Muslim Brothers

Muslim Brothers 🇵🇸🇵🇸 Genocide was committed against Palestine 🇵🇸🇵🇸

11/03/2026

ለይለቱል ቀድር እና ምልክቶቿ
⏬⏬ ➣➣➣➣ ⏬⏬
ስለለይለቱል ቀድር አዘውትረው የማይሰሙ ሃዲሶች እና ማረጋገጫ ምልክቶች

🔀ስለ ለይለቱል ቀድር የተረጋገጡ ሃዲሶች
እና ማረጋገጫ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው :– አንብበው ሲጨርሱ ሼር
ያድርጉ

⏩“ለይለቱልቀድር” ማለት ምን ማለት ነው? ከዑለማዎች አንደበት:

💫1.👉🏼 “ትልቅ ቀድር ወይም ደረጃ ያላት ለሊት ማለት ነው” ያሉ አሉ፡፡

💫2.👉🏼 “ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ማለት
ነው” ያሉም አሉ፡፡

የለይለቱልቀድር ደረጃዎች

💫1.👉🏼 ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች፡፡ ጌታችን እንዲህ ብሏል፡- “እኛ (ቁርኣኑን)
በለይለተልቀድር አወረድነው፡፡” [አልቀድር፡ 1]

💫2.👉🏼 በሷ ላይ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች በተለየ ምንዳው የበለጠ ነው፡፡

ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ለይለተልቀድር ከሺህ ወር በላጭ ናት፡፡” [አልቀድር፡
3]

💫3.👉🏼 በሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ፡፡

ጌታችን
እንዲህ ይላል፡- “በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው
ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡” [አልቀድር፡ 4]

💫4.👉🏼 ለሊቷ ዒባዳህ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት፡፡

ጌታችን እንዲህ
ብሏል፡- “እርሷ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡” [አልቀድር፡ 5]

💫5.👉🏼 የተባረከች ለሊት ናት፡፡

ጌታችን እንዲህ ብሏል፡- “እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች
ለሊት ውስጥ አወረድነው፡፡”
[አድዱኻን፡ 3]

💫6.👉🏼 በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜ እና የሲሳይ
ልኬታዎችን ይፅፋል፡፡

ጌታችን እንዲህ ብሏል፡- “በውስጧ የተወሰነው ነገር
ሁሉ ይልለያል፡፡”
[አድዱኻን፡ 4]

💫7.👉🏼 በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት
የበዛ ነው፡፡

[አልባኒ ሐሰን ብለውታል]

💫8.👉🏼 ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት ነች፡፡

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-
“ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል፡፡”

[ቡኻሪና ሙስሊም]

ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን
ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል፡፡

አልኢማም ኢብኑልቀይም
ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“ለይለተልቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እሷን ለማገኘት
ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር፡፡

በ(ረመዳን) አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ
ምን ነካህ? (እንዴት እዘናጋለሁ?!)” [በዳኢዑልፈዋኢድ፡ 1/55]

ለይለቱልቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?

ለይለተልቀድር የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው፡፡

ከረመዳንም ደግሞ
በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ነው፡፡

ይህንንም የሚያስረዳን ነብዩ ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ማለታቸው ነው፡- “ይቺን ለሊት እየፈለግኩ
የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፡፡

ከዚያም መካከለኛውን አስር
ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፡፡

ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ ‘እሷ በርግጥም
የመጨረሻው አስር ላይ ናት’ ተባለኝ” ማለታቸው ነው፡፡

ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ይገባል፡፡

ነብዩ
ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡- “በሱ (በረመዳን)
ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች፡፡

የሷን ኸይር የተነፈገ
በእርግጥም (ትልቅ ነገር) ተነፍጓል፡፡”

[አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]

መቼ እንፈልጋት?
ባይሆን እጅግ የምትገመተዋ ለሊት 27ኛዋ ለሊት ናት፡፡

ለዚህም ነብዩ ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ማለታቸው ማስረጃ መሆን ይችላል፡-
“ለይለተልቀድርን በ27ኛው ለሊት ውስጥ ፈልጓት፡፡” [አልባኒ ሶሒሕ
ብለውታል]

ላሂቅ ቢን ሐሚድ እና ዐክረማ እንዲህ ብለዋል፣
ዑመር (ረ ዐ) እንዲህ ብለዋል፣ ” ከናንተ ማነው ለይለቱል ቀድር መች
እንደሆነ የሚያውቅ?”

እነሱም መልሰው እንዲህ አሉ፣
” ነብዩ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምተናል ‘ እሷ (ለይለቱል ቀድር)

በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ናት፣ ሰባት ሲያልፍ፣ አልያም ሰባት ሲቀር’
አሉ።

ይህም 23ኛው ለሊት ወይም 27ኛው ለሊት”። ሙስነድ አህመድ ቁ – 2543
አብደላህ ኢብኑ ዐባስ እንዲህ ብለዋል ” አንድ ሰው ወደ ነብያችን (ሰ ዐ ወ)
(በረመዳን)
መጥቶ እንዲህ አላቸው ‘ የ አላህ ነብይ ሆይ እኔ ታማሚ ሽማግሌ ነኝ አላህ
እንዲወፍቀኝ በ
አንዷ ለሊት እዘዘኝ’ አሉ።

ነብያችንም (ሰ ዐ ወ) ‘ሐያ ሰባተኛዋን ለሊት ያዝ’ አሉዋቸው ።

ሙስነድ አህመድ ቁ –2149
ይሁን እንጂ “ለይለተልቀድርን በ23ኛዋ ለሊት ፈልጓት” ማለታቸው እንዲሁም
“ለይለተልቀድርን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) ፈልጓት፡፡

ከተረታችሁ
በመጨረሻዎቹ 7 ላይ አትረቱ” ማለታቸው ለይለተልቀድር ሁሌ በአንድ ለሊት
ላይ እንደማትገደብ ያስረዳል፡፡

በተለይ ደግሞ በዊትሮቹ (21፣ 23፣ 25፣ 27፣
29) የመሆን እድሏ ሰፊ ነው፡፡

ይህን አስመልክተው መልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ
ብለዋል፡-
“ለይለተልቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) በዊትሮቹ
ፈልጓት፡፡”

[ቡኻሪናሙስሊም]

ይህ ማለት ግን ከናካቴው በሸፍዕ ለሊቶችም ማለትም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣
30) አትሆንም ለማለት አይደለም፡፡

ይህንንም ከሚያስረዱን ማስረጃዎች
አንዱ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ለይለተልቀድርን በረመዳን የመጨረሻዋ
ለሊት ላይ ፈልጓት” ማለታቸው ነው፡፡

[አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል] ወሩ 30
ቀናት ከሆነ የመጨረሻው ለሊት ዊትር ቁጥር እንዳልሆነች ይስተዋል፡፡

ከዚህም
ባለፈ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የሚፈልጋት ሰው በመጨረሻዎቹ አስር
ይፈልጋት” በሌላ ዘገባ ደግሞ “የሚፈልጋት ሰው በመጨረሻዎቹ ሰባት ለሊቶች
ይፈልጋት” ማለታቸው ይህን ያስረዳል፡፡

[ቡኻሪና ሙስሊም]

ይህ አነጋገራቸው ዊትር ያልሆኑት ለሊቶች ተገንጥለው እንደማይወጡ
ያሳያል፡፡

በተለይ ደግሞ በአንዳንድ ዘገባ ላይ እንደመጣው ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ
ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተልቀድር ከረመዳን በመጨረሻው አስር
ፈልጓት፡፡

9 ሲቀር፤ 7 ሲቀር፤ 5 ሲቀር፡፡” [ቡኻሪ]
ወሩ 29 ቀን ከሆነ 9፣ 7፣ 5 ሲቀር ዊትር የሚሆኑት ከመጨረሻ ወደ ኋላ
ሲቆጠር ነው፡፡

ከመጀመሪያ ለሚቆጥር ግን ዊትር ሳይሆን ሸፍዕ ቁጥር ነው
የሚሆኑት፡፡

ይህም ሸፍዕ ለሊቶችም ላይ የመሆን እድል እንዳለ ያስረዳናል፡፡

ቢሆንም ግን
“ከ(መጨረሻው አስር) በዊትሩ ፈልጓት” ስላሉ ይበልጥ የሚተኮረው በዊትሩ
ሊሆን ይገባል፡፡

በለይለተልቀድር ጊዜ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
ዒባዳህ ማብዛት፡፡

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ለይለተልቀድር አምኖ እና
አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል” ይላሉ፡፡

[ቡኻሪና ሙስሊም]

እናም በዚች ለሊት ታላቅነትና መደንገግ አምኖ፣ ከዚያም ለመታየት ለጉራና
መሰል አላፊ ኒያ ሳይሆን አጅሩን ከአላህ በማሰብ እንደሶላት፣ ዱዓእ፣ ቁርኣን
መቅራት፣.. የፈፀመ ሰው ወንጀሉ ይታበስለታል ማለት ነው፡፡

ምልክቶቿ

💫1.👉🏼 “በዚያን ቀን ማለዳ ፀሀይዋ ነጭ ሆና ጨረር ሳይኖራት

ትወጣለች፡፡” [ሙስሊም]

ኢብኑ ዐባስ ረ ዐ እንዲህ ብለዋል ፣
ነብዩ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ አሉ ‘ ለይለቱል ቀድር ምሽቷ ቀለል ያለ እና ሠላማዊ
ነው፣

ማለዳውን ፀሐይ ደካማ ብርሃን ያላት ፣ የማትሞቅ የማትበርድ እና ና ቀይ
መልክ ኖሯት
ታነጋለች’ ብለዋል።

( ሰሂህ አልጃሚዕ ቁ – 5475)

እንዲሁም በሌላ ሐዲስ ፀሐይዋ ከፍ እስከምትል ብርሃኗ ደብዛዛ የነሃስ
አይነት መልክ
ይኖረዋል ብለዋል።

አቡ ሁረይራ(ረዐ) እንዲህ አሉ:–
ነብያችን (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል ‘ ለይለቱል ቀድር 27ኛ ወይም 29ኛ
ለሊት ነች፣
በዚያች ምሽት ወደ ምድር የሚወርዱ መላኢካዎች ቁጥር ካለው የድንጋይ
ቁጥር ይበልጣል’ ብለዋል ።

( ሙስነድ አህመድ ቁ – 10734)
በዚያን ለሊት ዝናብ ሊዘንብ ይችላል፡፡
[ቡኻሪና ሙስሊም]

ቀጣዩ ቀን አየሩ ሞቃትም ብርዳማም ሳይሆን የተስተካከለ ይሆናል፡፡

ፀሀይዋም ደካማና ቀይ ትሆናለች፡፡
[ሶሒሑልጃሚዕ]

ሸይኹልአልባኒ ረሒመሁላህ እንደሚሉት እነዚህ ምልክቶች አንፃራዊ ናቸው፡፡

በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ሊወሰን ይችላል፡፡

ስለሆነም በትክክል
ለይለተልቀድር በተከሰተበት ጊዜም እነዚህን ምልክቶች ብዙ የማያያቸው
ሊኖር ይችላል፡፡

ለይለተልቀድር ለሰጋጆች ብቻ አይደለችም!!

የወር አበባ ደም ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች… የዚች ለሊት
ትሩፋት አያልፋቸውም፡፡

ማስረጃው ጠቅላይ ነውና፡፡

ባይሆን በዚክርና መሰል ዒባዳዎች ሊበራቱ ይገባል፡፡

ይህን የሚጠቁም
ሀሳብም ከመልካም ሰለፎቻችን ተገኝቷል፡፡

በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛት ጥሩ
ነው፡፡

እንዳውም ሱፍያኑ አሥሠውሪ ረሒመሁላህ “በለሊቷ ከሶላት ይልቅ
ዱዓእ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው” ይላሉ፡፡

ለይለተልቀድር በአይን ትታያለች?
ለይለተልቀድር አላህ በአንዳንድ ባሮቹ ቀልብ ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ
የመረጋጋት ወይም የመለየት ስሜት ከማሳደሩ ውጭ በአይን የሚታይ ነገር
አይደለም፡፡

የሚታየው ምልክቶቿ እንጂ እራሷ አይደለችም፡፡

ነገር ግን ሰዎች
ሊጠመዱ የሚገባቸውም በዒባዳ፣ በዚክር፣ በሶላት፣ በዱዓእ፣ በቁርኣን እንጂ
በወሬ መሆን የለበትም፡፡

ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ለሊቱ ለይለተልቀድር መሆኑን ባያውቁ
እንኳን ትሩፋቷን አያጡም፡፡

ለይለተልቀድር እንደሆነ ውስጡ ያደረ ሰው ምን ያድርግ?

ማጠቃለያ: –
〰〰〰

– ለይለቱል ቀድር በረመዳን የመጨረሻ 10 ቀናቶች በ 21, 23, 25, 27 እና
29 መሆኑን

ሃዲሶች ያረጋግጣሉ።

– አንድ ሰው ሁሌም በትጋት አስካልተጠባበቀ ከነዚህ ቀናቶች በየትኛው
ሊሆን እንደሚችል
እርግጠኛ መሆን አይቻልም ።

– ከምልክቶቹ በሐዲስ በተደጋጋሚ የተረጋገጠው የዚያን እለት ማለዳ ፀሐይ
ስትወጣ ቀይ መልክ ያላትና ብርሃኗ ደብዛዛ የነሃስ መልክ ይኖረዋል፣
አስኪረፍድ ድረስ የሚለው በተደጋጋሚ ተገልጿል ፣
ለምሳሌ 27ኛው ለሊት ከሆነች የረመዳን 26 ፀሐይ ማለትነው።

አላህ ይቺን ታላቅ ለሊት ያድለን፡፡

የምንጠቀምባትም ያድርገን፡፡
ኣሚን፡፡

መልካም ሆኖ ካገኙት ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡

ሌሎችንም ተጠቃሚ
ያድርጉ፡፡

ወላሁ አዕለም
አላህ ሁላችንንም ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን

18/02/2026

✋አሰላሙ አሌኩም ወረሐመቱላ ወበረካቱሁ
🕋ውዶቼ እንኮን አደረሳችው🕋
🕌•••┈┈•••❅♡❅•••┈┈•••🕌
🕌ረመዳን ሲመጣ🕌
“እንኳን አላህ 14 47 ለረመዳን ፆም በሰላም አደረስን” በማለት ምስጋና
እናቀርባለን⁉
👉🏼ይህን የተከበረ የረመዳን ወር ሳንጠቀምበት እንዳያመልጠንና እንዳንከስር
የሚረዱንን
🌴👉🏼100 ምክሮች እንደሚቀጥለው እናቀርባለን፡-
ኢማናዊ ምክሮች
┈┈•••❅♡❅•••┈┈
🕌1👉🏼ይህ ወር ራስህን የምትመረምርበት፣ ሥራህን የምትገመግምበትና
ሕይዎትህን
የምታስተካክልበት ወር እንዲሆን ተግተህ ተንቀሳቀስ፤
‼

🕌2👉🏼ከሰሐባዎችና ከደጋግ ሰለፎች በዚህ ወር ለአንተ አርዓያ የሚሆንህን
ወስነህ ያዝ፤
‼

🕌3👉🏼የረመዳንን ጨረቃ ስታይ (ረመዳን መግባቱን ስታረጋግጥ) “ያ አላህ ይህን
ጭረቃ
በበረካ፣ በኢማን፣ በሰላምና በኢስላም በኛ ላይ አዝልቀው፤ የኔም የአንተም
ጌታ አላህ
ነው፤” 📖(አህመድና ቲርሚዚይ ዘግበውቴል)።

🕌4👉🏼ጌታህን በማምለክ ቀልብህ እንዲረጋጋና ጉዳይህንና ችግርህን ለፈጣሪህ
ለማቅረብ እንድትችል ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ መግባትን ራስህን
አለማምድ፤
‼

🕌5👉🏼የመጀመሪያውን ሶፍ ለማግኘት ታገል፡- “ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያው
ሶፍ
የሚገኘውን ደረጃ ቢያውቁ ኖሮ ቦታውን ለማግኘት በመካከላቸው እጣ
እስከመጣል
ይደርሱ ነበር፤”📖 (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌6👉🏼ከሶላት በኋላና በተመረጡ ወቅቶች፤ በሱሑር ሰዓት፣ ከአስር ሶላት በኋላ፣
ከመግሪብ
ሶላት በፊትና በማፍጠሪያ ጊዜ ዚክር፣ኢስቲግፋርና ዱዓ አብዛ “ፆመኛ
በሚያፈጥርበት
ጊዜ የማትመለስ ዱዓ አለችው፤” (ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል)።
🕌7👉🏼በየቀኑ 12 ረከዓ ትርፍ (ሱና) ሶላቶችን ጠብቀህ ስገድ፡- “ማንኛውም
ሙስሊም
የአላህ ባሪያ በየቀኑ ከፈርድ ሶላቶች ውጭ 12 ረከዓ ትርፍ ሶላቶችን ለአላህ
ብሎ
አይሰግድም፤ አላህ (ሱ.ወ) በጀነት ውስጥ ቤት የሚገነባለት ቢሆን
እንጂ፤” 📖(ሙስሊም
ዘግበውታል)።

🕌8👉🏼የተራዊህን ሶላት ሙሉውን በጀመዓ ስገድ፡- “ኢማሙ አስከሚጨርስ አብሮ
የሰገደ
ሌሊቱን ሙሉ እንደሰገደ ይጻፍለታል።”📖 (አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል)።

🕌9👉🏼ከፈጅር ቀደም ብለህ በየቀኑ የምትሰግዳቸው ሁለት ረከዓዎች እንኳ
ይኑሩህ፤
ከአላህ ጋር በመንሾካሾክህ (ሙናጃ) እርካታ የምታገኝበት ሰዐት ነውና
በጥብቅ
ለምነው።‼

🕌10👉🏼ውዱእ ካደረግክ በኋላ ሁሉ ሁለት ረከዓ ስገድ፡- “ማንኛውም ሰው
ውዱኡን
በትክክል አድርጎ በቀልቡም በፊቱም ወደ አላህ ዞሮ ሁለት ረካአ አይሰግድም
ጀነት ለሱ
የተገባቸው ቢሆን እንጂ፤” 📖(ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌11👉🏼ሁለት ረከዓ የዱሃ (የረፋድ ሰዐት) ሶላት ስገድ፡- “ማንኛችሁም በሰውነት
መገጣጠሚያዎቹ ቁጥር ሰደቃ (ምፅዋት) ኖሮበት ያድራል፤ ሱብሀነላህ ማለት
ሰደቃ
ነው፤ አልሐምዱሊላህ ማለት ሰደቃ ነው፤ ላኢላሃኢለላህ ማለት ሰደቃ ነው፤
አላሁ አክበር
ማለት ሰደቃ ነው፤ በመልካም ነገር ማዘዝ ሰደቃ ነው፤ ከመጥፎ ነገር
መከልከል ሰደቃ
ነው፤ ይህን ሁሉ ሁለት ረከዓ የዱሓ ሶላትን መስገድ ብቻ
ይተካዋል።”
📖(ሙስሊም
ዘግበውታል)።

🕌12👉🏼የተወሰኑ ትርፍ ሶላቶችን በቤትህ ውስጥ ስገድ፡- “ከሶላታችሁ ከፊሉን
በቤታችሁ
ውስጥ አድርጉ፤ ቤታችሁን እንደ መቃበር አታድርጓት።”
📖(ቡኻሪ ዘግበውታል)።

🕌13👉🏼ጌታህን የምትማፀንበትና በፊቱ የምታለቅስበት ጊዜ ይኑርህ! ይህ ቀልብህ
እንዲስተካከል ጠቃሚ ነገር ነውና።
‼

🕌14👉🏼ሱጁድ አብዛ፡- “አንድ ባሪያ የበለጥ ከጌታው የሚቀርበው ሱጁድ ላይ
በሚሆንበት
ጊዜ ነው፤ በሱም ውስጥ ዱዓ አብዙ።”
📖(ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌15👉🏼የሱብሂ ሶላትን ከሰገድክ በኋላ በቦታህ ተቀምጠህ አላህን አውሳ፤
“ፈጅርን ሰግዶ
ፀሐይ እስከምትወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠና ከዚያም ሁለት ረከዓ
የሰገደ ሰው
ሙሉ የሐጅና ዑምራ ምንዳ ያገኛል።” ነቢያችን 💞(ሰ.ዐ.ወ) “ሙሉ፣ ሙሉ፣
ሙሉ በማለት
ሦስት ጊዜ ደጋግመው ተናግረዋል።”
📖(ቲርሚዚይ ዘግበውታል)።

🕌16👉🏼የሶላት ሲጠናቀቅ የሚባሉ ዚክሮችን በትኩረት አከናውን “ከሶላት በኋላ
ሰላሳ ሦስት
ጊዜ አላህን ያጠራ (ሱብሐነላህ ያለ)፣ ሰላሳ ሦስት ጊዜ አላህን ያመሰገነ
(አልሐምዱ
ሊላህ ያለ)፣ ሰላሳ ሦስት ጊዜ አላህን ያላቀ (አላሁ አክበር ያለ)፣ ይህ ዘጠና
ዘጠኝ ነው፤
ከዚያ ላኢላሀ ኢለላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ
ወሁወ ዓላ
ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ንግስናም
ምስጋናም ለሱው
ብቻ ነው፤ እሱም በሁሉም ነገር ቻይ ነው)፤ ያለ ወንጀሉ የባህር ማዕበል
ቢያክል እንኳ
ይማርለታል።”
📖( ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌17👉🏼የአላህን ፍጡራን ለማስተዋልና ለመገንዘብ ልዩ ጊዜ ስጥ፤ ምክንያቱም
ተፈኩር
(ማስተንተን) ቀልብ የአላህን ታላቅነት እንዲያውቅና በአላህ ላይ ያለው
እምነት
እንዲጨምር ያደርጋል፤ አላህን እንዲወድና በአላህ ላይ እንዲንጠለጠል
እንዲሁም
ከአላህ እርዳታ ለማግኘትም ይረዳል፤
‼

🕌18👉🏼በመስጂድ ውስጥ የሚሰጡ የቁርኣን፣ የሀዲስ፣ የፊቅህና የሌሎችም
እውቀት
አይነቶችን ጠብቀህ ተከታተል።
‼

🕌19👉🏼በታናናሽ ወንድሞችህን እህቶችህ ክፍል ውስጥ አንዳንድ ዐረፍተ
ነገሮችና
ሐዲሶችን ለጥፍ፤ ለምሳሌ፡- “ረመዳንን አምኖና ምንዳውን አስቦ የፆመ
ያለፈው ወንጀሉ
ይማርለታል።”
‼

🕌20👉🏼የፍጡር ዱዓን አትዘንጋ፡- “ዘሀበ ዞመእ፣ ወብተለቲል ዑሩቅ፣ ወሰበተል
አጅር
ኢንሻአላህ (ጥሙ ተወገደ፣ ደም ሥሮች ረጠቡ፣ ምንዳው ተረጋገጠ
ኢንሻአላህ)”
📖(አቡ
ዳውድ ዘግበውታል)።

🕌21👉🏼ረመዳን የዱዓ ወር ነውና በአጠቃላይ ዱዓ አብዛ፡- “ባሮቼም ከእኔ
በጠየቁህ
ጊዜ፡- እኔ ቅርብ ነኝ። የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ። ስለዚህ
ለኔ ይታዘዙ፤
በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና።”
📖(አልበቀራ 2፤ 186)

🕌22👉🏼በነቢያችን 💞(ሰ.ዐ.ወ)ላይ ጁሙዓ ቀን ሰለዋትን አብዛ፤ “በኔ
ላይ አንድ
ሶለዋት ያወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድበታል።” 📖(ሙስሊም
ዘግበውታል)።

🕌23👉🏼ከአንድ ቦታ ስትንቀሳቀስ የሚደረገውን ዱዓ (ከፋረተል መጅሊስ)
ጠብቀህ አድርግ
“አንድ ቦታ የተቀመጠና ከመነሳቱ በፊት ሱብሐነከላሁመ ወቢሐምዲከ፣
አሽሀዱ አን
ላኢላሃ ኢላ አንተ፣ አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይከ (ጌታዬ ከምስጋና ጋር ጥራት
ይገባህ፣
ከአንተ በስተቀር አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ ይቅርታ በመጠየቅ ወደ አንተ
ተመልሻለሁ) ያለ ሰው በዚያ ቦታ ያለውን ወንጀል አላህ ይምርለታል።”
📖 (አቡ
ዳውድ
ዘግበውታል)።

🕌24👉🏼አንድ ወንጀል ከሰራህ ውዱእ አድርግና ሁለት ረከዓ ስገድ፡- “ማንኛውም
ሰው
ወንጀል ከሰራ በኋላ በትክክል ውዱእ አድርጎ ሁለት ረከዓ ሰግዶ ከአላህ
ማህርታን
አይጠይቅም፤ አላህ የማረው ቢሆን እንጂ።”
📖 (አቡ ዳውድ ዘግበውታል)።

🕌25👉🏼ከቻልክ በረመዳን ዑምራ ለማድረግ ሞክር፡- “በረመዳን ዑምራ ከሐጅ
ይስተካከላል፤ ወይም ከኔ ጋር እንደተሰራ ሐጅ ይቆጠራል።” 📖(ሙስሊም
ዘግበውታል)።

•••ዳዕዋዊ ምክሮች•••
┈┈❅💞🕋💞❅┈┈
🕌26👉🏼የአነጋገር ዘዴህን አድስ፤ ተስማሚ ጉዳዮችን ምረጥ።
‼

🕌27👉🏼በመሰጅድ የሚገኘውን የማስታወቂያ ሰሌዳና የሚለጠፉ መጣጥፎች፣
ፖስተሮችና
ሌሎች ጠቃሚ ፅሁፎች አሻሽለህ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ አድርግ።
‼

🕌28👉🏼በየሳምንቱ በመስጂዱ ተጠቃሚዎች መካከል ውድድር አዘጋጅና ከቻልክ
ከጁመዓ
ሶላት በኋላ ሽልማት ለመስጠት ሞክር።
‼

🕌29👉🏼የተለያዩ ፋንፍሊቶች /በራሪ ወረቀቶች/፣ ካሴቶች በመስጅድ፣ በሥራ
ቦታና በሠፈር
ለተጠቃሚዎች አዳርስ፤ አለያም ይህንን በመስራት ለሚታወቁ ማህበራት
በመስጠት
ለፈላጊዎች እንዲደርስ አድርግ።
‼

🕌30👉🏼ከበጎ አድራጎት ማህበራት ጋር በመተባበር የኢፍጧር ፕሮግራሞችን
በመጠቀም
ወደ አላህ ጥሪ ለማድረግ ሞክር።
‼

🕌31👉🏼ለመስጀዱ ሰዎች አንድ ቀን እንኳ ቢሆን የኢፍጧር ፕሮግራም አዘጋጀተህ
ትውውቅ በማድረግና ግንኙነታችሁን እንዲጠናከር አድርግ።
‼

🕌32👉🏼ጠቅላላውን የነቢያችንን 💞(ሰ.ዐ.ወ) አዳብ ለሰዎች አስተምር፤ በተለይም
የፆም
ሥነ-ሥርዓቶችን ለምሳሌ ፍጡርን ማቻኮል፤ በቴምር ወይም በውሃ ማፍጠርና
የመሳሰሉትን።
‼

🕌33👉🏼የሠፈሩን ድሃዎች ለይተህ በማወቅ በሚቻልህ መጠን በገንዘብና
በማህበራዊ
ጉዳዮች ተባበራቸው።
‼

🕌34👉🏼ሶላትን ጠብቀው ለሚሰግዱና በቁርኣን ሒፍዝ የተሻሉ ለሆኑ ታዳጊ
ወጣቶች
የማበረታቻ ሽልማቶችን አዘጋጅ።
‼

🕌35👉🏼ወንዶችና ሴቶች ጥያቄዎቻቸውን የሚያስቀምጡባቸውና መልስ
የሚያገኙባቸው
ሳጥኖች ለየብቻቸው አዘጋጅ።
‼

🕌36👉🏼ቤተሰቦችህን ለማንቃትና ደዕዋ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ተንቀሳቀስ።
‼

🕌37👉🏼ወጣቶችን ከእድሚያቸውና ከልምዳቸው ጋር የሚሄዱ የበጎ ፈቃደኝነት
ሥራዎች
ላይ እንዲሳተፉ እድል አምቻችላቸው።
‼

🕌38👉🏼በረመዳን መጠቀም እንዲችሉ አንዳንድ ጠቃሚ መልዕክቶችን
በባለቤትህ በኩል
ለጓደኞቿና ለጎረቢቶች እንዲደርስ አድርግ።
‼

🕌39👉🏼በመስጂድ ሐለቃ በማቋቋም ቁርኣን ያልተማሩ ሰዎች የቁርኣን አቀራር፣
ሒፍዝና
ጥናት አስተምር/ አስጀምር።
‼

🕌40👉🏼ለየቲም፣ ለተቸገሩ ሰዎች፣ ባጠቃላይ ዲኑን ለሚካድሙና ገቢ ለሌላቸው
ሰዎች
እርዳታና ድጋፍ እንዲያደርጉ አበረታታ።
‼

🕌41👉🏼በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት በቅርብ የሠፈርህ መስጂድ ኢዕቲካፍ
በማዘጋጀት
ተሳታፊዎች ከኢዕቲካፍ የበለጠ ተቅመው እንዲወጡ የሚረዳ ፕሮግራም
አዘጋጅላቸው።
‼

🕌42👉🏼ከአካባቢው ሰዎች በተለይም ደግ ሰዎችና ዱዓቶች ጋር ጥብቅ የሆን
ትስስር
መስርት።
‼

🕌43👉🏼በተለያዩ የቴሌቪዢን ጣቢያዎች በረመዳን ከሚተላለፉ ፕሮግራሞች
መካከል
ጠቃሚዎችን መርጠህ በመያዝ የአየር ጊዜያቸውን ለጓደኞችህና ጎረቢቶችህ
አሳውቅ።
‼

🕌44👉🏼በሰዎች ላይ የመጣውን አጠቃለይ የባህሪ ለውጥ በማየት በረመዳን
ከተሰጡ
ትምህርቶች ምን ያክል እንደተጠቀሙ መዝግበህ ያዝ።
‼

🕌45👉🏼(የረመዳን ወዳጆች) ኮሚቴ አቋቁምና ታማሚዎችን በሆስፒታል፤
ድሃዎችን ደግሞ
በቤታቸው በመጠየቅ ለረመዳን ወር እንኳን አደረሳችሁ መልክት
እንዲያደርሱላቸው፤
ካሴቶችንና ጠቃሚ ፋንፍሌቶችን እንዲያድሏቸው እንዲሁም ስለ አላህ
እንዲያስታውሷቸው በተጨማሪም ስለጦሃራና ሶላት እንዲያስተምሯቸው
አድርግ።
‼

🕌46👉🏼በአካባቢው የተስፋፉ መጥፎ ነገሮችን ለይቶ በመያዝ ተስማሚ የሆኑ
የማሰወገጃ
መንገዳቸውን በማፈላለግ እንዲቀየሩ አስተባብር።
‼

🕌47👉🏼ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ሙስሊሞች በብዛት በሚያዘወትሯቸው ተቋማት
ውስጥ
ጠቃሚ መጽሐፍትና ፋንፍሌቶችን በትን።
‼

🕌48👉🏼በየቀኑ ግማሽ ገጽ የሚሆን የደዕዋ መልክት በመጻፍ ኢሜልንና ፌስ
ቡክን
በመጠቀም በተቻለ መጠን ብዛት ላላቸው ሰዎች በተለይም ለሠፈር ሰዎችና
ዘመዶች
እንዲደርስ አድርግ።
‼

🕌49👉🏼ከመስጂዱ ኢማም ወይም ከዱዓቶች አንዱ ጋር በመተባበር አንድ ታላቅ
የአሊም
ፕሮግራም በማዘጋጀት ለሰዎች በህይዎታቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን
ነገሮች
እንዲጠይቁና መልስ እንዲያገኙ መድረክ አምቻች።‼

🕌50👉🏼ከጓደኞችህ ጋር በመተባበር የሚተርፉ ምግቦችን ከየቤቱ በማሰባሰብ
ለድሃዎችና
ችግረኞች እንዲዳረስ አድርግ፤ አጋጣሚውን በመጠቀም የተረፉ ምግቦችን
ሰብስቦ
የሚያከፋፍል ተቋም እንዲሆን ጣር።‼

መሰረታዊ ምክሮች
•••❅💞🕋💞❅•••

🕌51👉🏼አላህ (ሱ.ወ) ለሱ ሲባል ብቻ የተሠራን እንጂ አይቀበልም እና ኒያህን
ለአላህ
አጥራ፤ በፆምህም ወደ አላህ ብቻ ዙር።
‼

🕌52👉🏼በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ስራ ለመስራት ሞክር፤ ለምሳሌ እየሄድክ ዚክር
ማለትና
በትራንስፖርት ውስጥ ሆነህ
ቁርኣን መቅራት…።‼

🕌53👉🏼ሱሑር በመብላት ታገዝ፤ “ሱሑር ብሉ፤ ሱሑር መብላት በረካ
አለው።”
📖(ቡኻሪና
ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌54👉🏼ፊጥርን አቻኩል፤ “ሰዎች በኸይር ላይ ከመሆን አይወገዱም፤ ፊጥርን
እስካፋጠኑ
ድረስና ሱሑርን እስካዘገዩ ድረስ።” 📖(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌55👉🏼ማግኘት ከቻልክ በቴምር አፍጥር፡- “ቴምርን ያገኘ በሱ ያፍጥር፤ ቴምርን
ያላገኘ
በውሃ ያፍጥር፤ ውሃ ንጹህ ነውና።”
📖(አህመድ ዘግበውታል)።

🕌56👉🏼ቁርኣንን እያስተነተንክና እየተረዳህ በብዛት አንብብው፤ በየቀኑ
የምትቀራው
የተወሰነ የቁርኣን ክፍል ሊኖርህ ይገባል፤ ጅብሪል (ዐ.ሰ) ነቢያችን 💞(ሰ.ዐ.ወ)
ጋር
በየሌሊቱ እየተገናኘ ቁርኣንን ያጠኑ ነበር።
‼

🕌57👉🏼ምላስህን ከውሸት፣ ከሐሜት፣ ነገርን ከማዛመትና ከመጥፎ ንግግር
ጠብቅ።
ነቢያችን 💞(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ውሸት ንግግርንና በሱም መስራትን
ያልተወ ሰው
ምግቡንና መጠጡን መተው ለአላህ (ሱ.ወ) ጉዳዩ አይደለም።” 📖(ቡኻሪ
ዘግበውታል)።

🕌58👉🏼አይንህን ከሐራም ከልክል፡- “(የሐራም) እይታ ሰይጣን የሚወረውረው
ጦር ነው፤
እኔን ፈርቶ የተወን ሰው ጥፍጥናውን በልቡ የሚያገኘውን ኢማን
እተካዋለሁ።” 📖(ጦብራኒ
ዘግበውታል)።

🕌59👉🏼በሰዎች መካከል የሚካሄዱና አንተን የማይመለከቱህን ወሬዎችና
ውይይቶች
ከማዳመጥና ከመከታተል ጆሮህን ቆጥብ።
‼

🕌60👉🏼ራስህንና ስሜትህን እንዴት መቆጣጠር እንደምትችል ተማር፡- “ፆም ጋሻ
ነው፤
አንድኛችሁ ፆመኛ በሆነ ጊዜ መጥፎ ቃል አይናገር፤ አንድ ሰው ቢሰድበው
ወይም
ቢጋደለው እንኳ እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል።”
📖(ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌61👉🏼ሰደቃ አብዛ፤ ነቢያችን 💞(ሰ.ዐ.ወ) ኸይርን በመለገስ ከሰዎች ሁሉ ቀዳሚ
ነበሩ፤
በጣም የሚለገሱት ደግሞ በረመዳን ነበር።
‼

🕌62👉🏼በፍጡር ጊዜ ምግብ አታብዛ፤ ምግብ ማብዛት መዳከም ያመጣል፤
ሁልጊዜ
ጠግቦ መመገብ ደካማነትንና ቀልብ መድረቅን ያስከትላል፤“የሰው ልጅ
ወገቡን ቀጥ
የሚያደርጉለት ትንሽ ጉርሻዎችን መመገብ በቂው ነው፤ ከዚህ በላይ አብዝቶ
መብላት
ግድ ከሆነም አንድ ሦስተኛውን ለምግብ፣ አንድ ሦስተኛውን ለመጠጥ፣ አንድ
ሦስተኛውን
ደግሞ ለአየር ያድርግ።” 📖(ቲርሚዚይ ዘግበውታል)።

🕌63👉🏼ከፍጡር በኋላ ቀልብህን በአላህ ፍራቻና ተስፋ መካከል አድርግ፤
ምክንያቱም
ፆምህ ተቀባይነት አግኝቶ ከአትራፊዎች ትሆን ወይስ ፆምህ ተመልሶብህ
ከከሳሪዎች
መሆንህን አታውቅም።
‼

🕌64👉🏼ረመዳንን ግዴታነቱን አምነህና ምንዳውን አስበህ ፁም፤ “ረመዳንን
አምኖና አስቦ
የፆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።” 📖(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌65👉🏼ረመዳንን አምነህና ምንዳውን አስበህ ቁም (የሌሊት ስግደት አከናውን)፡-
“ረመዳንን አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።”
📖(ቡኻሪና
ሙስሊም
ዘግበውታል)።

🕌66👉🏼ለይለተል ቀድርን አምነህና ምዳውን አስበህ ቁም፡- “ለይለተል ቀድርን
አምኖና
አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።” 📖(ቡኻሪና ሙስሊም
ዘግበውታል)።

🕌67👉🏼በመጨረሻዎቹ አስር የረመዳን ቀናት በኢባዳ ታገል፡- “ነቢያችን
💞(ሰ.ዐ.ወ) አስሮቹ
ቀናት ሲገቡ ሌሊቱን ህያው ያደርጉ ነበር፤ ቤተሰቦቻቸውንም ያነቁ ነበር፤
እርሳቸውም
ታጥቀው ለኢባዳ ይነሱ ነበር።” 📖(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌68👉🏼የፆምን ፍሬና ግድ የተደረገበት ውስጠ ሚስጠር አብሮህ እንዲቀጥል
በነገርህ
ሁሉ የአላህን ትዕዛዝ ጠብቅ፤ በድብቅም በግልጽም እርሱን ተጠባበቅ
(ትዕዛዙን
ከመጣስ ተጠንቀቅ) “እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት
(ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ
ይከጀላልና።” 📖(አል-
በቀራ 2፤ 183)

🕌69👉🏼በድካም፣ በረሀብና ጥም በማመካኘት የረመዳንን ቀን እየተኛህ አላህ
ዘንድ እጅግ
ተወዳጅ የሆነው ጀማዓ ሶላት አይለፍህ።
‼

🕌70👉🏼በንግድና ገንዘብ ነክ ጉዳዮችም ይሁን በምክክርንና በውይይት ጊዜ
ከማታለል
በእጅጉ ራቅ፡- “ያታለለን ከኛ አይደለም።” 📖(ሙስሊም ዘግበውታል)።

🕌71👉🏼አደራ! ጥሩ ሥነ-መግባርን ተላበስ፤ ነቢያችን 💞(ሰ.ዐ.ወ) ሰዎችን በብዛት
ጀነት
የሚያስገበው ነገር ምንድን ነው ተብለው ሲጠየቁ “አላህን መፍራትና ጥሩ
ሥነ-ምግባር
ነው” ሲሉ መልሰዋል። 📖(ቲርሚዚ ዘግበውታል)።

🕌72👉🏼የታጋሽነት፣ ይቅር ባይነትና ቁጣን መዋጥ ችሎታ ይኑርህ፤ የበለጠ
ለማሻሻልም
ራስህን ታገል “ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም
ገቺዎች
ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)። አላህም በጎ ሠሪዎችን
ይወዳል።”📖 (አሊ ዒምራን 3፤ 134)

🕌73👉🏼ያለ አግባብ የያዝከውን ነገሮች ለባለቤቶቻቸው በመመለስ ከሰዎች ሐቅ
ነፃ ሁን፡-
“የወንድሙ ሐቅ ያለበት ሰው ዛሬውኑ ነጻ ይሁን፤ ነገሩ እዚያ (አኺራ) ወርቅም
ይሁን ብር
የለም፤ አንድ ሰው የወንድሙ ሐቅ ካለበት ከኸየር ሥራው እየተወሰደ
ለወንድሙ
ይከፈላል፤ ኸይር ሥራ ከሌለው ደግሞ ከወንድሙ ወንጀል እየተወሰደ እርሱ
ላይ
ይጣላል።”
📖(ቡኻሪ ዘግበውታል)።

🕌74👉🏼አገልጋዮችንና ሠረተኞችን በረመዳን ብዙ በማሰራት አታድክማቸው፤
“ከባሪያው
ያቃለለ ሰው አላህ (ሱ.ወ) ወንጀሉን ይምረዋል፤ ከሳትም ነፃ
ያወጣዋል።” 📖(ኢብኑ
ኹዘይማህ ዘግበውታል)።

🕌75👉🏼ወደኸይር ነገር ጥሪ ያደረገልህን ሰው ግብዣውን ተቀበል፤ “በአላህ
የተጠበቀን
ጠብቁት፤ በአላህ ስም የለመነን ሥጡት፤ ጥሪ ያደረገላችሁን ተቀበሉት፤
ለናንተ ውለታ
የዋለላችሁን ሰው ውለታውን መልሱለት።”
📖(አህመድ ዘግበውታል)።

🕌76👉🏼ቤተሰቦችህ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የረመዳን ወር ሲገባ አበስራቸው።
‼

🕌77👉🏼ረመዳንን ምክንያት በማድረግ በቤትህ ውስጥ ለውጥ አድርግ፤ ይህም
የሚሆነው
ቤቱን በማጽዳት፣ እቃዎችን እንደገና በማደራጀት፣ ቁርኣን የተጻፈባቸውን
ፍሬሞችና
ሌሎች ጠቃሚ ምክሮች ለማስታወስና ረመዳንን ለማድመቅ በግድጊዳ ላይ
ስቀል፣
ህጻናት በረመዳን መምጣት እንዲደሰቱና ደረጃውንም እንዲረዱት በክፍላቸው
ውስጥ
አንዳንድ ማስዋቢያዎችን ስቀልላቸው።
‼

🕌78👉🏼የረመዳንን ወር ጊዜያት በትክክል ለመጠቀም እቅድ አስቀምጥ፤ በየቀኑ
የምትቀራውን የቁርኣን መጠንና ተራዊህ ሶላት ለመስገድ ተስማሚ
የሚሆንልህን
መስጅድ ከአሁኑ ውስን።
‼

🕌79👉🏼በረመዳን ወር መስገጃ የሚሆን ቦታ በቤት ውስጥ ለይተህ አስቀምጥ።‼

🕌80👉🏼የቤተሰቦችህን ኢባዳና ሥነ-መግባር በመከታተል የተሳሳተ ሁኔታ ካለ
አስተካካል።
‼

🕌81👉🏼ለረመዳን የሚያገለግል እለታዊ ፕሮግራም በቤትህ ውስጥ በመስቀል
ሁሉም
የቤተሰብ አባላት እንዲሳተፉበትና እንዲጠቀሙበት አድርግ፤ ፕሮግራሙ
እንዳስፈላጊነቱ
መቀያያር የሚችል መሆን አለበት።
‼

🕌82👉🏼ፍጡርና ሱሑር ከቤተሰብህ ጋር ተመግብ፤ ምክንያቱም አብራችሁ
ስትመገቡ
ቤተሰባዊ ትስስሩን ያጠብቀዋልና ነው።
‼

🕌83👉🏼ከልጆችህ ጋር ሆነህ ለሱብሂ ሶላት ወደ መስጊድ ሂድ፤ የመጀመሪያ ሶፍ
ላይም
ስገዱ፤ እናት ደሞ ከሴት ልጆች ጋር በቤት ውስጥ ትሰገድ፤ ሁኔታዎች
ከተመቻቹ እናት
ከባሏና ከልጆቿ ጋር መስጅድ ትሂድ።
‼

🕌84👉🏼ከሳምንት አንድ ቀን ከልጆችህና ሚስትህ ጋር ከፈጅር ሶላት በኋላ
ተቀምጣችሁ
አንድ ጁዝ ቁርኣን ቅሩ፤ እነዲዚሁም ከሲራና ከፊቅህ (በተለይም ፆምን
በተመለከተ)
ተፍሲርና አቂዳ የተወሰነ ተማማሩ።
‼

🕌85👉🏼ዋጀብና ትርፍ ኸይር ሥራዎችን የምትከታተሉበት ሠንጠረዥ ከቤተሰቡ
ጋር
ተስማምተህ አስቀምጥ፤ ሌሎች እንዲነቃቁ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳዩትን
አበረታታቸው።
‼

🕌86👉🏼በኑሮህ መካከለኛነትን በመከተል ከገቢህ ጋር የሚመጥን የረመዳን በጀት
አስቀምጥ፤ ረመዳን አስፈላጊውን የሚሟላበት ወር እንጂ የብክነት ወር
አይደለም።
‼

🕌87👉🏼ከባለቤትህ/ሽ ጋር ሁናችሁ ለኸይር ጉዳይና ትርፍ ሰደቃ የሚውል ገንዘብ
ወስናችሁ አስቀምጡ።
‼

🕌88👉🏼የሚዲያን ብልሹ መልክቶች ተጠንቀቅ፤ በተለይም የሴቶችን ገላ
እያጋለጡ
የሚያሳዩና ወደ መጥፎ ነገርና ወንድና ሴትን ለማቀላቀል ጥሪ የሚየደርጉ
ጋዜጦችንና
መጽሔቶችን ራቅ።
‼

🕌89👉🏼ልጆችህ የሙስሊሞችን ስብስብ እንዲያዩ በአንድ ታላቅ መስጊድ
ለመስገድ ጥረት
አድርግ።
‼

🕌90👉🏼ልጆችህ ቀስ በቀስ ፆም እንዲለማመዱ አድርግ፤ ሱሑር ለመብላትና
ለፈጀር ሶላት
እንዲነሱ አበረታታቸው።‼

🕌91👉🏼ቤተሰቦችህ የጠዋትና የማታ አዝካሮችን (ውዳሴዎችን)፣ የፍጡር ዱዓና
የተሀጁድ
ዱዓ እንዲሐፍዙ አድርግ፤ ውድድር እያደረግክ ዱዓዎቹን በቃል ለሸመደዱና
ጠብቀው
ለሚጠቀሙ ሽልማት በመስጠት ልታበረታታቸው ትችላለህ።
‼

🕌92👉🏼በቤትህ ውስጥ ያሉትን ጥሩ ጎኖችና መጥፎ ጎኖች ለይተህ ጥሩውን
ለማሳደግ
መጥፎውን ደግሞ ለማስወገድ ሥራ።‼

🕌93👉🏼እናት ልጆቿን ምግብ በማዘጋጀትና በማቅረብ እንዲሳተፉ በማድረግ
በመካከላቸው
ተባብሮ የመስራት ዋጋን እንዲረዱ ማድረግ አለባት።
‼

🕌94👉🏼የኸይር ከረጢት (ሻንጣ) በያንዳንዱ ቤተሰብ አለያም በጎረቤቶች ደረጃ
አዘጋጅታችሁ ድሃዎችና ችግረኞች ለረመዳን እንዲጠቀሙበት በማድረግ
በሙስሊሞች
መካከል ሊኖር የሚገባውን ማህበራዊ ትብብር ህያው አድርጉ።
‼

🕌95👉🏼ከአጉል ወገንተኝነት፣ ከስሜታዊነትና ስሞታ ከማብዛት ተቆጠብ፤
በማንኛውም
ሁኔታ ልበ ሰፊና የተረጋጋህ ሁን፤ አላህን ሁል ጊዜ አውሳ።
‼

🕌96👉🏼ዚያራ በማድረግና ስጦታ በመለዋወጥ ማህበራዊ ኑሮ ላይ ተሳተፍ፤
ከቤተሰቦችህና ከጎረቢቶች ጋር ኢባዳ የምትሠሩበትና በመካከላችሁ ያሉ
አለመግባባቶችን የምታስተካክሉበት መገናኛ ጊዜያት አድርጉ።‼

🕌97👉🏼በየሳምንቱ ቤተሰብህን የምትይዝበት ሳምንታዊ መልክት ምረጥ፤
ለምሳሌ
“የማያዝን አይታዘንለትም” የሚለውን ሐዲስ የሳምንቱ መልክት በማድረግ
የእዝነት
ባህሪን አትኩሮት መስጠትና መላበስ ይቻላል። በሁለተኛው ሳምንት ደግሞ
“ጌታችሁን
ማህርታ ጠይቁት፤ እርሱ ማሀሪ ነውና።” የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ
በመጠቀም
የኢስቲግፋርን አስፈላጊነት ታስተምራለህ። በሦስተኛው “ጌታዬ ወደ አንተ
ፈጠንኩ”
የወሩ ግማሽ ተገባደደ፤ ስለዚህ አላህ (ሱ.ወ) እንዲቀበለን የበለጥ በኢባዳ
መጠናከር
አለብን። ከዚያም በአራተኛው ሳምንት ደግሞ “ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ
ከርሱ
ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና”
📖 (ዛሪያት 51፤ 50) ወይም “ይታዘንላችሁም ዘንድ
አላህንና
መልክተኛውን ታዘዙ።” 📖(አል-ኢምራን 3፤ 132) የሚሸሸው ወደ አላህና ወደ
ጀነቱ
መሆን አለበት። ይህን የመሳሰሉ መልክቶች…

🕌98👉🏼ሚስትህን የተለያዩ የምግብ አይነቶች በማዘጋጀት እንድትጠመድ
አታድርግ፤
በማዕድ ቤት ውስጥ ልትጠቀምበት የሚቻል ፕሮግራም እንዲኖራት አድርግ፤
ለምሳሌ
የቁርኣንና የዲን ካሴቶችን ማዳጥ…፤ ፆመኞችን ለማስፈጠር የምታደርገው
ትግል ትልቅ
ምንዳ የሚያስገኝላት መሆኑንም አስታውሳት።
‼

🕌99👉🏼በረመዳን ወር በሙሉ ለልጆችህ ሊጠቅማቸው የሚችል ማራኪ መጽሐፍ
በመምረጥ፣ የንባብ ውድድር አድርግ፤ ለምሳሌ ሐያቱ ሶሐባ (አብዱረህማን
ረእፈት
የጻፉት)… ለዚሁም ሸልማቸው፤

🕌100👉🏼በቤተሰብ አባላት መካከል ያለውን ልዩነት (የግል ባህሪ) አትዘንጋ፤
ለአንድኛው
የሚስማማው ነገር ለሌላው ላይሆን ይችላል፤ ከዚህም አኳያ አንዱን ልጅህን
በሒፍዝ
ላይ ልታበረታታው ትችላለህ፤ ሌላውን ደግሞ በቂራኣ ላይ…
አላህ ከኛም ከናንተም ሶላታችንና ፆማችንን ሌላውንም ሥራችንን ይቀበለን።
‼
•┈┈┈••❅💞🕋💞❅••┈┈┈•

👨‍👨‍👦‍👦ያጀመዓ
📩 Share👍 Like በማድረግ ለሌላ እህት ወንድም አስተላልፉ
📩ሌላላ ሰውም ማስተላለፍ ደአዋ ነው 4፡፡‼
የምታውቁትን አንዲትም ብትሆን ለህት ወንድምህ አካፍል ብለዋል እረሱል
💞 ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ💞
ስለዚህ ሼር Like በማድረግ
ያስተላችፉ
👍ስለመልካሙ ትብብራችው ሁሉ በአላህ ስም እናመሰግናለን!!
🎀መልካም የኢባዳ ወር
ተመኘንላችው
✋ማሰላማ
•┈┈┈••❅💞🕋💞❅••┈┈┈•

15/02/2026

እረመዳን በጣት የሚቆጠር ቀን ቀርቶታል
ህይወትህን አድስ …
◆━━━━━━◆❃◆━━━━━━◆
ታላቁ ጌታ አላህ (ሱ.ወ) እንድንኖረው የፈለገውን የደስታ ህይወት መንገድ ተወዳጁ ነብይ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) አብራርተው ነግረውናል።

ይህችን የደስታ ህይዎት ከቤተሰቦቻቸን፣ ከጎረቤቶቻችን፣ ከጓደኞቻችን፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከምናገኛቸውና ተጽዕኖ ከምንፈጥርባቸውም ይሁን ከሚፈጥሩብን ሰዎች ሁሉ ጋር እንኖራለን።

ከሰዎች በላጩ በተለያዩ የህይወት ዘርፎች ሰዎችን ለማገልገል አላህ (ሱ.ወ) ያቆመው ሰው ነው፤ ምንኛ ያማረና የተዋበ ህይዎት ነው! ለሚኖርበት ማህበረሰብ ሁሉ ደስታን፣ ሰላምን፣ ብልፅግናንና ጀነትን ይመኛል።

የህይወት ግቡን ተረድቶ፣ የጌታን ይሁንታ (ተውፊቅ) ታድሎ ራሱን ከህብረተሰቡ ሳያገልና እኔ ለኔ ብቻ ነው የምኖረው ሳይል ሐሳቡንና ጭንቀቱን ለነፍሱ ብቻ ከማድረግ ይልቅ ለሌላው የሚያስበውን ሰው አላህ ይዘንለት።

አዎ! እኔ የምኖረው ለራሴ ነው፤ ማዳን ያለብኝም ራሴን ብቻ ነው ብሎ ማስብ የተሳሳተ አመለካከት ነው፤ ወደ አላህ ቁጣም ይወሰዳል።

አላህ (ሱ.ወ) በአንድ ወቅት መላኢኮችን አንድን አገር (አካባቢ) እነዲያጠፉ ባዘዛቸው ጊዜ “ጌታችን ሆይ በዚች መንደር አንድ ጥሩ ያንተ ባሪያ አለና እንዴት እናድርግ” ሲሉት፤ ታለቁ ጌታም “በሱ ጀምሩ” ነበር ያላቸው፤ ይህ ሰው በራሱ ጥሩ ቢሆንም ጥሩነቱ ግን አልጠቀመውም ነበር፤ ምክንያቱም ጥሩ ሆኖ የኖረው ለራሱ ብቻ ስለነበር ነው፤ “ለራሱ ብቻ የኖረ ሰው መወለድ አይገባውም ነበር።”

ትክክለኛ ሙእሚን ግን ራሱን አግልሎ በመስጅድ ወይም በኸልዋ ለመኖር ነፍሱ አትቀበልም፤ ይልቁንም ወደ ህይዎት መስኮች በመውረድ ይሰጣል፤ ይቀበላል፤ ይጠቅማል፤ ይጠቀማል፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺍﺭْﻛَﻌُﻮﺍ ﻭَﺍﺳْﺠُﺪُﻭﺍ ﻭَﺍﻋْﺒُﺪُﻭﺍ ﺭَﺑَّﻜُﻢْ ﻭَﺍﻓْﻌَﻠُﻮﺍ ﺍﻟْﺨَﻴْﺮَ ﻟَﻌَﻠَّﻜُﻢْ ﺗُ
ﻔْﻠِﺤُﻮﻥَ ‏[ ٢٢: ٧٧ ]

“እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! (በስግደታችሁ) አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም ተገዙ፣ በጎንም ነገር ሥሩ፣ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና።
”(አል-ሐጅ 22፤ 77)

ከላይ በተጠቀሰው የቁርኣን አንቀጽ “በጎንም ነገር ሥሩ” የሚለው ትዕዛዝ ማንኛውምን መልካም ነገር አጠቃሎ የሚይዝ ነው።

ኢባዳ እዝነትን በልብ ውስጥ ይቀሰቅሳል፤የእዝነት ምልክት ደግሞ ኸይርን መስራት ነው።

ከሙእሚን ዋነኛ ባህሪያት መካከል አንዱ ለሁሉም የአላህ ባሪያዎች በጎ ነገር ማድረግ ነው።

ይህ በጎ አድራጎት በሰደቃ፣ በምግብ፣ ውሃ በማጠጣትና የባለእዳ ችግረኞችን ብድር በመክፈል የሚገለጽ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ተሰሚነትን ተጠቅሞ ሰዎች በማስታረቅና ሽምግልና በማድረግ ሊገለጽም ይችላል፤ አለያም ያለውን እውቀት ሌሎች በማስተማር ሊሆን ይችላል፤ ወይም የሰው ልጅ ማህበራዊ አስፈልጎቶች የሆኑት የታመመን ሰው መጠየቅ፤የተበደለን መርዳት፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ጥሩ ጉርብትና እና አስቸጋሪ ነገሮችን ከመንገድ ላይ ማስወገድ የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ።

እያንዳንዳችን በየንጋቱ ጠዋት በሦስት መቶ ስድሳ የሰዉነት መገጣጠሚያችን ልክ ሦስት መቶ ስድሳ ሶደቃ ይጠበቅበታል።

ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ“ማንኛም ሰው ፀሐይ በወጣችበት ቀን (በያንዳንዱ ቀን) ከራሱ ሰደቃ መስጠት አለበት” አቡዘር (ረ.ዐ) እኔ ገንዘብ የለኝም ከየት ሰደቃ ልስጥ አላቸው፤ ነቢያችንም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ “ከሰደቃ በሮች መካከል አላሁ አክበር፣ ሱብሀነላህ፣ አልሐምዱሊላህ፣ ላኢላሀኢለላህ ማለትና ኢስቲግፋር ማድረግ ይገኙበታል፤ በጥሩ ነገር ማዘዝህና ከመጥፎ ነገር መከልከልህ፣ እሾህ አጥንትና ድንጋይን ከሰዎች መንገድ ላይ ማስወገድህ፣ አይነ ሥውርን መምራትህ፣ መስማት የተሳነውንና ዱዳን እስኪገባው ድረስ ማስረዳትህ፣ አንድ ባለ ጉዳይ የሚፈልገውንና የምታውቀውን ነገር ማሳየትህ፤ ያለህን አቅም ሁሉ ተጠቅመህ የተጨነቀንና የሚማፀንን ሰው ለማዳን መሞከርህ፣ ባለህ አቅምና ሐይል ከደካሞች ጎን መቆምህ…

ይህ ሁሉ አንተ በራስህ ላይ የምታደርገው ሰደቃ ነው፤ ከሚስትህ ጋር ፆታዊ ግንኙነት ስትፈጽም እንኳ አጅር (ምንዳ) አለህ።”

ዘይኑል ዓቢዲን ዓሊይ ቢን ሑሰይን (ረ.ዐ) ዳቦ እየተሸከሙ በጨለማ ወደ ሚስኪኖች ቤት ይወስዱ ነበር (ይህን ምግብ ለነዚህ ሚስኪኖች ማን እንደሚያመጣላቸው እርሳቸውእስከሚሞቱ ድረስ አልታወቀም ነበር)።

ሰዎች ለመጥቀም መንቀሳቀስ ሠናይ ተግባርመሆኑን ለመረዳት የነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ባህሪ መሆኑ ብቻ ይበቃል።

ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ)በሒራ ዋሻ ውስጥ እያሉ መላአኩ ጅብሪል በድንገት ሲመጣቸው በሁኔታው በተደናገጡ ጊዜ እናታችን ኸድጃ (ረ.ዐ) ሲያረጋጓቸው በጎ ተግባራቸውን እያወሱ እንዲህ ነበር ያሉት“ወላሂ አንተን አላህ መቸም ለክፉ አይሰጥህም፤ ወላሂ አንተ ዝምድናን ትቀጥላለህ፤ ደካማን ትሸከማለህ (ታህሚሉ ከል)፤ ያጣን ታሸምታለህ (ቱክሲቡል ማዕዱም)፤ እንግዳን
ትቀበላለህ እውነት ላይም ታግዛለህ።”

ለዘመዶች መልካም መዋል “ደካማን ትሸከማለህ” (ታህሚሉ ከል) በሚል ተገልጧል።

“ከል’’ የሚለው ሸክም እንደ ማለት ሲሆን ወላጅ አልባ ህፃናት፣ ችግረኞች ወዘተ መርዳትን ያጠቃልላል።

“ያጣን ታሸምታለህ” (ቱክሲቡል ማዕዱም)፤ ማለት ሌሎች እንዲያገኙ
ትለግሳለህ እንደማለት ነው።

የአላህ ወዳጆች ሆይ…
ይኸው እኛ የአላህን ትዕዛዛትና የረሱልን ፈለግ በመከተል ልንኖረው በምንፈልገው ህይዎትውስጥ የአላህን ውዴታ እናገኝ ዘንድ ልንጠቀምባቸው የሚገቡን የተከበረው የረመዳን ቀናት ወደኛ እየመጡ ነው

ﻭَﻋَﺠِﻠْﺖُ ﺇِﻟَﻴْﻚَ ﺭَﺏِّ ﻟِﺘَﺮْﺿَﻰٰ ‏[ ٢٠ : ٨٤ ]

“ጌታዬ ሆይ! ትወድልንም ዘንድ ወደ አንተ ቸኮልኩ” (ጦሃ 20፤ 84)
ስለዚህ ከአሁኑ አላማችንን ወስነንና እቅዳችንን አስቀምጠን ወደ ሥራ መግባት ግድ ይለናል።

1ኛ. አላማን መወሰን
◆━━━━━━◆
i. ወደ አላህ መመለስ:- አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

ﻭَﺗُﻮﺑُﻮﺍ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﺃَﻳُّﻪَ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﻟَﻌَﻠَّﻜُﻢْ ﺗُﻔْﻠِﺤُﻮﻥَ ‏[ ٢٤: ٣١ ]

“ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ።”
(አን-ኑር 24፤31)

ኢማም ሙስሊም አቡ ሙሳ አብደላህ ቢን ቀይስ አል አሽዓሪይን ጠቅሰው እንደዘገቡት ነቢያቸን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

ﺇﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﻳﺒﺴﻂ ﻳﺪﻩ ﺑﺎﻟﻠﻴﻞ ﻟﻴﺘﻮﺏ ﻣﺴﻲﺀ ﺍﻟﻨﻬﺎﺭ، ﻭﻳﺒﺴﻂ ﻳﺪﻩ ﺑﺎﻟﻨﻬﺎﺭ ﻟﻴﺘﻮﺏ ﻣﺴﻲﺀ ﺍﻟﻠﻴﻞ ﺣﺘﻰ ﺗﻄﻠﻊ ﺍﻟﺸﻤﺲ ﻣﻦ ﻣﻐﺮﺑﻬﺎ

“አላህ (ሱ.ወ) በቀን ያጠፋ ተፀፅተው ይመለሱ ዘንድ እጁን በሌሊት ይዘረጋል፤ በሌሊት ያጠፋ ተፀፅተው ይመለሱ ዘንድ እጁን በቀን ይዘረጋል፤ ይህም የሚሆነው ፀሐይ በመግቢያዋ እስከምትወጣ (እስከ አለም ፍፃሜ) ድረስ ነው።”
(ሙስሊም ዘግበውታል)

ii. መዋብ (በመልካም ስራ)ና መላቀቅ
(ከመጥፍ ተግባራት) /ተሀሊ ወ ተኸሊ/:-
◆━━━━━━◆❃◆━━━━━━◆

አንዳንድ በረመዳን ልንላበሳውና ልንዋብባቸው የሚገቡ መልካም ሥነ መግባራትን ቀድመን መለየት፤

ለምሳሌ እውነተኛነት፣ ታማኝነት፣ ቃልን ማክበር ወዘተ።

እንደዚሁም በአንጻሩ ደግሞ ልንርቃቸው የሚገባንን አንዳንድ መጥፎ ባህሪያትን መለየትና ከነሱም መጥራት።

ለምሳሌ
ውሸት፣ሐሜት፣ በሀሰት መመስከር ወዘተ።

iii. ለቁርኣን ትኩረት መስጠት፡-
❃❃◆━━━━━━◆❃❃

ረመዳን የቁርኣን ወር ነው፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

ﺷَﻬْﺮُ ﺭَﻣَﻀَﺎﻥَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺃُﻧﺰِﻝَ ﻓِﻴﻪِ ﺍﻟْﻘُﺮْﺁﻥُ ﻫُﺪًﻯ ﻟِّﻠﻨَّﺎﺱِ ﻭَﺑَﻴِّﻨَﺎﺕٍ ﻣِّﻦَ ﺍﻟْﻬُﺪَﻯٰ ﻭَﺍﻟْﻔُﺮْﻗَﺎﻥِ ‏[ ٢ :
٥٨ټ ]

“(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው።”

(አል-በቀራ 2፤ 185)

ቁርኣን ጋር መኖር ስንል በየቀኑ አንድ ወይም ሁለት ወይም ሦስት ጁዝእ ሁሉም እንደየ አቅሙና ችሎታው መቅራት ማለት ነው።

አቡ ሙሳ አል ዓሽዐሪይ እንዳስተላለፉት ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ይህን ተናግረዋል፡-

ﺗﻌﺎﻫﺪﻭﺍ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﻘﺮﺁﻥ، ﻓﻮﺍﻟﺬﻱ ﻧﻔﺲ ﻣﺤﻤﺪ ﺑﻴﺪﻩ ﻟﻬﻮ ﺃﺷﺪُّﺗﻔﻠﺘًﺎ ﻣﻦ ﺍﻹﺑﻞ ﻓﻲ ﻋﻘﻠﻬﺎ

“ይህን ቁርኣን ጠብቃችሁ ያዙ፤ የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነቸው ጌታ እምላለሁ እሱ (ቁርኣን) የታሰረች ግመል በጥሳ ለማምለጥ ከምትፈጥነው የበለጥ ለመረሳት የፈጠነ ነው።”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

በመሆኑም በቃል የሸመደድናቸውን (የሀፈዝነውን) የቁርኣን ክፍሎች መከለስ ያስፈልጋል።

iv. የተሰራ በደልን ማስተካክል፡-
❃❃◆━━━━━━◆❃❃

የረመዳን ወር ከመግባቱ በፊት ከሰዎች ያለ አግባብ የወሰድናቸው ንብረቶች ካሉ ለባለቤታቸው እንመልስ።

ሰዎችን አምተንና ክብራቸውን ነክተን ከሆነም ይቅርታ በመጠየቅ ከሐቃቸው እንጥራ።

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

ﻣﻦ ﻛﺎﻧﺖ ﻋﻨﺪﻩ ﻣﻈﻠﻤﺔ ﻷﺧﻴﻪ ﻓﻠﻴﺘﺤﻠﻠﻪ ﻣﻨﻬﺎ، ﻓﺈﻧﻪ ﻟﻴﺲ ﺛﻢ ﺩﻳﻨﺎﺭ ﻭﻻﺩﺭﻫﻢ، ﻣﻦ ﻗﺒﻞ ﺃﻥ ﻳﺆﺧﺬ ﻷﺧﻴﻪ ﻣﻦ ﺣﺴﻨﺎﺗﻪ، ﻓﺈﻥ ﻟﻢ ﻳﻜﻦ ﻟﻪ ﺣﺴﻨﺎﺕ ﺃﺧﺬ ﻣﻦ ﺳﻴﺌﺎﺕ ﺃﺧﻴﻬﻔﻄﺮﺣﺖ ﻋﻠﻴﻪ

“ወንድሙን የበደለ ከወዲሁ (ከተበዳዩ ዘንድ በመሄድ) ራሱን ነፃ ያስደርግ፤ እዚያ (አኺራ) ወርቅም ብርም የለምና፤ ከሱ የስራ ምንዳው እየተወሰደ ለወንድሙ(ለተበዳዩ) ሳይሠጥና ኸይር ሥራው ካለቀ ወይም ከሌለው ደግሞ የወንድሙ ወንጀል እየተወሰደ በሱ ላይ ሳይጣል በፊት ዛሬ ከበደል ነፃ ይሁን።”
(ቡኻሪ ዘግበውታል)

v. ዱዓን ማዘውተርና ወቅቶቹን መከታተል፡-
◆━━━━━━◆❃◆━━━━━━◆
(በፊጡር ሰዓት፣ በሱሁር ሰዓት፣ ቁርኣን ሲኸተም፣ በአዛንና ኢቃም መሀከል፣ ከግዴታ ሶላቶች በኋላ፤ ጁምዐ ከአስር ሰላት በኋላ ወዘተ..)

የአላህ ባሪያዎች ሆይ…
በዱዓ ላይ ብርቱ ጥረት አድርጉ፤ የአላህን ውዳሴ አብዙ፤ ተስፋችሁን አሳድጉ፤ የዱዓ አዳቦችን ጠብቁ፤ የአላህ ካዝና ሙሉ ነው፤ እጆቹም በሌሊትም በቀንም ለጋስ ናቸው፤ ካዝናው በመስጠት አይጎድልም።

እሰኪ ተመልከቱ አላህ (ሱ.ወ) ሰማያትንና መሬትን ከፈጠረ ጊዜ ጀምሮ እየሰጠ እየለገሰ ቢሆንም እርሱ ጋር ያለው ድልብ ካዝና ግን መርፌ በባህር ውስጥ ገብታ እንደምታጎድለው አንጂ አለመጉደሉን አስተውላችኋልን?

በሐዲሰል ቁድስ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

ﻳﺎ ﻋﺒﺎﺩﻱ، ﻟﻮ ﺃﻥ ﺃﻭﻟﻜﻢ ﻭﺁﺧﺮﻛﻢ، ﻭﺇﻧﺴﻜﻢ ﻭﺟﻨﻜﻢ، ﺍﺟﺘﻤﻌﻮﺍ ﻓﻲ ﺻﻌﻴﺪ ﻭﺍﺣﺪﻓﺴﺄﻟﻮﻧﻲ، ﻓﺄﻋﻄﻴﺖ ﻛﻞ ﻭﺍﺣﺪ ﻣﻨﻬﻢ ﻣﺴﺄﻟﺘﻪ، ﻣﺎ ﻧﻘﺺ ﺫﻟﻚ ﻣﻤﺎ ﻋﻨﺪﻱ ﺷﻴﺌًﺎ

“ባሮቼ ሆይ!
መጀመሪያችሁም መጨረሻችሁም፤ ሰዋችሁም ጅናችሁም፣ በአንድ ቦታ
ተሰባስበው ቢጠይቁኝና ለያንዳንዳቸው የጠየቀኝን ብሰጥ፣ይህ እኔ ጋር ካለው ምንም አያጎድልም።”
(ሙስሊም ዘግበውታል)

vi. አላህ ብቻ የሚያውቃቸው በሚስጥር የሚሰሩ
በጎ ስራዎች ላይ መበርታት፡-
❃❃◆━━━━━━◆❃❃◆━━━━━━◆

እናታችን ዘይነብ (ረ.ዐ) በእጃቸው እየሰሩ ሰደቃ ይሰጡ ነበር። ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ከመሞታቸው በፊት እንዲህ ብለው ነበር“ከናንት መካከል ቀድማ እኔን የምትከተለኝ ከመካከላችሁ እጀ ረጅሟ ነች።”

እናታችን ዘይነብ (ረ.ዐ) ከነቢያችን ሞት በኋላ ከሌሎች ሚስቶቻቸው ቀድማ ነበር የሞተችው።

ዘይኑል አቢዲን የተቸገሩ ሰዎች ቤት ጨለማን ተገን አድርገው በመሄድ በራፉ ላይ ምግቦችን ያስቀምጡ የነበረ።

ይህ ድርጊታቸው የታወቀው ከሞቱ በኃላ እርዳታው ሲቋረጥ ነበር።

vii. ኢዕቲካፍ መቀመጥ፡-
ቡኻሪና ሙስሊም አብደላህ ኢብኑ ዑመርን ጠቅሰው እንደዘገቡት ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ከረመዳን ወር የመጨረሻዎችን አስር ቀናት ኢዕቲካፍ ይገቡ
ነበር (በመስጅድ ያሳልፉ ነበር)።

ስለዚህ ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ቢቻል ሁሉንም ካልሆን ከሶስት ቀናት ላላነሰ ጊዜ ኢዕቲካፍ መግባት ያስፈልጋል፤ ኢዕቲካፍ ለመቀመጥ
አስበን መስጅድ በምንገባበት ጊዜ መነየት ያስፈልጋል።

viii. ዝምድናን መቀጠል፡-
❃◆━━━━━━◆❃
አላህ (ሱ.ወ) እንህ ይላል፡-

ﻓَﻬَﻞْ ﻋَﺴَﻴْﺘُﻢْ ﺇِﻥ ﺗَﻮَﻟَّﻴْﺘُﻢْ ﺃَﻥ ﺗُﻔْﺴِﺪُﻭﺍ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻭَﺗُﻘَﻄِّﻌُﻮﺍ ﺃَﺭْﺣَﺎﻣَﻜُﻢْ ﺃُﻭﻟَٰﺌِﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻟَ
ﻌَﻨَﻬُﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻓَﺄَﺻَﻤَّﻬُﻢْ ﻭَﺃَﻋْﻤَﻰٰ ﺃَﺑْﺼَﺎﺭَﻫُﻢْ ‏[ ٤٧: ٢٢ - ٢٣ ]

“ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?

እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው፣ ያደነቆራቸውም፣ ዓይኖቻቸውንም ያወራቸው ናቸው።”

(ሙሐመድ 47፤ 22-23)

ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲሁ ይህን ተናግረዋል፡-

ﻣﻦ ﺃﺣﺐ ﺃﻥ ﻳُﺒﺴﻂ ﻟﻪ ﻓﻲ ﺭﺯﻗﻪ، ﻭﻳُﻨﺴﺄ ﻟﻪ ﻓﻲ ﺃﺛﺮﻩ، ﻓﻠﻴﺼﻠﺮﺣﻤﻪ

“ሲሳዩ እንዲሰፋለትና ፋናው እንዲቀርለት የፈለገ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።”
(ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል)።

ix. ሁሉንም ሶላቶች በጀመዓ መስገድ፡-
◆━━━━━━◆❃◆━━━━━━◆

አቡ ደርዳእ (ረ.ዐ) ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ በማለት አስተላልፈዋል፡-

ﻣﺎ ﻣﻦ ﺛﻼﺛﺔ ﻓﻲ ﻗﺮﻳﺔ ﻭﻻ ﺑﺪﻭ ﻻ ﺗﻘﺎﻡ ﻓﻴﻬﻢ ﺻﻼﺓ ﺇﻻ ﻗﺪ ﺍﺳﺘﺤﻮﺫ ﻋﻠﻴﻬﻤﺎﻟﺸﻴﻄﺎﻥ ﻓﻌﻠﻴﻚ ﺑﺎﻟﺠﻤﺎﻋﺔ، ﻓﺈﻧﻤﺎ ﻳﺄﻛﻞ ﺍﻟﺬﺋﺐ ﻣﻦ ﺍﻟﻐﻨﻢ ﺍﻟﻘﺎﺻﺔ

“በመንደርም ይሁን በዱር ሦስት ሰዎች ሶላተል-ጀመዓ ሳያቋቁሙ አንድ ላይ አይኖሩም ሰይጣን የተቆጣጠራቸው ቢሆን እንጂ፤ ጀመዓን (ህብረትን) አደራህን፤ ከፍየሎች መካከል ተኩላ የሚበላው ለብቻዋ ተነጥላ ያለችውን ነውና።”
(አቡ ዳውድ ዘግበውታል)።

x. የጠዋትና የማታ እንዲሁም በየሁኔታው የሚባሉ ዚክሮችን ጠብቆ ማለት፡- አብደላህ ቢን ቡስር እንደዘገቡት አንድ ሰው ወደ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) መጣና“የአላህ መልክተኛ ሆይ የኢስላም ህግጋቶች በዙብኝና አጥብቄ የምይዘው አንድ ነገር ይንገሩኝ አላቸው።

ነቢያችንም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉት “ምላስህ በአላህ ዚክር ከመርጠብ አትቦዝን።” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)።

xi. ግዴታ የሆነውን ዘካ ለማውጣት መፋጠን ፡-
◆━━━━━━◆❃◆━━━━━━◆
ﺇِﻥَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻭَﻋَﻤِﻠُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﺎﻟِﺤَﺎﺕِ ﻭَﺃَﻗَﺎﻣُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓَ ﻭَﺁﺗَﻮُﺍ ﺍﻟﺰَّﻛَﺎﺓَ ﻟَﻬُﻢْ ﺃَﺟْﺮُﻫُﻢْ ﻋِﻨﺪَ ﺭﺑِّﻬِﻢْ ﻭَﻟَﺎ ﺧَﻮْﻑٌ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻢْ ﻭَﻟَﺎ ﻫُﻢْ ﻳَﺤْﺰَﻧُﻮﻥَ ‏[ ٢ : ٢٧٧ ]

“እነዚያ ያመኑ።
መልካም ሥራዎችንም የሠሩ። ሶላትንም ያስተካከሉ።
ዘካንም የሰጡ ለነርሱበጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው።
በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም።”
(አል-በቀራ 2፤ 277)

አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋልለ፡-“አላህ ገንዘብ ሰጥቶት ዘካውን ያላወጣ ሰው ሁለት ጡቋቁር አይኖች ያለው ተናዳፊ እባብ ሆኖ የቂያማ ቀን ይመጣበታል፤ ከዚያም ጉንጭና ጉንጩን ይዞ ያጣብቀዋል፤ይነድፈዋል።

እኔ ያከማቸኸኝ ገንዘብህ ነኝ ይለዋል፤ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ይህን ተናግረው የሚቀጥለውን አንቀጽ አነበቡ፡

ﻭَﻟَﺎ ﻳَﺤْﺴَﺒَﻦَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺒْﺨَﻠُﻮﻥَ ﺑِﻤَﺎ ﺁﺗَﺎﻫُﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣِﻦ ﻓَﻀْﻠِﻪِ ﻫُﻮَ ﺧَﻴْﺮًﺍ ﻟَّﻬُﻢ ﺑَﻞْ ﻫُﻮَ ﺷَﺮٌّ ﻟَّﻬُﻢْ ﺳَﻴُﻄَﻮَّﻗُﻮﻥَ ﻣَﺎ ﺑَﺨِﻠُﻮﺍ ﺑِﻪِ ﻳَﻮْﻡَ ﺍﻟْﻘِﻴَﺎﻣَﺔِ ﻭَﻟِﻠَّﻪِ ﻣِﻴﺮَﺍﺙُ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻭَﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﻤَﺎ ﺗَﻌْﻤَﻠُﻮﻥَ ﺧَﺒِﻴﺮٌ ‏[ ٣: ١٨٠ ]

“እነዚያም አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ እርሱ ለእነሱ ደግ አይምሰላቸው።

ይልቁንም፤ እርሱ ለነሱ መጥፎ ነው። ያንን በርሱ የነፈጉበትን በትንሣኤ ቀን (እባብ ኾኖ) ይጠለቃሉ።

የሰማያትና የምድርም ውርስ ለአላህ ብቻ ነው። አላህም በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው።”
(ኣሊ ዒምራን 3፤ 180) (ቡኻሪ ዘግበውታል)።

ከዚህ በተጨማሪ ዘካተል ፊጥርን ከዒድ ሶላት በፊት ማውጣት።

xii. የኢድ ሶላት፡-
የኢድ ሰላትን በሰፊ ሜዳ ለመስገድ ቤተሰቡን በሙሉ ይዞ መውጣት።
2ኛ. በረመዳን ወር ከራሴ፣ ከቤተሰቤ፣ ከሥራ ባለደረቦቼ፣ ከሚስቴ/ከባሌ፣ ከልጆቼና በትራንስፖረት ላይ የሚኖረኝን ፕሮግራም ማስቀመጥ።

ከራስ ጋር ለተውበትና ኢስቲግፋር መፍጠን፤ በሳምንት አንድ ቀን አንድ ድሃ ሚስኪን ማብላት፤ በሳምንት አንድ ቀን አላህ ብቻ የሚያውቀው የሚስጥር ሰደቃ ማውጣት፤ በየቀኑ ከአንድ ጁዝ ያላነሰ ቁርኣን መቅራት፤ ኢማንን የሚያጠናክሩ ፕሮግራሞችን መከታታል፤ አላህን ለመታዘዝ ያወጣሁትን ፕሮግራም የሚያጠናክሩልኝ ፕሮግራሞችን ብቻ በመከታተል ቴሌቪዥኔን መቆጣጠር የወሩ መፈክሬ “ተስፋዬ አላህ እንዲቀበለኝ ነው’’ የሚል ማድረግ፤ ዝምድናየን መቀጥል (ዘመዶቼን የምዘይርበትን ጊዘያት ማስቀመጥ)፤ በወሩ አንድ ጊዜ ለመገሰጥና ለመመከር መቃብሮችንና ሆስፒታሎችን መጎብኘት የበደሉኝን ሰዎች ሁሉ ይቅር ማለትና በሌሉበት ለነሱ ዱዓ ማድረግ፤ መንገደኛን ወይም አላፊን በቴምር እንኳ ቢሆን ለማስፈጥር መጣጣር፤ቤተሰቦቼን ለኸይር ሥራ ላይ ማሰማራት ወደ አላህ ትዕዛዝ መገፋፋት በሥራዬ ሁሉ አዎንታዊ (ኢጃቢይ/positive) መሆንና ለጓደኞቼ ቅርብና አርአያ መሆን፤ ጓደኞቼን ለፍጡር ወደ ቤቴ መጥራትና አንዳንድ ስጦታዎችን ማቅረብ፤ የጠዋትና የማታ እንዲሁም የተለያዩ ገዜያት አዝካሮችን ዘወትር ማለት፤ ከአዛን በፊት መስጊድ መግባትና ቢያንስ በየቀኑ 12 ረከዓ ሱና ሶላቶችን መስገድ፤ በተለይም የፈጅር፣ የኢሻና የተራዊህ ሶላቶችን በጀመዓ ጠብቄ መስገድ።

ከቤተሰብ ጋር ከፍጡር በፊት የማታ ዚክርን ለማለት መሰባሰብ፤ ከአስር ሶላት በኋላ እለታዊ ቁርአን (ዊርድን) ለመቅራትና አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮችን
መለዋወጥ፤ በአንድ የተመረጡ ዲናዊ ፕሮግራም ዙሪያ መሰባሰብና መወያያት፤በአንድ ሰሐቢይ ወይም የቁርኣን ምዕራፍ ዙሪያ እለታዊ ውድድር ማካሄድ፤ በረመዳን ውስጥ አንድ ሱራ (ምዕራፍ) ለመሐፈዝ መስማማት፤ (ለምሳሌ ሱረት ኑር፣ አል- ሑጁራት፣ አል-ሙእሚኑን..)

ላሸናፊዎችም ሽልማት ማዘጋጀት፤ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ ለችግረኛ ሰደቃ ለመስጠት መስማማት (ለአላህ ብሎ መሥራትን ሁሉም የቤተሰቡ አካል እንዲወድና እንዲለማመድ ሰደቃውን በተለያየ ጊዜ የተለያየ ሰው
ቢሰጥ ይመረጣል)፤ በየሳመንቱ ቢያንስ አንድ ፆመኛ ለማስፈጠር ከረመዳን በፊት ፕረግራም ማውጣት፤ አንድ ቅርብ ዘመዳችንን ወደ ቤታችን መጥራት (ለዚህ ፕሮግራም የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን በዝርዝር አስቀምጥ)፤
በየዕለቱ ከምንሰራው ኢባዳዎች (ሶላት፣ ዚክር፣ ቁርኣን፣ ተስቢህ..) አኳያ ራሳችንን የምንገመግምበት መንገድ ላይ ተስማምተን ማስቀመጥ፤ በፍጡር ሰዓት ተሰባስበን ዱዓ ማድረግ፤ በዱዓችን ቤተሰቦቻችንን፣ ዘመዶቻችንን፣
ወንድሞቻችንንና ባጠቃላይ ሙስሊሙን ኡማ ማስታወስ፤ በተለይ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ሙስሊሞች ላይ ያጋጠመን ታላቅ ፊትና አላህ እንዲያከሽፈውና የሙስሊሙ አንድነት እንዲጠናከር ወደ አላህ መማጸን፤
ከቤተሰቦቻችን ጋር ሆነን በየቀኑ ጁዝ የሚቀራበት መስጅድ መሄድ (የራሳችንን ቁርኣንን ይዘን መሄድ፤ ለሰጋጆች ደግሞ ሐዲያ ይዘን መሄድ)፤ በሳምንት አንድ ጊዜ ለጎረቢቶቻችን ሐዲያ መስጥት (ይህንንም በሰንጠራዥ ሠርተን
ከእቅዳችን እናካተው)፤ ለዒድ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ቢበዛ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ሳምንታት ውስጥ ገዝተን እንጨርስ፤ አዋቂ ወንዶችና ወንድ ህጻናት በመስጅድ ውስጥ አዋቂ ሴቶችና ሴት ህጻናት ደግሞ በቤት ውስጥ ኢዕቲካፍ የሚቀመጡበትን ሁኔታ በፕሮግራም ማስቀመጥ፤
ለቤተሰቡ መፈክር ማስቀመጥ፤ (ለምሳሌ “ወደ አላህ ማንም አይቀድመኝም!”፣

“ረመዳን የደስታ በር!”፣ “በከዕባ ጌታ እምላለሁ ፍላጎቴን አገኘሁ!”፤ “የጀነት ሺታ ከረመዳን ጋር ይሸተኛል!”፤ “የተሰናባችን ፆም ፁሙ!”…)፤

ከሚስት ጋር በሁለታችሁ መካከል አላህ ብቻ የሚያውቀው የሚስጥር ኢባዳ ለመስራት መስማማት (ሰደቃ፣ ዚክር፣ ቂያም..)፤

ያስቀምጥነውን ፕሮግራምና ልጆችን በየጊዜው መከታተል፤ ባል ሚስቱን/ ሚስት ባሏን ለሌሊት ሶላት ማስነሳትና ማገዝ፤ ሚስት ፍጡር ስታዘጋጅ መርዳት፤ የፍጡር ምግብ አይነቶችን በማብዛት የሚስትህን ሂይወት
አታባክን፤ ሚስትህን ጥያቄ በማብዛት አለማድከም፤ የሁለቱንም ቤተሰቦች ለኢፍጧር መጥራት፤ ፍጡሩን ቀለል ማድረግ፤ ረመዳን የምግብ
ኤግዚቢሽን አይደለም!

በየዕለቱ ቁርኣን መቅራትና እስቲግፋርን በጋራ ማድረግ፤ በበጎ ስራዎች መተባበር (የረመዳን ስጦታ፣ ፆመኛን ማስፈጠር፤ ድሆችን መርዳት…)

ለሚስትህ በሌለችበት ዱዓ አደርግላት፤ ለስህተቶቿም ምክንያት ፈልግላት፤ ሚስትም ለባሏ እንደዚያው፤ ከልጆች ጋር ከልጆችህ ጋር ሆነህ ቴምርና ውሃ በማዘጋጀት በፉጡር ሰዓት በመንገድ ላይ ቆማችሁ/ በመስጊድ ፆመኞችን አስፈጥሩ፤ ለልጆች ሐዲያ በመስጠት ለጎሮቤቶችና ለጓደኞቻቸው እንዲሰጡ አድርግ፤ ልጆች ሶላተል ጀመዓ እንዲሄዱ ማበረታታት በተለይም ሱብሂና ኢሻ ሶላቶች፤ ልጆች ከግል ወጭያቸው ሰደቃ እንዲሰጡ ማበረታታት፤ ከልጆች እድሜ ጋር የሚመጥን ልዩ ውድድር ማዘጋጀት፤ ከልጆች ጋር በመወያየት የሚመጥናቸውን ፕሮግራም መምረጥ፤ ሁሉም ልጆች የሙሃሰባ (ራሳቸውን የሚገመግሙበት ፕሮግራም) ማድረግ፤ሁሉም ልጆች እንደየአቅማቸው እለታዊ የቁርኣን ዊርድ (መጠን) እዲኖራቸውና መቅራታቸውን መከታተል፤ በጣም ህፃን የሆነና መቅራት የማይችል ልጅ ሌላው ሲቀራ ያዳምጥ፤ በመመካከሪያ ፕሮግራም ልጆች (የሚሰማቸውን) ኻጢራ (ምክራዊ ሀሳብ/ ውልብታ) እንዲናገሩ እድሉን መስጠት፤ የሰሐባ ልጆች የረመዳን ውሎን መማማር።

ከጎረቤት ጋር የኢሻ፣ የተራዊህና የፈጅር ሶላት በጀመዓ ለመስገድ በአንድነት ወደ መስጊድ መሄድ፤ በረመዳን ወር ከአንድ ጊዜ በላይ ቁርኣን ለሚያኸትሙ ሽልማት ማዘጋጀት፤ የረመዳንን ፕሮግራም በተሻለ መልኩ ለሚፈጽሙ ቤተሰቦች ሽልማት ማዘጋጀት፤ በረመዳን ልንላበሳቸው የሚገባ አንዳንድ መልካም ባህሪያትን ለይቶ ማስቀመጥ (እውነተኝነት፣ አማና፣ ዝምታ፣ መቻቻል፣ይቅር ማለት፣ ቃል ኪዳንን መጠበቅ፣ ወላጆችን መንከባከብ…)፤
በቤት ውስጥ የቁርኣንና የጠቅላላ እውቀት ውድድር ለማድረግ መስማማት
በሳምንት አንድ ቀን የረመዳን ምሽት ፕሮግራም መያዝ ረመዳንን ለመቀበል ቤቶችን ማስዋብ ለራስና ለጎረቢት ቤቶች መፈክር (መልእክት) ማስቀመጥ፤ (ለምሳሌ “ኑእሚኑ ሰዓ”- ኑ አንድ ሰዓት እንመን /ለኢማን እንቀማመጥ!/)

የማፍጠሪያ ምግብ አሰባስቦ የአካባቢውን ድሃዎች በጋራ መጋበዝ
ከጓደኞች ጋር ረመዳንን ለመቀበል የሥራ ቦታዎችን ማዘጋጀትና ማስዋብና (የንግድ ቦታ፣ ካምፓኒ፣ ፋብሪካ..)፤

ጓደኞች ለሩብ ሰዓት ያህል ቁርኣን አብሮ የመቅሪያ ጊዜ ማዘጋጀት፤
ጓደኛሞች ከዙህር ሶላት በኋላ ኻጢራ (ውልብታቸውን) መነጋገር፤
በጓደኛሞች መካከል የጠቅላላ እውቀት ውድድር ማዘጋጀት፤
አንድ የቁርኣን ምዕራፍ ለመሐፈዝ መስማማት፤ ከኢስላም ታላላቅ ስብዕናዎች አንዱን መርጦ በዙሪያው ጥናት ማድረግ (ለምሳሌ ኡመር
ኢበን አብዱል አዚዝ)

አንድን ፕሮግራም መከታተልና በሱ ዙሪያ ውይይት ማድረግ፤ ማህበራዊ ኤግዚቢሽን ማዘጋጀት (አልባሳት፣ የትምህርት መሣሪያዎች….)

ገቢያቸው ውስን ከሆኑ የቅጥር ሠራተኞች ጋር የማህበራዊ ትብብር ፕሮግራም ማድረግ፤ ለሠራተኞች ለማከፋፈል የረመዳን ሻንጣ (ስጦታ) ማዘጋጀት (በወሩ ውስጥ ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ሊሆን ይችላል፣ ስጦታው ላይ “የረመዳን ስጦታ” ብሎ መጻፍ)፤

ዘካተል ፊጥርን ሰብስቦ ለድሃ ለሠራተኞች ማከፋፈል፤ ጓደኛሞች ጠቃሚ መጣጥፎች፣ ካሴቶችንና ሲዲዎችን መለዋወጥ፤ ጓደኛን ቤተሰቦች በአንዱ ጓደኛ ቤት ውስጥ ለፍጡር መጋበዝ፤ ፍጡሩን ቀለል ማድረግ፤ ጓደኛሞችን በጠቅላላ በምግብ ቤት ወይም በመስጅድ ክበብ ውስጥ በፊጡር ላይ ማሳተፍ

(ኢፍጣር ጀማኢ)

በካምፓኒ ወይም በፋብሪካ ውስጥ ሁሉም በዙሪያው የሚሰባሰቡበት አንድ መፈክር(መልዕክት) ማስቀመጥ፤ አንዳንድ ጓደኞችን በረመዳን ወር ዑምራ እንዲሰሩ ማበረታታትና ለሐጅ ዝግጅት ማድረግ።

በመኪና ውስጥ ቁርኣንን በካሴት ማዳመጥ፣ የጠዋትና የማታ አዝካሮች ካሴት መከታተል፤ ከጓደኞችና ከተሳፋሪዎች ጋር ልዩ የረመዳን ስጦታ መለዋወጥ፤ ወደ ቤታችን ስንመለስ ማፍጠሪያ ማዘጋጀት (የታሸገ ቴምር)፤ ፀሐይ በምትጠልቅበት ጊዜ ዱዓ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ማስታወስ፤ በየቀኑ ኸዋጢርን መነጋገር አስፈላጊ ስለመሆኑ መወያየት፤
በመንገድ ላይ ውድድር ማድረግና አስቸኳይ ሽልማቶችን ማዘጋጀት፤
በመንገድ ላይ ኢስቲግፋርና ተሲቢህ ማድረግ፣ ቁርዐን በኪስ ይዞ መዞርና መቅራት።

ጥሩውን ሰምተው ከሚተገብሩት ያድርገን፤ የተከበረውን ወር ይቀበለን ዘንድ አላህ (ሱ.ወ) እንለምን!

Address

Addis Ababa, Ethiopia, Saudi Arabia, Jeddah And Kenya
Addis Ababa
[email protected]

Website

http://www.instagram.com/muslim.brothers.islamic.image, https://youtube.com/@musl

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Muslim Brothers posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share