ፍልውሃ ተውፊቅ መስጂድ - Filwuha Tofik Mosque - Filwuhaa Masjiida Toofiq

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ፍልውሃ ተውፊቅ መስጂድ - Filwuha Tofik Mosque - Filwuhaa Masjiida Toofiq

ፍልውሃ ተውፊቅ መስጂድ - Filwuha Tofik Mosque - Filwuhaa Masjiida Toofiq እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆ?

20/07/2025
🛑 የጁምዓ ሰደቃችንን ለቦረና ወገናችን!በቦረና  የተከሰተው የተፈጥሮ ድርቅ ከምንጊዜውም በላይ በአሁኑ ጊዜ ከፍቶና ተባብሶ የቦረና ህዝብ ለከፍተኛ ረሃብ ፣እርዛት፣ ሞት፣ ለተለያዩ ተላለፊ በ...
09/03/2023

🛑 የጁምዓ ሰደቃችንን ለቦረና ወገናችን!

በቦረና የተከሰተው የተፈጥሮ ድርቅ ከምንጊዜውም በላይ በአሁኑ ጊዜ ከፍቶና ተባብሶ የቦረና ህዝብ ለከፍተኛ ረሃብ ፣እርዛት፣ ሞት፣ ለተለያዩ ተላለፊ በሽታ ተገላጭ መሆንና ከቀየው መፈናቀል እንዲሁም የቁም እንሰሳቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ እያለቁ ይገኛሉ።

ይህን ጊዜ የማይሰጠው የተፈጥሮ አደጋ ለወገኖቻችን በአስቸኳይ የምንችለውን በነብስ ወከፍ ከሃገር ቤት እስከ ሀገር ውጪ ያለን አነሰ በዛ ሳንል ከ50 ብር ጀምሮ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከትልቁ ባለፀጋ እስከ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያለው ኃይላችን አስተባብረን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለእለት አስቸኳይ ለምግብ ፣ለመድኃኒት ፣ለአልባሳትና ቁሳቁስ አቅርቦት ድጋፍ ለማደርግ ለነገ የማናሳድረው አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ ..

ሁላችንም አቅማችን በፈቀደው መልኩ ወገኖቻችን ለመርዳት ይረዳ ዘንድ በአዲስ አበባ መጅሊስ አስተባባሪነት በተከፈቱ አካውንቶችና ነገ ጁምዓ በየመስጂዱ በሚሰበሰቡ እርዳታዎች ላይ የአቅምዎን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።

ድጋፍ የሚሰበሰብባቸው አካውንቶች

🛑 የአካውንት ስም :- አዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት

📌 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000530094184

📌 ሂጅራ ባንክ 7030

📌 ዘምዘም ባንክ 220200

📌 አቢሲኒያ ባንክ 129915218

📌 ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1042900058298

📌 ኦሮሚያ ባንክ 1467369500001

📌 አዋሽ ባንክ 014101122923700

📌 ንብ ባንክ 7000040484537

ነገ ጁምዓ በአዲስ አበባና  በክልል ከተሞች በሚገኙ መስጂዶች ለቦረና ወገኖቻችን የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ስለሚደረግ ሁላችንም ከወዲሁ በመዘጋጀት ያለንን ለወገኖቻችን በማካፈል የተራቡ ወገኖቻች...
09/03/2023

ነገ ጁምዓ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በሚገኙ መስጂዶች ለቦረና ወገኖቻችን የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ስለሚደረግ ሁላችንም ከወዲሁ በመዘጋጀት ያለንን ለወገኖቻችን በማካፈል የተራቡ ወገኖቻችን ህይወት ልንታደግ ይገባል።

Guyyaa Jum'aa masjidoota guutuu biyyaa keessa jiraniin ummata keenya kan booranaatif gargaarsii deeggarsaa waan godhamuuf marti keenyaa ammarraa qophaa'uun waan qabnurraa ummata keenyaa qooduun beelarraa lubbuu ummata keenyaa hanbisuu qabna.

03/03/2023

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከከተማው ኢማሞች ጋር የድርቅ ተጎጂ ወገኖች ድጋፍ በሚደረግላቸው ሁኔታ ላይ ውይይት አድርጓል። ውይይቱን በንግግር ያስጀመሩት የከተማው...
03/03/2023

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከከተማው ኢማሞች ጋር የድርቅ ተጎጂ ወገኖች ድጋፍ በሚደረግላቸው ሁኔታ ላይ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱን በንግግር ያስጀመሩት የከተማው እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ እንዳሉት ሀገራችን በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ስተፈተን ቆይታለች፤ አሁን ደግሞ የድርቅ ሁኔታው አስከፊ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል። በመሆኑም የሃይማኖታችንን ትዕዛዝ በመከተልና የቆየውን የመረዳዳት ባህላችንን በመጠቀም ለቦረናዎች እንድረስላቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሼህ ሁሴን በሽር በበኩላቸው ድርቅ ሀገራችን እየተፈተነችባቸው ከቆዩ የተፈጥሮ አደጋዎች መካከል አንዱ መሆኑን አስታውሰው ሰሞነኛው የቦረና ዞን ድርቅም ከቀደመው ጉዳት ጋር ተያይዞ ጉዳቱ የከፋ መሆኑን አብራርተዋል።

ድርቁ ቦረና ዞን የሚታወቅበትን ከብት አርቢነቱን ለመንጠቅ የተከሰተ ይመስላል ያሉት ዋና ፀሐፊው ሼህ ሁሴን በሽር በድርቁ በሚሊየን የሚቆጠሩ ከብቶች መሞታቸውን እና የዞኑ ነዋሪዎችም ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም መላው የከተማው ሙስሊም ማህበረሰብ በሚደረገው የልገሳ ሂደት ውስጥ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በንቃት እንዲሳተፍና ለወገኖቹ ጥያቄ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ኢማሞች የዘወትር ዱዓችሁ እንዳለ ሆኖ በቀጣዩ ጁምዓ በየመስጅዳችሁ አብሯችሁ ለመስገድ የሚመጣውን ሙስሊም ማህበረሰብ በማስተባበር የተጎጂ ወገኖቻችንን እምባ መጥረግ ይገባናል ያሉት ሼህ ሁሴን ድርቁም በእናንተ ዱዓና በአላህ ፍቃድ ወደ ጠቃሚ ዝናብ የሚቀየር ይሆናል በማለት አደራቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ አባልና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ተጠሪ ኡስታዝ ሱፊያን ዑስማን እንዳሉት ቦረና ለሀገራችን የቀንድ ከብት ልማት ቀዳሚ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ቢሆንም አሁን ግን ድርቁ በመከሰቱ ሰፊ ሀብቱን እያጣ መሆኑን አንስተዋል።

ኡስታዝ ሱፊያን ዑስማን ቦረና ላይ በተከሰተው ድርቅ ሀገራችን በትንሹ ከ144 ቢሊየን ብር በላይ ማጣቷን አስረድተው 860 ሺህ አባወራዎች ከነ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመድረኩ የተገኙት ኡስታዝ በድር ሁሴን እንደገለፁት የአንድነት መንፈስ ከዚህ የበለጠ ችግር ቢመጣብን እንኳን እንድንመልስ ያደርገናል ነገር ግን ፍጥነት ያስፈልጋል በማለት አስተያየታቸውን አጋርተዋል።
በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የከተማችን መስጂድ ኢማሞች እንዳሉት መጅሊሱ የቦረና ተጎጂዎችን ለመደገፍ የወሰደው እርምጃ መልካም መሆኑን ገልፀዋል። በመሆኑም ከጁምዓ ጀምሮ በሚኖሩት የሰለመት ሰዓታት ሁሉ ለሁለት ሳምንታት ተገቢውን ርብርብ እንደሚያደርጉ ቃለሰ ገብተዋል።
ድጋፉ ከዛሬ ጀምሮ የሚካሄድ ቢሆንም የካቲት 24/2015 የሚጀምረው ዋነኛው የድጋፍ ማሰባሰብ መርሃ ግብር መጋቢት 1/2015 እንደሚያበቃ ታውቋል። ከግለሰብ ጀምሮ መስጅድ፣ ክፍለ ከተማ ፣ ማዕከል በሚል ለተዘረጋው የምግብ ማሰባሰብ ሥራ አውራ ዴሊቨሪ የተሰኘ ድርጅት የማሰባሰብ ስራ እንደሚሠራ በመድረኩ ላይ የተገለፅ ሲሆን ነጃሺ የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ነሲሃ የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ተአውን የመረዳጃ እድር፣ከይር ውሃ የበጎ አድራጎት ድርጅት፣አብሮነት የመረዳጃ እድር ከአዲስ አበባ መጅሊስ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ተገልፃል።
ቶፊቅ( ፍል ውሃ ) መስጅድ የቁሳቁስ ማሰባሰቢያው ማዕከል መሆኑ የተነገረ ሲሆን ዕለተ ዕሁድ መጋቢት 3/2015 የተሰበሰበው ድጋፍ ወደ ቦረና የሚጓጓዝበት ቀን እንደሚሆን ተገልጿል።

ሼይኻችን ሼይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጠፋ ህመም ላይ ናቸው! ባለንበት ሆነን የሁላችንንም ዱዓ ይሻሉሀገራችን ካሏት አሊሞች መካከል ታዋቂ የሆኑት ሼይኻችን ሼይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጠፋ ታመው ህክም...
29/01/2023

ሼይኻችን ሼይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጠፋ ህመም ላይ ናቸው!

ባለንበት ሆነን የሁላችንንም ዱዓ ይሻሉ

ሀገራችን ካሏት አሊሞች መካከል ታዋቂ የሆኑት ሼይኻችን ሼይኽ ሰዒድ አሕመድ ሙስጠፋ ታመው ህክምናቸውን በሆስፒታል ተኝተው እየተከታተሉ ይገኛሉ::

ሼይኽ ሰዒድ ከወጣትነት እድሜያቸው ጀምሮ ለሀገራችን ሙስሊም ማህበረሰብ ብዙ የለፉ፣ ብዙ ለውጥ ለማምጣትም የተጉ፣ የወጣቱን የኢልም አብዮት ከመሩ ታላላቅ አሊሞቻችን መካከል ከቀዳሚዎቹ የሚጠቀሱ ናቸው::

በረጅም አመታት በውጪ ሀገር ቆይታቸውም ህዝበ ሙስሊሙን ከማስተማር ሳይቆጠቡ ያላቸውን ኢልም በሚዲያዎች ጭምር በመታገዝ ለሁሉም ሲያደርሱ ቆይተዋል::

ወደ ሀገር ከተመለሱም ቡኃላ የአቅሷ መስጂድ ኢማም በመሆን የቁርኣን ተፍሲር ትምህርታቸውን በቋሚነት ማስተማራቸውን ቀጥለው ነበር::

በቅርብ አመታትም መጅሊሱን እንዲመሩ ከተመረጡ አሊሞች መካከልም አንዱ በመሆን የቻሉትን ያህል ተቋሙን ለማስተካከል ጥረት አድርገዋል::

እኚህ ታላቅ አሊም አሁን ላይ ባጋጠማቸው ህመም ሆስፒታል የገቡ ሲሆን ህክምናቸውንም ሆስፒታል ተኝተው እየተከታተሉ ይገኛሉ::

ሼይኽ ሰዒድ አላህ የሰጣቸውን እውቀት ሁሉ ሳይሰስቱ ለኡማው እንዳበረከቱት ሁሉ እኛም እሳቸው በሚፈልጉን ቦታ ሁሉ ሳንሰስት መገኘት ይጠበቅብናል::

እኚህን የመሰሉ ታላቅ አሊም ከገጠማቸው ህመም አገግመው ወደ ቀድሞ አገልግሎታቸው ይመለሱ ዘንድ የሁላችንንም ዱዓ እና እገዛ ይሻሉ::

ወደ ሙሉ ጤንነታቸው እንዲመለሱ ህክምናቸውን በሆስፒታል ከመከታተላቸው ጋር ብዙ ሰው ማነጋገር ስለማይችሉ ባለንበት ቦታ ተወስነን (ወደ ሆስፒታል ባለመሄድ) ሁላችንም በዱዓ እና በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ከጎናቸው ልንቆም እንደሚገባ ለማስታወስ እወዳለው::

ሼይኻችንን አላህ ሙሉ አፊያቸውን ይመልስላቸው!
አሚን

08/01/2023

የእናት ነገር
''እንኳንም እግሬ ተቆረጠ ልጄን ለማየት ታደልኩኝ '' ልብ የሚነካ ገጠመኝ
=====================================
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ እንዴት ነህ አብዱረሂም ሁሉ ሰላም አልሀምዱሊላህ እኔጋ ሁሉ ሰላም ዛሬ አንድ የገጠመኝን ገጠመኝ ላካፍልህ ወደድኩ አንተም ፍቃድህ ከሆነ ባንተ በኩል ለብዙሃኑ ደርሶ ለታደሉት ሰበብ ይሆን ዘንድ በማሰብ ነው ።
ነገሩ እንዲህ ነው ሰሞኑን እኔ በምኖርባት በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ የመኪና አደጋ ደርሶ ነበር በአደጋውም አንዲት እናት በሲኖ ተገጭታ አላህ አትርፏት ወራቤ ሆስፒታል ገባች ። በሆስፒታል እግሯ በጣም ተጎድቶ ስለነበር እንድትቆረጥ ሆነ እኛም ከቀናት በኋላ ልናያት ብቅ ባልን ግዜ ሁኔታዋ በተወሰነ ሻል ብሎ ማውራት ጀምራ ነበር ። እኛም ስለሁኔታው በጠየቅናት ግዜ እንዲህ ስትል ልባችንን የነካውን ንግግር ተናገረች ''እኔ አሁን ደህናነኝ ሆኖም እንኳንም አደጋው ደረሰብኝ እንኳንም እግሬ ተቆረጠ አለችን '' ፈገግ ብላ እኛም ግራ በመጋባት ለምን እንደዛ አልሽ ስንል ጠየቅናት እሷም ለስንት አመት የናፈቅኩትን የልጄን ፊት አየሁበት እግሬ ባይቆረጥ መች አገኘው ነበር ሳልሞት አገኘሁት አቅፌም ሳምኩት እንኳንም እግሬ ተቆረጠ ስትል ደስ ብሏት አወራችን ።
የልጇን ፊት ለማየት በግሯ መቆረጥ የምትደሰት እናት ስንቶቻችነን እድለኛ ሆነን አባትና እናቶቻችን በህይወት ኖረውልን በዚህ ልክ እንደሚናፍቁን የምንረዳው ፣ግዜ የምንሰጣቸው፣የምንከባከባቸው፣የእናትና የአባት ሀቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ የምንረዳው ፣እውነተኛ ፍቅር እነሱጋ ብቻ መሆኑን የምንረዳው፣ሁሉን ለሆኑልን ወላጆቻችን ግዜና ገንዘባችንን ለመስጠት ምን ያህል እንሰስታለን ሁላችንም ቆም ብለን ልናስብ ይገባል የሁላችንም እናት ልክ እንደዚህች እናት ትናፍቀናለችና በህይወት እያለች እንካድማት እንቅረባት ጀነት መግቢያችን ናትና ።
መልእክቱን ያደረሰኝ Nesre hamdno ከስልጤ ዞን
እናቶቻችሁ በህይዎት ያሉ ዘይሯቸው፣ጠይቋቸው

08/01/2023

የቁርኣን አንዱ ሚና
በኡስታዝ ማህሙድ ሀሰን

ነሲሐ ቲቪን እንደግፍ"ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል ለህዝበ ሙስሊሙ ኢስላማዊ ትምህርቶችን ሲያቀርብ የነበረው ነሲሐ ቲቪ ስርጭቱ ተቋርጧል::የስርጭቱ መቋረጥ የዳዕዋ ክፍተት የሚፈ...
25/12/2022

ነሲሐ ቲቪን እንደግፍ

"ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል ለህዝበ ሙስሊሙ ኢስላማዊ ትምህርቶችን ሲያቀርብ የነበረው ነሲሐ ቲቪ ስርጭቱ ተቋርጧል::

የስርጭቱ መቋረጥ የዳዕዋ ክፍተት የሚፈጥር በመሆኑ ሁላችንም ድጋፍ በማድረግ ስርጭቱ ዳግም ተመልሶ ለህዝበ ሙስሊሙ ተደራሽ ይሆን ዘንድ የበኩላችንን ሃላፊነት እንወጣ::

ድጋፍ ለማድረግ ለምትፈልጉ ወንድም እና እህቶች በተከታዩ የባንክ አካውንት ድጋፍ በማድረግ ለነሲሓ ቲቪ ቀጣይነት አስተዋፅኦ ያበርክቱ
***
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 444
ወይም 1000145615929

– ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል 1445091300001

– አቢሲኒያ ባንክ 73169062

– ንብ ኢንተርናሽናል 7000025634638

– ዘምዘም ባንክ 7122

– አዋሽ ባንክ 01410844116300

ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ ዕውቀት ለሁሉም!

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል። መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ትወዳደሩ ዘንድ ሙሉ ማስታወቂያው ከዚህ በታች ቀርቧል...
10/12/2022

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል። መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ትወዳደሩ ዘንድ ሙሉ ማስታወቂያው ከዚህ በታች ቀርቧል ።

የሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨረስቲ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የግምባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም  እየተካሄደ ይገኛል።..ሀሩን ሚዲያ ታህሳስ 1/2015..በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ለሚገነባው ሂክማ ኢስላማዊ ...
10/12/2022

የሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨረስቲ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የግምባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።..
ሀሩን ሚዲያ ታህሳስ 1/2015..
በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ለሚገነባው ሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨረስቲ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የግምባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራል መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች ናየአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች አመራሮች የስልጤ ዞን ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች የአከባቢው ማህበረሰቦች ሌሎች በርካታ ኡለማዎች በተገኙበት የሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ማስጀመሪያ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በድምቀት እየተካሄደ ነው።

ከ15 ዓመታት በፊት ሊገነባ ታቅዶ የነበረው የሂክማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን የዘገየ ቢሆንም በዛሬው ዕለት የግንባታ ማስጀመሪያና የገቢ ማሰባሰቢያ ኘሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

የሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ መገንባት የሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ ሀላፊነት በመሆኑ ሁሉም ወገን በተቻለው መጠን ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዲስ መልኩ እንዲዋቀር ተደረገህዳር 25/ 2015የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ቤት በአዲስ መልኩ  ለማዋቀር የምስረታ ጉባኤ በተ...
04/12/2022

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዲስ መልኩ እንዲዋቀር ተደረገ

ህዳር 25/ 2015

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ቤት በአዲስ መልኩ ለማዋቀር የምስረታ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ በክልሉ መዲና በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል::

ይህን የሪፎርም ስራም የተሳካ እንዲሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል::

በጉባኤው ላይ በአማራ ክልል ከሁሉም ዞኖች የተውጣጡ ተወካዮች የታደሙ ሲሆን ከመንግስት በኩል በታዛቢነት የጠቅላይ ሚኒስተር ፅ/ ቤት ተወካዮች፣ የክልሉ መስተዳደር እና የክልሉ ፀጥታ እና ደህንነት ቢሮ ተወካዮች ታድመውበታል::

በአማራ ክልል ሁሉንም ህዝበ ሙስሊም ሊወክሉ በሚችል መልኩ 29 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት የተመረጡ ሲሆን 11የሚሆኑት ለስራ አስፈፃሚነት ተመርጠዋል::

እጅግ ሰላማዊ እና መግባባት በሰፈነበት ጉባኤ ህዝበ ሙስሊሙን በቅንነት እና በታማኝነት ያለምንም ልዩነት ለማገልገል ይችላሉ የተባሉ ኡለሞች እና አመራሮች የተመረጡ ሲሆን አመራሮቹም በጉባኤው ፊት ቃለ መሀላ በመፈፀም ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል::

በነገው እለት ሰኞ ጠዋት 4 ሰዓት ላይም የሃላፊነት ርክክብ እና ለቀድሞ አመራሮች የምስጋና እና የሽኝት ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል::

የዛሬው የባህር ዳሩ ጉባኤ በተሳካ እና በመግባባት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ድጋፍ ላደረገው የክልሉ ህዝበ ሙስሊም እንዲሁም ከመንግስት የሚጠበቀውን ድጋፍ በማድረግ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ለተወጡት ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ፣ ለክልሉ መንግስት አመራሮች እና የፀጥታ ክፍል ሃላፊዎች ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል::

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህዝበ ሙስሊሙን በሚመጥን ቁመና ላይ እንዲገኝ የክልል መጅሊሶች መጠናከር ወሳኝ በመሆኑ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሪፎርሙን ወደ ክልሎች በማወረድ የተሳካ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል::

Address

Taitu Street Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፍልውሃ ተውፊቅ መስጂድ - Filwuha Tofik Mosque - Filwuhaa Masjiida Toofiq posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category