Janderebaw Media

Janderebaw Media የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

የኦሪየንታል ኦርቶዶክስና የኢስተርን ኦርቶዶክስ ልዩነት ምንድን ነው? ልዩነቱ ከምን ተጀምሮ እስከ ምን ድረስ ደረሰ? ልዩነቱን ለማጥበብስ ምን ሥራዎች ተሠሩ? ምን ያህል ተሳካ? የዶግማ ልዩነ...
21/05/2026

የኦሪየንታል ኦርቶዶክስና የኢስተርን ኦርቶዶክስ ልዩነት ምንድን ነው? ልዩነቱ ከምን ተጀምሮ እስከ ምን ድረስ ደረሰ? ልዩነቱን ለማጥበብስ ምን ሥራዎች ተሠሩ? ምን ያህል ተሳካ? የዶግማ ልዩነቶች ጀርባ ያለው ችግር ምንድን ነው?

ጃንደረባው ሚድያ | ጉባኤ ፊልጶስ | ዘወትር ሐሙስ ምሽት

ማስታወሻዎን አዘጋጅተው ይማሩ

19/05/2026
በድሬዳዋ ዐሥራ ስድስት ሙሽሮች ጋብቻቸውን ፈጸሙ| ጃንደረባው ሚድያ | ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም.| ድሬዳዋ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጃን ቃና ዘገሊላ ...
19/05/2026

በድሬዳዋ ዐሥራ ስድስት ሙሽሮች ጋብቻቸውን ፈጸሙ
| ጃንደረባው ሚድያ | ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም.| ድሬዳዋ ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጃን ቃና ዘገሊላ የቅድመ ጋብቻ ትምህርት ካስተማራቸው ጥንዶች መካከል ጋብቻቸውን ለመፈጸም በመምህረ ንስሐዎቻቸው ተፈቅዶላቸው ዝግጁ የሆኑ ዐሥራ ስድስት ሙሽሮች (ስምንት ጥንዶች) ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በድሬዳዋ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ጋብቻቸውን ፈጽመዋል።

የብዙኃን ጋብቻ ዓላማ ወጣቶች በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጋብቻቸውን እንዲፈጽሙ ለማድረግ፣ ቤተ ክርስቲያን ልጆቿን በኅብረት ሙሉ ወጪ ሸፍና የምትድርበትን ሁኔታ ለመፍጠርና በሰርግ ምክንያት አድርጎ የሚሰባሰብ ትልቅ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብና ማኅበረሰብን ለመገንባት ነው:: ምእመናን ጋብቻቸውን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመፈጸማቸው በፊት ምሥጢረ ንስሐን ፣ ምሥጢረ ቁርባንና ምሥጢረ ተክሊልን እንዲሁም የጋብቻ ሕይወትንና የልጅ አስተዳደግን ፣ የግጭት አፈታትን የመሰሉ መሠረታዊ ትምህርቶችን እንዲማሩ ማድረግ የጃን ቃና ዘገሊላ ፕሮጀክት ዋነኛ ሥራ ነው::

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በአዲስ አበባ ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም የመጀመሪያው በሆነው የብዙኃን ጋብቻ መርሐግብር 23 ጥንዶች መዳራቸውን እንዲሁም በወርኃ መጋቢት 2017 ዓ.ም 44 የሚሆኑት ጥንዶች የብዙኃን ጋብቻ በተሰኘው ቤተ ክርስቲያን ልጆቿን በኅብረት በምትድርበት ልዩ መርሐግብር ተሳታፊ እንደነበሩ ይታወሳል።

በያዝነው ዓመት ደግሞ ለኢጃት ድሬ የመጀመሪያው የሆነው መርሐግብር ከ የካቲት ወር መጀመሪያ ጀምሮ እስከ መጋቢት መጨረሻ ድረስ የቅድመ ጋብቻ ትምህርት ሲያስተምራቸው የነበሩ ጥንዶች መካከል 8 የሚሆኑት ጥንዶች ግንቦት 9/2018 ዓ/ም በተዘጋጀው መርሐግብር ላይ ተሞሽረዋል፡፡

በጋብቻው ሥርዓት ላይ በድሬዳዋ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ መጋቤ ሠናያት ቀሲስ ኃይለ ማርያም እና የየመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት ባማረው የቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት ተፈጽሞአል፡፡ ምዕመናን በዚሁ ቀን በካቴድራሉ ተገኝተው የደስታቸው ተካፋይ የሆኑ ሲሆን ከዚህ በኋላም ሙሽሮቹንም በጸሎት እንዲያስቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡ ከቤተ ክርስቲያን መልስም ለሙሽሮቹ በተዘጋጀ አዳራሽ የሰርጉ በዓል ተከብሮአል::

በቀጣይ እነዚህ ሙሽሮች በተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶች ላይ በኅብረት የሚሳተፉበት መንገድ የተዘጋጀ መሆኑን የኢጃት ድሬ ጃን ቃና ዘገሊላ አስተባባሪ ወ/ሮ እጹብድንቅ እንዳሻው የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ዓመትም ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ጋብቻቸውን የፈጸሙ ምዕመናን ቃል ኪዳነቸውን የሚያድሱበት፤ በጋራ ስጋውና ደሙን የሚቀበሉበት መርሐግብር እንደሚዘጋጅም አሳውቀዋል፡፡

በብዙኃን ጋብቻ ላይ የሚሞሸሩ ምእመናን ሙሉ ወጪያቸውን በኢጃት አስተባባሪነት ቤተ ክርስቲያን የምትሸፍን ስሆን ትምህርቱን በአግባቡ ከመማር ያለፈ ምንም ዓይነት ክፍያ ከሙሽሮች አይጠየቅም:: በድሬዳዋ የተደረገው ይህ ሥነ ሥርዓት በደጋግ ክርስቲያኖች የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ሲሆን ዓላማው ገብቷቸው ፤ የቤተ ክርስቲያንን አደራ ተቀብለው ይህ ታሪካዊ መርሐግብር እንዲሳካ የበኩላቸውን ጥረት ላደረጉ ሁሉ ከድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ጀምሮ ለተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ማኅበሩ በቤተክርስቲያን ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ እስከ አሁን 150 ሙሽሮችን በሦስት ዓመታት ውስጥ በብዙኃን ጋብቻ የዳረ ሲሆን በመጀመሪያው ሁለት ዙር የተዳሩ ሙሽሮች በድምሩ ወደ ዐርባ የሚጠጉ ልጆችን ወልደዋል:: በጋራ የተዳሩ ሙሽሮች በየወሩ የሚገናኙ ሲሆኑ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ::


ለሰባ ስድስት እናቶች የንግድ ሥራ ሥልጠና ተሠጠ👉🏼 የ2.4 ሚልዮን ብር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል👉🏼 የስድስት ወራት የባለሙያ ክትትል ያገኛሉ👉🏼 በያዝነው ወር አምስት ሕፃናትን ለማደጎ ወላጆች ተ...
16/05/2026

ለሰባ ስድስት እናቶች የንግድ ሥራ ሥልጠና ተሠጠ

👉🏼 የ2.4 ሚልዮን ብር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል
👉🏼 የስድስት ወራት የባለሙያ ክትትል ያገኛሉ
👉🏼 በያዝነው ወር አምስት ሕፃናትን ለማደጎ ወላጆች ተሠጥተዋል

ጃንደረባው ሚድያ
ግንቦት 2018 ዓ.ም. | አዲስ አበባ

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን ቂርቆስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ እናቶችን ለማገዝ በሚሠራው ፕሮጀክት በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል እና ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አጥቢያዎች ለሚገኙ 76 እናቶች ከአጥቢያዎቹ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ከሚያዝያ 16 እስከ ሚያዝያ 20 ድረስ የአራት ቀናት የንግድ ሥራ ሥልጠና ተሰጠ።

እነዚህ እናቶች ለሚሰማሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ሥራ ማስጀመሪያ የሚሆናቸውን ግብአት በ2,400,000 (ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሺ ብር) ተዘጋጅቶላቸዋል:: እናቶቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ የሚገቡ ሲሆን ድጋፉም፤ በዋነኛነት በሚኒሶታ ከሚገኙ በጎ አድራጊዎች እንዲሁም በሲያትል ከሚገኙ "የተዘረጉ እጆች" ከሚባል ድርጅት በልግስና የተገኘ ነው።

በተጨማሪም እናቶቹ በሥራቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ለስድስት ወራት የሚቆይ ክትትል እና የማማከር አገልግሎት ይሰጣቸዋል። ይህ ድጋፍ ከ2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከ110 በላይ ለሚሆኑ እናቶች የተደረገ ሲሆን በመጪው አመትም ከበጎ አድራጊዎች ጋር በመተባበር እስከ 200 ለሚሆኑ እናቶች ተመሳሳይ ድጋፍ ለማድረግ እቅድ ተይዟል።

በተያያዘ ዜና ጃን ቂርቆስ በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትን በኦርቶዶክሳዊያን ወላጆች በማደጎ ማሳደግ ላይ እንደሚሠራ ይታወቃል:: በመሆኑም በያዝነው ወር ሕፃናቱን ወስደው ለሚያሳድጓቸው ወላጆች ከሚያዝያ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት ሲሰጣቸው ከነበሩ በርካታ ቤተሰቦች መሐል አምስት የሚሆኑት ቤተሰቦች ሕጋዊ ሂደቱን ጠብቀው በአዲስ አበባ ከሚገኘው ክበበ ፀሐይ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋም እንዲሁም ሀዋሳ ከሚገኘው ሮኆቦት የሕፃናት መርጃ ማእከል ልጆቻቸውን ተረክበዋል ። ኢጃት በፊታችን ሰኔ ወር ላይ "የማደጎ ልጅ ማሳደግ"ን የተመለከት ሀገር አቀፍ ዐውደ ጥናት ለማካሔድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የጃን ቂርቆስ አስተባባሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ገልጸዋል::


በሐረር ከተማ የሱባኤ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ | ጃንደረባው ሚዲያ |  ግንቦት 2/2018ዓ.ም.ሐረር - ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ሐረር የሱባኤ ጉባኤ ትምህርት በሁለተኛ ዙር ...
16/05/2026

በሐረር ከተማ የሱባኤ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ

| ጃንደረባው ሚዲያ | ግንቦት 2/2018ዓ.ም.
ሐረር - ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ሐረር የሱባኤ ጉባኤ ትምህርት በሁለተኛ ዙር ያስተማራቸውን 107 ተማሪዎች በደመቀ ሁኔታ አስመረቀ።

የኢጃት ሐረር ቅርንጫፍ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አቤል ተኮላ "የሱባኤ ጉባኤ ዓላማ ምእመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን: እንዲያይዋት : እንዲያውቋት እና እንዲወዷት የሚያነሣሣ ከምሥጢራት እንዲካፈሉ እና የቤተ ክርስቲያንን ችግር "እነሆ ውኃ” በማለት ለማገልገል ማስቻል ነው።

በሱባኤ ጉባኤ የተሰጡት ትምህርቶች በውስጣችሁ የመንፈሳዊ ዕውቀትን ረሃብና ጥም እንዲጭሩ የተዘጋጁ የዕውቀት ረሃብ አስነሺ ትምህርቶች ናቸው። ከዛሬ በኋላ የተሰጣችሁን መሠረት ይዛችሁ በጸሎት፣ በንባብ፣ አባቶችንና መምህራንን በመጠየቅ እንዲሁም በተለያዩ መንፈሳዊ መንገዶች ዕውቀታችሁን ልታዳብሩ ይገባል። ቅዱስ ጳውሎስ ለደቀ መዝሙሩ ጢሞቴዎስ "እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ትጋ" (፩ኛ ጢሞ ፬፥፲፫) እንዳለው፣ እናንተም ዕውቀታችሁን ለማሳደግ ዘወትር የምትተጉ ሊሆን ይገባል" ብለዋል:: ለጉባኤው መሳካት አስተዎጽኦ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነዋል::

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ በዲያቆን ኢዮኤል ትምህርተ ዋንጌል የተሠጠ ሲሆን በተመራቂዎች ዝማሬም ቀርቦአል::
የኢጃት ሥራ አመራር ቦርድ ሰብባቢ የሆኑት ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት ከበደ የ21ቀኑ የሱባኤ ጉባኤ ትምህርት ዓላማ "ቤተ ክርስቲያንን ጠንቅቃችሁ እንድታውቋት ሳይሆን ፊልጶስ ጃንደረባውን በሰረገላ ላይ ሰብኮ እንዳጠመቀው ያለ አጭር ትምህርት ተምራችሁ የመማር ፍላጎታችሁን ለመክፈት ነው" ብለዋል:: በኢጃት ሐረር ቅርንጫፍ በጃን ማዕተብ እየተሠራ ያለውን የንዑሰ ክርስቲያን አገልግሎት እጅግ የሚያስቀና መሆኑን ገልጸዋል::

በዕለቱ መላከ ሰላም ጥበቡ መላኩ የሐረር መካነ ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ ለተመራቂ ተማሪዎች አባታዊ ምክር እና ቡራኬ ሰጥተው በጸሎት ዘግተዋል።


_አዘዘ

የእመቤታችን በዓለ ልደታ በድምቀት ተከበረ:: የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን ወለተ ጴጥሮስ ያዘጋጀው የእመቤታችን ልደት ልዩ ጉባኤ በድምቀት ተከበረ:: በጉባኤው ላይ የውዳሴ ማርያም ዜማ...
09/05/2026

የእመቤታችን በዓለ ልደታ በድምቀት ተከበረ:: የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን ወለተ ጴጥሮስ ያዘጋጀው የእመቤታችን ልደት ልዩ ጉባኤ በድምቀት ተከበረ:: በጉባኤው ላይ የውዳሴ ማርያም ዜማ በዲያቆናት ፣ በጃን ያሬድ ኅብረ ዝማሬ ፣ በቀሲስ ቡሩክ ሽታዬና በቀሲስ ተቅዋመ ማኅቶት ትምህርተ ወንጌልና ቃለ ምዕዳን በደማቅ ሁኔታ ተካሒዶአል:: ጃን ወለተ ጴጥሮስ የግንቦት ልደታን በዓል ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ እንዲከበር ዐውደ ጥናቶችን ከማካሔድ የጀመረው የዘንድሮው በዓል የ2017 ዓ.ም. በዓለ ልደታ ላይ ስእለት ተስለው የሠመረላቸውን ምስክርነት በጽሑፍና በቃል በማሰማት ለመጪው ዓመትም ስእለትን በመሣል ልብ በሚነካ መንፈሳዊ ድባብ ተከናውኖአል::

ግንቦት ልደታን በየመንደሩ ከሥጋዊ አከባበርና ከባዕድ አምልኮ መተናኮል በጸዳ መንፈሳዊነት በሥርዓተ ቤተክርስቲያን እናክብር:: እንኳን አደረሰን

09/05/2026

ሙሉ መዝሙሩን በጃንደረባው ሚዲያ የዩትዩብ ገጽ ላይ ያገኙታል

እንኳን ለወላዲተ አምላክ ለእመ ብርሃን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደታ በሰላም አደረሳችሁ!"እመቤቴ ሆይ የሚወድዱሽ የተወደዱ ናቸው"                         ...
09/05/2026

እንኳን ለወላዲተ አምላክ ለእመ ብርሃን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደታ በሰላም አደረሳችሁ!

"እመቤቴ ሆይ የሚወድዱሽ የተወደዱ ናቸው"
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ

4K likes, 265 comments. "ንዒ እምሊባኖስ | የልደታ ለማርያም አዲስ መዝሙር | በ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የጃን ያሬድ መዘምራን"

መጪውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል (ግንቦት ልደታ) ለምን፣ እንዴት እና በምን አይነት የአከባበር ስርዓት ማክበር እንዳለብን የሚያሳይ የኦንላይን ስልጠና በኢትዮጲያዊ...
05/05/2026

መጪውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል (ግንቦት ልደታ) ለምን፣ እንዴት እና በምን አይነት የአከባበር ስርዓት ማክበር እንዳለብን የሚያሳይ የኦንላይን ስልጠና በኢትዮጲያዊው ጃንደርባ ትውልድ የጃን ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ፕሮጀክት አዘጋጅቷል። የዚህ ስልጠና ተሳታፊ መሆን የምትፈልጉ ወጣቶች ከታች በተያያዘው ሊንክ በመመዝገብ ስልጠናውን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeRvipiuCXKfIrOIPZfzTKJUT3DwXCcKaVPiUz9tXV-Sg3vRQ/viewform?usp=publish-editor

“ሳትታመም በፊት ባለመድኃኒትን ፈልግ የኖኅ መርከብ የተሠራችው በጤና ጊዜ ነውና" ማር ይስሐቅ
01/05/2026

“ሳትታመም በፊት ባለመድኃኒትን ፈልግ የኖኅ መርከብ የተሠራችው በጤና ጊዜ ነውና" ማር ይስሐቅ

3 likes. "ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ | በጉባኤ ፊልጶስ"

Address

2QR3+JJV Commercial Bank Dejach Wube Branch
Addis Ababa
3RDFLOOR

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Janderebaw Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share