Tad.B Christian's

Tad.B Christian's God is good all the time, all the time God is good.

ነቀምቴ መካነየሱስ 100 ዓመት ሞላት..."ጊዜው 1924 ዓ.ም በፈረንጆቹ አቆጣጠር ነበር ከ100 ዓመት በፊት ንጉሥ ኩምሳ ሞሮዳ ሞተው ልጃቸው ደጃዝማች ሀብተማርያም የሌቃ ነቀምቴ ንጉሥ የሆ...
28/09/2023

ነቀምቴ መካነየሱስ 100 ዓመት ሞላት...

"ጊዜው 1924 ዓ.ም በፈረንጆቹ አቆጣጠር ነበር ከ100 ዓመት በፊት ንጉሥ ኩምሳ ሞሮዳ ሞተው ልጃቸው ደጃዝማች ሀብተማርያም የሌቃ ነቀምቴ ንጉሥ የሆኑበት ወቅት ።
ኦኔሲሞስ እግሩ ነቀምቴን ከረገጠ 20 ዓመት ሞላዉ።
የሲውዲን ዜጋ የሆኑት ዶ/ር ሴደስትሮም እና ባለቤታቸው ነቀምቴ መኖር ከጀመሩ ሁለት ዓመት አስቆጥሯል ።
ቄስ ማርቲን ፎርድፌልት እና ባለቤታቸው እንድሁም ቄስ ኦሎፍኤሪክሴን ከጥቅት ቀናት በፍት ከሲውዲን ሃገር ነቀምቴ ገብተዋል። ሁሉም የነቀምቴ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያንን ምረቃ በጉጉት እየተጠባበቀ ነዉ። ሲጠበቅ የነበረውም ቀን ደረሰ ታህሳስ 25,1924 ዓ.ም በፈረንጆች አቆጣጠር የክርስቶስ ልደት ቀን።
የነቀምቴ መካነየሱስ ቤተክርስቲያንም በዚሁ ዕለት ተወለደች ። በዚህ ታሪካዊ ሥነሥርዓት ለመታደም 150 የሚሆኑ ምዕመናን ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል። ፕሮግራሙም ጀመረ ቄስ ኦሎፍ ኤርክሰን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጌታን ከአመሰገኑ በሃላ አጭር ንግግር በማድረግ ፕሮግራሙን ከፍተው በመምራት ቀጠሉ። የዕለቱን ቃል ግን ያካፈሉት ዶ/ር ኤሪክ ሴዴስትሮም ሲሆኑ የስብከቱም ሪዕስ "በበረት የተወለደው ህፃን" የሚል ነበር ።ኦኔሲሞስ ደግሞ ቆሞ ወደ አፋን ኦሮሞ እየተተረጎመ ነው። የፀሎት ፕሮግራሙም ከተፈፀመ በሃላ ከቤተክርስቲያኗ ደጅ በሚገኘው ሰፊ አደባባይ ለሁሉም ምዕመናን ምግብና የሚጠጣ ቀርቦ ትልቅ ግብዣ ተደረገ..."

የነቀምቴ መካነየሱስ ማህበረ ምዕመናን ከጥቂት ወራት በሃላ ይሄው 100ኛ ዓመቷን ልታከብር ነው።

እንኳን ደስያላችሁ!!! እንኳን ደስያለን!!

(Adapted from: Aren, Gustav. Envoys of the Gospel in Ethiopia: In the Steps of the Evange
Via Robsan Mako , September 2023
http://www.youtube.com/channel/UCt3blVWzKDJpTAsZvVRNr-g?sub_confirmation=1

07/08/2023

ዛሬ በአማራ ክልል የተፈጠረው ቀውስ የሦስት አካላት ድምር ውጤት ነው። >

1.ግብ የሌለው ጃውሳ፣
2.አቋምና አቅም የሌለው አመራር፣
3.ባንዳ መግዛት የለመደ የውጭ እጅ።

ጃውሳ፦ ሽፍታ፣ ወንበዴ፣ ነጣቂ፣ ቀማኛ፣ በጎደጎደ ምድር፣ በጨፈቀ ዱር እያደባ መንገድ ዐላፊውን እየደበደበ የሚቀማ ወንበዴ።

11/01/2023
29/10/2022
13/09/2022

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tad.B Christian's posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Tad.B Christian's:

Share