Niftalem-Ministries International

Niftalem-Ministries International Founded by Prophet Tadesse

16/07/2026
10/07/2026



በመላው ወንገል አማኞችና ለሎች እምነት ተከታዮች ተሳትፎ በወላይታ ዞን በጠበላ ከተማ የሚገነበው የወንገል አርበኛ የነበሩት አባባ ዋንዳሮ መታሰቢያ ሀውልትና አደባባይ ግንባታ ለመጀመር በቦታው የፀሎት ፕሮግራም መካሄዱ ተሰማ።

በዛሬው ዕለት በቦታው ተገኝቶ የፀሎት ፕሮግራም ያደረጉት በኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን የወላይታ ቀጠና ቃለሕይወት ቤተ/ያን የአባቶች ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ናቸው።

የአባቶች ጠቅላላ ጉባኤው በቅርቡ የሚጀመረው የአባባ ዋንዳሮ መታሰቢያ ሀውልትና አደባባይ በተለይ በኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተ/ያን ዘንድ ትልቅ ትርጉም ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መላው የቤተክርስቲያኒቱ አባላት የተለመደውን ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን የወላይታ ቀጠና ቃለሕይወት ቤተ/ያን ጽ/ቤት ኃላፊ መጋቢ አብርሃም ቦቶ ተናግረዋል።

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ነህምያ 2:20 የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን፤ ተብሎ እንደተፃፈው የራዕይ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር በድል ያስጨርሰናል እኛም እንነሳለን የሚል እምነት ቃል የተናገሩ ስሆን ለራዕዩ ስኬት ሁሉም በመንበርከክ በአንድ መንፈስ ሆኖ ፀሎት አድርገዋል።

የወንገል አርበኛ የነበሩ አባባ ዋንዳሮ ትውልድ አካባቢያቸው በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ በመሆኑ የወረዳው ማዕከል በሆነችው በጠበላ ከተማ የመታሰቢያ ሀውልትና አደባባይ እንዲገነባ በተደረገው ስምምነት መላው የወንገል አማኞችና ለሎች እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ደስታ መፈጠሩንና ግንባታው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሁላችንም የበኩላችን ኃላፊነት እንወጣለን ስሉ የጠበላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር ታረቀኝ ገቸሬ እና የሁምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ገቡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዛሬ በሁምቦ አጥቢያ ቤተ/ያናት ኅብረት የሚጀመረው የወላይታ ቀጠና ቃለሕይወት ቤተ/ያን የአባቶች ጠቅላላ ጉባኤ በሚቀጠሉ ሶስት ተከታይ ቀናት በተለያዩ ርዕሶች ፀሎት እንደሚደረግም ተገልጿል።

በከተማው ወደ ወላይታ ሶዶ መውጫ ላይ አውራጎዳና ተብሎ በሚጠረው አከባቢ 7200 ካ.ሜ ላይ የሚያርፈው ይህ አደባባይ በመላው ወንገል አማኞችና ለሎች እምነት ተከታዮች በጋራ አንድነት እንደሚገነባም ተገልጿል።

True Gospel for Life

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Niftalem-Ministries International posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share