Christ City Church

Christ City Church ራዕያችን: የመንግሥቱን መልዕክት ለትውልድ ሁሉ ማድረስ ፤ የሰማያዊ መንግሥት ህይወት እና ክብር መግለጥ ነው።
አድራሻችን: ሳሪስ አደይ አበባ
https://maps.app.goo.gl/77xmRScVZpKMpinE7
ለበለጠ መረጃ +251975152422

25/08/2026

የመንግሥቱ ፕሮቶኮል ኮንፍራንስ 2018
ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኋል!

23/08/2026
23/08/2026

ያዕቆብ 1:27
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ነውር የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው፤ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ልጆችና ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳትና ከዓለም ርኩሰት ራስን መጠበቅ ነው።

📣የእሁድ ፕሮግራም📣ነገ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በሚኖረን ልዩ:  የፀሎት ፣ የአምልኮ ፣ የምስክርነት እና የእግዚአብሔርን ቃል የምንማርበት ጊዜ ላይ ተገኝተው አብረውን እግዚአብሔርን እንዲያመል...
22/08/2026

📣የእሁድ ፕሮግራም📣

ነገ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በሚኖረን ልዩ:
የፀሎት ፣ የአምልኮ ፣ የምስክርነት እና የእግዚአብሔርን ቃል የምንማርበት ጊዜ ላይ ተገኝተው አብረውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ እና የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጋብዘኖታል፤ እርሶም ሌሎችን ይጋብዙ!

የመስፋፋት አመታችን ነው!

⛪️የክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን
ሳሪስ - አደይ አበባ
📞 +251975152422

🔸🔸የመንግስቱ ተልእኮ አገልግሎት🔸🔸“ሕይወት በዚህ ዓለም ኖሮ በመሞት አያበቃም!there is more to life than this world!🔸 " ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለም...
22/08/2026

🔸🔸የመንግስቱ ተልእኮ አገልግሎት🔸🔸

“ሕይወት በዚህ ዓለም ኖሮ በመሞት አያበቃም!

there is more to life than this world!

🔸 " ምስክርነቱም ይህ ነው፤ እግዚአብሔር የዘላለምን ሕይወት ሰጠን፤ ይህም ሕይወት ያለው በልጁ ነው።" 1 ዮሐንስ 5:11

🔸 "States that God has granted us eternal life through His Son." 1 John 5:11

የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ቀድሞ የምታከብሩትን አስንቆ ፤ ቀድሞ የምትንቁትን እንድታከብሩት ያደርጋል!ሐዋሪያ ቅዱስ ተካልኝ ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚህ ዓለም ጥበበኛ የሆነ ...
20/08/2026

የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ቀድሞ የምታከብሩትን አስንቆ ፤ ቀድሞ የምትንቁትን እንድታከብሩት ያደርጋል!
ሐዋሪያ ቅዱስ ተካልኝ

ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚህ ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው፣ ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ራሱን እንደ ሞኝ ይቍጠር። የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤ “እርሱ ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኰል ይይዛቸዋል፤” በሌላ ስፍራ ደግሞ፣ “ጌታ የጥበበኞች ሐሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል” ተብሎ ተጽፏል፤
1 ቆሮንቶስ 3:18-20

📍አንድን ማህበረሰብ ከሌላው ማህበረሰብ እንዲለይ ከሚያደርገው ነገር አንዱ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው እሴት ከሌላው መለየቱ ነው።
📍እሴት ማለት በማህበረሰቡ ውስጥ የተገነባ የዋጋ ስሌት ነው።
📍በአንድ ማህበረሰብ የተከበረ ነገር በሌላው ማህበረሰብ የተናቀ ሊሆን ይችላል። በሌላኛው ማህበረሰብ የተናቀው ነገር ደግሞ በዚህኛው ማህበረሰብ የተከበረ ሊሆን ይችላል።
📍የእግዚአብሔር መንግሥት ከአለም የተለየ እና የተቀደሰ እሴት አለው።
🔸በእግዚአብሔር መንግሥት የተከበረው ነገር ፤ በአለም የተናቀ ነው። አለም የምታከብረው ነገር ሁሉ ደግሞ በእግዚአብሔር መንግሥት የሚናቅ እና ቦታ የሌለው ነገር ነው።

📖 የእግዚአብሔር ቃል በአለም ሳለን የምናከብረው የነበረውን አስንቆ ፤ የምንንቀው የነበረውን እንድናከብር ያደርገናል!
📖 የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር መንግሥትን እሴት በልባችን ላይ ይገነባል!

ተባርካችኋል!

🔸🔸🔸🔸🔸
የክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን
ሳሪስ አደይ አበባ
ለበለጠ መረጃ +251975152422

✨✨የመንግስቱ ፕሮቶኮል ኮንፍረንስ 2018✨✨ስለ ግንኙነት ህይወት ለዋጭ ትምህርቶች የተማርንበት እና በየአመቱ በጉጉት የምንጠብቀው አመታዊው የመንግስቱ ፕሮቶኮል ኮንፍረንስ እነሆ ደረሰ!🗓 ነ...
18/08/2026

✨✨የመንግስቱ ፕሮቶኮል ኮንፍረንስ 2018✨✨

ስለ ግንኙነት ህይወት ለዋጭ ትምህርቶች የተማርንበት እና በየአመቱ በጉጉት የምንጠብቀው አመታዊው የመንግስቱ ፕሮቶኮል ኮንፍረንስ እነሆ ደረሰ!

🗓 ነሐሴ 23 እና 24/2018
ቅዳሜ እና እሁድ
⏰ ማለዳ ከ4:00 ጀምሮ ሙሉ ቀን
📍 በክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን

📌 ከወዲሁ ወዳጅ ዘመድዎን መጋበዝ አይርሱ!!
ይህ መልዕክት ለሌሎች እንዲደርስ ያጋሩ!!

🔸🔸🔸🔸🔸
የክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን
ሳሪስ አደይ አበባ
ለበለጠ መረጃ +251975152422

🙏የቀጥታ ስርጭት የፀሎት ጊዜ🙏ዘወትር ማክሰኞ በምናደርገው የፆም እና የፀሎት ጊዜ ነገ ከንጋቱ 10:00 ጀምሮ በቴሌግራም ገፃችን በቀጥታ ስርጭት የጋራ ፀሎት ላይ በመገኘት አብረውን ይፀልዩ ...
17/08/2026

🙏የቀጥታ ስርጭት የፀሎት ጊዜ🙏

ዘወትር ማክሰኞ በምናደርገው የፆም እና የፀሎት ጊዜ ነገ ከንጋቱ 10:00 ጀምሮ በቴሌግራም ገፃችን በቀጥታ ስርጭት የጋራ ፀሎት ላይ በመገኘት አብረውን ይፀልዩ ፤ የበረከቱ ተካፋይም ይሁኑ!

📌ነገ ማክሰኞ ከማለዳ 10:00 እስከ 12:00

የክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን
ለበለጠ መረጃ
+251975152422

🔸🔸የጽዮን ድምፅ አገልግሎት🔸🔸Worshiping God  lifts us upእግዚአብሔርን ስናመልክ ከፍ እንላለን።📖 Psalm 121:1–2"I lift up my eyes to the hills—whe...
17/08/2026

🔸🔸የጽዮን ድምፅ አገልግሎት🔸🔸

Worshiping God lifts us up
እግዚአብሔርን ስናመልክ ከፍ እንላለን።

📖 Psalm 121:1–2
"I lift up my eyes to the hills—where does my help come from? My help comes from the LORD, the Maker of heaven and earth."

📖 መዝሙር 121፥1–2
"ዓይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣለሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይመጣል? ረዳቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።"

True worship does not merely lift our hands it lifts our hearts above our circumstance noise of earth into the beauty of God's presence. There, burdens become lighter, faith grows stronger, and our souls remember that help is near.

እውነተኛ አምልኮ እጆቻችንን ብቻ ሳይሆን ልባችንን ከሁኔታዎቻችን እና ከሚሰማው ድምፅ ላይ አንስቶ በምስጋና ወደ እግዚአብሔር መግኘት እንድንገባ ያደርገናል ። በዚያ ሸክማችን ይቀላል፣ እምነታችን ይጸናል፣ በነፍሳችን ረዳታችን ቅርብ እንደሆነ እናውቃለን።
ከፍ እንላለን ሀሌሉያ!!

🔸🔸🔸🔸🔸
የክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን
ሳሪስ አደይ አበባ
ለበለጠ መረጃ +251975152422

🔸በቤተክርስቲያን የሚደረግ የምልጃ ፀሎት🔸“ጴጥሮስም በዚህ መሠረት እስር ቤት ተጣለ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን ስለ እርሱ አጥብቃ ወደ እግዚአብሔር ትጸልይ ነበር።”  📖ሐዋርያት ሥራ 12:5📖🟡 ...
14/08/2026

🔸በቤተክርስቲያን የሚደረግ የምልጃ ፀሎት🔸

“ጴጥሮስም በዚህ መሠረት እስር ቤት ተጣለ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን ስለ እርሱ አጥብቃ ወደ እግዚአብሔር ትጸልይ ነበር።”
📖ሐዋርያት ሥራ 12:5📖

🟡 በጨለማ አገዛዝ እና በእስር ላሉ የሚደረግ የምልጃ ፀሎት የሰማይን ሀይል ለማንቀሳቀስ ቁልፍ ነው!

🟨 ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 1 ሰአት እስከ 3 ሰአት

📌 በቤተክርስቲያን መገኘት ለማትችሉ በቴሌግራም በተመሳሳይ ሰአት የሚተላለፍ ይሆናል።

📌 ኑ አብረን እንፀልይ!
የሚሰማ፣ የሚመልስም አምላክ አለ!

የመንግስቱ ተልእኮ አገልግሎት

የክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን
ለበለጠ መረጃ
251975152422

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christ City Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category