የወርቅ ዘንግ ሚዲያ - Yewerk zeng media

የወርቅ ዘንግ ሚዲያ - Yewerk zeng media ከምጥቀት በላይ ከጥልቀት በታች ያለ ፍጥረት ሁሉ የተፈጠረው በወርቅ ዘንግ እየተለካ ነው!!! 777

06/06/2023

የማይቀርበት ታላቅ የጥበብ መርሀግብር ሰኔ 11/2015 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ 4ኛ ፎቅ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ

አኮቴት ኦርቶዶክሳዊ የጥበቅ ማዕድ
ትኬቶችን ለማግኘት
1.ሜክሲኮ ሀ ሁ የመጻሕፍት መደብር
2.አራት ኪሎ ቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ1ኛ ፎቅ ሐኒ ሞባይል ቤት
3.ቦሌ አለምነሽ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ ካበን ሆም ዲኮር
4.መገናኛ ገነት ኮሜርሻል ምድር ላይ ሠራዊት እስቴሽነሪ
5.ኮተቤ 02 ጆሲ ሞል 2ኛ ፎቅ ዶልፊን ካፌና ሬስቶራንት
6.ፊጋ አንበሳ ባንክ ያለበት ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ

በተጨማሪም በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ቀድመው ቦታ ይያዙ አኮቴት ኦርቶዶክሳዊ የጥበብ ማዕድ።

30/05/2023

እመቤታችንን ማመስገን የሚቻለው ም አንደበት ነው

ዐቢይ ነገር ኮነ  በደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የሚገኘው የደብረ ምጥማቅ ማርያምና የጻድቃኔ ቅድስት ማርያም መካነ ቅዱሳን አንድነት ገዳም በ15ኛው መቶ...
30/05/2023

ዐቢይ ነገር ኮነ በደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም

በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የሚገኘው የደብረ ምጥማቅ ማርያምና የጻድቃኔ ቅድስት ማርያም መካነ ቅዱሳን አንድነት ገዳም በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አማካይነት እንደተመሠረተ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ቤተ ክርስቲያኑን ሊያሠሩ የቻሉበት ዋነኛ ምክንያትም፤ በግብፅ ሀገር ሃይማኖት፤ ዘር፤ ቀለም ሳትለይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትገለጽ የነበረችበት ቤተ ክርስቲያን እሰላሞች በማቃጠላቸው እጅግ አዝነው ስለነበር በኢትዮጵያ ውስጥ ሰሜን ሸዋ ላይ ቤተ ክርስቲያኑን እንዳሠሩ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡
በኢትዮጲያ ከሚገኙ የተባህትዎ ቦታዎች አንዷ የሆነችው ይህች ጻድቃኔ ማርያም ገዳም ከጥንት ጀምሮ ነገሥታት፣ ካህናትና ምእመናን ደጅ የጠኑባት፤ ሥጋቸውን ለነብሳቸው ያስገዙባት፤ ቃለ እግዚአብሔርን የሚማሩባት ነበረች፡፡ ለ500 ዓመታት ያህል ገዳሟ መናንያን የማይኖሩባት በቅዱሳን የምትጠበቅ ሆና ኖራለች፡፡
ከ500 ዓመታት በኋላ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር እንዲሉ በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻና በ21ኛው መቶ ክፈለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ገዳሟ ዳግም አንሰራራች፡፡ ገዳሟ ምእመናን ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው የሚያስገዙባት ፤ ፈውስ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ የሚያገኙባት ፤ ሱባኤ ይዘው ከእግዚአብሔር መልስ የሚያገኙባት ፤ መናንያን እንደ መላእክት የሚኖሩባት ፤ የጽድቅ ተግባራት የሚከናወንባት ፤ የእግዚአብሔር ቸርነቱ የበዛባት ፤ የእመቤታችን ፍቅሯና ምልጃዋ የነገሰባት ቦታ ናት፡፡
በንጉሥ ዘርዐ ያዕቀብ የተመሠረተው ይህ ገዳም አሁንም ባለንበት ዘመን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሕልም፤ በራዕይና በተከስቶ እየተገለጸች ምእመናንን እየተራዳች፤ በስሟ ከፈለቀው ጸበል እየጠጡና እየተጠመቁ ከተለያዩ ደዌያት ይፈወሳለቸ፡፡
ታዲያ ይህ ድንቅ መካን የቅዱሳን ስፍራ በትናንትና ው ዕለት ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቤተክስቲን ሊቃንት እንዲሁም ከተለያዩ አከባቢዎች የተገኙ በርካታ ምዕመናን ባሉበት በታላቅ ድምቀት ተመርቃች እጅግ ድንቅ እና የበረከት ቀን ሆኖ ሁሉም በእናታችን በድንግል ማርያም ሲባረክ ቆይቶ ሁሉም ወደየመጣበት በሰላም ተመልሷ፡፡
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጸጋና በረከት በሀገራችን በኢትዮጵያ እና በሕዝቦቿ ይደር ለዘልዓለሙ አሜን፡፡
*****የወርቅ ዘንግ ሚዲያ-Yewerk zeng media******
ከምጥቀት በላይ ከጥልቀት በታች ያለ ፍጥረት ሁሉ የተፈጠረው በወርቅ ዘንግ እየተለካ ነው!!! 777
ግንቦት 22/2015 ዓ.ም

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251977170707

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወርቅ ዘንግ ሚዲያ - Yewerk zeng media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የወርቅ ዘንግ ሚዲያ - Yewerk zeng media:

Share