Good Tube - መልካም ቲዩብ

Good Tube - መልካም ቲዩብ መልካም Tube መንፈሳዊ መልዕክቶችን እና እንዲሁም አስተማሪ የ?

12/09/2022

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል...

"ውጊያችሁን እኔ እዋጋለሁ"
ዘጸአት 14፡14

12/09/2022

ያለ እርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትም ተድላን የቀመሰ ማን ነው?
መክብብ 2÷25

12/09/2022

ተአምራትን የምታደርግ የእግዚአብሔር "ክንድ" በነገራችሁ ላይ ተዘርግታለች !

11/09/2022

ከዚህ ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር አምላክ ሕይወታችሁን በመደነቅ ይሙላ !

 #ዛሬ ቀኑ መስከረም 1/1/2015 ዓ.ም የመጀመሪያው ቀን ላይ እንገኛለን ። በአዲስ ዓመት ብዙዎቻችን እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ብለን ብዙ የምናቅዳቸው የምናልማቸው ነገሮች ይኖሩናል እ...
11/09/2022

#ዛሬ ቀኑ መስከረም 1/1/2015 ዓ.ም የመጀመሪያው ቀን ላይ እንገኛለን ። በአዲስ ዓመት ብዙዎቻችን እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ብለን ብዙ የምናቅዳቸው የምናልማቸው ነገሮች ይኖሩናል እርግጥም ነው። ቢሆንም አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ምርጡ መንገድ ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ቅዱስ ቅዱስ ቃሉ መዞር ነው።

እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ዓመት ያቀዳችሁትን ሁሉ መከናወን ይስጣችሁ !

መልካም ቲዩብ !

11/09/2022
 #ማን አስታዋሽ አለው ?ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአቅመ ደካሞችና ለአረጋዊያን የአዲስ ዓመት ስጦታና ማዕድ አጋሩ*******ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቂርቆስ ልደታና አራዳ ክፍለ ከሞች ለመጡ...
11/09/2022

#ማን አስታዋሽ አለው ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአቅመ ደካሞችና ለአረጋዊያን የአዲስ ዓመት ስጦታና ማዕድ አጋሩ
*******

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቂርቆስ ልደታና አራዳ ክፍለ ከሞች ለመጡ ለአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ነው ማዕድ ያጋሩት፡፡

ለእንግዶቹ የአዲስ ዓመት ስጦታ በመስጠት መልካም በዓልን ተመኝተዋል።

በአዲሱ አመትም ሁሉም ዜጋ ለሰላም መትጋት እንደሚገባውም አረጋዊያኑ አንስተዋል።

አዲሱ ዓመት የሰላምና የስኬት ዘመን እንዲሆንም ተመኝተዋል።

 #ለመልካም ቲዩብ ቤተሰቦች በ 2014 ለእናንተ ይጠቅማል ብለን ባስተላለፍናቸው መልዕክቶቻችን ያሳዘናችሁ የተቀማችሁን ብትኖሩ በመልካም ቲዩብ ስም ሁላችሁንም ፍጹም "ይቅርታ" እንጠይቃችኋለን...
10/09/2022

#ለመልካም ቲዩብ ቤተሰቦች በ 2014 ለእናንተ ይጠቅማል ብለን ባስተላለፍናቸው መልዕክቶቻችን ያሳዘናችሁ የተቀማችሁን ብትኖሩ በመልካም ቲዩብ ስም ሁላችሁንም ፍጹም "ይቅርታ" እንጠይቃችኋለን።

#ለ 2015 አዲሱ ዓመትም በምትሰጡን ገንቢ አስተያየታችሁ እያስተካከለ መልካም የሆኑ መልዕክቶቻችን በማስተላለፍ አብረን የምንቀጥል መሆኑን ስናሳውቅ ደስታ ይሰማናል። አብረንም እንቀጥላለን ።

#አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር ፣የአንድነትና፡ የምስጋና ዓመት ይሁንልን ። ተባረኩ ❤ መልካም አዲስ ዓመት !!!

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን!ዘመን አልፎ ዘመን ሊተካ፣ አሮጌ ምዕራፍ ተዘግቶ አዲስ ምዕራፍ ሊገለጥ፣ መጪውን ዘመን ልንቀበለው በምንዘጋጅበት በዛሬው የዋዜማ ምሽት ላይ ሆነን፣...
10/09/2022

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
ዘመን አልፎ ዘመን ሊተካ፣ አሮጌ ምዕራፍ ተዘግቶ አዲስ ምዕራፍ ሊገለጥ፣ መጪውን ዘመን ልንቀበለው በምንዘጋጅበት በዛሬው የዋዜማ ምሽት ላይ ሆነን፣ ዐይነ ሕሊናችን ያሳለፍነውን ዓመት በትውስታ፣ መጭውን ደሞ በአዲስ ተስፋ ማስተናገዱ አይቀርም።

ያገባደድነውን ዓመት ስናስብ ትውስታችን በብዙ መልካምና እኩይ አጋጣሚዎች ተሞልቶ እናገኘዋለን። በአንድ በኩል ዓመቱ ጠላቶቻችን ግንባር ፈጥረው ጥቃታቸውን ያጠነከሩብን፣ ገሚሶቹ በሀገር ውስጥ ንጹሐን ለሞት ጭዳ ሊያደርጉ ጦር ያዘመቱበት፣ ገሚሶቹ በውጪ ዓለም አቀፍ ጫና በሚያሳድሩ መድረኮችና ሚዲያዎች አማካኝነት የቅጥፈት ዘመቻ ያጧጧፉበት፣ እንደ ሀገር የተፈተንንበት ዓመት ነው።

በሌላ በኩል ተስፋችንን የሚያለመልሙ፣ ወደፊት እንድንጓዝ ስንቅ የሚሆኑ ድሎች የተመዘገቡበትም ዓመት ነበር። ተደራጅተው በዘመቱብን ቁጥር ተደራጅተን መመከት እንደምንችል ያሳየንበት፣ የማዕቀብ ውርጅብኞችን መሻገር ወደሚያስችሉ መንገዶች ጥርሳችንን ነክሰን የገባንበት፣ በምግብ ራስን የመቻል ጉዟችን ተስፋ የፈነጠቀበት፣ ሉአላዊነታችን እንዲታፈር የሚያስችል ዐቅም እንድናደረጅ እድል የተፈጠረበት ጊዜ ስለነበር፣ ዓመቱን በምሬት ብቻ ሳይሆን በምስጋናም ጭምር እንድናስበው ያደርገናል።

አዲሱን ዘመንን በጉጉት ስንቀበለው እንደ መስከረም አደይ ተስፋችን እንደሚፈካ፣ እንደ አዝመራው ውጥናችን ፍሬ አፍርቶ እንደምናይ፣ እንደ በጋ ወንዝ ሰላማችን ከአደፍራሾች እንደሚጠራ፣ ጭጋግ ጭለማው ከላያችን ተገፍፎ ብርሃን እንደሚፈነጥቅብን በመተማመን ነው። ይኽ እምነታችን እንዲሳካ ከዘመኑ ጋር እኛም አብረን መቀየር ይኖርብናል። ምክንያቱም የእኛ መለወጥ ነው የዘመኑን ለውጥ እውነተኛ የሚያደርገው። እኛ ሳንቀየር፣ አሮጌ አስተሳሰባችንን አውልቀን ሳንጥል፣ ዓመት ሄዶ ሌላ ዓመት ቢመጣ የዘመን ለውጡ የቁጥር እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም።

ውድ የሀገሬ ልጆች፣
አሁን አንድ፣ ምንም ያልተነካ ተአምር ሊሠራበት የሚችል ውድ ሀብት ከፊታችን ቆሞ ይጠብቀናል። የመለወጥ እድሎችን የያዘ ዓመት። ዓመቱ ብንጠቀምበትም ባንጠቀምበትም መሄዱን አይተውም። ልክ እንደ ወራጅ ውኃ ያገኘውን ሁሉ ይዞ ይጓዛል። ከልደት እስከ እርጅና፣ ከእርጅናም እስከ ሞት ያደርሳል። መምሸትና መንጋት፣ ሳምንታትና ወራት፣ ዓመታትና ዘመናት ከኛ ቁጥጥር ውጭ ናቸው። ወቅቶችና ጊዜያትን መቁጠር ብቻ፣ መኖርን የማይገልጠው ለዚህ ነው። ውኃ ይዞት የሄደ ሁሉ ዋናተኛ አይባልምና። አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ከዋናተኛ በላይ ውኃ ይዞት የሚሄድ ነገር በፍጥነት ይጓዛል። ችግሩ፣ ፍጥነቱ ወዳልፈለገው ቦታ ይዞት እየተላተመ በመከራ ይጓዛል።

በጊዜ ውስጥ መሄድ ግን ከዚህ ሁሉ ይለያል። በማይቀየረው ጊዜ የሚቀየር ታሪክ ለመሥራት መጓዝ ነው። ሲቻል ከጊዜ መቅደም፣ ሳይቻል ከጊዜ ጋር አብሮ መጓዝ ነው። በጊዜ ውስጥ መጓዝ ጊዜ ወደሚወስደው የተለመደ ጉዞ ሳይሆን በጊዜ ውስጥ ልናሳካው ወደምንፈልገው ግብ ለመጓዝ መቻል ነው።

አዲስ ዓመት ማክበር ትርጉም የሚኖረው በጊዜ ውስጥ ለማለፍ የምንችል ከሆነ ነው። ጊዜ ይዞን ለሚሄድ ሰዎች አዲስ ዓመት የሚባል ነገር የለም። የጊዜ ዑደት ከጥንት እስከዛሬ የታወቀ፣ የተለመደ ነገር በመሆኑ። በሌሎች ያልተደረገ ነገር በእኛ ላይ ስለማይደረግ፤ ከዚህ በፊት ያልሆነ ነገር ዛሬ አዲስ ነገር ስለማይሆን። ሁሉም ቀናት፣ ሁሉም ሳምንታት፣ ሁሉም ወራት አምናም ነበሩ።

በጊዜ ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች አዲስ ዐሻራ በየዘመኑ ያሳርፋሉ። ትናንት ያልታሰበና ያልተደረገ አዲስ ዐሻራ። ታሪክን ይቀይሩታል፤ አስተሳሰብን ይቀይሩታል፤ የሰውን ልጅ የአኗኗር ዘይቤ ይቀይሩታል። አዲስ ዕይታ፣ አዲስ ዓለም፣ አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ መንገድ፣ አዲስ ሀብት፣ አዲስ ቴክኖሎጂ፣ አዲስ፣ አሠራር፣ አዲስ ዘይቤ ይፈጥራሉ። በዚህም ምክንያት ትናንትን ከትናንት ወዲያ፣ ዛሬን ከትናንት፣ ነገን ከዛሬ ይለዩታል። አዲስ ነገር በማድረግ፣ ዘመኑ ብቻ ሳይሆን ቀኑም አዲስ እንዲሆን ያደርጋሉ። ዓለም ዘወትር ስታስታውሳቸው የምትኖረው እንዲህ ያሉትን ሕያው ሰዎች ነው። ጊዜ ብዙዎችን ሲሽር በማይሻር ሥራቸው ሕያውነትን ተጎናጽፈው ጊዜን ራሱን አሸንፈውታልና።
ውድ ኢትዮጵያውያን፣
ሀገራችን ጊዜን የሚያሸንፉ ሕያዋን ዜጎች ትፈልጋለች። ዘመኑ እንደ ቁጥሩ አዲስ እንዲሆንላት አዲስ ሥራ በአዲሱ ዘመን የሚሠሩ ዜጎች ትፈልጋለች። ነባር ችግሮቿን በአዳዲስ መፍትሔዎች የሚተኩ፤ ነባር ፈተናዎቿን በአዳዲስ መድኃኒቶች የሚፈውሱ፤ ነባር ዕንቅፋቶቿን አንሥተው አዳዲስ መንገዶች የሚገነቡ፤ የተለመዱ የታሪክ አንጓዎቿን በአዳዲስ የታሪክ ምዕራፎች የሚቀይሩ፤ የርሃብ ታሪኳን በብልጽግና፤ የጦርነት ታሪኳን በዘላቂ ሰላም፤ የመከፋፈል ታሪኳን በኅብረ ብሔራዊ አንድነት፤ የግጭት ታሪኳን በወንድምና እኅታማችነት፤ የኋላቀርነት ታሪኳን በዘመናዊነት፤ የሚቀይሩ ሕያዋን ጀግኖች ትፈልጋለች። አዲሱ ዓመት በርግጥም አዲስ እንዲሆንላት አዲስ ታሪክ የሚጽፉላትን ትፈልጋለች።

የዘንድሮ መስከረምና ጥቅምት፣ የካቲትና ግንቦት ካምናው፣ ከካቻምናው፣ ከጥንቱ፣ ከቀደምቱ የተለየ ሆኖ እንዲከበር የሚያደርጉ፣ ዘመን ቀያሪ ልጆች ትፈልጋለች። የዘመን መቀየር አይቀሬ ነገር ነው። ዘመንን ራሱን መቀየር ግን የጀግኖች ሥራ ነው። አረንጓዴ ዐሻራ፣ የበጋ ስንዴ፣ የቱሪዝም ሀብቶቻችንን በራሳችን ዐቅም የመጠቀም ጅማሮ፣ ሀገራዊ ችግሮቻችንን በውይይት የመፍታት ውጥን፣ ከውጭ ተጽዕኖ ለመላቀቅ በገቢ ራስን የመቻል እንቅስቃሴ፣ የዚሁ አካል ነበሩ። ዘመንን የመቀየር ፍላጎት ውጤቶች።

እነዚህ ግን ማሳያዎች እንጂ ፍጻሜዎች አይደሉም። አገልግሎት አሰጣጥን ከሌቦች በማጽዳት፣ የፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማ በማድረግ፣ የኑሮ ውድነትን ጫና በመቀነስ፣ የአምራች ዘርፉን ድርሻ በማሳደግ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር፣ ግጭቶችን በማስወገድ፣ ግብርናን ይበልጥ በማዘመን፣ የውጭ ግንኙነትን ይበልጥ በማጠናከር፣ መልካም አስተዳደርን በማስፈን፣ ዴሞክራሲን በማጽናት፣ ያለንን የተፈጠር ጸጋ በሚገባ በመጠቅም፣ ወዘተ. የሚቀሩን ነገሮች አሉ። እነዚህ ሁሉ፣ ዘመን የሚቀይሩ ጀግኖችን ይፈልጋሉ።

አዲሱን ዓመት አዲስ እናድርገው። በራሱ ጊዜ የሚሄድና የሚመጣን ዓመት፣ አዲስና አሮጌ ማለት ትርጉም የለውም። የራሳችንን አዲስና አሮጌ ዘመን እንፍጠር። አሮጌው ዘመን ለዕጽዋትም፣ ለእንስሳትም፣ ለግዑዝ ነገሮችም አሮጌ ሆኗል። አዲሱ ዓመትም ለእነዚህ ሁሉ አዲስ ነው። ሰው የመሆናችን ልዩነት የሚፈጠረው የራሳችንን አዲስ ዓመት ራሳችን ስንፈጥረው ነው። ያን ማድረግ የምንችለው ደግሞ አዲስ ሥራ በመሥራት ነው። አምና ያልነበረ ለውጥ፣ ሥራና ተአምር ከፈጠርን ዓመቱ አዲስ ዓመት ይሆናል፤ በአምናው በሬ ዘንድሮም ካረስን ግን ምኑን አዲስ ዓመት ሆነው

ለኢትዮጵያችን አዳዲስና ዘመናዊ አሠራሮች፣ አዳዲስ መፍትሔዎች፣ አዳዲስ መንገዶች፣ አዳዲስ ዕይታዎች፣ አዳዲስ ዐሻራዎች፣ አዳዲስ ምርቶች፣ አዳዲስ የኪነ ጥበብ ሥራዎች፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣ አዳዲስ የሳይንስ ግኝቶች፣ አዳዲስ ፍልስፍናዎች፣ አዳዲስ የአገልግሎት አሰጣጥ መንገዶች፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶች፣ አዳዲስ መሠረተ ልማቶች፣ አዳዲስ የዕውቀት ብልጭታዎች፣ አዳዲስ የግብርና ዘይቤዎች በማምጣት ዘመኑን አዲስ እንድናደርገው ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ ዘመኑን በአዲስ ሥራ አዲስ አድርገነው አዲስ ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጳጉሜን 5፣ 2014 ዓ.ም

ጠ/ሚ አብይ አህመድ

 #ለአዲስ ዓመት ስጦታ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው !***ለብዙ ዘመን በኢትዮጵያ ምድር እናቶቻችን እንባቸውን አፍስሰዋል ። አሁን እግዚአብሔር አምላክ ቸርነት የሚያደርጉ መሪዎችን ለምድ...
10/09/2022

#ለአዲስ ዓመት ስጦታ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው !
***ለብዙ ዘመን በኢትዮጵያ ምድር እናቶቻችን እንባቸውን አፍስሰዋል ። አሁን እግዚአብሔር አምላክ ቸርነት የሚያደርጉ መሪዎችን ለምድራችን ሰጥቶን እንባቸው እየታበሰ ነው።

#ከእግዚአብሔር እርዳታ ውጪ ይሄን መልካም ነገር የሚያደርግ የለም !!

#የተመረቁ መሪዎች 🙏❤

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮልፌ ቀራኒዮ ያስገነቡትን የመኖሪያ ቤትና ሱቆች አስረከቡ።

#በ75 ቀናት ውስጥ 20 የመኖሪያ ቤቶች እና 15 ሱቆች ግንባታቸው ተጠናቆ ዛሬ ለነዋሪዎች ተበርክቷል።
#ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ዘነበወርቅ፣ ዘውዴ ሜዳ አካባቢ ያስገነቡትን የመኖሪያ ቤቶችና ሱቆችን ለነዋሪዎች አስረከቡ።

#የቤት ስጦታ የተበረከተላቸው በዋናነት የስጋ ደዌ ተጠቂዎች፣ አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኞች ናቸው ተብሏል።

#ለነዋሪዎች የተበረከተው የአዲስ አመት የቤት ስጦታ ሶፋ ፣ አልጋ፣ ፍራሽ፣ የማብሰያ እቃዎችን ጨምሮ የመጸዳጃ እና የመታጠቢያ ክፍሎችን ያሟላ ነው።

#ቀዳማዊት እመቤቷ ዛሬ ለነዋሪዎች ያስረከቡት ብርሃን የመኖሪያ መንደር-1 የሚል ስያሜ ተስጦቷል።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀላሉ ! 👇
https://t.me/+HSITlofNPss2ZWE0

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ 👇

https://youtube.com/channel/UCOByIQ1UD_ExcYF7tQqGYCw

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Good Tube - መልካም ቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Good Tube - መልካም ቲዩብ:

Share