Amen Spiritual Ministry -ASM

Amen Spiritual Ministry -ASM Share the word of God when we receive in spirit.

14/05/2024
18/04/2024

“ልዑል አምላክም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ የሚወድደውንም እንዲሾምበት እስኪያውቅ ድረስ ከሰው ልጆች ተይለቶ ተሰደደ፥ ልቡም እንደ አውሬ ልብ ሆነ፥ መኖሪያውም ከምድረ በዳ አህዮች ጋር ነበረ፤ እንደ በሬ ሣር በላ፥ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ።”
— ዳንኤል 5፥21

28/01/2024

3668 likes, 628 comments. “ 🇪🇹 🙏 #ተናገርእውነቱን 🇪🇹...

21/10/2023

በጠላት ከበባ ውስጥ ሆነህ ተፈርተህና ተከብረህ ከፍ ብለህ እንድትኖር ያደረገህ ዋናው ምስጢር እግዚአብሔር ከአንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ነው።

እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦
“እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔር ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ?”
— ዘኍልቁ 23፥8

የእስራኤል ህዝብ የሚጠፋ የሚረገም ህዝብ አይደለም። ዛሬም ዘርህን ሊያጠፉ ይሞክሩ ይሆናል፤ ግን አይችሉም።

“ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ።”
— ቆላስይስ 2፥18

ከአጋንንት ጋር ኪዳን ያለው ነገር አንገቱ ላይ እያንጠለጠለ፤ ዛፍና ድንጋይ ፥ ጨረቃና ወንዝ እያመለከ ማንም አይፍረድብህ ወገኔ። ኪዳንህን ከጌታህ ጋር አዲስ። በጠላትህ የምትበላው ከጌታ ጋር ያለው ኪዳንህ ሲበላሽ ነው።

ፀጋህ ይብዛልን!

07/09/2023

“ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።”
— መዝሙር 121፥8

03/09/2023

ዘኍልቁ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
²³ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦
²⁴ እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤
²⁵ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤
²⁶ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።

02/06/2023

“በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።”
— መዝሙር 91፥1

11/05/2023

አብረኸኝ መከራ ተቀበል

“እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥8

“እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል።”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥3

ስንተቻችን ነን ስለ ወንጌል ከመሪዎቻችን ጋር መከራ የምንቀበለው?
ስንተቻችን ነን የወገንን ጥቅም እንጂ መከራቸውን የማንፈልግ?
ብዙዎች የሚቆሙት በጥቅማቸው ጎን እንጂ በመከራቸው አይደለም!

ዛሬ ግን እላለሁ አብረህ ከበላህ፤ አብረህ ከሰራህ፤ አብረህ መከራን ተቀበል።

05/05/2023

የኑሮ መክበዱን ሁሉ ነገር መወደዱ
እህል ከጐተራ ሲጠፋ ፍሬም ባትሰጥ መሬት ታርሳ
ቀና ብሎ ዓይን ሲያይ ደመና የለም በላይ
ምድር ከሰማይ ይጠብቃል ሰማይ በምድር ላይ አፍጡዋል
ጊዜው ቢወስድ ይህ ዝምታ አምላኬ ምድሬን እየረሳ
ግን ጨለማው መበርታቱ ሊነጋ ነው ሌሊቱ ( 2x)

አዝ፦ አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ
አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ

የእግዚአብሔር ክንድ በምድሬ ሲነሳ
የመከራው ዘመን ሲረሳ
እምባ ካለቀሰው ሲታበስ
የዘመናት/የአባቶቼ ጸሎት ሲመለስ ( 2x)
አያለሁ አያለሁ አያለሁ አያለሁ

አዝ፦ አያለሁ አያለሁ ገና ገና ገና ብዙ አያለሁ
አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ

የጦርነት ድምጽ ፈርቶ
ካደገበት ቀይ ሸሽቶ
በሰው ሃገር አንገት የደፋ
የተናቀን የተገፋ
ምድረ በዳውን ሲያቋርጠው
በረሃው ሁሉም ሱያስጥለው
ግን ሃገሩን ይዞ በልቡ
ተበትኗል ሰሜን ደቡቡ
ተስፋ ቢጨልም በሁሉ ነገር
አንደበት ግን ክፉ አይናገር
ያለፈው ይብቃ እርግማኑ
የምትሰማ አያለሁ ( 2x)

አዝ፦ አያለሁ አያለሁ ገና ገና ገና ብዙ አያለሁ
አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ

ሽባዎች አንካሶች ሲዘሉ
ዲዳዎች ተናግረው ዕልል ሲሉ
የታወረው ዓይን ሲበራ
እግዚአብሔር/የማመልከው እራሱ ሲሰራ
አያለሁ አያለሁ አያለሁ አያለሁ (፭x)

ሃሌሉያ አያለሁ
እኔ እኔ እኔ አያለሁ

15/04/2023

“ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።”
— ሉቃስ 24፥5

ዛሬ የሚነሳው ያንተ የሞተ ነገርህ ነው!
ፈርተህ አቀርቅረህ ከሆነ ቀና ማለት ይሆንልሃል!
በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥም ይሁንላችሁ!

Address

Addis Ababa

Telephone

+251993632469

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amen Spiritual Ministry -ASM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Amen Spiritual Ministry -ASM:

Share