Christ Witnesses Church/Apostle Agegnew Shukka

Christ Witnesses Church/Apostle Agegnew Shukka እውነት:ሕይወት መንገድ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው

🕊በአሁኑ ዘመን  ነቢያት አሉን? 🗣አዎን አሉ📖✍️የቃሉ ትርጓሜ በሶስት ቋንቋዎች ሲታይ:-👉ከቃሉ ምንጭ/Etymology/ እንመልከት:-1) በዕብራይስጥ(Hebrew)✍️"ነቢይ"= nabû/Nāvī...
22/05/2026

🕊በአሁኑ ዘመን ነቢያት አሉን? 🗣አዎን አሉ📖
✍️የቃሉ ትርጓሜ በሶስት ቋንቋዎች ሲታይ:-
👉ከቃሉ ምንጭ/Etymology/ እንመልከት:-
1) በዕብራይስጥ(Hebrew)
✍️"ነቢይ"= nabû/Nāvīʼ/(נָבִיא) ማለት ሲሆን ትርጓሜውም የመለኮትን ቃል ከምንጩ ተቀብሎ ለሕዝቡ ሳይጨምር እና ሳይቀንስ የሚያውጅ(proclaim)፤ የህዝቡንም ጩኸት ለአምላክ የሚያቀርብ የያህዌ ተወካይ እና አፍ ማለት ነው።
✍️በብሉይ ኪዳን በተለያዩ ስፍራዎች ላይ ነቢያት "seer/“רֹאֶה” (Ro’eh) ወይም “חֹזֶה” (Chozeh) ተብሎም ተጠርተዋል ትርጓሜውም 👉"ባለራዕይ/visionary ፣ ባለመገጥ እና ራዕይ የሚያይ" ማለት ነው።1ሳሙ9:9፤ 2ሳሙ24:11፤2ዜና9:29
ወይም ኢሳ1:1፤ሕዝ1:1፤ዳን7:1-2
✍️ሌላኛው የነቢያት መጠሪያ=’Ish HaElohim (ኢሽ ሃኤሎሂም) ትርጓሜውም "የእግዚአብሔር ሰው" ማለት ነው።አንድ ሰውን "የእግዚአብሔር ሰው ስንል:- ለእግዚአብሔር የተለየ፤ በመንፈስ የሚመራ፣የእግዚአብሔርን ቃል የሚናገር፣ በቅድስና የሚመላለስ እና ሕዝቡን የሚያገለግል ማለታችን ነው። ዘዳ33:1፤ 1ኛሳሙ9:6፤1ኛነገ17:18፤1ጢሞ6:11፤2ጢሞ3:17።
2) በግሪክ(Greek) ነቢይ
✍️προφήτης (Prophētēs) ማለት ሲሆን የሁለት ቃላት ውህደት ነው:_
pro = ውክልና/ስም / on behalf of
phemi = መናገር / to speak
ስለዚህ ትርጓሜው፦
Prophet = one who speaks for God
“በእግዚአብሔር ስምና ውክልና የሚናገር ሰው” ማለት ነው።
3)በግዕዝ (Ge’ez) "ነቢይ"
✍️ነቢይ (Nabiy) በቀጥታ ከሴሜቲክ ቋንቋ ዕብራይስጥ የተወረሰ ሲሆን ያለፈውንና የሚመጣውን በእግዚአብሔር መንፈስ ተነድቶ የሚያውጅ ማለት ነው።(በ1970ዓ.ም በካህናት እና በሀገረሰብ ቋንቋ ከታተመው የደስታ ተከለወልድ ያማረኛ መዝገበ ቃላት የተወሰደ።)
👉ነቢየ ጽድቅ:- ከእግዚአብሔር የሰማውንና ያየውን በቅዱስ መንፈስ ተመርቶ የሚናገር/የሚገልጥ።
👉ነቢየ ሐሰት:- ያላየውን አየኹ፤ ያልሰማውን ሰማኹ ወይም እግዚአብሔር ሳያዛቸው ታዝዣለሁ በማለት ከራሳቸው/ከሌላ አለም በመኮረጅ የሚናገር/ሩ።(ት.ሕዝ13:1-23/ት.ኤርሚ14:14-16/ዘዳ 18/ዘዳ13/1ኛ ነገ22:23/1ነገ13:18
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
"ነቢይ/ነቢይት":- የወደፊቱን እና የአሁኑን ቃል/ድምጽ/መልዕክትን ከእግዚአብሔር ተቀብለው ለሕዝቡ የሚናገሩ የእግዚአብሔር አፍ ናቸው።
📖የነቢይ ዋና ተግባራት📖
1)የእግዚአብሔርን ቃል ማወጅ
2)ሕዝብን ወደ ንስሐ መጥራት
3)ስለ ወደፊት ነገር መናገርና መግለጥ
4)መንፈሳዊ መሪነት/ምሪት መስጠት
5) ማስጠንቀቅ
6) ማጽናናት
7) የእግዚአብሔር ፈቃድ መግለጥ
📖የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን ነቢያት📖
✍️የብሉይ ኪዳን ነቢያት የተላኩት ለእስራኤል ሕዝብ ነው።በእግዚአብሔር እና በእስራኤላውን ዘንድም መካከለኛ ሆነው አገልግለዋል።ይሁን እንጂ ስለ መሲሁ መገለጥ፣መንግስት እና ስለ ሐዲስ ኪዳን ተመልክተው አውጀዋል።
🗣ንስሐ፤ፍርድ፤ የመሲሑ መምጣት እና የእስራኤል ዕጣ ፈንታ ይተነቢዩ ነበር።
🗣መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ አይኖርባቸውም ነበር።ስለዚህ ይመጣል፣ ይፈጽምና ይመለስ ነበር።
🗣ቃላቸው እንደ እግዚአብሔር ቃል ይቆጠራል
🗣ብቸኛ መልዕክተኞች ናቸው(ካልተደመጡ እግዚአብሔር ፈጣን ፍርድን ይፈርዳል)
🗣ቅዱሳት መጽሐፍትን የመጻፍ ስልጣን ነበራቸው
🗣በሐሰተኛ ነቢያት ላይ ፍርዱ ከባድ ነበር።(ዘዳ18:20)
✍️የአዲስ ኪዳን ነቢያት የተላኩት ለቤተክርስቲያን ሲሆን የተገለጠውን ወንጌል(ኢየሱስን) ከሐዋርያት፣ ከወንጌላውያን፥ ከመምህራንና ከእረኞች ጋር ያገለግላሉ። አማኞችን በክርስቶስ እውነት ላይ ያንጻሉ፣ በፈተና ውስጥ ያጽናናሉ፤ አማኙን ለታላቁ ተልዕኮ ያበረታታሉ።
🗣መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ይኖራል
🗣ትንቢታቸው ይመረመራል(እንደ ብሉይ ኪዳን ነቢያት በቀጥታ አይወሰድም።1ቆሮ14:29
🗣ክርስቶስ የፈጸመውን ሥራ ያብራራሉ
🗣ቅዱሳት መጽሐፍትን የመጻፍ ስልጣን የላቸውም።
📖የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን ነቢያት📖
ለመጀመሪያ ጊዜ ነቢይ በመባል የተጠራው "የእምነት አባታችን አብርሃም ነው::"ዘፍ20:7 በይሁዳ መልዕክት ቁጥር 14 ላይ "ሄኖክ" ነቢይ እንደነበር ይናገራል።
፩] መሠረተ/ቀደምት ነቢያት (Former / Foundational Prophets)
1) ነቢይ ሄኖክ
2) ነቢይ አብርሃም
3) ነቢይ ሙሴ
4) ነቢይት ማርያም(ዘጸ15:20)
5) ነቢይ ኢያሱ(የሙሴ ተተኪ)
6) መሳፍንት/መስፍኖች
7) ነቢይት ዲቦራ(መሳ 4:4)
8)ነቢይት ሕልዳና(2ነገ22:14)
9)ነቢይት ኖዓድያን (ነህ6:14)ተቃዋሚ
10) ነቢይ ኤሊያስ
11) ነቢይ ኤልሳ
12) ነቢይ ሳሙኤል
13) ነገስታት(1ኛ እና 2ኛ ነገስት) ዳዊት፣ሰለሞን..ወዘተ
14) ነቢይ ናታን
፪] ኋለኞቹ ነቢያት (Latter Prophets)
ነቢይ ኢሳይያስ / Isaiah
ነቢይ ኤርምያስ / Jeremiah
ነቢይ ሕዝቅኤል / Ezekiel
ነቢይ ዳንኤል /Daniel
ነቢይ ሆሴዕ / Hosea
ነቢይ ኢዮኤል / Joel
ነቢይ አሞጽ / Amos
ነቢይ አብድዩ / Obadiah
ነቢይ ዮናስ / Jonah
ነቢይ ሚክያስ / Micah
ነቢይ ናሆም / Nahum
ነቢይ ዕንባቆም / Habakkuk
ነቢይ ሶፎንያስ / Zephaniah
ነቢይ ሐጌ / Haggai
ነቢይ ዘካርያስ / Zechariah
ነቢይ ሚልክያስ / Malachi
🗣እነዚህ በቀጥታ የእግዚአብሔርን ቃል፣ ራእይ፣ ፍርድ፣ ንስሐ እና የወደፊት ትንቢት የሚያወጁ ነቢያት ናቸው።
📖የአዲስ ኪዳን ነቢያት📖
1) ነቢይ ዮሐንስ(መጥመቁ) ማቴ 11:9
2) ኢየሱስ ክርስቶስ ሉቃ 24:19
3) ነቢይት ማርያም(የኢየሱስ እናት-ሉቃ1:26-38)
4) ነቢይት ሐና(የፋኑኤል ልጅ 2:36)
5) 4 ሴት ልጆች(የወንጌላዊ ፊልጶስ ልጆች)ሐ.ሥራ21:9
6) ነቢይ አጋቦስ (ሐ.ሥራ 11:27)
7) ነቢይ ስላስ(ሐ.ሥራ15:32)
8) ነቢይ ይሁዳ በርሳባስ(ሐ.ሥራ 15:32)
9) ነቢይ ስምዖን-ጥቁሩ(ሐ.ሥራ 13:1
10) ነቢይ ምናሔ(ሐ.ሥራ13:1)
11) ነቢይ ሉክዮስ የቀሬናው(ሐ.ሥራ13:1)
📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ነቢያት እና የነቢያት አገልግሎት በብሉይ ኪዳን ሳይወሰን በአዲስ ኪዳን በተለየ መልኩ መቀጠሉን የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ያስረዱናል።
🗣በአንጾኪያ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ ሐ. ሥራ 13:1
🗣"አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ አንዳንዶቹ ነቢያት፣ አንዳንዶቹም ወንጌል ሰባኪዎች፣ ሌሎቹ ደግሞ እረኞችና አስተማሪዎች ይሆኑ ዘንድ የሰጠ እርሱ ነው፤"ኤፌ4:11
📖ወንድና ሴት ነቢያት ዛሬም አሉ🕊ለወደፊትም ይኖራል። እሰከ ቤተክርስቲያን ንጥቀትና ታላቁ መከራ ቀን ድረስ የሚቋረጥ የጸጋ ስጦታና አገልግሎት የለም።
👇👉ክፍል 3 ይቀጥላል👉...
ሐዋርያ ዶ/ር አገኘው ሹካ
የክርስቶስ ምስክሮች ቤተክርስቲያን
ግንቦት 14/2018ዓ.ም
አዲስአበባ

🗣ሐዋርያትና ነቢያት በዚህ ዘመም አሉን??“ሐዋርያ” የሚለው ቃል በመሠረቱ የግዕዝ ቃል ነው፤ ከዚያም ወደ አማርኛ ገብቶ በተለምዶ ጥቅም ላይ ውሏል።ሐዲስ ኪዳን የተጻፈው በግሪክ ቋንቋ በመሆኑ...
21/05/2026

🗣ሐዋርያትና ነቢያት በዚህ ዘመም አሉን??
“ሐዋርያ” የሚለው ቃል በመሠረቱ የግዕዝ ቃል ነው፤ ከዚያም ወደ አማርኛ ገብቶ በተለምዶ ጥቅም ላይ ውሏል።
ሐዲስ ኪዳን የተጻፈው በግሪክ ቋንቋ በመሆኑ አባቶቻችን የቃሉን ሐሳብ የተዋሱት ከግሪክኛ ቋንቋ “ἀπόστολος” (Apostolos) ሲሆን ትርጉሙም፦
“የተላከ”=“መልእክተኛ”=“ወኪል”
“ለስራ የተላከ ሰው” ማለት ነው::
👉"ሐዋርያ" የሚለው የግዕዝ ቃል ከሁለት ተለዋጭ ስረዋ ቃል ተመስርቷል "ሐወረ" ወይም "ሖረ" ትርጓሜውም "መንገደኛ"="መልዕክተኛ"="ኻያጅ" ማለት ነው።(በ1970ዓ.ም በካህናት እና በሀገረሰብ ቋንቋ ከታተመው የደስታ ተከለወልድ ያማረኛ መዝገበ ቃላት የተወሰደ።)
📖አዲስ ኪዳናዊ "የሐዋርያ" ትርጓሜ📖
"የሐዋርያት ሥራ"= ከክርስቶስ ኢየሱስ እና ከቤተክርስቲያን መልዕክት ተቀብለው ከቦታ ቦታ በመዘዋወር በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና ኃይል የሠሩትን መለኮታዊ ክንዋኔዎችን የሚዳስስ መጽሐፍ ነው።
✍️"ሐዋርያ"= የምስራቹን ቃል በስልጣን ለመሰበክ፣ የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለመትከል እና ለማደራጀት በመንፈስ ቅዱስ የተሾመ፥ የተላከ፥ በመንፈስ የተነቃቃና ለዓላማው የተሰጠ ተራማጅ/ኻያጅ መልዕክተኛ ሰውን ያመለክታል።
አስቀድመው 12ቱ የእስራኤልን ነገድን በመወከል በኢየሱስ የተመረጡ ሐዋርያት ዝርዝር፦(
1) ✝️የበጉ ሐዋርያት✝️
ሐዋርያ ስምዖን ጴጥሮስ(ኬፋ)
ሐዋርያ እንድሪያስ(የጴጥሮስ ወንድም)
ሐዋርያ ያዕቆብ( የዘብዲዮስ ልጅ)
ሐዋርያ ዮሐንስ (የያዕቆብ ወንድም)
ሐዋርያ ፊሊጶስ
ሐዋርያ በርተሎሜዎስም
ሐዋርያ ቶማስ
ሐዋርያ ማቴዎስ
ሐዋርያ ያዕቆብ(የእልፊዬስ ልጅ)
ሐዋርያ ታዲዮስ
ሐዋርያ ስምዖን(ቀናተኛው)
ሐዋርያ ይሁዳ አስቆሮቲ በኋላ በማቲያስ ተተክቷል(ሐዋ.ሥራ 1:13/26)
ምንጭ:- (ማቴ 10:2-4፤ማር:3፥16-19፤ሉቃ 6፥13-16)
✍️ከመንፈስ ቅዱስ መውረድና ከቤተክርስቲያን ልደት በኋላ ሹመቱና አገልግሎቱ ቀጥሏል።
2)✝️⛪️የቤተክርስቲያን ሐዋርያት⛪️✝️
ሐዋርያ ጳውሎስ ሮሜ 1:1
ሐዋርያ በርናባስ ሐ.ሥራ14:14
ሐዋርያ ያዕቆብ(የማርያም ልጅ) ገላ1:19
ሐዋርያ አንዲራኒቆን ሮሜ 16:7
ሐዋርያ ዩልያን(ሴት) ሮሜ 16:7
3)📖የሐዋርያት ልጆች/ተኪ ሐዋርያት👪
ሐዋርያ አፍሮዲጡ ፊሊ 2:25
ሐዋርያ ጢሞቴዎስ
(1ኛጢሞ4:14፤ 2ኛጢሞ1:6፤ 1ኛተሰ1:1፤ 1ኛተሰ2:6)
ሐዋርያ ስላስ
(ሐ.ሥራ15:40/1ኛተሰ1:1/2ኛቆሮ1ኛቆሮ:19)
ሐዋርያ ቲቶ
(2ኛ ቆሮ8:23/ቲቶ 1:4-5)
ሐዋርያ አጵሎስ
(1ኛ ቆሮ 4:6-9/ሐ.ሥራ18:24-28/1ኛ ቆሮ3ቆሮ:4-6)
✝️የሐዋርያነት የጸጋ ስጦታና አገልግሎቱ ቀጣይነት አመላካች ኩነቶች✝️
👉የጸጋው እና የስጦታው ባለቤት መንፈስ ቅዱስ ዘርን፥ ብሔርን፥ ሐገርን፥ ጾታን፥ ወዘተ ሳይለይ ባመኑት ሁሉ ላይ መውረድ መቻሉ።አማኙም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ኃይልን በነጻ መቀበል መቻሉ። ሐ.ሥራ 2:17-18/ገላ3:28/ሐ.ሥራ10:44-48
👉የሐዋርያ ጳውሎስ ምስክርነት
🧾"አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ አንዳንዶቹ ነቢያት፣ አንዳንዶቹም ወንጌል ሰባኪዎች፣ ሌሎቹ ደግሞ እረኞችና አስተማሪዎች ይሆኑ ዘንድ የሰጠ እርሱ ነው፤"ኤፌ 4:11
🧾"እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንደኛ ሐዋርያትን፣ ሁለተኛ ነቢያትን፣ ሦስተኛ መምህራንን፣ ቀጥሎም ታምራት አድራጊዎችን፣ የመፈወስ ስጦታዎች ያላቸውን፣ ሌሎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፣ የማስተዳደር ስጦታ ያላቸውንና በልዩ ልዩ ልሳን የመናገር ስጦታ ያላቸውን ሰዎች መድቦአል።"1ኛ ቆሮ 12:28
🕊የስጦታዎች ሁሉ ባለቤት፥ ምንጭ፥ ሰጪ፥ ሿሚና ላኪ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው🕊
👉"ስጦታዎች ልዩ ልዩ ሲሆኑ፣ መንፈስ ግን አንድ ነው፤ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ሲሆን፣ ጌታ ግን አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ሲሆን፣ ሁሉን በሁሉ የሚሠራው ግን ያው አንዱ እግዚአብሔር ነው።"1ቆሮ 12:4-6
✝️የሐዋርያት ተልዕኮና ዓላማ✝️
🧾"በእርሱ በኩል ስለ ስሙ ከአሕዛብ ሁሉ መካከል ሰዎችን በእምነት አማካይነት ወደሚገኘው መታዘዝ ለመጥራት ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን።"ሮሜ 1:5
🧾"ይኸውም የክርስቶስ አካል ይገነባ ዘንድ፣ ቅዱሳንን ለአገልግሎት ሥራ ለማዘጋጀት ሲሆን፣ ይህም የሚሆነው፣ ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኘው አንድነት በመምጣትና ሙሉ ሰው በመሆን፣ በክርስቶስ ወዳለው ፍጹምነት ደረጃ እስከምንደርስ ነው።"ኤፌሶን 4:12-13
1) ወንጌልን በግልጽና በኃይል መስበክ ማር16:15/2ቆሮ5:20
2)ቤተክርስቲያን መትከል፥ ማደራጀትና መሠረት መጣል። ሐ.ሥራ16:5/1ቆሮ3:10
3) ለክርስቶስን ቤተክርስቲያን መሠረት መሆን። ኤፌ 2:20
4)ደቀመዛሙርትን ለተልዕኮ ማሰልጠንና ማብቃት። ኤፌ 4:12
5)የሕይወት፣የአስተምህሮ እና የአገልግሎት መመሪያ እና እርማት መስጠት። 2ጴጥ3:2/ገላ1:8
6)በድንቅ፥ በተዓምራትና በኃይል የኢየሱስን ማዳንና ክብሩን በመንፈስ ቅዱስ መግለጥ። 2ቆሮ 12:12
7)በቤተክርስቲያን ህብረት እና መንፈሳዊ ብስለት እንዲኖር መትጋት። ኤፌ4:13/1ቆሮ3:1-23
8)ቤተክርስቲያንን ማደራጀት(መሪዎችን መለየትና መሾም)፣ መገምገም እና የምዕመናንን መንፈሳዊ ሕይወት በንቃት መከታተል/መጎብኘት። ሐ.ሥራ14:21-23/ቲቶ1:5/ሐ.ሥራ 15:36-41/ሐ.ሥራ20:20-21 &ቁ 31/፤1ተሰ2:7/2ጢሞ2:2
✝️ሐዋርያት እና ነቢያት በዚህ ዘመን አሉን?
ይህን ጥያቄ ለመመለስ ቀጥሎ ያሉት ጥያቄ አስቀድመን ልንጠይቅ ይገባል።
1) መንፈስ ቅዱስ አሁን በምድር አለ ወይ?
2)ቤተክርስቲያን በዚህ ዘመን አለች ወይ?
3)በክርስቶስ አምነው የዳኑ አማኞች አሉ ወይ?
4)ታላቁ ተልዕኮ(ማቴ28:19) የኛም ተልዕኮ ነው ብለህ ታምናለህ?
5)የሁሉም ስጦታዎችና ጸጋ ምንጭ መንፈስ ቅዱስ ነው ብለህ ታምናለህ?
🗣መልስ አዎ ከሆነ👉በትክክል መልሰሃል። የጸጋው እና የስጦታው ባለቤት፣ እንዲሁም ምንጭ መንፈስ ቅዱስ እስካለ ድረስ ስጦታዎች አይቋረጡም።ለአማኞችም መታነጽና ሙሉ ሰው ወደ መሆንም የሚያደርሱ የተሟሉ የጸጋ ስጦታዎች በቤተክርስቲያን ሲገለጡ ብቻ ነው።
✝️በቀደሙ የበጉ ሐዋርያት/የቤተክርስቲያን ሐዋርያት እና ተተኪ ሐዋርያት ዘንድ ብቻ የተወሰኑ እና ያልተላለፉ ስልጣኖች:-
ሀ) ቀኖናዊ (ቅዱሳት መጽሐፍትን መጻፍ)
ለ) አዲስ የእምነት መሠረትን መጣል
✝️እስካሁን ያልተገደቡ እና ያልተቋረጡ ሐዋርያዊ አገ/ትና ስልጣን:-
1) የክርስቶስን ሞት፥ ትንሳኤና ዳግም ምጻቱን መመስከር
2) የኢየሱስን መካከለኛነት እና ብቸኛ አዳኝነት ማወጅ/መስበክ
3)አማኞችን በማዕዘኑ ድንጋይ(በክርስቶስ እምነት) በማያያዝ በሐዋርትና ነቢያት ትምህርት(መሠረት) ላይ በማነጽና(መትከል) በመገንባት ወደ ፍጹምነት ማድረስ።1ቆሮ3:10
4) እጅ በመጫን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ማስተላለፍ እና መሪዎችን ለይቶ መሾም።ሐ.ሥራ8:17
5) የቤተክርስቲያን ሥርዓቶችንና አደረጃጀቶችን መዘርጋት።1ቆሮ14:40
6) በኃይልና በታምራቶች መገለጥ።2ቆሮ12:12
7)የቤተክርስቲያን አንድነትን መጠበቅ ኤፌ4:3
8) መሪዎችን ማሰልጠንና መላክ።2ጢሞ2:2....ይቀጥላል ክፍል 2
✝️ሐዋርያ ዶ/ር አገኘው ሹካ✝️
የክርስቶስ ምስክሮች ቤተክርስቲያን
ግንቦት 13/2018ዓ.ም
አዲስአበባ

Address

New
Addis Ababa

Opening Hours

Friday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251972763678

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christ Witnesses Church/Apostle Agegnew Shukka posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Christ Witnesses Church/Apostle Agegnew Shukka:

Shortcuts

Share