ክርሰቲያን ፖስት አማርኛ/ Christian Post Amharic

ክርሰቲያን ፖስት አማርኛ/ Christian Post Amharic ክርቲያናዊ መረጃ ማድረስ!

12/11/2024

With Nebyu F. Zeberga – I just got recognized as one of their top fans!

“ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።”  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17
17/08/2024

“ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17

02/10/2022

ጎስቋላ ሰው #ዘምራለሁ!🙌🥰

🙌🥰
02/10/2022

🙌🥰

የአንተ መልካምነት ዙሪያዬን ከቦታል
እንዳንተ የሚወደኝ ከወዴት ይገኛል
ምህረት ቸርንትህን ነፍሴ እያሰበች
በቀንም በማታም ትባርክሀለች
, and is what my life story is all about.

24/05/2022

የነፍስ ሽንቁር

ከ Nathinael Bekele ገጽ የተወሰደ!

"መንነህ ከበረሓ ግባ የሚያሰኝ ብዙ ነገር አለ፡፡ ርግጥ እንደ አተያይህ፣ እንደ አሰማምህ ነው፡፡ ሐሰትን እያላመጡ እውነትን በአደባባይ ማረድ፣. . . ወጣሪ ጥያቄዎችን መሸሽ፣. . . የህሊናን እሪታ፡-- በሳቅ፣ በሜም፣ በቀልድ፣ በኮሚክ፣ በሙድ፣ በሐሜት፣ ፀጥ፣ ጭጭ፣ ዝም ማሰኘት፣. . . በስውር አጉብጦ የሚያዳፋንን የሐጢያት ሸክም ያለ አንዳች መወቀስ እና ሰቀቀን አሳምኖ ተሸክሞ መኖር፣. . . ያገጠጡ ቅሌቶቻችንን በገንዘብ ሐይል ተቆጣጥሮ በሰላም መውጣት፣ በሰላም መግባት፣. . . አለመፀለይን፣ አለመቀደስን፣ ቃሉን በግል አለማንበብን ሳያቋርጡ መለማመድ፣. . . ሌላም ሌላም፡፡ ካንጀት-ላንጀት እናውራ ካልን የውድቀታችን ከረጢጥ ቢፈታ ንፍገት ያፈነው ጥፋታችን ከነጓጓላው ተቦትርፎ ይንፎለፎላል፡፡

በተለይም ደ’ሞ ብዙ ልብ ነዛሪ፣ ቅስም ሰባሪ፣ አንገት አስደፊ ውድቀቶች መሰወር [ጠብቆ] አቅቷቸው የአደባባይ ሚስጥር ይሆኑና ሳይውል ሳያድር ወዲያው በነጋታው ተዘንግተው ሕይወት ከቆመችበት የምትቀጥለው ነገር ሌላው ጨናቂ ጉዳይ ነው፡፡

ብቻ ስም ሊሰጠው የሚገባ አንድ እንግዳ የሆነ የ‘’ክርስትና’’ ሕይወት በየአደባባዩ እያናፋ ሲሄድ ይታየኛል። ከቅዱሳት መፅሐፍት ጋር የተሳሰርንባቸውን የትምህርት ክሮች በጣጥሶ ከአንድ ሰብኮ-አዳሪ ከንፈር ስር በሚወጡ ግላዊ ሐሳቦች ላይ የእምነት ጎጆችንን እንድንቀልስ የሚያደርግ ለዘብተኛነት [Liberalism] እና አጥን-ለግለሰብ [Personality cult] ፡፡

ብዙ ያልተደፈነ የነፍስ ሽንቁር አለ። እጅን ደረት ላይ አሳርፎ "የመስቀሉን አሁንነት" እና "የድነታችንን ልበ-ምት" ማድመጥ ያስፈልጋል፡፡ ክርስቶስን በሌላው ትከሻ ላይ ተንጠልጥሎ መከተል አይቻልምና መንፈሳዊ ግለ-ግንኙነቶቻችንን እናድስ፡፡ ግድ የለም፡-- ሐሜቱም፣ ቀልዱም፣ ምድራዊ ተድላውም፣ በምላስ ቀስት መወጋጋቱንም ለጊዜው ገታ አድርገን በውስጥ ሰውነታችን እንጠንክር፡፡ በድካም ሐሞታችን የፈሰሰም ካለን፣ ግድ የለም ፡-- ጤዛ ልሰን፣ ኮሶ ቆርጥመን፣ የሙት ሙታችንን እናንሰራራ፡፡ . . . ያኔ ሁላችንም ብርሃናችን እንደ ማለዳ ጀምበር በሰው ሁሉ ፊት ያበራል፡፡ ከተመሳስሎሽነት ካቴና ወጥተን አይቀሬ ግዴታዎቻችንን በአግባቡ እንወጣ፡፡"

"ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና. . . አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፣ መከራን ተቀበል፣ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፣ አገልግሎትህን ፈፅም፡፡"

ነገረ ውርጃ[ረዘም ያለ ጽሑፍ]ከ Aman Shalom ገጽ የተወሰደ!(ሁለት ደርዝ ሙግት - ከክርስትና እና ከሞራል አመክኒዮ አኳያ)በዚህ ርዕስ ላይ ልጽፍ ሳስብ ከርምያለሁ:: ሰሞኑን አለም አ...
09/05/2022

ነገረ ውርጃ

[ረዘም ያለ ጽሑፍ]
ከ Aman Shalom ገጽ የተወሰደ!

(ሁለት ደርዝ ሙግት - ከክርስትና እና ከሞራል አመክኒዮ አኳያ)

በዚህ ርዕስ ላይ ልጽፍ ሳስብ ከርምያለሁ:: ሰሞኑን አለም አቀፍ ተቋማትና የዜና አውታሮች እንዲሁም ከአገር ቤት አንዳንድ ስለጉዳዩ እዚህም እዚያም በየ ማህበራዊ ድህረ ገጽ ላይ ርዕስ ሲሆን መጻፍ እንዳለብኝ ተሰማኝ:: ውርጃን በተመለከተ ነጮቹ "ፕሮ ቾይስ እና ፕሮ ላይፍ" ብለው አተካራ ውስጥ ከገቡ ሰንብተዋል:: ፕሮ ቾይስ እንደስሙ ውርጃ ሰብዓዊ መብት ነው ያንን ለማጽደቅ ብዙ ምክኒያቶችን ማቅረብ እችላለሁ የሚለው ጽንፍ ሲሆን ፕሮ ላይፍ ደግሞ ጽንሱ ሰው ነው ውርጃ ደግሞ ያልተወለደ ህጻን መግደል ነው የሚለው ነው:: ውርጃን የሚደግፉ አካላት ክርስቲያኖች ያልሆኑ ብቻ ሳይሆኑ ራሳቸውን ክርስቲያን እንደሆኑ የሚያስቡ ጭምር መሆኑ ነገሩ ምን ያህል የተወሳሰበ መሆኑን ያሳያል:: "I am Christian and I'm prochoice" የሚል ባነር ይዘው ሊወጡ የሚደፍሩ አሉ:: ከሌሎች አቅጣጫዎች የሚነሱትን ክሶች እና ለውርጃ ሃሳብ ድጋፍ ይሆናሉ ተብለው የሚቀርቡ መከራከሪያዎችን ከማየታችን በፊት እውን መጽሐፍ ቅዱስን እያነበቡ ውርጃን መደገፍ ይቻላልን? የሚለውን ጥያቄ በወፍ በረር እንመልስና ወደ ሌሎቹ ክሶች እንሔዳለን:: መሰረት ሳይጣል ወደ ቀጣይ ፍሎሮች መሄድ አይቻልምና::

መጽሐፍ ቅዱስ ስላልተወለዱ (በማሕጸን ውስጥ ስላሉ ልጆች) ምን ይላል?
----------------------//---------------------

1. "ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ #ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት (ሉቃ 1:41-44) በዚህ ክፍል ውስጥ [ፅንሱ] ተብሎ የተተረጎመው ቃል በግሪክ βρέφος {ቢሪፖስ) የሚል ሲሆን ትርጉሙም እንግሊዝኛዎቹ ትርጉሞች እንዳስቀመጡት "ልጅ" በተለይም "ጨቅላ ልጅ" የሚል ትርጉም ይይዛል:: በዚሁ ክፍል ውስጥ እስከ ቁጥር 44 የተረገዘው በማሪያም ማህጸን ውስጥ ያለው ልጅ ከመሆኑም ባሻገር "ጌታዬ" ተብሏል (ቁ. 43) "የማህጸንሽ ፍሬ" (ቁ.42) ላይ የተባለው (ቁ.44) ላይ በድጋሚ "ቢሪፖስ" ልጅ - ሰው መሆኑ የጸናለት ኢየሱስ ነው:: ይህ ህጻን እያለ ለልጅ የገባው የግሪክ ቃል ልጁ ከተወለደም በኋላ ተመሳሳይ ቃል ሲመጣ እናያለንብ (ሉቃ 2:16 እና ሌሎች ክፍሎች ሉቃ 18:15; 2 ጢሞ 3:15)::

2. አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል። (መዝ 139:13) በአዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢንግሊዝኛው "You formed my inward parts;
you knitted together in my mother’s womb" ይላል:: "አንተ ውስጣዊ ሰውነቴን ፈጥረሃልና: በእናቴ ማህጸን ውስጥ አበጃጅተህ ሰራኸኝ" ይላል:: እዚህጋ ከማህጸን ተወልዶ የወጣውና አሁን ላይ ንጉስ ሆኖ እየተናገረ ያለው በመጀመሪያ መደብ ተውላጠ ስም "እኔ" እያለ በማህጸን ውስጥ የነበረው ሰው መሆኑን ይስረግጣል::

3. "ልጆችም በሆድዋ ውስጥ ይገፋፉ ነበር፤ እርስዋም፦ እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔ ምኔ ነው? አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች። እግዚአብሔርም አላት፦ ሁለት ወገኖች በማኅፀንሽ ናቸው፥ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።" (ዘፍ 25:22-23)

ርብቃ መንዮችን (ያዕቆብንና ኤሳውን) አርግዛ ሳለ ነው ይህ እውነት የሆነው:: መጽሐፍ ቅዱስ በሆዷ ውስጥ ይገፋፉ የነበሩ መንትዮችን "ልጆች" ብሎ ይጠራና ልጅን በማጸን የሚሰጥ እግዚአብሔር በተራው ደግሞ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ ልጆቹ "ወገኖች" ወይም እንግሊዝኛው "nations" የሚለው የህዝብ ቡድን ከሁለቱ መንትዮች እንደሚፈልቁ ይናገራል:: ህዝብ ደግሞ የሰዎች ድምር ውጤት ነውና ማህጸን ውስጥ ያሉ "ልጆችን" እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያያቸው ይህ ክፍል ግልጽ ያደርጋል::

4. ዘጸ 21:22-25 ባለው ክፍል ውርጃንና ጽንስን በተመለከተ መዝገብን ሊዘጋ የሚችል የእግዚአብሔር ህግ ተቀምጧል:: የክፍሉ የኋልዮሽ ታሪኩ ሁለት ወንዶች እርስ በርስ ቢጣሉና ቢደባደቡ በመሃል እርጉዝ ሴት በድንገት ብትጎዳ ወይም ጽንሱ ቢጎዳ ስለሚመጣ ፍርድ የሚናገር ክፍል ነው:: እንዲህም ይላል

"ሁለት ሰዎች ቢጣሉ፥ ያረገዘችንም ሴት ልጁን እስክትጨነግፍ ቢገፉአት ባትጐዳ ግን፥ የሴቲቱ ባል የጫነበትን ያህል ካሳ ይስጥ፤ ፈራጆቹም እንደ ፈረዱበት ይክፈል። ጕዳት ግን ቢያገኛት ሕይወት በሕይወት፥ ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ መቃጠል በመቃጠል፥ ቍስል በቍስል፥ ግርፋት በግርፋት ይከፈል።" ይላል::

እዚህ ክፍል ላይ ሁለቱም: ማለትም ህጻኑና ጽንሱ(ልጁ) እየተዳሰሱ መሆኑን የምናውቀው "ልጁን እስክትጨነግፍ ቢገፉአት ባትጐዳ ግን" የሚል ቃል አለ:: ይህም አንድ: በግፊቱ የልጁ መጨንገፍ እና ሁለት ደግሞ በግፊት ነፍሰ ጡሯ ላይ ጉዳት ባይደርስ (ቁ.22) እና ጕዳት ግን ቢያገኛት (ቁ>23) የሚመጣን ፍርድ ያሳያል:: ስለዚህ እግዚአብሔር እያወራ ያለው ስለ ጽንሱም ስለ እርጉዟ ሴት ነው ማለት ነው:: ይህ በሁለት ወንዶች መካከል የተነሳ ግጭት እንጂ ሴቲቱን ያካተተ አይደለም:: ነገር ግን [ድንገት] ነፍሰ ጡሯን ቢያገኛት እንኳን ፍርዱ ወደ በዳዩ ግለሰብ የሚዞር ነው:: ሴቲቱ እና ጽንሱ ተጎድቶም ሆነ ባይጎዳ በሁለቱም ከፍርድ አያመልጥም:: ነገር ግን ተጎድቶ ቢሆን ወይም ጽንሱ ጨንግፎ ከሆነ ያንን ያደረሰው ግለሰብ እጣ ፈንታ ትልቁ ቅጣት ሞት ነው:: ለምን? እግዚአብሔር እያየ ያለው ማህጸን ውስጥ ህይወት እንዳለፈ ነው:: በሙሴያዊ ኪዳን ውስጥ ምናልባት ትልቁ የሞት ፍርድ ሆኖ የተመዘገበው ይህ ነው:: ሌላ ሰው ሰውን ቢገድል (ሳያስብ እንኳን) ወደ መማጸኛ ከተሞች እንዲሄድ እና ሌላ ሞት ከመፍጠር የሚታደግ ህግ አለ:: ነገር ግን የትም ቢሄድ እንዳያመልጥ የተደረገበት (እንደዚህኛው ክፍል ድንገት ቢሆንም እንኳን) ህግ እርጉዝ ሴትንና በማህጸኗ የተሸከመችው ህጻንን በተመለከተ ከወጣው ህግ ማምለጥ አይቻልም:: በድንገት ለሆነ ነገር ህጉ እንዲ ከጠጠረ በእቅድ ለሚሆን እንዴት ይሆን?

በድምዳሜው:- መጽሐፍ ቅዱስን ይዘን ውርጃን ስለመደግፍ በምንም ተዓምር ልናወራ እንደማንችል አይተናል:: እግዚአብሔር በማጸን ውስጥ እያበጃጀ ያለው ስም አልባ - ጾታ አልባ - መድረሻ አልባ [ነገር] ሳይሆን በመልኩ እንደ አምሳሉ የፈጠረው ሰው መሆኑን ቃሉ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያረጋግጣል:: ይህንን የምታነቡ ውርጃን የፈጸማችሁ ልትኖሩ ትችላላችሁ:: ሌላውንም ውርጃ እንዲያደርግ ያበረታታችሁ ጭምር . . . የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ውርጃ ነፍስ ማጥፋት እንደሆነ ከመሰከረ በእግዚአብሔር ፊት ጥፋተኛ ያደርገናል:: ነገር ግን አሁንም ይሄው የእግዚአብሔር ቃል በዚያው አንደበት በአዲሱ ኪዳን "በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።" (1 ዮሐ 1;9) ይላል ንስሃ በድልን ያጥባል:: ዳግመኛ ይህንን በደል በፊት ላለማድረግ ጸጋው ይርዳን::

በዚህ ላይ የሚነሱ ክሶች!
-------//-----------

ውርጃን ከሚደግፉ ወይም ስለ ውርጃ መጥፎ ግንዛቤን ከማይዙ ሰዎች የሚነሱ ክሶች ቢበዙ ከሶስት ዋና ዋና ጭብጦች የሚያልፉ አይደሉም:: እነዚህም:-

1. ተደፍራ ያረገዘች ከሆነና በተለይም ቤተሰባዊ ወይም የዘመድ ጥቃት ከሆነ

2. በኢኮኖሚ ልጁን ማሳደግ የማይችሉ ከሆነና "ለምን ልጁ ላይ ሌላ ችግር አመጣለሁ?" ከሚል

3. ጽንሱ ለእናቲቱ ህይወት አደጋን የሚደቅን ከሆነ

4. ብዙ ያልተለመደ ቢሆንም በተለይም ጽንሱ "ጤነኛ" እንዳልሆነ በምርመራ ከተረጋገጠ (ኖርማል ብለን የማንስባቸው ነገሮች ባኖሩበት) ወላጅንም ልጅንም ከእድሜ ልክ ስቃይ መታደግ ነው ውርጃ ይሻላል የሚሉ ይገኙበታል::

ለክሶቹ አጭር መልሶች!
------//-----------

1. ተደፍራ ያረገዘች ወይም በዘመድ በቤተሰብ ጥቃት ደርሶባት ያረገዘች ሴትን ስነ ልቦናዊ እና አካላዊ ህመም ማሰብ እጅጉን ከባድ ነው:: የምድር ላይ ገሃነምን ሴቲቱ ታሳልፋለች:: በዚህ ውስጥ የሚያልፉ እና ያለፉ ሴቶችን መጠጋት መንከባከብ እና መራዳት የእኛ ድርሻ ነው:: ምክኒያቱም ወደው ሳይሆን ተደፍረው የገቡበት ስለሆነ:: ነገር ግን አንድ ነገር እውነት ነው:: በየትኛውም አጋጣሚ በሆዷ ውስጥ የተፈጠረው [ሰው] ነው:: ጽንስን ሰው እንደሆነ አምነን ከተነሳን ሆድ ውስጥ እያለ መግደል እና ከተወለደ በኋላ መግደል ምንም ልዩነት አያመጣም:: የባህር ውስጥ ሰርጓጅ መርከብ ውስጥ እያለ አንድን ባልደረባ መግደል እና ከውሃ ውስጥ ከወጣ በኋላ ቤቱ እያለ መግደል የቦታ ልውጥ እንጂ ሁለቱም ግድያ ነው:: መደፈሩ የተጸነሰው ልጅ ጥፋት አይደለም:: ጽንሱ በሌላ ሰው በደል (በደፋሪው) ጥፋት ሞት ሊፈረደበት አይገባም:: ጥፋቱ የደፋሪው እንጂ ሆድ ውስጥ የተፈጠረው ሰው (ህጻን) አይደለም:: ስለዚህ ለውርጃ በቂ ምክኒያት ሊሆን አይችልም:: በ'ንዲህ አይነት መንገድ ተወልደው ያደጉ ብዙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሶውች ምድራችን አፍርታለች:: በመደፈር የተወለዱ ብዙ ደስተኛ ህይወት እየመሩ ያሉ አለማችንንም እየጠቀሙ ያሉ ሰዎች ለዚህ ምስክር ናቸው:: ተደፍራ ያረገዝችው ሴት የደፋሪዋን ፊት በልጇ መልክ ላይ ማየት ባያሰኛት መግደል ሳይሆን ምርጫ መሆን ያለበት ለአሳዳጊ ተቋማት መስጠትም ሊሆን ይችላል:: ይህ ክስ ብዙ የማያስኬድበት ሌላኛው ምክኒያት ደግሞ በዚህ መንገድ የሚያረግዙ እና ውርጃን የሚፈጽሙ ሴቶች ቁጥር በአሃዝ ከ 1 % ሲያልፍም ከ 1% በታች a1 መሆኑ በጥናት የተረጋገጠ መሆኑ ነው::

2. ለሁለተኛው ክስ አሁንም ምላሹ ተመሳሳይ ነው:: ልጁ ተወልዶ የሶስት ወር ወይም የአንድ ወር ህጻን ቢሆን እያየን ልጁን እንገድለዋለን ወይ? የሚል ነው:: በኢኮኖሚ ምክኒያት የሚለው ብዙም የማያዋጣ ሙጉት ሲባል ይተቻል:: እርግዝናን ቀድሞ መከላከል እየተቻለ ከተፈጠረ በኋላ ግን የኢኮኖሚ ሁኔታን ማየት መጀመር እንዝላልነትም ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል:: አሁንም ከተፈጠረ በኋላ ነፍስን ከማጥፋት ለአሳዳጊዎች በጉዲፈቻ መስጠት እጅጉን የከበረ ምርጫ ነው:: ምናልባት ለጉዲፈቻ መስጠት ሃፍረትን ሊፈጥር ይችል ይሆናል - ነገር ግን ከገዳይነት እጅጉን የከበረ እና የተሻለ ምርጫ ነው::

3. ጽንሱ ለእናቲቱ ህይወት አደጋን የሚደቅን ከሆነ የሚለው ክስ ክብደትን ማግኘት ያለበት ነው:: ከሌሎች ክሶች ይሄኛው ክብደት ማግኘት ያለበት ምርጫው ከሁለት ሊጠፋ ካለ ነፍስ አንዱን ማዳን ስለሆነ ነው:: ልጁን ማጣት ወይም ልጁንና እናትዬውንም ማጣት:: በህክምና ስሙ "ectopic pregnancy" የሚባለው ሲሆን ልጁ ማህጸን ውስጥ ከመሆን ይልቅ ፋሎፒያን ቱቦ ውስጥ ሲያድግ ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ውርጃ ሊካሄድ ይችላል:: አላማውም የተለየ የሚያደርገው ከሌሎቹ ነፍስን የማትረፍ እንጂ በእቅድ ልጅን የመግደል ስላልሆነ ነው:: ብዙ ነገረ መለኮታዊያን ሆኑ ጤነኛ አሳቢ ሃኪሞች ይሄኛው ምርጫ ብቻ ውርጃን ለማካሄድ ምክኒያት ሊሆን እንደሚችል ይስማማሉ:: በአሜሪካ የበሽታዎች ቁጥጥር ማዕከል (CDC) ባደረገው ጥናት ከሌሎች ውርጃዎች ጋር ሲነጻጸር ይሄኛው ማለትም እናትን ከሞት ለመታደግ የተደረገ ውርጃ በአሃዝ ከ 0.118% በታች a2 እንደሆነ ያትታል:: በዩናይትድ ኪንግደም የተካሔደ ጥናት ደግሞ 0.006% እንደሆነ a3 ያሳያል::

4. ይሄኛው በብዙ መንገድ ተፋልሶዎችን "ፋላሲስ" የምናወጣለት ክስ ነው:: ልጅን ማህጸን ውስጥ የሚሰራ እግዚአብሔር ነው (ሌላ ትርጉም ካላችሁም ያዙት) ምንደርስበት ድምዳሜ በእኛ ላይ የሚሆን ነገር ግን በእኛ ዲዛይንና ክትትል የሚፈጠር የሚያድግ ነገር አለምሆኑ ነው:: ኦቲዝም ያለበት ልጅ መውለድ የሌለበትን ልጅ ከመውለድ እኩል ደስታ አይኖረውም እሙን ነው:: ነገር ግን የተለያየ እክል በአካል እና ስነ እድገት ላይ ያለባቸው ልጆች አሁንም [ሰዎች] መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም:: በሁኔታቸው ደስተኛ መሆን አለመሆናቸውን የሚወስኑት ራስቸው ይሆናሉ እንጂ እኛ ልንሆን አንችልም:: አንድ አይነ ስውር ልጅን ካለመወለድ እና አሁን ካለህበት ሁኔታ ተብሎ ቢጠየቅ መኖሩን በብዙ እንደሚመርጥ የታወቀ ነው:: በአጭሩ የመኖር አለመኖርን ምርጫ ከእርግዝና በፊት እንጂ ከጽንስ በኋላ የማድረግ መብት አልተሰጠንም በሞራልም ስህተት ሆኖ ይገኛል::

አጠቃላይ ድምዳሜ:- የሴት ማህጸን ውስጥ እንቁላል እና ስፐርም ዘረመል ከተገናኙ በኋላ የሚፈጠረው አካል የሆነ የሴቷ የሰውነት አካል ሳይሆን በሴቷ ውስጥ ያለ ነገር ግን ከሴቷ የተለየ አዲስ ፍጡር እርሱም ሰው የሆነ አካል መሆኑን ሳይንሱም የማይክደው ሃቅ ነው:: በተለይ ሳይንስን ይዞ የሰው ሰውነት ውስጥ በእንቁላልና በስፐርም ሴል ግንኙነት የተፈጥረው አዲስ ስብዕና ያለው - አዲስ ማንነት ያለው - አዲስ የእሳቤ ማዕከልን የገነባ [ሰው] አይደለም የሚል ዘመናዊ ሳይንስ የደረሰበት ሙግት ሊያቀርብ የሚችል ማንም የለም:: አዎን የለም:: መጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃል ብለን የምናምን ጉዳዩን መጽሐፉ በ 4 ነጥብ ሲዘጋው ተመልክተናል:: ውርጃን ያደረጋችሁ ከእግዚአብሔር የምህረት እጆቹ ውጭ አይደላችሁም እና ንስሃ ሃጢአትን ሊያጥብ እንደሚችል አይተናል:: ለውርጃ የሚቀርቡ ክሶች ብዙዎቹ በአማራጭ ውሳኔ ሊተኩ እንደሚችሉና ውርጃን ሊያጸድቁ አመክኒዮአዊ መሰረት እንደሌላቸው እንዲሁም ውርጃን የምንፈቅድበት አንድ መንገድ እሱም የመከሰት እድሉ ከዜሮ በታች መሆኑን ተመልክተናል:: እናቲቱን ነፍስ ከማታደግ ውጭ ያሉ የውርጃ ማጽደቂያ ክሶች ልጅን ማህጸን ውስጥ እያለ መግደል ሴቲቱ እንደ መብት የምታደርገው ነገር ይሆናል እንጂ በየትኛውም መንገድ ማጽደቂያ ሊገኝለት የማይችል ክስ ነው::

ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ
Aman Shalom

Christian Ethics: An Introduction to Biblical Moral Reasoning በ Wayne Grudem እና Introducing Christian Ethics: A short guide to moral choice በ Scott B. Rae ዋቢ አድርግያለሁ

👇👇👇
25/12/2021

👇👇👇

የወንጌል አማኞች ለመጀመሪያ ጊዜ በታላቁ መስቀል አደባባይ የፊታችን ጥር አንድ እግዚአብሔርን ያመልካሉ።
ጥር 1
በመስቀል አደባባይ
የምልጃና የአምልኮ ፕሮግራም።
እያመለክን ወገኖቻችንን የምንረዳበት ድንቅ ጊዜ
አዘጋጅ ዘፀአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን

24/10/2021

የሕክምና ባለሙያዎች ፈውስን በተመለከተ ለቤተ ክርስቲያን የምክር ሐሳብ ሰጡ :__ከሰማያዊ ሓሳብ ገጽ የተወሰደ

መግቢያ

የክርስቲያን ሐኪሞች እና ዴንቲስቶች ማኅበር - በኢትዮጵያ፣ በአባላቱ መካከል መተናነጽን ለመፍጠር እንዲሁም ለአብያተ ክርስቲያናት እና ለአገር ጠቃሚ ጕዳዮችን ለማበርከት በሚል ዐላማ የተሰባሰቡ የወንጌላውያን ክርስቲያን ሐኪሞችን በማቀፍ ከ30 ዓመታት በፊት የተመሠረተ መንፈሳዊ ማኅበር። ማኅበሩ ከዚህ በፊት የጤና እና የሕክምና ጕዳዮችን በተመለከተ ለአብያተ ክርስቲያናት አስፈላጊውን ትምህርትና ምክር ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ በተለይ ኤች አይ ቪ - ኤድስ የአገርም ሆነ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ተግዳሮት በነበረበት ወቅት፣ የቅድመ ጋብቻ የኤች አይ ቪ ምርመራ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲተገብሩት ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። ይህም ድርጊት በብዙ አብያተ ክርስቲያናት እና አባላት ዘንድ ከጕዳዩ ጋር ለተያያዙ ውስብስብ ችግሮች መፍትሔን አምጥቷል። በኢትዮጵያ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በፈውስ አገልግሎት ዙሪያ ስላሉት አንዳንድ ተጨባጭ ክስተቶች የማኅበሩ አባላት በተከታታይ ከተወያዩ በኋላ፣ ለአብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮች እና ምእመናን ሁሉ ጠቃሚ ነው ያሉትን መልእክት አስተላልፈዋል።



ማኅበሩ በሕክምናና በሽታን በመከላከል ሙያ ሕዝባችንን የሚያገለግሉ አባላትን የያዘ የወንጌላውያን ክርስቲያኖች ማኅበር ሲሆን፣ በሽታንና ፈውስን በተመለከተ የማኅበሩ አባላት ያላቸው እምነትና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በሚገኙ በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በፈውስ ዙሪያ ስላሉት ክስተቶች ያለው ግንዛቤ እንደሚከተለው ነው፡-



በሚታወቅም ሆነ በማይታወቅ ምክንያት በሰው ላይ የሚከሰት በሽታና ስቃይ ከመጀመሪያዎቹ ከሰው ልጆች (ከአዳም እና ሄዋን) በኀጢአት ከመውደቅ ጋር ተያይዞ እንደ መጣ ከእግዚአብሔር ቃል እንረዳለን (ዘፍ 3፥7-19)።
ሰዎች ከውድቀት በኋላ በምድር ላይ በብዙ ድካምና ወዝ እንዲኖሩ እንደ ታዘዙ ሁሉ፣ የሚደርስባቸውን ችግርና በሽታም ራሳቸውንና አካባቢያቸውን በአግባብና በንጽሕና በመጠበቅ ለሕመም ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች እንዲጠበቁ መጽሐፍ ቅዱስ ያዛል (ዘዳ 23፥12-14)።
በተላላፊ ሕመም የተያዘ ሰው በሽታውን ወደ ሌላ ሰው እንዳያስተላልፍ ከሕመሙ እስኪድን ድረስ ራሱን ከሰው ለይቶ እንዲያቆይ መጽሐፍ ቅዱስ ያሰተምራል። ብሉይ ኪዳን ስለ እባጭ፣ ስለ ፈሳሽ፣ ሰለ ቆዳ በሽታ ካህኑ እንዲመረምርና እንዲያክም የመከላከል ርምጃም እንዲወስድ መመሪያ ይሰጣል (ዘሌ 13-15)።
ይህን ሁሉ አልፎ በሰው ላይ ለሚከሰት ሕመም ግን እግዚአብሔር በቸርነቱና በርኅራኄው ከሕመሙ የሚድንበትን መድኃኒትና ያለ መድኃኒትም በመለኮታዊ ኀይል የሚፈወስበትን መንገድ አዘጋጅቷል። ይህም በቀደሙት የመጽሐፍ ቅዱስ አባቶችም ዘንድ ሆነ በዘመናችን ሲገልጥ ታይቷል (ኢሳ 38፥21፤ ኤር 8፥22፡ 46፥11፡ 51፥8፤ ሕዝ 47፥12፤ ቆላ 4፥14)።
የማኅበሩ አባላት የተገለጠውን የእግዚአብሔር ጥበብና ማስተዋል ተምረው በሳይንሳዊ መንገድ ሰዎችን የመርዳት ተግባራቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን፣ ይህም ተግባር ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው ኃላፊነት መሆኑን ያምናሉ።
በዚህም ሳይንሳዊ ጥበብ አማካኝነት በርካታ ሰዎች ከስቃይና ከበሽታ ድነው የቀደመው ጤንነታቸው ተመልሶላቸው ሲሄዱ፣ አንዳንዶች ደግሞ መድኃኒታቸውን ያለ ማቋረጥ እየወሰዱ በተሻለ የጤንነት ሁኔታ ሲኖሩ ማየት የተለመደ ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ ከሳይንሱና ከሌሎችም የአቅም ውስንነቶች የተነሣ የሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ማየት የማኅበሩ አባላት በሙያቸውም ሆነ በማኅበራዊ ኑሯቸው ዙሪያ የሚያጋጥሟቸው ክስተቶች ናቸው።
ይህ በእንዲህ እያለ፣ የማኅበሩ አባላት በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ እንደምናነብበው ሁሉ፣ ዛሬም እግዚአብሔር የሰው አእምሮ ሊረዳው በማይችለው መለኮታዊ መንገድ ወይም በተኣምር ሰዎችን ከሕመማቸው ይፈውሳል ብለው ያምናሉ፤ ጸሎትን ያበረታታሉ፤ ራሳቸውም ለሕመምተኞች ይጸልያሉ፣ በጸሎታቸውም እግዚአብሔር ሲፈውስ አይተዋል።
ይህ መለኮታዊና ተኣምራዊ ፈውስ በማንም፣ በምንም ምክንያት ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነትና ለሰው ልጆች ባለው ርኅራኄ ምክንያት አምነው እርሱን ለሚለምኑት የሚሰጥ በጎ ችሮታ ነው ብለው ያምናሉ።
በሕክምና ሳይንስ አማካኝነት የሚፈወሱትንም እግዚአብሔር ለሰዎች በገለጠላቸው ጥበብ የተገኘ ፈውስ ነው ብለው ያምናሉ። ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ የሚደግፈውና የቀደሙት የብሉይና የአዲስ ኪዳን አባቶችም የተቀበሉትና የተለማመዱት መሆኑን አባላቱ ያምናሉ።
የማኅበሩ አባላት በጌታ በኢየሱስም ሆነ በሐዋርያት አገልግሎት ተፈውሳችኋል የተባሉ ሕመምተኞች ሁሉ መፈወሳቸውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ይረዳሉ (ማቴ 9፥32፡ 17፥14-18፤ ማር 2፥3-7፡ 5፥5-31፤ ሉቃ 4፥33-39፡ 5፥12-14፡ 7፥14-15፡ 9፥42፡ 13፥10-13፡ 14፥1-4፡ 17፥11-16፤ ዮሐ 11፥43-44፤ ሐሥ 3፥16)።
ለፈውስ ከተጸለየላቸው ሰዎች መካከል እኛ በማይገባንና እግዚአብሔር በሚያውቀው ምክንያት ሳይፈወሱ የቀሩ ሊኖሩ እንደሚችሉ እናምናለን። ስለዚህ ያልተፈወሱትን ሰዎች ሁሉንም ከእምነት ማነስ ነው ብሎ መፈረጅ ተገቢ እንዳልሆነ እናምናለን (2ቆሮ 12፥8-10፤ 2ጢሞ 4፥20)።
አሁን በአገራችን በሚታየው ሁኔታ በትክክል በጸሎት የተፈወሱ መኖራቸውን የሚመሰክሩት ሐቅ ቢሆንም፣ በተቃራኒው ደግሞ ተፈውሳችኋል የተባሉ ሁሉ እንዳልተፈወሱ፣ አንዳንዶችም እንደተባባሰባቸው፣ አንዳንዶችም እንደ ሞቱ፣ አንዳንዶችም ሳይፈወሱ ተፈውሳችኋልና መድኃኒታችሁን ጣሉ እንደ ተባሉ አባሎቹ በሥራቸው ምክንያት ካጋጠማቸውና ከሌሎችም ሰዎች ባገኙት ምስክርነት መረዳት ችለዋል። ይህ ደግሞ ለሰዎች ጉዳትን ያስከተለ፣ ለቤተ ክርስቲያን ነቀፋን ያመጣ፣ ሲቀጥልም በሕግ ተጠያቂነትን ሊያስከትል የሚችል ተግባር መሆኑን ማኅበሩ ይረዳል።
ተፈውሳችኋል፣ ተብለው ሳይፈወሱ የቀሩ ወይም ተፈውሰናል ብለው በማመን መድኃኒታቸውን አቋርጠው ጉዳት የደረሰባቸው፣ ሲከፋም የሞቱ ሰዎች በአብዛኛው የውስጥ ደዌ ወይም የአእምሮ ሕመም ያለባቸውና የነበራቸው መሆናቸውን የማኅበሩ አባላት ይረዳሉ።


ስለዚህ የሕዝባችንን ጤንነት ከጉዳት መጠበቅ የሙያ ግዴታችን፣ የቤተ ክርስቲያንን እውነተኛነትና በኅብረተ ሰቡ ዘንድ ተአማኒነትዋን ለመጠበቅ አስተዋጽዖ ማድረግ ደግሞ ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው ብለን እኛ የማኅበሩ አባላት ስለምናምን እና ጤና ነክ በሆኑ ጕዳዮች ዙሪያ ቤተ ክርስቲያንን ለማማከር ማኅበራችን ከተቋቋመባቸው ዐላማዎች አንዱ በመሆኑ፣ ጤንነትንና መለኮታዊ ፈውስን በተመለከተ ለወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያናት የሚከተለውን መልእክት/ምክር ማስተላለፍ እንወዳለን።



ሰውነታችን የእግዚአብሔር መንፈስ ማደሪያ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚናገረው (1ቆሮ 3፥16-17፡ 6፥19-20) ጕዳይ ስለ ሆነ ሰውነታችንን በጥንቃቄ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚያስፈልግ፣ መነሻቸው ከሚታወቁ የበሽታ ዐይነቶችም መከላከል እንደሚያስፈልግ ቤተ ክርስቲያን ማስተማር ይኖርባታል ብለን እናምናለን። ይህም የራስንና የአካባቢን ንጽሕና መጠበቅን፣ ከልዩ ልዩ ሱስ የጸዳ ሕይወት መኖርን፣ አመጋገብን ማስተካከል፣ የአካል እንቅስቃሴን ማዘውተር ወዘተ. የሚያጠቃልል ይሆናል። ስለዚህ ጕዳይ አጥብቀው የሚያስተምሩ አማኞች ላይ በአሜሪካን አገር የተደረጉ ጥናቶች አባሎቻቸው ከሌላው ኅብረተ ሰብ በተሻለ ጤንነት ሕይወታቸውን እንደሚመሩና ረጅም ዕድሜ እንደሚኖሩ አሳይተዋል። ይህም ለጠቃሚነቱ ማሳያ ሆኖ ሊወሰድ ይችላል ብለን እናምናለን።

በሚታወቅም ሆነ በማይታወቅ ምክንያት ሰዎች ሕመም በሚያጋጥማቸው ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈውስ በእምነት እንዲጠይቁ ማስተማሩ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፣ የግድ በዚህ መንገድ ብቻ ነው ሰው ሁሉ መፈወስ ያለበት በማለት ዘመናዊ ሕክምናን መፈለግን ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚያጣላ ድርጊት አድርጎ ማስተማር እንዳይኖር እንመክራለን።

አንዳንድ የሕመም ዐይነቶች፣ በተለይም የውስጥ በሽታዎች ለምሳሌ፡- የጨጓራ፣ የጉበት፣ የሳምባ፣ የኩላሊት፣ የአእምሮ ወዘተ. የመሳሰሉት ፈውሳቸው በጊዜ ሂደት ካልታየ በስተቀር ርግጠኛ መሆን ስለሚያስቸግር፣ ሕመሙ ያለባቸው ሰዎች ከተጸለየላቸው በኋላ ተፈውሳችኋል ተብለው ወዲያውኑ ለምስክርነት እንዳይቀርቡ እንመክራለን። ምክንያቱም በአብዛኛው ስሕትት እየታየባቸው ያሉ ሕመሞችና የፈውስ መልእክቶች ከእነዚህ ዐይነት በሸታዎች ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ማረጋገጡን ተገቢ ያደርገዋል።
በግልጽ ከማይታዩ በሽታዎች ተፈውሰዋል የተባሉ ሰዎች ሁሉ ፈውሳቸው እውነተኛ ለመሆኑ በሕክምና ምርመራ ቢረጋገጥ ብዙ ጥቆሞች ስላሉት ተፈውሰሃል/ተፈውሰሻል የሚል መልእክት የመጣላቸው ሰዎች ሁሉ ምርመራ እንዲያደርጉ ቤተ ክርስቲያን አጥብቃ እንድታስተምር እንመክራለን። ምናልባት ይህ ምክር በጣም ግልጽና ውጫዊ የሆነ በሽታ ስለነበረባቸው ሰዎች፣ ለምሳሌ በግልጽ ስለሚታይ የአካል ጉዳት፣ የማየት፣ የመስማት ወዘተ. ዐይነት ችግሮች ፈውሱ በግልጽ ስለሚታወቅ እውነት ለመሆኑ ልዩ ማረጋገጫ ላያስፈልጋቸው ይችል ይሆናል።


ሆኖም ግን የሕክምና ምርመራ ማድረጉ ብዙ ጥቅሞች አሉት ብለን እናምናለን። እነዚህም፡-



ተፈውሰሃል ለተባለው ሰው የበለጠ ርግጠኝነትን ስለሚሰጠው፤

በሽታውን መርምሮ ላገኘውና ላረጋገጠው የሕክምና ባለ ሙያ ስለ እግዚአብሔር
ፈዋሽነት ምስክር ስለሚሆነው፤

የፈውስ መልእክቱን ያመጣው ግለ ሰብ እውነተኛ የእግዚአብሔር መልእክተኛ መሆኑን
ለማረጋገጥ፤ እውነተኛ ካልሆነ ከስሕተቱ እንዲታረም ለማስተማር/ለመምከር፣
እውነተኛውን ደግሞ ለማበረታታትና ለመደገፍ ስለሚረዳ፤

የቤተ ክርስቲያንን ተአማኒነት ለመጠበቅና አባላትን ከስሕተት ለማዳን ስለሚጠቅም
ነው።
በምርመራ ፈውስን ማረጋገጥ እግዚአብሔርን እንዳለማመን ወይም እርሱን እንደ መፈታተን አድርገው የሚወስዱና ይህ እንዳይሆን የሚመክሩ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን። ይህንን ምክር በእኛ በኩል የተሳሳተ ምክር ነው እንላለን። ይህንንም የምንልበት ምክንያት ምርመራ የሚደረገው እግዚአብሔርን በመጠራጠር ሳይሆን፣ የመልእክቱን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው። ይህ ደግሞ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መርምሩ፣ ፈትኑ፤ ብሎ ከሚመክረን ከመጽሐፍ ቃል ጋር ይስማማል ብለን እናምናለን። የእግዚአብሔር ሥራ/ፈውስ ማንኛውንም ዐይነት ምርመራና ጥያቄ የሚያልፍ፣ ከሰው አእምሮ በላይ የሆነ ነው እንጂ ምርመራን ወይም ጥያቄን የሚፈራና የሚደነግጥ አይደለም (1ዮሐ 4፥1፤ 1ተሰ 5፥19-22)።

በዘመኑ ባለው የሕክምና ሳይንስ መስፈርት መሠረት፣ ምርመራ አካሂዶ በሽታው አለብህ/አለብሽ ብሎ የተናገረው ባለ ሙያ በተመሳሳይ መልኩ ምርመራ አድርጎ የለብህም/የለብሽም ቢል ከሥነ ምግባርም፣ ከሕግም አንጻር ትክክል ስለሚሆን ይህን ማድረግ የሚመከር መሆኑን እንደገና እየገለጽን መድኃኒት አቁሙ ብሎ ሕመምተኛውን መምከርንም ለባለ ሙያ መተው አስፈላጊ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን አምና ለአባሎቿ እንድታስተምር እንመክራለን።

የዚህ መልእክት ወይም ምክር ዐላማ በማንም ላይ ትችትን ለመሰንዘር ሳይሆን፣ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆኑ ልምምዶችን ለማደፋፈር እንዲሁም በሙያችን ዙሪያ ካጋጠሙንና በቤተ ክርስቲያን እየተከሰቱ ስላሉ ስሕተቶች ጥቆማን ለመስጠትና ለመፍትሔውም የሚሆኑ ሐሳቦችን ለመሰንዘር ነው። ስለሆነም በዚህ ርእሰ ጕዳይ ዙሪያ ጥያቄዎች ለማንሣት፣ ለመወያየት፣ ለመመካከር ፍላጎት ላላቸው ቤተ ክርስቲያኖች፣ ድርጅቶች፣ ቡድኖችም ሆነ ግለ ሰቦች ሁሉ ይህን ለማድረግ ማኅበራችን ዝግጁ መሆኑን መግለጽ እንወዳለን፤ ይህም እንዲሆን እናደፋፍራለን።

በዚህ አጋጣሚ ቤተ ክርስቲያን አባሎቿን፣ ስለ ግል መንፈሳዊና ሥጋዊ ሕይወት ንጽሕና፣ ስለ ማኅበራዊ ተሳትፎ፣ ስለ ቃልና ተግባራዊ ምስክርነት እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኋለኛው ዘመን ሊመጣ ስላለው የመንፈስ የስሕተት አሠራር በማስተማር ሕዝቧን ከጉዳት ለመጠበቅ ሁለንተናዊ ኀለፊነትዋን ለመወጣት በምታደርገው ጥረት ማኅበራችን ከጎኗ የሚቆም መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

የክርስቲያን ሐኪሞችና ዴንቲስቶች ማሕበር - በኢትዮጵያ
አድራሻ፡- ስልክ 0910133019 ኢሜይል፡ [email protected]

Address

Piazza
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ክርሰቲያን ፖስት አማርኛ/ Christian Post Amharic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ክርሰቲያን ፖስት አማርኛ/ Christian Post Amharic:

Share