መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም, Church, 5 Kilo, Addis Ababa.
(1)

"ዕጣን ይእቲ ማርያም፣ ዕጣን ውእቱ እስመ ዘውስተ ከርሣ ዘይትሜዓዝ እምኩሉ ዕጣን ዘወለደቶ መጽአ ወአድኀነነ"(ማርያም ዕጣን ናት፤ በማኅፀንዋ ያደረው ከተመረጠ ዕጣን ሁሉ የተለየ መዓዛ ያለው...
19/07/2025

"ዕጣን ይእቲ ማርያም፣ ዕጣን ውእቱ እስመ ዘውስተ ከርሣ ዘይትሜዓዝ እምኩሉ ዕጣን ዘወለደቶ መጽአ ወአድኀነነ"
(ማርያም ዕጣን ናት፤ በማኅፀንዋ ያደረው ከተመረጠ ዕጣን ሁሉ የተለየ መዓዛ ያለው ዕጣን ነው፤ የወለደችው መጥቶ አዳነን)

ሥርዓተ ቅዳሴ

ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ“እንኳንስ ሕዝቡ ምድሪቱም  [ኢትዮጵያም]  እንዳትገዛላቸው አውግዣለሁ”           (ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ)                    ...
28/07/2024

ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

“እንኳንስ ሕዝቡ ምድሪቱም [ኢትዮጵያም] እንዳትገዛላቸው አውግዣለሁ” (ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ)

“አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ”
(ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 12 ቀን 1998 ዓ.ም)

“አቡነ ጴጥሮስ የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት”
(MARTYR OF THE MILLENIUM)
(የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (United Nations)

መ/ር ጌታቸው በቀለ
የሃያኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕት የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ለሀገራቸውና ለቤተክርስቲያናቸው ሲሉ ሰማዕት ሆነዋል፡፡ ዘንድሮ በ፳፻፲፮ ዓ.ም የሰማዕቱን ፹፰ኛ ዓመት እናዘክራለን፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስም በቆራጥነት የሚከተለውን መለሱ፡- ‹‹አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ» አሉ፡፡

‹‹ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲመለከት ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእክት አስተላለፉ፡- ‹አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፤ እንጂ በጎ ለመሥራት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ፡፡ ነጻነታችሁ ከሚረክስ ሙታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን፡፡ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን› ብለው አወገዙ፡፡

ቀጥሎም ብፁዕነታቸው በፍጥነት ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለ እርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ፡፡ ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣሊያ የእጅ ሰላምታ ዓይነት እጁን እንዲያነሳ ታዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ፡፡ በዚህን ጊዜ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር፡፡ የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣሊያዊው ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ታላቅ ፍርሃም በፊቱ ላይ ይታይ ነበር፡፡ የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኳቸው፡፡

የሀገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒያ እውነተኛ ጳጳስ እንዲገደሉ ሲወሰዱ ጥይት አልፎ ሌላ ሰው እንዳይመታ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡፡ ሩቅ ባለመሄድ ከመካነ ፍትሑ ዐሥር ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወሰዱ፡፡ ከገዳዮቹም አንዱ ‹ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉን?› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ‹ይህ ያንተ ሥራ ነው› ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ፡፡

ከመግደያውም ቦታ እንደደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ አድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ፡፡ ከዚያም በኋላ ስምንት ወታደሮች በስተ ጀመርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ፣ ወዲያው አዛዡ ‹ተኩስ!› በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቱዋቸው፡፡ ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ፡፡ መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ፡፡ ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ፡፡ ከዚያም በኋላ አንድ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው፡፡ ብፁዕነታቸው የተገደሉበት ቦታ መሐል አዲስ አበባ ላይ ዛሬ መታሰቢያ ሐውልታቸው ቆሞ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው›› በማለት የጋዜጣ ወኪልና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛው ፖጃሌ ስለ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ‹‹አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ?›› ሲል በወቅቱ አባታችን ሰማዕትነትን ሲቀበሉ በቦታው ላይ በአካል በመገኘት ሁኔታውን ይከታተሉ የነበሩትን ሙሴ ፓይላክን ጠይቋቸው እርሳቸውውም የሚከተለውን ተናረዋል፡- ‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት፡፡ ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡ ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ፡፡ ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹በዚህ ቄስ መገደልኮ ሕዝቡ ተደስቷል› አለኝ፡፡ ‹እንዴት?› ብለው ‹አላየህም ሲያጨበጭብ?› አለኝ፡፡ ‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል› አልኩት፡፡ ‹እንዴት?› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡ ‹ከዚህ በኋላ የሆነው ቢሆን እኔ ትልቅ ማስታወሻ አግኝቻለሁ› ብሎ አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረውን መስቀልና መጽሐፍ ቅዱስ የኪስ ሰዓታቸውንም ጭምር አሳየኝ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ መሐል ለመሐል በጥይት ተበስቷል፡፡ መስቀሉም ልክ በመሐሉ ላይ ጥይት በስቶት ወጥቷል፡፡ የኪስ ሰዓታቸውንም እንዳየሁት እንዲሁ ጥይት በስቶታል›› ብለው በወቅቱ የተመለከቱትን መስክረዋል፡፡

የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል በሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ሰማዕቱን አቡነ ጴጥሮስን ገድሎ አስክሬናቸው አደባባይ ላይ ጥሎ ከዋለ በኋላ ቀብራቸው በምሥጢር መፈጸሙን አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡

ሰማያዊ ክብርን የሚያስገኝ አኩሪ ገድል በመፈጸም የቤተክርስቲያን ታላቅ አለኝታ አባትና መሪ የሆኑት የዘመናችንን ታላቅ ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ትውልዱ ሊያስባቸውና ሊዘክራቸው ይገባል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (united nations) አቡነ ዼጥሮስን "የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት" ወይም በፈረንጅኛው አፍ (MARTYR OF THE MILLENIUM) በሚል መጠሪያ ሰይሟቸዋል፡፡ ላልተነገረላቸውና ላልተዘመረላቸው ለእኚህ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያናችን ድንቅ አባት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ፲፪ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም እኚህን ሰማዕት ‹‹አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ›› ተብለው እንዲጠሩ ወስኗል፡፡ በስማቸውም መቅደስ እንዲታነጽ ፈቅዶ በመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ መሠረት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጻድቁ በተወለዱበት ሥፍራ መታሰቢያ አቁማላቸዋለች፡፡

ጠላት ድል ተደርጎ ሀገራችን ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የአባታችንን የሰማዕቱን አኩሪ ታሪክ ትውልድ ሲያዘክራቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት አሳሳቢነት ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ.ም በአዲስ አበባ መሐል ከተማ ላይ ሐውልት ቆሞላቸዋል፡፡

የሰማዕቱ የብፁዕ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ በረከት ይደርብን። አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቤ መጻሕፍት
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት፡፡ ትንሣኤ መጽሔት፡፡ ቁጥር 58፡፡ 1978 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን፡፡ ሐመር መጽሔት ግንቦት/ሰኔ ፲፱፻፺፮ ዓ.ም.
መርሻ አለኸኝ (ዶ/ር) (1996)፡፡ ዜና ጳጳሳት፡፡ አዲስ አበባ፡፡ ሜጋ ማተሚያ ቤት፡፡
ዜና አቡነ ጴጥሮስ መጽሔት

+++++++++++++++++++++++

የገዳማችንን መልእክቶች በቋሚነት ለማግኘት በሚከተሉት ልሳኖቻችን ይከታተሉን።

✅ ለቴሌግራም:
https://t.me/menberepatriarch

✅ ለዩቲዩብ:
www.youtube.com/

✅ ለፌስቡክ
https://www.facebook.com/menberepatriarch

📍 Addis Ababa, Ethiopia
ARADA S.S. 09 - p.o.b. 80309
Patriarchate Head Office - EOTC

28/07/2024
28/07/2024

እንኳን ለእመቤታችን ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !“እግዚኦ ሚ በዝኁ እለ ይሣቅዩኒ፦አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ ! ” (መዝ. 3፡1)         አባታዊ የማጽናኛ መልእክት በጎፋ...
25/07/2024

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

“እግዚኦ ሚ በዝኁ እለ ይሣቅዩኒ፦አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ ! ” (መዝ. 3፡1)

አባታዊ የማጽናኛ መልእክት

በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ እጅግ ብዙ የሚሆኑ ወገኖቻችን በመሞታቸው ታላቅ ኀዘን ተሰምቶናል ። ምንም እንኳ የመከራ ድሀ ባንሆንም ይህ መከራ ለነጋሪውም ለሰሚውም ከባድ መሆኑን እንገነዘባለን ።

ይሁን እንጂ ጭንቀታችን ብዙ ቢሆንም እግዚአብሔር መልካም የምንሰማበትን ዘመን እንደሚያመጣ ተስፋ እናደርጋለን ።

በተለይም ደግሞ እኛ ክርስቲያኖች በወገኖቻችን መጎዳት ብናዝንም በትንሣኤ ሙታን ስለምናምን የምጽናና በመሆኑ የሞቱት ልጆቻችን ዕረፍተ ነፍስ እንዲያገኙ እየጸለይን፤ የመከራው ገፈት ቀማሽ ለሆኑት የአካባቢው ማኅበረሰብእ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ሁሉም አቅሙ በፈቀደው መጠን እንዲደርስላቸው ስንል አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ለቤተሰቦቻቸውና ለሕዝቡ መጽናናትን ይስጥልን፤ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም.
ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ

++++++++++++++++++++++++

የገዳማችንን መልእክቶች በቋሚነት ለማግኘት በሚከተሉት ልሳኖቻችን ይከታተሉን።

✅ ለቴሌግራም:
https://t.me/menberepatriarch

✅ ለዩቲዩብ:
www.youtube.com/

✅ ለፌስቡክ
https://www.facebook.com/menberepatriarch

📍 Addis Ababa, Ethiopia
ARADA S.S. 09 - p.o.b. 80309
Patriarchate Head Office - EOTC

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የብዙ ወገኖች ሕይወታቸው በማለፉ ጥልቅ ኀዘናቸውን ገለጹ።"ትግሁ እንከ እስመ ኢተአምሩ በዓይ ሰዓት ይመጽእ እግዚእክሙ ፤ጌ...
24/07/2024

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የብዙ ወገኖች ሕይወታቸው በማለፉ ጥልቅ ኀዘናቸውን ገለጹ።

"ትግሁ እንከ እስመ ኢተአምሩ በዓይ ሰዓት ይመጽእ እግዚእክሙ ፤ጌታችሁ በማናቸውም ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ኑሩ።ማቴ ፳፬፥፵፪"

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ድንገት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰው አሰቃቂና አሳዛኝ አደጋ ታላቅ ሀዘን ተሰምቶናል።

በመሆኑም የድንገተኛ አደጋው ተጎጂ ለሆኑ ወገኖቻችን እግዚአብሔር አምላክ በወዲያኛው ዓለም ዕረፍተ ነፍስን፣
ለተጎጂ ቤተሰቦች፣ ለአካባቢው ነዋሪዎችና ለመላው ኢትዮጵያውያንም መጽናናትን እንዲሰጥልን በመለመን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን።

"አምላካችን እግዚአብሔር ለአገራችንና
ለዓለሙ ሁሉ ሰላምን ይስጥልን!"

አባ አብርሃም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና
ሥራ አስኪያጅ፣የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም
አህጉረስብከት ሊቀ ጳጳስ

©የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

++++++++++++++++++++++++

የገዳማችንን መልእክቶች በቋሚነት ለማግኘት በሚከተሉት ልሳኖቻችን ይከታተሉን።

✅ ለቴሌግራም:
https://t.me/menberepatriarch

✅ ለዩቲዩብ:
www.youtube.com/

✅ ለፌስቡክ
https://www.facebook.com/menberepatriarch

📍 Addis Ababa, Ethiopia
ARADA S.S. 09 - p.o.b. 80309
Patriarchate Head Office - EOTC

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜንከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ  በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕ...
12/07/2024

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ
የተሰጠ መግለጫ

‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ
በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን፣ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ አበክሮ ይነግረናል፡፡
በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡
ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››

ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የፎቶ ማስታወሻ:ፎቶ: ዲ/ን ሚሊዮን ወ/አማኑኤል
29/06/2024

የፎቶ ማስታወሻ:
ፎቶ: ዲ/ን ሚሊዮን ወ/አማኑኤል

እንኳን ለእመቤታችን ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!
27/06/2024

እንኳን ለእመቤታችን ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!

06/06/2024

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤

በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤

የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡

ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

Address

5 Kilo
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም:

Share

Category