Tulumu Media

Tulumu Media Tulumu online Trading

08/06/2026

የመጀመሪያ 1 ሚሊዮን ብር በስንት አመት ሰራችሁ?💰🤔

07/06/2026

ኢትዮጵያን ማን ቢመራት ነው እኛ ዜጎቿ የምንስማማው?

የኢራን ሚሳዔል ማዕበል እስራኤል ላይ ። ። ። ። ። ። ። ። ።። ። ።የእስራኤል ጦር በኢራን ሚሳዔሎች ጥቃት እንደደረሰበት አስታወቀ።እስራኤል አዲስ የሚሳዔል ማዕበል ከቴህራን ተተኩሶብኛል...
07/06/2026

የኢራን ሚሳዔል ማዕበል እስራኤል ላይ

። ። ። ። ። ። ። ። ።። ። ።
የእስራኤል ጦር በኢራን ሚሳዔሎች ጥቃት እንደደረሰበት አስታወቀ።

እስራኤል አዲስ የሚሳዔል ማዕበል ከቴህራን ተተኩሶብኛል በሚል ያረጋገጠች ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም ሚሳኤሎች ወደ ግዛቷ እየተመዘገዘጉ መሆኑን አሳውቃለች።

ሁሉንም ሚሳዔሎች አክሽፊያለሁ ያለችው እስራኤል ዜጎች ወደ መጠለያ እንዲገቡ አዛለች።

ኢራን እስራኤል በቤይሩት የሰነዘረችውን ጥቃት ተከትሎ አፀፋዊ ምላሽ ለመስጠት ያደረገችው ወታደራዊ እርምጃ ነው።

የኢራኑ ሁለንተናዊ መሪ ሞጅታበ‍ኣ ኻሚኒ ወታደራዊ አማካሪ ሞህሰን ረዛኢ በሊባኖስ ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት አንታገስም ብለዋል።

የእስራኤል ቀኝ ዘመም አክራሪው የብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ግቪር ቴህራን መቃጠል አለባት በሚል ዝተዋል።

የ ኢራን አብዮታዊ ዘብ ሀይል(አይ አር ጂ ሲ )የእስራኤልን አየር ሀይል ጦር ሰፈር በባሊስቲክ ሚሳዔል ዒላማ ማድረጉንም ይፋ አድረጓል።

እናመሰግናለን 🙏🙏🙏
06/06/2026

እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

ስንት ድመት ይታያቸዋል
05/06/2026

ስንት ድመት ይታያቸዋል

27ኛው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ‼የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ሌሊቱን...
05/06/2026

27ኛው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ‼

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ሌሊቱን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ከ1990 እስከ 1995 ዓ.ም 27ኛው የአዲስ አበባ ከንቲባ በመሆን ያገለገሉት አምባሳደር ዓሊ፣ በትዳር ሕይወታቸው የአራት ልጆች አባት ነበሩ።

የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ዛሬ ከጁምዓ ሶላት በኋላ በዳለቲ ሙስሊሞች መቃብር ሥፍራ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸውና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይፈጸማል።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።

በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ...
05/06/2026

በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ፣ ከሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ኸይረዲን ተዘራ እና ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን የቤተክርስቲያኗ ሕዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

ልዑካን ቡድኑ በምሥራቅ አርሲ በአሰኮ፣ በሺርካ እና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በታጣቂዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ በደረሰው የሕይወት ሕልፈትና በጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን መቃጠል የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገልጸዋል።

መንግሥት የችግሩን ምንጭ አጣርቶ ዘላቂ ሰላም እንዲያሰፍን፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ እና ወንጀለኞች ለሕግ ቀርበው ቅጣታቸውን እንዲያገኙ ጠይቀዋል።

የምሥራቅ አርሲ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕም የተከሰተውን ችግር በቊጥራዊ ማስረጃ አስደግፈው አቅርበዋል።

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ በተፈጠረው አደጋ ማዘናቸውን ገልጸው፣ አስቸኳይ አጣሪ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንና በሪፖርቱ መሠረት እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኃላፊዎችና የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አመረሮች በበኩላቸው ተጨማሪ አደጋን ለመከላከል ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰው፣ አጥፊዎችን ለሕግ ለማቅረብና ቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናንን ለመደገፍ በምታደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ፣ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለመገንባትና መሰል ችግሮች ዳግመኛ እንዳይከሰቱ ለማድረግ ከተጠናከረ ሥራ ጋር በትኩረት እንደሚንቀሳቀሱ አስታውቀዋል።

መረጃው ከኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ነው የመጣው።

ይህች ወጣት ዳኛ በሆለታ ከተማ ፍርድ ቤት ውስጥ ፍርድ እየሰጠች ሳለ ከተከሳሹ በተተኮሰ ጥይት መገደሏ ተሰምቷል !በጣም ያሳዝናል
05/06/2026

ይህች ወጣት ዳኛ በሆለታ ከተማ ፍርድ ቤት ውስጥ ፍርድ እየሰጠች ሳለ ከተከሳሹ በተተኮሰ ጥይት መገደሏ ተሰምቷል !

በጣም ያሳዝናል

የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም የእሳት አደጋ ተነስተዋል የሚመለከተው አፋጣኝ እርምጃ ይዉሰድ
04/06/2026

የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም የእሳት አደጋ ተነስተዋል

የሚመለከተው አፋጣኝ እርምጃ ይዉሰድ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አደነቁ የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ በጋራ ባወጡት መግለጫ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ...
03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ በጋራ ባወጡት መግለጫ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቀዋል።

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለእጩዎች እና ለሲቪል ማኅበራት ለምርጫው ስኬት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም ለአፍሪካ ኅብረት እና ለኢጋድ የምርጫ ታዛቢነት ሚና እውቅና ሰጥተዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tulumu Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Tulumu Media:

Share