Getesemani Gospel Ministry

Getesemani Gospel Ministry A Gospel is Good News

24/08/2023
07/12/2020



በነብይ ኪሩቤል

03/09/2020

ድንቅ ትምህርት

 በአብዛኛው ለሰዎችም ይሁን ለራሳችን በምንፀልይበትወቅት በራሳችን አቅምና ኃይል ወይም ብርታትና ድካም ላይ ስንመረኮዝ ይታያል ። ነገር ግን ጌታ የስሙን ኃይል በእምነት ተጠቅመን እንድንፀልይ...
12/06/2020



በአብዛኛው ለሰዎችም ይሁን ለራሳችን በምንፀልይበት
ወቅት በራሳችን አቅምና ኃይል ወይም ብርታትና ድካም ላይ ስንመረኮዝ ይታያል ።
ነገር ግን ጌታ የስሙን ኃይል በእምነት ተጠቅመን እንድንፀልይና እንድንቀበል አስተምሮናል።

ዮሐንስ 16 : 23 - 24
" በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።"

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ሊነግራቸው የፈለገው ነገር ግልፅ ነው ። አብ ፀሎታችሁን የሚሰማው በእኔ ስም በእምነት ስትለምኑት ነው በማለት አስረዳቸው ።

ወገኖቼ እኛም በዚህ ዘመን የጌታን ስም በህይወታችን ከፍ እንዲል በማድረግ በስሙ የለመንነውን ሁሉ ልንቀበል ቃሉ የስሙን ስልጣን ሰጥቶናል ።



ማርቆስ 16 : 17-18
" ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።"

"በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ" _ ከጨለማ መናፍስት አየሩ ላይ ከሚሰሩ ኃይላትና ስልጣናት በላይ ያደረገን የጌታችን የኢየሱስ ስም ነው ።
ወገኖቼ አጋንንትን ማውጣት ለአንድ ለተቀባ ሰው ብቻ የተሰጠ አይደለም ። እንደ እምነታችን መጠን እንጂ የስሙ ኃይል የተሰጠው ለሚያምን ሁሉ ነው ።

አስተውሉ ዲያብሎስን ከሚያስደነግጠው ነገር ዋናውና አንደኛው ስሙን በሚወድና በሚያከብር ህይወቱን ለጌታ ከሰጠ ሰው በእምነት የሚወጣውን የጌታችንን የኢየሱስን ስም ነው ።

የስሙን ኃይል አጥብቆ የተረዳና የሚጠቀምበት ህዝብ እጅግ የተባረከ የጌታ ህዝብ ነው ።

እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብከዋለን
04/06/2020

እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብከዋለን

"መታዘዝ"ዘፍጥረት 22 (አዲሱ መ.ት)¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹ ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” አለው። እርሱም “አቤቱ አለሁ” አለ።² እግዚአብሔርም (ኤ...
27/02/2020

"መታዘዝ"

ዘፍጥረት 22 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” አለው። እርሱም “አቤቱ አለሁ” አለ።
² እግዚአብሔርም (ኤሎሂም)፣ “የምትወደውን አንዱን ልጅህን፣ ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።
³ በማግስቱ ጠዋት አብርሃም ማልዶ ተነሣ፤ አህያውን ጭኖ፣ ሁለት አገልጋዮቹንና ልጁን ይስሐቅን ይዞ፣ ለመሥዋዕት የሚበቃውን ዕንጨት ከቈረጠ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞውን ጀመረ፤
⁴ በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ቦታውን ከሩቅ ተመለከተ፤
⁵ አገልጋዮቹንም “እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቈዩን፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ሰግደን እንመለሳለን” አላቸው።
⁶ አብርሃም ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን ዕንጨት ወስዶ፣ ልጁን ይስሐቅን አሸከመው፤ እሳቱንና ቢላዋውንም ራሱ ያዘ። ሁለቱም አብረው ሄዱ።
⁷ ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን፣ “አባቴ ሆይ” አለው። አብርሃምም፣ “እነሆኝ፤ አለሁ ልጄ” አለው። ይስሐቅም፣ “እሳቱና ዕንጨቱ ይኸው፤ ነገር ግን የሚቃጠለው መሥዋዕት የት አለ?” ብሎ ጠየቀ።
⁸ አብርሃምም፣ “ልጄ ሆይ፤ ለሚቃጠለው መሥዋዕት የሚሆነውን በግእግዚአብሔር ራሱ ያዘጋጃል (ኤሎሂም ይሬህሎ)” አለው። ሁለቱም አብረው ጒዞአቸውን ቀጠሉ።
⁹ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወዳመለከተው ቦታ እንደ ደረሱ፣ አብርሃም መሠዊያ ሠራ፤ በላዩም ላይ ዕንጨት ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ዕንጨት ላይ አጋደመው።
¹⁰ ከዚያም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላዋውን አነሣ።
¹¹ የእግዚአብሔር (ያህዌ) መልአክ ግን ከሰማይ፣ “አብርሃም፤ አብርሃም፤” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ።
¹² እርሱም፣ “እጅህን በብላቴናው ላይ አታሳርፍ፤ ምንም ጒዳት አታድርስበት፤ እነሆ፤ እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፤ ልጅህን፣ ያውም አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና” አለው።
¹³ አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት በቊጥቋጦ መካከል ቀንዶቹ የተጠላለፉ አንድ አውራ በግ ከበስተ ኋላው አየ፤ ወደዚያው ሄዶ በጉን አመጣና የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው።
¹⁴ ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል (ያህዌ ይርኤ)” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል።
¹⁵ የእግዚአብሔርም (ያህዌ) መልአክ አብርሃምን ከሰማይ ዳግመኛ ጠራው፤
¹⁶ እንዲህም አለው፤ “እግዚአብሔርም (ያህዌ) በራሴ ማልሁ አለ፤ አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና፣
¹⁷ በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት፣ እንደ ባሕር ዳር አሸዋም አበዛዋለሁ። ዘሮችህም የጠላቶቻቸውን ደጆች ይወርሳሉ፤
¹⁸ ቃሌን ስለ ሰማህ የምድር ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።”
¹⁹ ከዚያም አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰ፤ ተያይዘውም ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ኖረ።

ስለ መልካምነቱ እግዚአብሔር ይመስገን
27/02/2020

ስለ መልካምነቱ እግዚአብሔር ይመስገን

እግዚአብሔር ይችላልየጠበቃችሁት ጌታ በነገራችሁ ላይ ሁሉ እጁ ተገለጠ
27/02/2020

እግዚአብሔር ይችላል
የጠበቃችሁት ጌታ በነገራችሁ ላይ ሁሉ እጁ ተገለጠ

13/02/2020

Jesus Is Merciful Lord , Love him More & Follow him as a true Desciple You will Never Regreat .
Have A Blessed Day , In Jesus Name

Address

Gurdsholla , Salitemihret
Addis Ababa
113

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Getesemani Gospel Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Getesemani Gospel Ministry:

Share