ኤፍራታ እና አካባቢው ሕብረት Efrata Ena Akababiw Hibret

ኤፍራታ እና አካባቢው ሕብረት Efrata Ena Akababiw Hibret Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኤፍራታ እና አካባቢው ሕብረት Efrata Ena Akababiw Hibret, Religious Center, Addis Ababa.

አጣዬ ፣ ካራቆሬ ፣ ማጀቴ ፣ አላላ ፣ በርጊቢ እና አካባቢው በሙሉ
11/08/2026

አጣዬ ፣ ካራቆሬ ፣ ማጀቴ ፣ አላላ ፣ በርጊቢ እና አካባቢው በሙሉ

የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የላቀ የሥራ አፈጻጸም በአማራ ክልል ከሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መካከል አንደኛ ደረጃ በመውጣቱ የሆስፒታሉ ሥራ ...
02/08/2026

የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የላቀ የሥራ አፈጻጸም በአማራ ክልል ከሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መካከል አንደኛ ደረጃ በመውጣቱ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ መስፍን አስፋው ከክልል ሲመለሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ የኤፍራታና ግድም ወረዳና የአጣዬ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሆስፒታሉ ሠራተኞች፣ የባጃጅ አሽከርካሪዎችና የማኅበረሰብ ክፍሎች በመገኘት በሆስፒታሉ የተገኘውን ውጤት በጋራ በመሆን የስኬቱን ደስታ ተጋርተዋል።
👉 (ኤፍራታ ኮሙኒኬሽን)

ይሄ ሙስሊም ወጣት ልጅ አባን "ልሸኝዎት" ብሎ መኪናው ውስጥ  ያስገባቸዋል። መንገድ እንደጀመሩ "ለወትሮዬ እናቶችን ነበር የምሸኘው፣ እርስዎን ሳይ ግን ወላሂ አልፌ መሄድ አልቻልኩም!" አላ...
17/07/2026

ይሄ ሙስሊም ወጣት ልጅ አባን "ልሸኝዎት" ብሎ መኪናው ውስጥ ያስገባቸዋል። መንገድ እንደጀመሩ "ለወትሮዬ እናቶችን ነበር የምሸኘው፣ እርስዎን ሳይ ግን ወላሂ አልፌ መሄድ አልቻልኩም!" አላቸው።

አባም "እንዲህ ያለህ ማር የሆንክ ልጅ ከየት ተገኘህ?" ብለው ምርቃት ሲያሽጎደጉዱለት "አላህአምዱላሂ" ደስ እያለኝ የማደርገው ነው፣ የሚሄዱበት ድረስ ነው የማደርስዎት" እየተባባሉ ከጀሞ ሚካኤል ገላን አድርሷቸው ሊመለስ ሲል ስልኩን ወሰዱ፣ እደውልልሀለሁ ወንድሜ አሉት፣ ሁሌም እጸልይልሀለሁ" አሉት እሱም "እሺ አባቲ እኔም እዘይሮታለሁ" ካላቸው በኋላ ወርደው ሄዱ።

ይቺ ናት ኢትዮጵያ! ለዚህ ነው በወጣቶቻችን ተስፋ የማደርገው! ልጁን የምታውቁት ምርቃቴን አድርሱልኝ! የሚኮረጅ መልካም ስራህን አብዝተህ እንድትባረክበት ጤና እና እድሜ ይስጥህ በሉት!

19/03/2026
14/03/2026

የካራቆሬ ጥያቄ
👉ፖለቲካዊ አይደለም
👉 የመልማት እንጂ።🙏
👉 ባንኩ ይፈቀድላት 👍

🔉 ካራቆሬ ትጣራለች🔊።።።።።።።።።።።።።።።።።።።በአመሰራረቷ በአካባቢዋ ያሉ የዞን ከተሞች እንኳን ሳይቀር በእድሜዋ ትተካከላቸዋለች። እድሜ ጠገብ የአሁኗ ቀበሌ የቀድሞ ከተማ ነች። ይህ ደ...
13/03/2026

🔉 ካራቆሬ ትጣራለች🔊
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በአመሰራረቷ በአካባቢዋ ያሉ የዞን ከተሞች እንኳን ሳይቀር በእድሜዋ ትተካከላቸዋለች። እድሜ ጠገብ የአሁኗ ቀበሌ የቀድሞ ከተማ ነች። ይህ ደግሞ የማይካድ ሃቅ ነው። ነገር ግን አሁን ላይ ያለችበት እድገት ግን የተተወችና የተረሳች ያስመስላታል። ከደሴ ፣ ከወልድያ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ እንዲሁም ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ እንኳን ሳይቀር እጅግ በጣም በርካቶች መኪናዎቻቸውን አቁመው አገር አቋራጭ አውቶብሶችም ጤፋቸውን ገዝተው ጭነው ፣ የሸንኮራ አገዳው ፣ የሙዙ እናም ሌሎች ፍራፍሬዎችንም ጭምር ሸምተው ከተማይቱን እና ማሕበረሰቡን አመስግነው ይሰናበቷታል።
ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ ስንመለከታት በተወሰነ ደረጃ ክፍቶች የበርካታ መሠረተ ልማቶችን ተጠምታለች፣ ችላም ተብላለች ቢባል ማጋነን አይሆንም።
የተከበሩ የካራቆሬ ተወላጆች ፣ በካራቆሬ ምድር ላይ ተወልዳችሁ በተለያዩ አካባቢዎች የምትኖሩ ውድ የካራቆሬ ተወላጅ ዲያስፖራዎች የተከበሩ ሊቀ መንበር የከተማዋ አስተዳዳሪ አቶ አዲስ በረደድ እንዲሁም የተከበሩ የወረዳችን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበራ መኮንን ፣ የካራቆሬ ከተማ ወዳጆቿ የመልማት ፍላጎቷ የሚያስደስታችሁ በሙሉ 👉 ከባንክ ጀምሮ ሌሎችም መሠረታዊ ፍላጎቶች ለአካባቢው ማሕበረሰብ እንዲሟሉ የበኩላችሁን ትወጡ ዘንድ ለመጠየቅ እንወዳለን።!!!💚💛❤
ለምታደርጉት አፋጣኝ ምላሽ ከወዲሁ እናመሰግናለን🙏
የካራቆሬ ወጣቶች!!!




ኤፍራታ እና አካባቢው ሕብረት Efrata Ena Akababiw Hibret

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኤፍራታ እና አካባቢው ሕብረት Efrata Ena Akababiw Hibret posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share