ገዳሜ ተዋህዶ_Gedame tewahido

ገዳሜ ተዋህዶ_Gedame tewahido ቤተክርስቲያን ዘኢትዮጵያ

  ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ-መላእክት አንዱ ነው። ሊቀ-መላእክትነቱም ❝መናብርት❞ በሚባሉ መላእክት ላይ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊትም ለማማለድና ትእዛዝ ለመቀበል ከሚቆሙት ሰባቱ መላ...
07/09/2026

ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ-መላእክት አንዱ ነው። ሊቀ-መላእክትነቱም ❝መናብርት❞ በሚባሉ መላእክት ላይ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊትም ለማማለድና ትእዛዝ ለመቀበል ከሚቆሙት ሰባቱ መላእክት ሦስተኛው መልአክ ሩፋኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ለሰውና ለእንስሳት ርኅሩኅ መልአክ ነው፡፡ በርኅራኄውም የሰው ልጆች ምሕረትን፣ ብዕልና ክብርን ያገኙ ዘንድ ይልቁንም የመካኖችን ማኅፀናቸውን ይፈታ ዘንድ ወላጆችም ያለ ጽኑ ምጥ ይወልዱ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቀርቦ እንደሚለምን በቅዱሳን ዘንድ በስፋት የታወቀ መልአክ ነው፡፡

በዕብራይስጥ ቋንቋ ❝ሩፋ❞ ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት፣ መስተፍሥሒ፣ ድንቅ ማለት ነው፡፡ ❝ኤል❞ ማለትም አምላክ ማለት ስለ ሆነ ሁለቱ ቃላት ሲጣመሩ ሩፋኤል የሚል ይሆናል፡፡ ይህም ከአምላክ የተሰጠ ድንቅ ፈውስ ማለት ነው፡፡

❝ስሙሂ ብሂለ ሩፋኤል መስተፍሥሒ ወመድምም ብሂል ወትርጓሜሁ ፈውሰ አምላክ ውእቱ — ሩፋኤል የተባለ ስሙ ደስ የሚያሰኝ ትርጓሜውም ድንቅ የአምላክ ፈውስ❞
— እንዳለ (ድርሳነ ሩፋኤል ዘጥር) እርሱም የሰዎች ነፍሳትን በምልጃው ለማዳን የተሾመ የዋህ መልአክ እንደ ሆነ ነቢዩ ሄኖክ:-
❝ሩፋኤል ፩ዱ እመላእክት ቅዱሳን ዘመናፍስተ ሰብእ — ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ሩፋኤል በሰዎች ነፍሳት ላይ የተሾመ ነው❞

— (ሄኖ፮÷፫) ካለ በኋላ በሌላ አንቀጽ ሁለተኛውም በበሽታው ሁሉ ላይና በሰው ልጆች ቊስል ላይ የተሾመ ❝ቅዱስ ሩፋኤል ነው❞ በማለት ያስረዳናል (ሄኖ፲፥፲፫)።

የነፍሳት ጠባቂ ለመሆኑ መጽሐፈ ሜላድ ነፍሳትን ለመጠበቅ በሰዎች ነፍሳት ላይ ከተሾሙ ቅዱሳን መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው ይላል (መጽሐፈ ሜላድ ዘጥቅምት)

❝የነፍስ ጠባቂ ለሆነ ሩፋኤል ሰላምታ ይገባል

— (ተአምኆ ቅዱሳን ዘሰሉስ) ቅዱስ ሩፋኤል ለሄኖክ መካነ ነፍሳትን እንዴት እንደ ሆነ ተርጕሞ አስረድቶታል።

ዳግመኛም ❝ሩፋኤል❞ ማለት ልቡናን ደስ የሚያሰኝ፤ ያዘኑትን የሚያረጋጋ፤ መፈውስ፣ የዋህ፣ ይቅር ባይ ማለት ነው፡፡

❝ወአንሰ ስምየ ሩፋኤል መስተፍሥሔ አልባብ የዋህ ወኄር ወመሐሪ ላዕለ ኀጥአን — የመላእክት አለቃ ሩፋኤልም ለሐዋርያት ስሜ ሩፋኤል ነው፤ ትርጓሜውም የዋህና ሰውን አስደሳች፤ ቸር ለኃጥአን ይቅር ባይ ማለት ነው፤ ኃጥአንን ስለበደላቸው ወደ እግዚአብሔር አላሳጣቸውምና፥ ነገርግን ስለ የዋህነቴና ስለ ማዳኔ የሰውንም ልጅ እጅግ ስለ መውደዴ ከኃጢአታቸው ተመልስው ንስሓ ይገቡ ዘንድ በዘመን ላይ ዘመንን እጨምርላቸዋለሁ አስፈጻሚ መላእክትንም እልክላቸዋለሁ❞

— እንዳለ ድርሳነ ሩፋኤል ዘጳጕሜን።

የሰማያትን መክፈቻ ስለያዘ ሕፃናትን ገና በናታቸው ማኅፀን ጀምሮ ይጠብቃቸዋል። ኃጢአተኞችን ለንስሓ እያበቃ በንስሐ የተመለሱ የቅዱሳን ነፍሳትን ወደ ገነት፤ ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡም ያደርጋል፡፡ በወርኃ ጥር የሚነበብ ድርሳኑ እንዲህ ይላል:-

❝አዳም ሚስቱ ሔዋንን ዐወቃት፡፡ ያን ጊዜም የዲያብሎስ ሠራዊት ከሚስቱ ሔዋን ማኅፀን የአዳምን ዘር ያጠፉ ዘንድ በፅንስ በሽታ ተመስለው ተነሡ:: ስለዚህም እግዚአብሔር ሊቀ-መላእክት ቅዱስ ሩፋኤልን መርጦ ከሌሎች ይልቅ የሰውና የእንስሳን ማኅፀን ይፈታ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠው:: ለደካሞች የሚያዝን፤ የሚራራ፤ የተበደሉትንም የሚበቀልላቸው ልዑል እግዚአብሔር ይኸን ሥልጣን ባይሰጥ ኑሮ ከዲያብሎስ ሠራዊት የተነሣ አጋንንት ሾተላይ፣ የሐኬት ቊራኝነት የተነሣ ይህ ዓለም ያለ ፍጥረት ምድረ በዳ ሆኖ በቀረ ነበር። ርጉም ዲያብሎስ ከኃጥአን ማኅፀን ከሚገኙ ልጆች በቀር ደጋግ ጻድቃን እንዲፈጠሩ አይሻም
ና።❞

ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

‹‹ጳጉሜ›› የሚለው ስያሜ ከግሪክ ቃል ‹‹ኤፓጉሜኔ›› የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው። ጳጉሜን የዓመቱ 13ኛ ወር ስትሆን በዘመነ ዮሐንስ 6 ቀናት፣ በሌሎቹ ዘመናት ደግሞ 5 ...
07/09/2026

‹‹ጳጉሜ›› የሚለው ስያሜ ከግሪክ ቃል ‹‹ኤፓጉሜኔ›› የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ‹‹ጭማሪ›› ማለት ነው።

ጳጉሜን የዓመቱ 13ኛ ወር ስትሆን በዘመነ ዮሐንስ 6 ቀናት፣ በሌሎቹ ዘመናት ደግሞ 5 ቀናት ትኖራለች።

ይህች ወር ካለፈው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከክረምትም ወደ ጸደይ የምንሸጋገርባት የመሸጋገሪያ ጊዜ ናት። ስለዚህም የዓለም ፍጻሜንና ዳግም ምጽአትን ለማሰብ ልዩ ትርጉም አላት። ጳጉሜን የክረምት ማብቂያ እንደሆነች ሁሉ፣ ምጽአትም የዚህ ዓለም ኑሮ ማብቂያና ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት መሸጋገሪያ ናት።

እንደ አዲሱን ዓመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ ሆና እንደምታገለግል፣ ምጽአትም ጻድቃን አዲሲቷን ምድርና መንግሥተ ሰማያትን የሚወርሱበት ዕለት ናት።

በጳጉሜን 3 የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል ሲከበር፣ ርኅዎተ ሰማይ ማለትም ሰማያት የሚከፈቱበት ዕለት በመሆኑ ምእመናን በትጋት ይጸልያሉ። ቅዱሳን መላእክትም በምልጃቸው ጸሎታችንን ያሳርጉልን ዘንድ እንማጸናቸዋለን።

ከፈቃድ አጽዋማት መካከል የሆነው ጾመ ዮዲትም በዚህ ወር ይጾማል።

🙏 ወርኃ ጳጉሜንን በመልካም ሥነ ምግባር ታንጸን፣ በሃይማኖት ጸንተን፣ ለዘመነ ሉቃስ እንድንደርስ አምላካችን እግዚአብሔር ይርዳን። አሜን! 🙏

 ~~~~~~~~~‹‹መልዐኩ ቅዱስ ሱርያል›› ወር በ27 የሚታሰብ ሲሆን ከ7ቱ ሊቃነ መላዕክት አራተኛው ሊቃነ መላዕክት ነው።ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብ...
01/09/2026

~~~~~~~~~

‹‹መልዐኩ ቅዱስ ሱርያል›› ወር በ27 የሚታሰብ ሲሆን ከ7ቱ ሊቃነ መላዕክት አራተኛው ሊቃነ መላዕክት ነው።

ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም።

የመላእክት መዓርግ ሲነገር ሚካኤል: ገብርኤል: ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው።

በሦስቱ ሰማያት ካሉት ዘጠኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ (የሥልጣናት) መሪ (አለቃ) ነው። መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው። ለኖኅ መርከብን ያሳራው: ከጥፋት ውኃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::

በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: ቅዱስ ሱርያል በሌላ ስሙ "እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት ነው።

አባታችን ኖህን ከጥፋት ውሃ መርከብን ሰርቶ ያሻገረው ቅዱስ ሱርያል ነው አብዝተን ስሙን እንጥራው እኛንም ከክፉ ዘመን እንዲያሻግርን እንለምነው።

መልዐኩ ቅዱስ ሱርያል በምልጃው አይለየን🙏

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜንእንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ዕረፍት ፤ ለጻድቁ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ በዓለ ዕረፍት ፤ ለእናታችን ቅድስት ክርስቶ...
29/08/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ዕረፍት ፤ ለጻድቁ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ በዓለ ዕረፍት ፤ ለእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዓለ ዕረፍት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ

ነሐሴ ፳፬ በዓለ ዕረፍቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ ዓ.ም ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው«አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡

በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በአሥራ አምስት ዓመታቸው ከ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ /ጌርሎስ/ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ በዚህም ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጓደኞቻቸው ጋር ወደ ዱር አደን ሄደው ሳለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ ለኢትዮጵያ ውያን ክርስቲያኖች ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ መረጣቸው። ስማቸውንም «ተክለ ኃሃይማኖት» አለው፡፡ ትርጓሜውም የኃይማኖት ፍሬ ማለት ነው፡፡

አባታችንም ሐዋርያዊ ጉዟቸውን ሲጀምሩ /ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ ፳፰ ቁ ፪ - ፫/ ትሕትና በተሞላበትና በተሰበረ ልብ ወደ ፈጣሪያቸው ከለመኑ በኋላ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሃይማኖት መልሰዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ፀሐይ ተብለዋል፡፡

አባታችን በዳዊት ፀሎት ከነቢያት ምስጋና ሌሊቱን ሙሉ ይተጉ ነበር በያንዳንዱ መዝሙርም 10፣ 10 ስግደትን ይሰግዱ ነበር፡፡ በሕዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው (አወጣቸው) ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበረን “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት አጥነዋል ፡፡ በሐይቅ 10 ዓመት በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡ ለ22 ዓመት ቆመው በመፀለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በፀሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በፀሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ አባታችን ባረፉ 54 ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም ለአባታችን ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል ፡፡
የጻድቁ መላ ዕድሜያቸው 99 ዓመት ከዐሥር ወር ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ የጻድቁን ፅንሰታቸውን መጋቢት 24 ቀን፣ልደታቸውን ታኅሣስ 24 ቀን፣ ስባረ ዐፅማቸውን ጥር 24 ቀን፣ ዕረፍታቸውን ነሐሴ 24 ቀን፣ ፍልሠተ ዐፅማቸውን ግንቦት 12 ቀን እግዚአብሔርን በማመስገን ጻድቁን በማክበር በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ታከብራለች፡፡ የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ትሁን አሜን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

🔴 🔴⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳ #  ደብረ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 572 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን...
19/08/2026

🔴 🔴
⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳ #

ደብረ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 572 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ምሳሌና ትንቢት ተነግሯል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትበትንቢቱ “ታቦርና አርሞንኤም በስም ደስ ይላቸዋል” ብሎ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን በዚህ ተራራ ላይ ገልጧል /መዝ. 88፥12/፡፡ በዘመነ መሳፍንት ባርቅ ሲሣራን ከነሠራዊቱ ድል ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነው፡፡ ምሳሌነቱም ባርቅ የጌታችን ሲሣራ ደግሞ የአጋንንት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር ክብሩን በመግለጥ በአይሁድ እያደረ አምላክነቱን እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸውን አጋንንት ድል የማድረጉ ምሳሌ ነው /መሳ. 4፥6/፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱንበቂሳርያ “የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ከጠየቃቸው ከስድስት ቀን በኋላ አዕማድ ተብለው የሚጠሩ ሦስቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ ረጅም ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ በዚህ እንሥራ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡፡ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ ሐዋርያት ይህንን ሰምተው የጌታችንን መለኮታዊ ክብር አይተው በፊታቸው ወደቁ እጅግ ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችንንም ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ በዚህ መልኩ አምላክነቱን ገለጠላቸው /ማቴ. 17፥1-10/፡፡

🔴 አዕማደ (የምስጢር) ሐዋርያት ለምን ተመረጡ?

አዕማደ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን “አዕማድ ሐዋርያት” እያለ ጠርቷቸዋል /ገላ. 2፥9/፡፡ ስያሜውን ያገኙበት ዋናው ምክንያት የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያን በሓላፊነት ያስተባብሩ ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህን በተጨማሪ ጌታችን በኢያኢሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ፣ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይና በደብረ ታቦር ምስጢረ መለኮቱን ሲገልጥ ከእሱ ስላልተለዩና ይዟቸው ስለሔደ ነው /ማር.5፥37-43/፡፡

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተመረጡበትን ምክንያት ሲያትቱ እንዲህ ብለዋል፡፡ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ሃሳብ እንዲወጡ ከብልየታቸው እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሕማማቱ በሞቱ ቤዛ የሚሆነን አምላክ “ልሰቀል ነው” ባላቸው ጊዜ “አይሁንብህ” ብሎት ነበር፡፡ እንዲህ ያለው ሃሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኀነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው ብሏልና “አይሁንብህ” አለ፡፡ /ማቴ. 16/ በሌላም ስፍራ እንዲሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንግዲያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት ይጠይቃል፡፡ /ማቴ.19/፡፡ ጌታ ግን ዋጋችሁ ሰማያዊ ክብራችሁ ዘላለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/ አድርሶ ብርሃነ መለኮትን ገልጦ ተስፋውን ነገራቸው፡፡

ሁለቱ ወንድማማች ደቀ መዛሙርትም እናታቸውን ልከው ሹመት ሽልማት መዓርግ ለምነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን በደብረ ታቦር “በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ነገር” ስለሞቱ እንዲነጋገሩ አደረገ፡፡ ሞቱ እርግጥ ሆነ ማለት ነው፡፡ አባቱም “ኦሆ በልዎ ለክርስቶስ”፤ እሺ በሉት እርሱን ስሙት፡፡ ሞቱ እርግጥ በመሆኑ ከልባቸው እንዲጠፋ መርጦ ወደ ቅዱስ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል፡፡

“እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዲል /ሚል 3፥6/ በእርሱ ዘንድ ወረት የለም፡፡ አስቀድሞ ከተዓምራቱ ከምሥጢሩ አይለያቸውም ነበርና ብርሃነ መለኮትን ለማየት አበቃቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለማወቅ፣ ለመማር፣ ለመጠየቅ ያሳዩት ትጋት ምስጢር ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ምስጢር ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦ የሚቀር አይደለም፡፡ እስከ ዓለም ፍፃሜ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሲገለጥ፣ በመረጣቸውም ሲነገር የሚኖር ነው፡፡

ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስ “አልክድህም አልተውህም” የሚለው /ማቴ. 26፥35/ ቢወድደው አይደለምን? ፍቅሩን መግለጡ ለክብር አብቅቶታል፡፡ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም “ጽዋዬን ልትጠጡ አትችሉም” ቢላቸውም /ማቴ. 20፥22/ አንዳችን በቀኝ ሌላችን በግራ ሆነን አብረንህ እንሞታለን ሲሉ በምስጢር ለምነዋል፡፡ ሞታቸውን ከሞቱ ጋር መደመራቸው ፍቅራቸውን መግለጣቸው ነው፡፡

🔴 ከተራራው ግርጌ

ከቅዱሱ ተራራ ግርጌ ዘጠኙ ደቀ መዛሙርት ተቀምጠዋል፡፡ ነቢዩ “አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውስ ተራራህ ማን ይኖራል” /መዝ.14፥1/ በማለት ጠይቆ ወደ ተቀደሰው ተራራ የሚወጡ ሰዎች ምን ዓይነት ሕይወት ያላቸው ሊሆን እንደሚገባ ሲገልጥ “… በአንደበቱ የማይሸነግል፤ በባልንጀራው ላይ ክፉትን የማያደርግ … በንፁሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል ….” በማለት የጠቀሳቸው ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ /መዝ. 14፥1-5/ ወደ ቅድስናው ስፍራ ወጥቶ ምስጢር ለማየት ብቃት ያልነበረው ይሁዳን ለመለየት አምላክ ባወቀ ዘጠኙን ከተራራው ግርጌ አቆይቷቸዋል፡፡

“የኃጥእ ዳፋ ጻድቁን ያዳፋ” የሚል ብሂል አለ፡፡ ይህ አባባል ግን ከተራራዉ ግርጌ ለቀሩት ደቀ መዛሙርት አይሆንም፡፡ ይሁዳን በጥበብ ከምስጢር ለየው እንጂ ጌታ ስምንቱ ደቀ መዛሙርቱን የምስጢሩ ተካፋይ አድርጓቸዋል፡፡ ለጥፋቱ ምክንያት እንዳያገኝ ከምስጢሩ ቢለየኝ ከሞቱ ገባሁበት እንዳይል በጥበብ ይህን አደረገ፡፡ ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ግን በንጹሕ ልቡና ከተራራው ግርጌ ተቀምጠውም ምስጢር አልተከለከላቸውም፡፡ ምክንያቱም “ልበ ንጹሐን ብፁዓን ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና” /ማቴ.5/፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ እግዚአብሔርን ለማየት ለሚወዱ “ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚቻለው የለምና” እንዲል፡፡ /ዕብ.11/፡፡

🔴ሙሴና ኤልያስ ለምን ተመረጡ?

ሙሴንና ኤልያስን ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት የባሕርይ አምላክ መሆኑን እንዲመሰክሩ ነው፡፡ ሙሴን ከመቃብር ተነሥቶ ስለጌታችን እንዲህ የሚል ምስክርነት ሰጥቷል፡- “እኔ ባሕር ብከፍልም፤ ጠላት ብገድልም፤ ደመና ብጋርድም፤ መና ባወርድም እስራኤልን ከክፋታቸው መልሼ ማዳን ያልተቻለኝ ደካማ ነኝ፤ የእኔን ፈጣሪ እንዴት ሙሴ ይሉሃል? የሙሴ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” ኤልያስም ደግሞ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ “እኔ ሰማይ ዝናብ እንዳይሰጥ ብለጉም፣ እሳት ባዘንብም፣ እስራኤልን ከክፋታቸው ማዳን የማይቻለን ነኝ እንዴት የእኔን ፈጣሪ ኤልያስ ነህ ይሉሃል? የኤልያስ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” ብለው የባሕርይ አምላክነቱን በደብረ ታቦር ላይ መስክረዋል፡፡ በማቴ.16፡14 ላይ “አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።” ይላልና፡፡

ሙሴና ኤልያስ የተመረጡበት ሌላው ምክንያት ሙሴ “ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም” ተብሎ ስለተነገረለት /ዘጸ.33፡23/ ኤልያስ “በኋለኛው ዘመን ምስክሬ ትሆናለህ” ስለተባለ ያንን ለመፈጸም ነው፤ ካገቡት ሙሴን ከደናግል ኤልያስ ያመጣቸው መንግሥተ ሰማያት በሕግ የተጋቡ ሕጋውያንና ሥርዐት ጠብቀው የሚኖሩ ደናግላን እንደሚወርሷት ለማስተማር ሁለቱን መርጧቸዋል፡፡

🔴የደብረ ታቦር ምሳሌነት

የወንጌል ምሳሌ ነው፡፡ ተራራ ሲወጡ በጣም ያስቸግራል፤ ከብዙ ድካምና ውጣ ውረድ በኋላ ተራራውን ጨርሰው ከላይ ሲወጡ ግን አባጣ ጎባጣውን ሜዳና ገደሉን ያሳያል፡፡ ወንጌልንም በሚገባ ከተማሯት ጽድቅን ከኃጢአት ለይተን እንድናውቅ ታደርገናለች፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በደብረ ታቦር ምስጢረ ሥላሴ እንደተገለጠ በቤተ ክርስቲያንም የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታል፡፡ ተራራ መሠረቱ ከመሬት አናቱ ከሰማይ እንደሆነ ሁሉ፤ ቤተ ክርስቲያንም መሠረቷ በምድር ሲሆን ራሷ በሰማይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮቿ የተጠሩት ከምድር (ከዓለም) ሲሆን ክብራቸው ግን በሰማይ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እኛስ ሀገራችን በሰማይ ነውና›› እንዲል /ፊልጵ. 3፥20/፡፡

የደብረ ታቦር ተራራ ይህን ሁሉ ምስጢር የያዘ በመሆኑ በክርስትና ታሪክ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮት የተገለጠበት፣ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው፤ በምእመናንም ዘንድ ቡሔ ይባላል፡፡ የቡሔ በዓል ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ የያዘ በመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ልናከብረው ይገባናል፡፡

🔴ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡

ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፤ የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

🔴ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር ይዞ የሚከወን ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ እንዲሁም ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፣ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

🔴ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ የት መጣ ግን በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ ምሳሌ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡

🔴ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ቡሄ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር፡፡🔴በዓለ ደብረ ታቦር🔴
⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳

ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

✝ ጽሕምን መላጨት ይገባልን? ✝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ነገር ሥርዓት አላት። ከበርካታ ሥርቶቿ ውስጥም የጸጉር አያያዝ አንዱ ነው። የራስ ጸጉሩን የሚያሳድግ ወንድ እየበረከተ ያለው ...
09/08/2026

✝ ጽሕምን መላጨት ይገባልን? ✝

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ነገር ሥርዓት አላት። ከበርካታ ሥርቶቿ ውስጥም የጸጉር አያያዝ አንዱ ነው። የራስ ጸጉሩን የሚያሳድግ ወንድ እየበረከተ ያለው አንድም ካለማወቅ ሲሆን ሲቀጥልም የፈረንጅ ፋሽን ተከታይ በመሆን ነው። አባቶቻችን ግን ጸሩሩን የሚያሳድግ ወንድ እንዳይኖር አስረግጠው ተናግረዋል። (፩ኛ ቆሮ ፲፩፥፲፬)

ወንድ ልጅ ከወጣትነት የዕድሜ ደረጃ ላይ ሲደርስ በጉንጭ እና በአገጩ ገጹ ጸጉር ያበቅላል። ይህ ጸጉር #ጽሕም ተብሎ ይጠራል። በተለምዶ ደግሞ "ጢም" ወይም "ጺም" እየተባለ ይጠራል። ከዚህ የተፈጥሮ ጸጋ ጋር ተያይዞ ጥያቄዎች ይነሣሉ። ጥያቄውም ጽሕምን መላጨት ይገባል ወይስ አይገባም ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚል ነው። እስኪ በጉዳዩ ላይ ከቅዱሳት መጻሕፍት ትቂት ቃላትን እንመልከት፦

❖ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ በኦሪት ዘሌዋውያን እንዲህ ይላል፦ «ወኢትግበሩ ለክሙ ቈናዝዕተ እምጸጉረ ርእስክሙ - ከራስ ጸጉራችሁ ቁንጮ ጉተና አታውጡ» ይልና «ወኢትላጽዩ ጽሕመ ገጽክሙ - የፊታችሁንም ጽሕም አትላጩ» (ዘሌ ፲፱፥፳፯) በማለት አስረግጦ ይገልጣል።

❖ ከክርስቶስ የተማሩ ንጹሐን ሐዋርያት ደግሞ የቀኖና መጽሐፍ በሆነው በመጽሐፈ ዲድስቅልያ እንዲህ ያዝዛሉ፦ «ወባሕቱ ኢመፍትው ለነ ንላጺ ጽሕመነ፤ ወኢንወልጥ ፍጥረተ ብእሲ ውስተ ካልዕ ግዕዝ - ነገር ግን ጽሕማችንን እንላጭ ዘንድ ለእኛ አይገባም። የሰውንም ባሕርይ ወደ ሌላ አንለውጥ።» (መጽሐፈ ዲድስቅልያ አንቀጽ ፩፥፳፱) ይህም ማለት ጽሕምን መላጨት ከተፈጥሮ ጸጋ መራቅ ነው ማለት ነው። በተለይም ደግሞ የተለያዩ ጌጣጌጦችን በጽሕም ላይ በማውጣት ብዙ የሚደክም አለ። ቅባት ሲቀባ፣ በማበጠሪያ ሲያበጥር የሚውል ሞኝ ምእመንም አለ።

❖ አርዮስን ያወገዙ፣ ሃይማኖትን ያቀኑ አባቶቻችን ሠለስቱ ምዕትም (፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት) በጉዳዩ ላይ እንዲህ በማለት ጽፈዋል፦ «ወኢትንሣእ እምጽሕምከ ከመ ትላጺ ርእሰከ - ራስህን በተላጨህ ጊዜ ጽሕምህን አትንካ/አትላጭ» (ሃይ/አበው ምዕ ፳፩፥፲፬)

❖ መጽሐፈ ምዕዳን በተባለው መጽሐፍ ላይ ደግሞ ሰባቱ መነኰሳት እንዲህ ይገልጹታል፦ «ጽሕምን ግን መቆረጥ አይገባም፤ አርዓያውን መለወጥ ሴት ነኝ ማለት ነው» በማለት ሆምጠጥ ባለ ቃል ገልጸውታል። እንግዲህ ጽሕሙን የሚላጭ ወንድ «ሴት ነኝ» ማለቱ ነው።

በአጠቃላይ ከምዕመን እስከ ካህን፣ ከጳጳስ እስከ ሊቀ ጳጳስ፣ ሁሉም ሰው ማለትም ሁሉም ወንድ ጽሕሙን ባለመላጨት፣ ቢሆንም እንኳ ቍመቱን ብቻ በማሳጠር ትእዛዝ ማክበር አለበት። ያለፈውን እያሰቡ ማዘከር ሳይሆን «ለዘኃለፈ ይመሐረነ ለዘይመጽእ ይዕበነ - ላለፈው ይማረን ለሚመጣውም ይጠብቀን» እያሉ በቍርጥ ሐሳብ ላለመላጨት መወሰንና ወደ ተግባር መግባት ይገባል። በተለይም ጌጣጌጥ በማውጣት ብዙ ባንሰናከልና ባናሰናክል መልካም ነው እንላለን።

ገዳሜ ተዋህዶ_Gedame tewahido

  ≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡   ፍልሰታ የሚለው ቃል የተገኘው ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ መለየት፣ማረግ፣ወደላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ይይዛል። በእዚህ መሠረትም ጾመ ፍ...
06/08/2026

≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡

ፍልሰታ የሚለው ቃል የተገኘው ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ መለየት፣ማረግ፣ወደላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ይይዛል። በእዚህ መሠረትም ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን የሥጋዋ ከመቃብር መለየት እና ማረግን ያመለክታል። ይህ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከተወሰኑት ሰባቱ አጸዋማት ውስጥ ለዓመቱ የመጨረሻው ጾም ነው።

👉ፍልሰታ ጾም ለምን እንፆማለን?

የፍልሰታ ጾም ከነሐሴ 1 እስከ 15 የሚጾም ሲሆን በቤተ ክርስቲያናችን አስተምሮ መሠረት እመቤታችን ያረፈችው በጥር 21 ቀን ነው። ሐዋርያትም አስከሬኗን ሊቀብሩ ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሔዱ አይሁድ በምቀኝነት ልጇ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል። አሁንም እርሷ ገቢረ ተአምር ልታደርግ አይደል? ብለው አስከሬኗን ተሸክመው የሚሔዱትን ሐዋርያትን በታተኗቸው። በዚህን ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስከሬን ከአይሁድ ነጥቀው በገነት አኖሩት። በስምንተኛው ወር በነሐሴ ሐዋርያት ከነሐሴ 1 እስከ 14 ሁለት ሱባዔ ገብተው ከጌታችን ተቀብለው በጸሎትና በምህላ ቀበሯት። በዚህ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቶማስ የተባለው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወጥቶ ነበር እና መገኘት አልቻለም ነበር።

እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ከላይ እንደተጠቀሰው በነቢያት ትንቢት እንደተነገረላት እንደ ልጇ ተነሥታ ስታርግ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ አገኛት። በዚህን ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት በረከት ቀረብኝ ሲል ተበሳጨ።ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንችን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ እራሱን ከደመና ላይ ሊወረውር ቃጣው። በዚህን ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናናችው ከእርሱ በቀር ትንሣኤዋን ያየ አለመኖሩን ነገረችው።ለምስክርነት እንዲሆንም በቀብሯ ጊዜ የነበረውን ሰበኗን ሰጥታው አረገች።

👉ሞት በጥር፣በነሐሴ መቃብር

ቶማስም ሰበኗን ደብቆ ይዞ ሐዋርያት ካሉበት ደረሰ። ሐዋርያትንም የእመቤታችን ነገር ምን ደረሰ? አላቸው። ሐዋርያትም እመቤታችን ሱባዔ ገብተን ጌታችን አስከሬኗን ከዕፀ ሕይወት አምጥቶ ሰጥቶን በክብር ቀበርናት አሉት። ቶማስም መልሶ ሞት በጥር፣በነሐሴመቃብር?አላቸው።ሐዋርያትም መለሱለት ቶማስ አትጠራጠር። ቀድሞ ጌታችን በተገለጠ ጊዜ ትንሣኤውን ጣቶቼን በተቸነከሩ እጆችህ ካላስገባሁ ብለህ የደረሰብህን ታውቃለህ አሁንም የእመቤታችንን መቀበር አላመንክምን? አሉት። ቶማስ ግን ሐዋርያትን ይዞ ወደ መቃብሯ ሔደ። መቃብሯን ከፍተው ሲመለከቱ ሐዋርያት ደነገጡ። በዚህን ጊዜ ቶማስ አታምኑኝም ብየ ነው እንጂ እመቤታችን አርጋለች። ስታርግም በደመና ከሀገረ ስብከቴ ስመጣ ተገናኘን ለምልክቱም ይኸው የቀበራችሁበት ሰበን አላቸው።ሐዋርያትም ለበረከት ሰበኗን ተከፋፍለው ወደየሀገረ ስብከታቸው ሔዱ።

በዓመቱ ግን ሐዋርያት ተሰበሰቡ እና ትንሣኤሽን ቶማስ አይቶ እኛም በረከት አይቅርብን ብለው ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባዔ ገቡ።በነሐሴ 14 አስከሬኗን ትኩስ በድን አድርጎ አምጥቶ ሰጥቷቸው ከቀበሯት በኋላ በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 እመቤታችን ተነሥታ ጌታችን ከመላእክት እና ቅዱሳን ጋር ሆኖ ሐዋርያትን አቁርቧቸዋል።(ውዳሴ ማርያም ትርጉም)።

ከበረቱ ያሳትፈን🙏🙏🙏

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ገዳሜ ተዋህዶ_Gedame tewahido posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share