም ፣ ለምንስ እንደዚህ አደረክ የሚል የለውም። እግዚአብሔር በነገር ሁሉ አዋቂ ነው ፣ በብርሃን ብንሄድም ፣ በጨለማ ብሆንም በዚህ ሁሉ የሚሆነውን ሲያደርግ እርሱ ለኛ ይራራልም ያስተምረናል ደግሞም እንዳንጠፋ ይጠነቀቅልናል።
በተለይ እርሱን ለሚወዱትና እንደ አሳቡም ለተጠሩት የሚያደርገውን ሁሉ ለበጎ ነው የሚሠራው። "

እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።"(ሮሜ 8:28)
የእግዚአብሔር ትልቁ ባሕርይ ጨርሶ ይጀምራል እንጂ እንደ ሰው ጀምሮ አይጨርስም። ገና ዓለም ሳይፈጠር በፊትና በእናታችን ማሕጸን ሳንታሰብ እሱ የእኛን ፍጻሜ ያዉቃል። ከእኛ የሚጠበቀው እርሱን መውደድና እንደ አሳቡ መኖር ነው።

እግዚአብሔርን መውደድ ማለት ፈቃዳችንን ለእርሱ መስጠት ማለት ነው። ፈቃዳችንን ለእግዚአብሔር ስንሰጥ እርሱ ስለእኛ ይኖራል። እርሱ ስለእኛ ሲኖር በድካማችን ሁሉ ያግዘናል ፣ ያስተምረናል ፣ ይገስጸናል ፥ የሚረባንን ሁሉ ለይቶ ያሳየናል።

የእግዚአብሔር ቃል እንደምናገረው እግዚአብሔር ያውቀናል፥ ይሰማናል ደግሞም ኃይልና ብርታት ይሰጠናል። ኃይልንና ብርታትን ሲናገኝ እርሱን በመተማመን እንጠባበቃለን።

(ኢሳ ምዕ. 40) 28፤ አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።

29፤ ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። 30፤ ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤

31፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።

በመተማመን ስንጠባበቅ ኃይላችን ይታደሳል ፥ እንወጣለን፥ አንደክምም ደግሞም መሄድ ይሆንልናል።።።።።።።።። አሜን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ወንድማችሁ መስፍን ነኝ።

"23 For Yahweh will pass through to strike the Egyptians; and when he sees the blood on the lintel, and on the two doorp...
22/04/2020

"23 For Yahweh will pass through to strike the Egyptians; and when he sees the blood on the lintel, and on the two doorposts, Yahweh will pass over the door, and will not allow the destroyer to come in to your houses to strike you."
(Exodus 12:23)

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Rock Was Christ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to The Rock Was Christ:

  • Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship?

Share