ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖታዊ ትዉፊት፤ቀኖና ስርዓት በጠበቀ መልኩ በተለያዩ አማራጭ የሚቀርብ ተመራጭ ቻናል ነዉ !!

ታላቅ መንፈሳዊ የቤተክርስቲያን ምረቃ ወደ አምባሰል ዉጫሌ ቅዱስ ገብርኤልያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመዉ ይመዝገቡ ሸር በማድረግ ሀይማታዊ ግዴታዎን ይወጡ!!
20/05/2026

ታላቅ መንፈሳዊ የቤተክርስቲያን ምረቃ ወደ አምባሰል ዉጫሌ ቅዱስ ገብርኤል
ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመዉ ይመዝገቡ ሸር በማድረግ ሀይማታዊ ግዴታዎን ይወጡ!!

ቢስቲማ ጉቤሳ ቅዱስ ሚካኤል ጻጻሳቱ ምዕመኑ በተገኘበት ከተለያዩ ሀገር በመጡ አባቶች በታላቅ ድምቀት ተመረቀ !! ሚያዚያ25/2018ዓም በደቡብወሎ ሀገረስብከት በወረባቦ ወረዳ ቤተክነት ስር ...
03/05/2026

ቢስቲማ ጉቤሳ ቅዱስ ሚካኤል ጻጻሳቱ ምዕመኑ በተገኘበት ከተለያዩ ሀገር በመጡ አባቶች በታላቅ ድምቀት ተመረቀ !!
ሚያዚያ25/2018ዓም በደቡብወሎ ሀገረስብከት በወረባቦ ወረዳ ቤተክነት ስር የሚተዳደረው ጊቢሳ ደብረ ኃይል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በ5አመት የህንጻ ስራ ቆይታ በቦታው ተወላጅ በሆነው በአቶ/ዶክተር ሉሉ እና 6ጎደኞቹ በጋራ በመሆን ከ35ሚሊየን ብር በላይ ወጭ አድርገው በዛሬው እለት ብጹእ አቡነ ኤርሚያስ የሰሜንና ደቡብ ወሎ ሀገረርብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ለመመረቅ ችሎል
ፎቶ -ደሬ ዲጂታል ስቱዲዮ እና ህትመት

ዓ.ም  ሸር በማድረግ ሀይማታዊ ግዴታዎን ይወጡ !!…… ሸር ይደረግ
25/04/2026

ዓ.ም ሸር በማድረግ ሀይማታዊ ግዴታዎን ይወጡ !!…… ሸር ይደረግ

የማይቀርበት የንግስ በዓል
24/04/2026

የማይቀርበት የንግስ በዓል

ገብረ ሰላመ በመስቀሉእንኳን አደረሳችሁ*ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)*_*🌿ቀዳም_ሥዑር ይባላል፡-*__♦️በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል ...
11/04/2026

ገብረ ሰላመ በመስቀሉ
እንኳን አደረሳችሁ
*ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)*
_*🌿ቀዳም_ሥዑር ይባላል፡-*_

_♦️በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡_

_*🌿ለምለም_ቅዳሜ ይባላል፡-*_

_♦️ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡_

_♦️(የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)_

_*🌿ቅዱስ_ቅዳሜ ይባላል፡-*_

29/03/2026
ኒቆዲሞስ የዐብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት። ''እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወ...
29/03/2026

ኒቆዲሞስ
የዐብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት።

''እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። (ዮሐ 3:3-6)

ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር። በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡ መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው የተከተሉትም ነበሩ፡፡

ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች። ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡

ኒቆዲሞስ ማነው?

፩. ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው《ዮሐ 3-1》
፪. ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው《ዮሐ 3-1》
፫. ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው《ዮሐ 3-10》
፬. ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው 《ዮሐ 7-51》

ኒቆዲሞስ ምን አደረገ?

ለምስጢረ ጥምቀት መገለጥ ምክንያት ሆነ《ዮሐ 3:1-21)
አዋቂ ነን የሚሉትን አሳፈራቸው 《ዮሐ 7-51》
ጌታን ለመገነዝ በቃ《ዮሐ 19-38》

=> ከኒቆዲሞስ ምን እንማር?
አትኅቶ ርእስ ጎደሎን ማወቅ የእውነት ምስክር《ስምዐ ጽድቅ》መሆን ትግሃ ሌሊት እስከ መጨረሻ መጽናት በአጠቃላይ ከኒቆዲሞስ ህይወት ብዙ ቁምነገሮችን እንማራለን፡፡

የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት ለምስጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን ምክንያት ነውና በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡

🕯መጋቢት15🕯🌟📖 የውዳሴ ማርያም ደራሲ እና የጥዑመ ልሳን ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ 🕊️🌿​ወር በገባ  #በ15 የጥዑመ ልሳን፣ የቤተ ክርስቲያን ዓምድ፣ የሶርያው ኮከብ የቅዱስ ኤፍሬም መታሰቢያ ...
24/03/2026

🕯መጋቢት15🕯
🌟📖 የውዳሴ ማርያም ደራሲ እና የጥዑመ ልሳን ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ 🕊️🌿
​ወር በገባ #በ15 የጥዑመ ልሳን፣ የቤተ ክርስቲያን ዓምድ፣ የሶርያው ኮከብ የቅዱስ ኤፍሬም መታሰቢያ ነው። ⛪✨ ዛሬ የምንጸልየውንና ጸጋ በረከት የምናገኝበትን “ውዳሴ ማርያምን” ለዓለም ያበረከተው ይህ ታላቅ አባት ታሪኩ እጅግ ድንቅና አስተማሪ ነው።
​የሕይወት መነሻና ጥሪው ✝️🌱
ቅዱስ ኤፍሬም በ306 ዓ.ም ገደማ “ንጽቢን” (በአሁኑ ቱርክና ሶርያ ድንበር) ተወለደ። 🌍 ምንም እንኳን አባቱ የጣዖት ካህን ቢሆንም፣ የእግዚአብሔር ቸርነት ቀስቅሶት የንጽቢን ጳጳስ ወደነበረው ወደ ታላቁ አባት ቅዱስ ያዕቆብ ዘንድ በመሄድ የክርስትናን ትምህርት ተማረ፤ ተጠመቀም። 💧🕊️ በዚያም በብሕትውና፣ በጾምና በጸሎት በመወሰን፣ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አድሮበት አሕዛብንና መናፍቃንን በዕውቀት ይረታ ጀመር። 🛡️📜
​ከቅዱስ ባስልዮስ ጋር የነበረው ተአምራዊ ትስስር 🤝🔥
በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ ላይ 318ቱ ሊቃውንት አርዮስን ባወገዙበት ወቅት ቅዱስ ኤፍሬም ተገኝቶ ነበር። 🏛️ በዚያችም ሌሊት ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ በማየቱ፣ የራእዩን ምሥጢር ሲጠይቅ “ይህ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ባስልዮስ ነው” የሚል ድምጽ ሰማ። 🌌 እርሱን ለማየት ቂሣርያ በደረሰ ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በቅዱስ ባስልዮስ ላይ ሲያርፍ፣ ከአፉም የእሳት ነበልባል ሲወጣ ተመለከተ። 🕊️🔥 ሁለቱ ቅዱሳን ቋንቋ ሳይከለክላቸው በመንፈስ ቅዱስ ግልጸት ያለ አስተርጓሚ የእግዚአብሔርን ምሥጢር ተነጋገሩ፤ አባ ባስልዮስም ቅዱስ ኤፍሬምን ዲቁናና ቅስና ሾመው። ✨
​የኃጢአት ደብዳቤና የተደመሰሰው በደል 📝💧
አንዲት በወገን የከበረች ሴት የሠራችውን ኃጢአት በሙሉ በክርታስ (በወረቀት) ጽፋ እንዲደመስስላት ቅዱስ ባስልዮስን ለመነችው። 😔 ከአንዲት ከባባድ ኃጢአት በቀር ሁሉም ቢደመሰስላትም፣ ለቀረችው አንዲት ኃጢአት ወደ ቅዱስ ኤፍሬም እንድትሄድ ነገራት። እርሷም ስትሄድ ቅዱስ ኤፍሬም “ፈጥነሽ ተመለሺ፣ ነገር ግን ሞቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱት ታገኚዋለሽ፤ ይህን ክርታስ በላዩ ላይ ጣይው” አላት። 🏃‍♀️
በተባለችው መሠረት በእምነት ሆና ብትጥለው፣ ያች የቀረች ኃጢአቷ ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰችላት! 🤍✨
​ውዳሴ ማርያም እንዴት ተጻፈ? 👑✍🏽
ቅዱስ ኤፍሬም ቢረሌ፣ መርጠብና ብርጭቆ እየሠራ የዕለት ጉርሱን እያስቀረ ይመጸውት የነበረው በእመቤታችን ስም ነበር። 🏺 እመቤታችንን ከመውደዱ የተነሳ፣ “ምነው የእመቤቴ ምስጋናዋ እንደ ሰማይ ኮከብ፣ እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው፣ እንደ ምግብ ተመግቤው...” እያለ ይመኝ ነበር። 🌌🌊
​ከዕለታት በአንዱ ቀን ሰኑይ (ሰኞ) ጠዋት፣ የብርሃን ምንጣፍ ተነጥፎ እመ ብርሃን አእላፍ መላእክትን አስከትላ መጣች። 👸🏽
✨ “ሰላም ላንተ ይሁን ወዳጄ ኤፍሬም፤ አመስግነኝ (ወድሰኒ)” አለችው። “መላእክትና ጻድቃን አንቺን ማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል?” ቢላትም፣ “መንፈስ ቅዱስ እንዳቀበለህ ተናገር” ብላ ባረከችው። 🕊️ እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ምስጋናዋን በ7 ቀናት ከፍሎ ደረሰው። 📖
​የሰባቱ ዕለታት ጥልቅ ምሥጢር፦ 🌈
​🌍 እሑድ፡ አሥራወ ፍጥረታት መገኘታቸው፤ ክርስቶስ ዓለምን ያለ እርሱ ካለመኖር ወደ መኖር ማምጣቱ።
​🌌 ሰኞ፡ የብርሃን ማኅደር ጠፈር መገኘቱ፤ ከእርሷም ብርሃን ክርስቶስ መገኘቱ።
​🌳 ማክሰኞ (ሠሉስ)፡ ምድር ያለ ዘር በቃሉ ብቻ አዝርዕትን ማብቀሏ፤ ከእርሷም ያለ ወንድ ዘር ፍሬ ሕይወት የሆነው ጌታ መገኘቱ።
​☀️ ረቡዕ፡ የብርሃናት መፈጠር፤ ከእርሷም የጽድቅ ፀሐይ የሆነው ጌታ መወለዱ።
​🌊 ሐሙስ፡ ከባሕር ሕያዋን ፍጥረታት መገኘታቸው፤ ለምእመናን የሕይወት ምክንያት የሆነው ክርስቶስ መገኘቱና በውሃ (ጥምቀት) ሕይወትን መስጠቱ።
​👤 ዓርብ፡ በኩረ ፍጥረት አዳም መገኘቱ፤ ከድንግል ማርያም ደግሞ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስ መገኘቱ።
​🕊️ ቅዳሜ (ቀዳሚት)፡ የሥጋ ዕረፍት መገኘቱ፤ በክርስቶስ ደግሞ የመንፈስ ዕረፍትን ማግኘታችን።
​(ይህን ድንቅ ዜማ ቆይቶ በአክሱም ጽዮን እመቤታችን ተገልጻለት ያሬዳዊ ዜማ ያደረገው ቅዱስ ያሬድ ነው። 🎶)
​በዓለም ዙሪያ የሚታወቅባቸው 7ቱ የክብር ስያሜዎቹ፦ 🏆
1️⃣ ቅዱስ ኤፍሬም 🌟
2️⃣ ማሪ ኤፍሬም 🌟
3️⃣ አፈ በረከት ኤፍሬም 🌟
4️⃣ ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም 🌟
5️⃣ ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም 🌟
6️⃣ አበ ምዕመናን ኤፍሬም 🌟
7️⃣ ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም 🌟
​📜🖋️ ለጥዑመ ልሳን ለቅዱስ ኤፍሬም የተሰናዳ ግጥም(ከኔ)
​የንጽቢኑ ኮከብ የሶርያ ማኅቶት፣ 🌟
በጾም በጸሎትህ የጸናህ በእምነት። 🙏
ከአባ ያዕቆብ ዘንድ ጥበብን የቀሰምክ፣ 📖
ስለ ቀናች እምነት አሕዛብን የረታህ። 🛡️
​የብርሃን ምሰሶ ከምድር እስከ ሰማይ፣ ✨
ተውቦ ሲታይህ ያ ታላቅ ራእይ። 👁️
ከባስልዮስ ጋራ ምሥጢር ስትካፈል፣ 🤝
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ቋንቋ ሲገለጥልህ። 🕊️
​"ምነው የእመቤቴ ምስጋና ቢበዛልኝ፣" 🌌
ብለህ ስትመኝ ጸሎትህ ሰምሮልህ። 🤲
በብርሃን ምንጣፍ ላይ እመ ብርሃን ወርዳ፣ 👑
"አመስግነኝ" አለችህ ልሳንህን ፈትታ። 🗣️
​ሰባቱን ዕለታት በምሥጢር ከፋፍለህ፣ 🌈
ከአሥራወ ፍጥረት ክርስቶስን ስበከህ። ✝️
በውዳሴ ማርያም ዓለምን አጥግበህ፣ 🍞
ዛሬም ይኖራል በረከትና ጸጋህ። 🌿
​አፈ በረከት ነህ ጥዑመ ልሳን፣ 🍯
አበ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን ዓምድ። 🏛️
በአንተ ጸሎት ኃይል እኛም እንድንድን፣ 🤍
አማልደን ዘወትር ከፈጣሪ ዘንድ። 🙏✨
​🙏 መዝጊያ ጸሎት፦
እመቤቴ ሆይ! ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን፣ ክብሩን፣ አእምሮውንና ለብዎውን በልቡናችን አሳድሪብን። አሜን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ የአባታችን የቅዱስ ኤፍሬም ረድኤት በረከቱ ይደርብን። አሜን። ✝️🤍🕊️
​📖 ምንጭ፦ ውዳሴ ማርያም አንድምታ፣ ስንክሳር፣ ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ።
​✍🏽 ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ኃይለማርያም
🗓️ ቀን፦ መጋቢት 15 2018 ዓ.ም

ልጅ ጥርሱን አስወጥሮ መሎክሴ መስሎ ሲያታልል ተያዘ    በየሚድያው የሞሎክሴ ልብስ ለብሰው መጠጥ ሲጠጡ ሲጨፍሩ የሚውሉት እነማን እንደሆኑ ገባችሁ  ኦርቶዶክስ እንዲሀ በሌባ የምትወረረው እው...
23/03/2026

ልጅ ጥርሱን አስወጥሮ መሎክሴ መስሎ ሲያታልል ተያዘ በየሚድያው የሞሎክሴ ልብስ ለብሰው መጠጥ ሲጠጡ ሲጨፍሩ የሚውሉት እነማን እንደሆኑ ገባችሁ ኦርቶዶክስ እንዲሀ በሌባ የምትወረረው እውነትን ስለያዘች ነው ቄስና ሞሎክሴ አልባሌ ነገር ሲያረጉ ካያችሁ መፈተሽ አለባችሁ ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኖራለች ሸር ይደረግ !!!🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ይህንን ጎረምሳ ታስታውሱታላችሁ? ቆሞስ ነኝ በማለት በTikTok ''አባ'' የሚል አካውንት ከፍቶ አስተምራለሁ በሚል ሲንቀሳቀስ የነበረ፣ ባለ ብሬሱ መነኩሴ እየተባለ የሚጠራው አባ አቡሽ ነው...
22/03/2026

ይህንን ጎረምሳ ታስታውሱታላችሁ? ቆሞስ ነኝ በማለት በTikTok ''አባ'' የሚል አካውንት ከፍቶ አስተምራለሁ በሚል ሲንቀሳቀስ የነበረ፣ ባለ ብሬሱ መነኩሴ እየተባለ የሚጠራው አባ አቡሽ ነው።
​ይህ አweናባጅ ጎረምሳ በትግራይ ክልል በሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወጣቶች እጅ ከፍንጅ ተይዟል። ግለሰቡ ከሚኖርበት ከተማ ርቆ በሌላ ከተማ ከሚገኝ መስኪድ የምንኩስና ልብሱን ቆቡን አውልቆ ገብቶ ሲወጣና የሐሰት የክህነት ማስረጃውን በመያዝ ዳግም የምንኩስና ልብሱን ሲለብስ በቁጥጥር ስር አውለውታል።
ከሁሉ በላይ የሚገርመው ግብረ ድቁና መጨረስ በማይችልበት እድሜ ቆሞስ ነኝ በማለት ከማጭበርበሩም በላይ፣ ሚዲያ ላይ መሰረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት አስተምራለሁ በሚል በ Telegram እና Tiktok ላይ ሰዎችን በመመዝገብ ላይ መቆየቱ ነው።

 ! !   "ሂድ ራስህን ለካህን አሳይ" ማቴ 8፥4በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም!                                                                      ...
21/03/2026

!
!
"ሂድ ራስህን ለካህን አሳይ" ማቴ 8፥4
በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም!
ተወዳጆች ሆይ ይሄ የንስሐ መግቢያ የኃጢአት ዝርዝር የተዘጋጀው በቀሲስ ሄኖክ ወልደ ማርያም ሲሆን የተዘጋጀበትም ምክንያት በአገልግሎቱ በአብዛኛው ለቄደር እና ለንስሐ የሚመጡትን ምዕመናን ምን ተብሎ ንስሐ እንደሚገባ ለማሳወቅ ነው። ሁለተኛው አንድ ኃጢአት ዙርያ ጥምጥም አድርጎ ከመናገር በቀጥታ የሰሩትን ኃጢአት ብቻ በአጭሩ እንዲናገሩ ከማሰብ ነው!
1) ከእግዚአብሔር ውጭ ሌላ ባዕድ አምልኮ አምልክያለሁ ፣ ለባዕድ አምልኮ ሰግጃለሁ!
2) የእግዚአብሔርን እና የቅዱሳንን ስም በከንቱ ጠርቻለሁ ፣ በነሱ ስም በሐሰት ምያለሁ፣ በእነሱ ስም ዋሽቻለሁ!
3) የሰንበትን ቀን አላከበርኩም፣ ሰንበትን ሽርያለሁ!
4) አባቴን፣ እናቴን፣ ቤተሰቦቼን እንዲሁም ሰዎችን አላከበርኩም ፣ ተሳድብያለሁ!
5) ሰውን ገድያለሁ፣ ሰውን አስገድያለሁ!
6) ውርጃ ፈጽምያለሁ ወይም ጽንስ አጨናግፍያለሁ። ጽንስ ለማጨናገፍ በገንዘቤ፣ በሐሳቤ ተባብርያለሁ!
7) ዝሙት ፈጽምያለሁ! ከተለያዩ ሰዎች ጋር ዝሙት ፈጽምያለሁ!
😎 ገንዘብ፣ ዕቃ፣ ንብረት ወዘተ ሰርቄያለሁ!
9) በሐሰት መስክርያለሁ!
10) የባልንጀራዬን እና የሰዎችን ገንዘብ ተመኝቻለሁ!
11) ባልንጀራዬን እና ጠላቴን እንደ ራሴ አልወደድኩም!
12) አባቴን፣ እናቴን፣ ወንድሞቼን፣ እህቶቼን፣ እንዲሁም ሰዎችን ተቆጥቻለሁ
13) ሴቶችን ለዝሙት ተመኝቻለሁ!
14) ወንዶችን ለዝሙት ተመኝቻለሁ!
15) ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቴን/ባሌን ፈታሁ!
16) ያለ ዝሙት ምክንያት የፈታውን/የፈታችውን አገባሁ!
17) በሐሰት ምያለሁ፣ ዋሽቻለሁ!
18) ክፉውን በክፉ ተቃውሜያለሁ!
19) ለተራበ አላበላሁም፣ ለተጠማ አላጠጣሁም፣ እንግዳ አልተቀበልኩም፣ ለታረዘ አላለበስኩም፣ የታመመን አልጠየኩም፣ የታሰረን አላስፈታሁም፣ የሞተ አልቀበርኩም!
20) ኩል ተኳልኩ ፣ ከንፈሬን ፊቴን ምናምቴ ተቀባሁ!
21) ጸጉሬን ተቀለምኩ፣ ሌላ ጸጉር ቀጠልኩ!
22) ራሴን የሚያራቁት/ዝሙት የሚያነሳሳ/ ልብስ ለበስኩ!
23) ጉቦ ሰጠሁ ጉቦ ተቀበልኩ፣ የሰው አደራ በልቻለሁ፣ ተበድሬ አልመለስኩም፣ ከሌባ ጋር ገንዘብ ተካፈልኩ!
24) ጾም ሻርኩ ፣ ረቡዕ እና አርብ የፍስክ በላሁ!
25) ከሃይማኖቴ ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ፈጸምኩ!
26) በልጅነት እና ካደኩ በኋላ ግብረ ሰዶም ፈጸምኩ!
27) ከእንስሳት ጋር ግንኙነት አደረኩ!
28) በልጅነት መሬትን ወስቤያለሁ!
29) ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ፈጽሜያለሁ!
30) ቅዱስ ቁርባን ተቀብዬ በዝሙት ወደኩ፣ በግለ ወሲብ ወደኩ!
31) በቅዱስ ቁርባን አግብቼ በባሌ/በሚስቴ ላይ ዘሙቻለሁ!
32) ኢ- ሩካቤ ፈጽሜያለሁ (ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ፈጽሜያለሁ)
33) የአሕዛብን ምግብ በልቻለሁ!
34) ኦርቶዶክስ ሆኜ ወደ ሌላ እምነት ገብቼ ተመልሻለሁ!
35) ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ገብሬያለሁ፣ የተገበረውን መስዋዕት በልቻለሁ!
36) ጠንቋይ ቤት ሄድኩ፣ ዛር አንጋሽ ጋር ሄድኩ!
37) ግለ ወሲብ ፈጽሜያለሁ!
38) የወር አበባ ላይ ሆኜ ግንኙነት አድርግያለሁ !
39) የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት አደረኩ!
40) ጫት ቅምያለሁ! መጠጥ ጠጥቼ ሰክርያለሁ!
41) ሲጋራ፣ ሺሻ፣ ጋንጃ፣ ሀሺሽ ተጠቅሜያለሁ!
42) ህልመ ሌሊት መቶኝ ቤተክርስቲያን ገባሁ ፣ ጸበል ተጠመቅሁ
፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀበልኩ!
43) የወር አበባ ላይ ሆኜ ቤተክርስቲያን ገባሁ ፣ ጸበል ተጠመቅሁ ፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀበልኩ
44) በጸሎት፣ በቅዳሴ ጊዜ አውርቻለሁ፣ ስቅያለሁ!
45) በእግዚአብሔር እና በቅዱሳን ስም ቃል ኪዳን ገብቼ አፍርሻለሁ!
46) የዝሙት ፊልም አይቻለሁ! የዝሙት ምስል ተመልክቻለሁ፣
47) የግብረ ሰዶም ፊልም፣ የግብረ ሰዶም ምስል አይቻለሁ!
48) ዘፈን ዘፍኛለሁ
ዘፈን ሰምቻለሁ
ዳንስ አይቻለሁ፣ ደንሻለሁ!
49) በጾም፣ በግዝት እንዲሁም በበዓላት ጊዜ ሩካቤ ሥጋ ፈጽምያለሁ!
50) በቤተ ክርስቲያን ነክ ነገሮች ላይ ቀልጃለሁ!
51) ካህን ገዝቶኝ አፍርሻለሁ፣ ንስሐ ገብቼ ከእንደገ በኃጢአት ወድቅያለው፣ የተሰጠኝን የንስሐ ቀኖና አልጨረስኩም!
52) ፓትሪያሪኩን፣ ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ መነኮሳትን፣ ባህታውያንን፣ ካህናትን፣ ዲያቆናትን፣ መምህራንን አምቻለሁ፣ ተሳድብያለሁ!
53) ከሰው ጋር ተጣልቻለሁ፣ ይቅርታ እናእርቅን እምቢ ብያለሁ!
54) እራሴን ላጠፋ አስብያለሁ ፣ እራሴን ለማጥፋት በተግባር ሞክርያለሁ!
55) የእግዚአብሔርን ገንዘብ ወስጃለሁ/አስራት በኩራት አላወጣሁም/
56) ልጆቼን ያለ ጥፋታቸው መትቻለሁ፣ የሰውን ልጅ መትቻለሁ!
57) ወፍ፣ ድመት፣ ውሻ ወዘተ እንስሳትን ገድያለሁ!
58) የሰው ገንዘብ ክጃለሁ፣ የካድኩትን ገንዘብ አልመለስኩት!
59) ቅዱስ ቁርባን ተቀብዬ እለቱን ምራቄን ተፍቻለሁ፣ ቆርቤ ተሳድብያለሁ፣ ሰው አምቻለሁ!
60) በሐሊዮ፣ በነቢብ እና በገቢር ወይም በሐሳብ፣ በንግግር እያ በተግባር የሠራሁትን ኃጢአት፤ እኔ የረሳሁትን እግዚአብሔር የሚያውቀውን ይቅር ይበለኝ!
መጋቢት 12-7-2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share