Mamo beyene beyi

Mamo beyene beyi Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mamo beyene beyi, መድኃናልም አከባቢ, Addis Ababa.

07/01/2023

መልካም የገና በዓል ይሁንልዎት

07/01/2023
06/01/2023

አስሩ ኢትዮጵያዊያን ቢሊየነሮች እነማን ናቸው?

1ኛ.. ሼህ መሀመድ አልአሙዲ፦

ሼህ አልአሙዲ በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በአፍሪካም ጭምር ከቀዳሚዎቹ ቢሊየነሮች መካከል አንዱ ነው። ሼህ አልአሙዲ ከሚድሮክ በተጨማሪ በሳኡዲ አረቢያ ነዳጅ በማውጣትና ለተለያዩ ሀገራት በማከፋፈል ይታወቃል። በተለያዩ የማእድንና የኢንቨስትመንት ስራዎችም ላይ ተሳትፎ አለው። የሼህ አልአሙዲ አጠቃላይ ሀብት 10 ቢሊየን ዶላር ነው

2ኛ.. እዮብ ማሞ ፦

እዮብ ማሞ የሚኖረው በአሜሪካን ሀገር በዋሺንግተን ዲሲ ሲሆን ከሼህ አልአሙዲ ቀጥሎ ሁለተኛ ኢትዮጵያዊ ቢሊየነር እሱ ነው። እዮብ ቀዳሚ የሀብት ምንጩ የሪልስቴት እና የነዳጅ ቢዝነስ ነው። እዮብ በጣም ጠንካራ ሰራተኛ ነው። ከነዳጅ ማደያ ሰራተኝነት ወደ ካፒታል ፔትሮሊየም ካምፓኒ ባለቤትነት የተቀየረ ሰው ነው። የእዮብ አጠቃላይ ሀብት 7 ቢሊየን ዶላር አካባቢ ይገመታል

3ኛ.. ሳሙኤል ታፈሰ ፦

ሳሙኤል ታፈሰ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ ሂደቶችንና ውጣ ውረዶችን ያለፈ እጅግ ጠንካራ ሰራተኛ ነው። ሳሙኤል በኮንስትራክሽንና በሪልስቴት ዘርፍ የተሰማራ ባለሀብት ሲሆን አጠቃላይ ሀብቱም 4.3 ቢሊየን ዶላር አካባቢ ነው

4ኛ... በላይነህ ክንዴ፦

በላይነህ ክንዴ ከአባይ ወንዝ መነሻ ከሆነችው ሰከላ ወረዳ ነው የተወለደው ።ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ አስመጪ እና ላኪ ባለሀብቶች መካከል አንዱ ነው። በሰፊው የተሰማራበት የስራ መስክ ቡና እና የቅባት እህሎችን ኤክስፖርት በማድረግ ላይ ነው። በላይነህ ክንዴ ለብዙ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል። ጥሩ አስተዳዳሪም እንደሆነ ይነገርለታል። የበላይነህ አጠቃላይ ሀብት 4 ቢሊየን ዶላር ነው

5ኛ.. ወርቁ አይተነው ፦

ወርቁ አይተነው ትውልድና እድገቱ በምስራቅ ጎጃም ሲሆን ሀገራችን ውስጥ ካሉ ቢሊየነሮች መካከል አንዱ ነው። ወርቁ አይተነው W Investment የሚባል ትልቅ ካምፓኒ ያለው ሲሆን ከዛ በተጨማሪ ደግሞ በቡና እና የቅባት እህሎች ላኪነትም ይታወቃል። ወርቁ አይተነው ዛሬ ላይ የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ ውጣ ውረዶችን አይቷል። በጣም ጠንካራና ጀግና ሰው ነው። የወርቁ አጠቃላይ ሀብት 3 ቢሊየን ዶላር ነው

6ኛ.. ቴዎድሮስ አሸናፊ ፦

ቴዎድሮስ አሸናፊ የመጀመርያው የሀገር ውስጥ ዘይትና ነዳጅ ድርጅት ባለቤትና ስራአስኪያጅ ነው። በአምቦ ከተማ የሚገኘው የአምቦውሀ ድርጅት ባለቤትም ነው። የቴዎድሮስ አጠቃላይ ሀብት 2.7 ቢሊየን ዶላር አካባቢ ይገመታል

7ኛ.. ኡመር አሊ ፦

ኡመር አሊ ሌላኛው የሀገራችን ቢሊየነር ነው። ኡመር ወደ ንግዱ የገባው በደርግ ዘመን ሲሆን በ 5,000 ብር ካፒታል ነበር ንግዱን የጀመረው። ኡመር በስፋት የተሰማራበት መስክ የፕላስቲክ ማምረቻ ፋብሪካ ዘርፍ እና አስመጪና ላኪነት ነው። ከዛ በተጨማሪ የቡና ላኪም ነው። የኡመር አጠቃላይ ሀብት 2 ቢሊየን ዶላር አካባቢ ይገመታል

8ኛ.. ሱሁራ እስማኤል፦

ሱሁራ እስማኤል ኢትዮጵያ ውስጥ በአመት ለመንግስት በሚሊየኖች ግብር ከሚከፍሉ ህጋዊ የጫት ላኪዎች መካከል አንዷ ናት። ከጅጅጋ ከተማ የጫት ንግድ ተነስታ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ የቻለችው ይህቺ ሴት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ቢሊየነሮች መካከል አንዷ ናት። ሱሁራ በቀን ከ 50 ሺ እስከ 60 ሺ ኪሎግራም የሚሆን ጫት ለውጭ ገበያ ታቀርባለች። የሱሁራ አጠቃላይ ሀብት 1.5 ቢሊየን ዶላር አካባቢ ነው

9ኛ... አኪኮ ስዩም ፦

አኪኮ የታዋቂው የኮንስትራክሽን ካምፓኒ ባለቤት የስዩም አምባዬ ልጅ ናት። አኪኮ ኦርካይድ ቢዝነስ ግሩፕ የሚባል ትልቅ ድርጅት አላት። ኦርካይድ በሀገራችንን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ የተሳተፈ ግዙፍ ድርጅት ነው። የአኪኮ አጠቃላይ ሀብት 1 ቢሊየን ዶላር ነው

10ኛ... ትልቅሰው ገዳሙ ፦

ትልቅሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ቢሊየነሮች መካከል አንዷ ናት። ለበርካታ ዜጎችም የስራ እድል መፍጠር የቻለች ሰው ናት። ትልቅሰው በስፋት የተሰማራችው በሆቴል ኢንቨስትመንት ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የራዲሰን ሆቴሎች ባለቤት ናት። የትልቅሰው አጠቃላይ ሀብት 1 ቢሊየን ዶላር ነው።

21/11/2022

የጣናው ሞገድ ድል ተቀዳጅቷል💙 በጣና ሞገድ ቡና ታጥቦ ተሰጣ ማለት ነው😍 በርግጥ ለአሸናፊነቱ ፍቅር የሆኑ ደጋፊዎች ሚና ትልቅ ቦታ አለው። የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች በእስታዲዮሙ እንደ ጣና ማዕበል ሲገማሸሩበት ይታያሉ፤ አንዳንዴ በፀጥታ ይቆዩና በሆነ ቅፅበት ልክ እንደ ጣና ማዕበል ይነሳሉ፤ በዚህ የደጋፊዎች ማዕበል ከሩቅ ሰማያዊ ጭስ ወደሰማይ ሲተም ይታያል፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ እና የከነማ አርማ ወደላይ ይውለበለባሉ። በዚህ አስገራሚ የከነማ ደጋፊዎች ትርዒት "አለን፤ አለን" የሚለው መዝሙር ከእስታዲዮሙ ጣሪያ አልፎ ወደ ከተማዋ እስከ ጣና ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል።

ለዚህ ይመስለኛል ፍፁም አለሙ በአንድ ወቅት ከሀትሪክ ጋዜጣ ጋር በነበረው ቆይታ፣ "…የባህር ዳር ከተማ ደጋፊን መዝሙር እየሰማሁ በእነሱ ድጋፍ ታጅቦ መጫወት ከምንም ነገር በላይ ናፍቆኛል” ያለው።

Melkam Gebeya

Address

መድኃናልም አከባቢ
Addis Ababa
መንእስ

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mamo beyene beyi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share