09/01/2023
#ጭንቀት
መጨነቅ በእግዚአብሔር አለመታመን እንደሆነ ታውቃላችሁ?
ምን ልላችሁ ፈልጌ መሰላችሁ የሰማይ ወፎች አይዘሩም፣አያጭዱም፣ከዛም በጎተራ ምግብን አያከማቹም ነገር ግን አምላካችን እግዚአብሔር ይመግባቸዋል።
ታዲያ እኛን #በመልኩና #በምሳሌው ፈጥሮን እንዴት ችላ ሊለን ይችላል?
ወዳጆቼ እግዚአብሔር መልካም ነውና ስለ ህይወታቹ በፍፁም አትጨነቁ ምክንያቱም መጨነቅ በእግዚአብሔር አለመታመን ነው።ስለዚህ የምታመልኩትን አምላክ በፍፁም ልብ እመኑት። ይህን ስናደርግ በህይወታችን ስኬትና መከናወን ይሆንልናል።ቀኖቻቹ ያማሩ ይሁኑ፤ተባረኩ
#ኪሩቤል
👇ይህን ድንቅ ቃል በማስተዋል አንብቡት👇
“ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጥ፣ እናንተንም የሚጠቅም እንጂ የሚጐዳ አይደለም።”
ኤርምያስ 29፥11