Halwot Emmanuel Church

Halwot Emmanuel Church Vision
To see the Church that creates a righteous influence in Addis Ababa, through the imitation of Christ Jesus
(1)

በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን ሀልዎት አጥቢያ
#አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፊውቸር ታለንት ት/ት ቤት አጠገብ
ACCOUNTS
Berhan Bank- 2600260021701
CBE-1000421805718
Awash - 01352574197600
Emmanuel United Church of Ethiopia Halwot Local Church A.A
Phone Number:- ☎️ +251118407763 ☎️ +251118633493 📱+251 973 422024

    📌 አደራን እንዴት መጠበቅ ይቻላል?1) በመንፈስ ቅዱስ በመጠበቅ (2ጢሞ 1)2) በጸጋው መበርታት (2ጢሞ 2)- በጸጋው ለመበርታት የሚያስፈልገን የሕይወት ጥራት * የማያሳፍር ምንነትና...
24/07/2026





📌 አደራን እንዴት መጠበቅ ይቻላል?
1) በመንፈስ ቅዱስ በመጠበቅ (2ጢሞ 1)
2) በጸጋው መበርታት (2ጢሞ 2)
- በጸጋው ለመበርታት የሚያስፈልገን የሕይወት ጥራት
* የማያሳፍር ምንነትና
* የማያሳፍር ሠራተኛ
- ምሳሌዎች:-
* ልጅ
* ወታደር
* አትሌት
* ገበሬ
* ሠራተኛ
* እቃ
* ባሪያ :- ብስለትና ጥበብ ያለው፣ የሚጸና፣ የማይጣላ፣ ተስፈኛ ባሪያ
- በእነዚህ እውነተኛ የማያሳፍር ሠራተኛ ሆነን ስንመጣ ከፍ ሳይሆን ዝቅ ነው የምንለው። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሥራ የሚሠራው ራስን በመካብ ሳይሆን ዝቅ በማድረግ ነው።
3) በእግዚአብሔር ቃል በመጽናት (2ጢሞ 3)
- የእግዚአብሔር ቃል ያሻግርሀል፣ በቃሉ ላይ ትኩረት አድርግ ይለዋል።
* ነገ የሚመጣውን አስቸጋሪ ሕይወት ለመኖር (አደራን ለመወጣት):-
➥ ትንቢታዊ ጥበቃ ይኑርህ
➥ እንደቃሉ የሚሔዱ ሠዎችን/ምሳሌዎችን ተከተል
➥ በጸናው ቃል ላይ ጽና
* ባለሥልጣን ነው :- የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለበት ነው። ይህ ቃል:-
* ለድነት ይሆናል፣
* ለጥበብ (ለሕይወት) ይሆናል፣
* ለበጎ ሥራ /ለአገልግሎት ጠቃሚ ያደርጋል
* ስበከው/ ተናገረው
- እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል አደራውን በእኛ ይፈጽማል።
- በዚህ ጸንተን ከቀጠልን አክሊል ይጠብቀናል።
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን ሀልዎት አጥቢያ
አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፊውቸር ታለንት ት/ት ቤት አጠገብ
☎️ +251118633493 📱+251 973 422024

ልዩ የአገልጋዮች ኘሮግራም በሀልዎት አማኑኤል ኀብረት ቤተክርስቲያን 📆 ዛሬ /  አርብ / ሐምሌ 17/2018⏰ 11:30 ሰዓት📍በሌሎችም አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የምታገለግሉ ሁሉ ተጋብዛችኋል!
24/07/2026

ልዩ የአገልጋዮች ኘሮግራም
በሀልዎት አማኑኤል ኀብረት ቤተክርስቲያን
📆 ዛሬ / አርብ / ሐምሌ 17/2018
⏰ 11:30 ሰዓት

📍በሌሎችም አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የምታገለግሉ ሁሉ ተጋብዛችኋል!

የልጆች ሰመር ካምፕ ስምንተኛ ቀንበዕለቱ ልጆች ዘምረዋል፣ተጫውተዋ፣ፕሮጀክት ሰርተዋል፣ጥያቄ እና መልስ ውድድር አድርገዋል እንዲሁም ትምህርት-6"አስርቱ ልጃገረዶች እና ታማኙ አገልጋይ" የተሰ...
23/07/2026

የልጆች ሰመር ካምፕ ስምንተኛ ቀን
በዕለቱ ልጆች ዘምረዋል፣ተጫውተዋ፣ፕሮጀክት ሰርተዋል፣ጥያቄ እና መልስ ውድድር አድርገዋል እንዲሁም ትምህርት-6"አስርቱ ልጃገረዶች እና ታማኙ አገልጋይ" የተሰኘውን ትምህርት ተምረዋል። የክርስቶስ መምጫ ቀን በድንገት ስለሆነ ሁሌም ዘይታችን ሳይጎድል እና እግዚአብሔር ባስቀመጠን ቦታ(እንደልጅ፣እንደተማሪ፣እንደአገልጋይ) በታማኝነት መኖር እንዳለብን አውርተናል።

22/07/2026
   ጋር📌መሰዊያ📖2ተኛ ነገ 16 ፥ 10 - 14👉በአይሁዳውያን የአምልኮ መሰዊያ በጣም አስፈላጊ ነው።👉መሰዊያ ማዕከላዊ ሲሆን እግዚአብሔር ከነሱ ጋር የሚገናኝበት ስፍራ ነው። 👉እግዚአብሔርን...
20/07/2026


ጋር
📌መሰዊያ
📖2ተኛ ነገ 16 ፥ 10 - 14
👉በአይሁዳውያን የአምልኮ መሰዊያ በጣም አስፈላጊ ነው።
👉መሰዊያ ማዕከላዊ ሲሆን እግዚአብሔር ከነሱ ጋር የሚገናኝበት ስፍራ ነው።
👉እግዚአብሔርን ለማግኘት ሲመጡ የሚጀምሩት ከመሰዊያው ነው፤ ይሄ መሰዊያ ለህይወታቸው ማዕከላዊ ነው።
👉መሰዊያው ንሰሀ የሚገቡበት እና እግዚአብሔርን የሚገናኙበት ዋነኛ ቦታቸው ነው።
👉አሁን ላይ በብዙ ቤቶች ውስጥ መሰዊያችን ፈቀቅ ብሏል ይሄን መሰዊያችንን መመለስ አለብን።
👉መሰዊያችንን ወደ ስፍራው መመለስ አለብን። 👉መሰዊያ ከሌለ እራሳችንን ነው የምናጠፋው ጠላት መሰዊያችንን በሌላ ተክተን ከመንግስቱ በማራቅ እራሳችንን እንድናጠፋ ያደርገናል።
👉መሰዊያችን ከህይወታችን ፈቀቅ ካለ ወደ እግዚአብሔር ቤት አያቀርበንም ፣ መጨረሻችን አያምርም እድሚያችን የበዛ አይሆንም።
👉መሰዊያ የሌለበት ስኬት የለም እግዚአብሔር ቤቱ ያለ መሰዊያ እንዲሆን አይፈልግም።
👉መሰዊያችን ምህረት ማግኛ ስፍራ ነው።
👉መሰዊያ በሌለበት ስፍራ እሳት መጠበቅ የለም።
📖 2ተኛ ዜና 28
📖 1ኛ ዜና 29
ህዝቂያስ :- በእግዚአብሔር ቤት የገቡትን በአድ ነገሮችን አወጣ።
👉መሰዊያ ይታደሳል እንጂ አዲስ የሚሰራ መሰዊያ የለም ኤልያስ መሰዊያውን አደሰ መሰዊያ ሲታደስ አብሮ እሳት ይመጣል ሙሴም መሰዊያን ከሰዋ በኋላ እሳት ከሰማይ መጣ እሳቱ የሚመጣው ከላይ ነው እኛ የምናደርገው እንዳይጠፋ ነው።
👉መሰዊያ በጥንቃቄ ነው የሚያዘው በእዛ ጊዜ እሳት ከሰማይ ይመጣል።
📖 ሮሜ 12 ፥ 1
👉የማይጠፉ እሳት እንዲመጣ ከፈለግን ፈቀቅ ያደረግነውን መሰዊያችንን እናድስ።

📌 እውነተኛው መሰዊያ ከቤታችን አይታጣ።

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን ሀልዎት አጥቢያ
አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፊውቸር ታለንት ት/ት ቤት አጠገብ
☎️ +251118633493📱+251 973 422024

   ሀልዎት_ቴሌግራም_ፋሚሊን_ለመቀላቀል! 👇https://t.me/+jYFLz5UZB4k0ZDA0ሀልዎት_ቴሌግራም_ቻናልን_ለመቀላቀል👇https://t.me/halwotchurch🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐...
20/07/2026


ሀልዎት_ቴሌግራም_ፋሚሊን_ለመቀላቀል! 👇
https://t.me/+jYFLz5UZB4k0ZDA0
ሀልዎት_ቴሌግራም_ቻናልን_ለመቀላቀል👇
https://t.me/halwotchurch
🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐
🖐 እግዚአብሔር አይኖቻችሁን ይክፈት በኢየሱስ ክርሰቶስ ስም፣ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ የሕዝቅያስን ልብ ያነሳሳ እግዚአብሔር በአቋሙም እንዲጸና እንዳያመቻምች እንደሆነ ሁሉ ሕዝቅያስ ባለመቻመች፤ እውነትን እውነት፤ ትክክል ያልሆነውን አይደለም ለማለት፤ የተቀላቀለውን ለመለየት፤ በስውር እየተሠራ ያለውን የትኛውም መናፍስታዊ ምክርን ሁሉ ለመለየትና ገንጥሎ ለመምታት እግዚአብሔር አይኖቻችሁን ይክፈት
🖐 ሳናውቅ ተቀላቅሎ፤ ተመቻምቾ ከመኖርና ለሀጢአት ጭከናን ከማሳየት ወደኋላ አለማለትን ትተን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም ብርቱ አቋምና ልብን መያዝ በሁላችንም ላይ እንዲሆን እግዚአብሔር በዚህ እንዲባርከን፤ እንዲባርካችሁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እጸልያለሁ
🖐 እንደዛ መቅደስ እንዳለ ካህን እንግዳን ምክር ለመቀበል ልቡን እንደከፈተ፤ እንግዳን መሰዊያ ደግሞ ከአህዛብ ይደረግ ሲባል ንጉሱን እንዳልተቃወመ ደግሞም እንዳደረገለት፤ በመቅደስ ሆኖ፤ በቤት ሆኖ፤ እያገለገለ እያለ ትክክኛ ስፍራ ላይ ሆኖ፣ ግን ደግሞ ያልተገባ ምክርን፤ ያልተገባን የእግዚአብሔር ያልሆነውን ምክር ለመፈጸም እድል እንዳገኘ ካህን እንደዛ እንዳንሆን፤ ነውርን ነውር፤ ጽድቅን ጽድቅ፤ ሀጢአትን ሀጢአት የሚል፤ የማያመቻምች ልብ እንዲኖረን እግዚአብሔር በጠላቶቻችን ላይ አይኖቻችንን ይክፈት
🖐 የእግዚአብሔር ምህረት በእናንተ ላይ ይሁን፣ ሊይቀይር የፈለገውን ይቀይርባችሁ፣ ሊያራግፍ የፈለገውን አቧራ ያራግፍባችሁ፣ ሊያድስ የፈለገውን ያድስባችሁ፣ እንደነሕዝቅያስ መሰዊያን ዋና ከእግዚአብሔር መገናኛ ዋናው መስመር ላይ አይኑን እንደከፈተ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ለመቀጠል፤ በፊቱ ለመሆን፤ ደጁንም ለመጥናት፤ ከእርሱ ምክርንም ለመስማት፤ ደግሞ የእርሱን እሳት ይዞ ለመውጣት በዚህ የተባረካችሁ እንድትሆኑ፣ በዚህ ደግሞ አይኖቻችሁ የተከፈተ፤ ለእግዚአብሔርም ልባችሁ የሚፈቅድ እንዲሆን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ባረኳችሁ፣
🖐 እጁ በእናንተ ላይ ትሁን፣ ተከናወኑ፣ ከነጋልን አይቀር፤ ቀን ከተጨመረ አይቀር፤ ኑሩ ካለን አይቀር፤ ፈቃዱን በመስራት፣ ለእግዚአብሔር ፈቃድ በመኖርም አምላኬ ይባርካችሁ
🖐 እግዚአብሔር ይባርካችሁ ይቀድሳችሁ፣ ፊቱንም ያብራላችሁ፣ ሕይወት ይቅለላችሁ፣ ኑሮ ይቅለላችሁ፣ የተባረከ ቀንና ሳምንት ይሁንላችሁ፣ ያቀዳችሁትን በመኖር እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ ደግሞ ይምራችሁ፣ ወዳቀደበት ወደሚፈልገው ጋር ያውላችሁ፣ ከክፉ ሁሉ እየጠበቀ ደግሞ ለሌሎች በመትረፍ የሚፈልገውን ሕይወት በመኖርና ፈቃዱን በማገልገል እግዚአብሔር ከሰኞ እስከ እሁድ ያሉ ቀኖቻችሁን በዚህ ይባርክላችሁ፣ ጤና ይስጣችሁ፣ በሚያስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር መግቦትና በረከት በእናንተና በቤታችሁ ሁሉ ላይ ይሁን፣ አምላኬ ይባርካችሁ፣ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን
🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐
በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን ሀልዎት አጥቢያ
አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፊውቸር ታለንት ት/ት ቤት አጠገብ
☎️ +251118633493 📱+251 973 422024

Address

Halwot Emmanuel United Church
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halwot Emmanuel Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Halwot Emmanuel Church:

Shortcuts

Share

Category