22/02/2025
✝✝✝ የካቲት ➊➏ ኪዳነ ምህረት ✝✝✝
➣እንኳን አደረሰን!!!
ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው።
ከ 33 ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው።
✔ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችም እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ
ዘጠኝ ወር ከ 5 ቀን በማኅጸኔ ያደረክ።
ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች ።
✔ በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውትል ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቁ ጌታሽንም እልፍ ከእልፍ መላእክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለምኚኛለሽ አላት ።
✔ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ
የሚራራውን በስሜ ቤተክርስቲያን ያነጸወን መባዕ የሰጠውን
ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው ።
✔ ጌታችንም ይህን ሁሉ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ህያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል ።
✔ ከመረጥኳቸው ጋራ ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል ፤ወደፊትም ያደርጋል ።[
መዝ 89፥3 ] ቃል ኪዳኑም የምህረት ቃል ኪዳን ነው ።
ቅዱሳኑ
ወስበሀት ለእግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በርከት ይክፈለን ✔✔~~ አሜንንንንንንንንንንንንንን