Mercy Reformed Church

Mercy Reformed  Church Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mercy Reformed Church, Religious organisation, Addis Ababa.

Sermon audio of Mercy Reformed Church telegram Channal
11/03/2024

Sermon audio of Mercy Reformed Church telegram Channal

26/02/2024

ቅድስና (scancitification) . . . መግቢያ

በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል ፡፡ 1ዮሐ 2፡6

አግዚአብሔር አብ ማን እንደሆነ እና ለኛ ያለው ፈቃዱ ምን እንደሚመስል ያሳየበት ትልቁ መገለጥ እንዲሁም የቅድስናችን ትልቁ ማሳያ እና ምሳሌ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ ኢየሱስ ማንም ያላየውን እግዚአብሔርን የገለጠ የእግዚአብሔር የመልኩ ማሳያ (ምሳሌ) ነው (ዮሐ 1፡18 ፤ 14፡9)፡፡ ያደረገውን ሁሉ ዱካውን እየተከተልን እንድናደርግ በምድር ላይ ምሳሌውን ትቶልን አልፏል (ዮሐ 13፡15 ፤ ማቴ 10 ፡44፤45 ፤ 1ጴጥ 2፡21 ፤ ፊል 2፡5)፡፡

ለመሆኑ ለምንድን ነው ክስቲያኖች ክርስቶስን እየመሰሉ መኖር ያለባቸው ? ለራሳቸው ሲሉ ነው ፡፡ ከኃጢአት በሽታ እና ውጤት መፈወስ እና መዳን ከፈለጉ እርሱ እንደተመላለሰ ሊመላለሱ ይገባል ፡፡ አኛ ክርስቲያኖች አዲስ ፍጥረት ነን ፡፡ አዲሱ ተፈጥሯችን ደግሞ የእግዚአብሔርን እውቀት ፤ ጽድቅ እና ቅድስና ለመያዝ የተፈጠረ ነው (ኤፌ 4፡24 ፤ ቆላ 3፡10) ፡፡ እግዚአብሔርን ሳይመስሉ (በቅድስና ፍጹም ሳይሆኑ) ደህንነትን አግቻለሁ ብሎ ነገር የለም ፡፡ እግዚአብሔር አብ ዓለም ሳይፈጠር የወሰነው የደህንነት ግብ የልጁን መልክ በመምሰል እንድንለወጥ ክርስቶስም በወንድሞቹ መካከል በኩር ይሆን ዘንድ ነው (ሮሜ 8፡29 ፤ ኤፌ 1፡4) ፡፡

ደህንነታችን እሱን ከመምሰል ጋ የተያያዘበት ምክንያት ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ስለሆነ እግዚአብሔርን ከመምሰል ያነሰ ሕይወት በመምራት የማንነት ቀውስ፤ አጠቃላይ ውድቀት ፤የኃጢአት በሽታ እና የኃጢአት ውጤት እና ቅጣት ውስጥ ይገባል እንጂ ደህንነትን አገኘ ሊባል አይችልም ፡፡ ስለሆነም ደህንነታችን ግቡን የሚመታው እግዚአብሔር ያቀደው ሲከናወን ብቻ ነው ፡፡ታዲያ እግዚአብሔር የጀመረውን የቅድስና ስራ እንደ ዱላ ቅብብሎሽ ሩጫ የራሱን ጨርሶ እኛ ድርሻችንን በመፈጸም የዘላለም ሀሳቡን ተጋግዘን እንድናከናውን “ፈረሱም ያው ሜዳውም ያው ብሎ እየጠበቀ ነውን” ? በፍፁም ፡፡ ለኛ የተተወ አንድም ነገር የለም ፡፡ በእኛ የጀመረውን መልካሙን ስራ እንደጀመረው ሁሉ የሚያጠናቅቀውም ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው (ፊልጵ 1፡6) ፡፡ ታዲያ ለምን እንደሱ ተመላለሱ ይላል ? በተጨማሪም አንደ 2 ጢሞ 2፡21 . . . ራሱን ቢያነጻ ፤ 2ጴጥ 3፡18 . . . በእውቀት እደጉ ፤ 2 ቆሮ 7፡1 . . . ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ፤ ማቴ 5፡48 . . . አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ ፍጹማን ሁኑ ፤ ፊል 2፡12. . . የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ ። የሚሉ ትእዛዛዊ መልክቶችን ያስቀመጠልን ለምንድን ነው ? ይሄን ለመረዳት ቅድስና ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ መረዳት እጅግ ወሳኝ ነው ፡፡

የተወደዳችሁ . . በሚቀጥለው ጌታ ቢፈቅድ ቀጣይ ሃሳቡን እንመለከታለን ፡፡

በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ፤ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፤ እጁንም የሚከለክላት ወይም፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም።ዳን 4፡34...
19/08/2023

በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ፤ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፤ እጁንም የሚከለክላት ወይም፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም።
ዳን 4፡34

በህይወታችን በየእለቱ የምናየው የምናስተውለው እንዲሁም የማናየው የማናውቀውም የተለያዩ ብዙ ነገሮኖች ይደረጋሉ ፤ ሰይጣን ያደረገው በሚመስለን ስንራገም (ስንገስጽ) ፤ እኛ ራሳችን ያረግነው በሚመስለን ደግሞ አንዳንዴ ተጸጽተን ንሥሀ ሥንገባ እና ሌላ ጊዜ ደሞ ራሳችንን ስናሞካሽ ፣ እግዚአብሔር አርጎታል ብለን ባሰብናቸው ነገሮች ደሞ ስናመስግን ፣ አንዳንዴም .. ግን እውነት እግዚአብሔር ይወደኛል ? እያልን ፍቅሩን ጥያቄ ውስጥ ሥንከት እና ማመስገን ሲያቅተን እንገኛለን ...ሌላም ሌላም ... ፤
ሆኖም እግዚአብሔር ለጠራቸው ሁሉ አሁን ያሉበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን " ......ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን "። ሮሜ 8:28

03/05/2023
12/03/2023

በመከራ ውሰጥ ያለ ልበ ሙሉነት ( መዘ 102፡ 1-14 )

አንተ ግን አቤቱ ለዘላለም ትኖራለህ ፡ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው ፡፡ አንተ ተነስ ጽዮንንም ይቅር በላት ፤ የምህረትዋ ጊዜ ነውና ዘመንዋ ደርሷልና ፤

መጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ ድነታችን በገዛ ራሰችን እምነት ላይ እንጂ ሌላ ሰው ስለኛ ባመነልን መሰረት ላይ ሊገኝ እንደማይችል ይነግረናል ፡፡ አውነት ነው በዚህ ጉዳይ ላይ እያንዳንዳችን ተነጥለን (ራሳችንን ችለን) የቆምን እና የምናደርገው ጥሩም ይሁን መጥፎ ውሳኔ ከራሳችን ጋ ብቻ የተያያዘ ነው ፡፡ ሌላውን ሊጠቅምም ሆነ ሊጎዳ አይችልም ፡፡ ከዚህ ውጭ ባለ ጉዳይ ግን ነገሩ ሌላ ነው ፡፡

ይህን ለመረዳት የእሰራኤልን ታሪክ ማጤን ጥሩ ነው ፡፡ በእስራኤል የበረከት እና የብልጽግና ጊዜ በእስራኤል የሚኖር ሰው ሁሉ የበረከቱ ተካፋይ ይሆናል ፡፡ ምንም እነኳን በግሉ እግዚአብሔርን የማይፈራ እርኩሰ ሰው በመካከላቸው ቢኖርም ለጻድቃን የመጣ ለሱም ይተርፍለታል ፡፡ ለምሳሌ ፡- የህዝቅያስ ታማኝነት ሰናክሬብ አገርን እየወረረ ባለበት ዘመን እስራኤላውያን ከአሶራውያን እንዲጠበቁ ምክንያት ሆኗል (ኢሳ 36 እና 37) ፡፡ በአብዛኞቹም የእስራኤላውያን ኃጢአት ምክንያት በነፍስ ወከፍ ለያንዳንዱ ፍዳ ይመጣ ነበር ፡፡የንስሀ ልብ በሌላቸው ብዙ ሰዎች አማካይነት እግዚአብሔር ህዝቡን ለስደት ሲዳርግ ታማኞቹ እንደ ኤረምያስ እና ሕዝቅኤል አይነቶቹም አብረው የመሰደድ እጣ ፈንታን ደርሶባቸው ነበር (2 ነገ 25 ፤ ኤር 43 ፡ 1-7 ፤ ህዝ 1፡1) ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ባህሪ ነው (ዘጸ 34 ፡ 7)

በመዝ 102 ላይ ባለው የኃዘን እንጉርጉሮ የጸሃፊው ማንነት ባይታወቅም በስደት ወቀት የተጻፈ እንደሆነ ይታመናል ፡፡ ቁጥር 4 ፤ 5 እና 9 በስደቱ ወቅት የነበረውን የመጀመሪያዎችን አሳዛኝ እና ታላቅ የመከራ እና የድህነት ጊዜያቶች በአይምሯችን እንዲሳሉ ያደረጋል ፡፡

ቁጥ 4 . . . እህል መብላት ተረስቶኛልና ተቀሰፍሁ ልቤም እንደሳር ደረቀ ፡፡

ቁጥ 5. . . . ከጩኃኸቴ ድምጽ የተነሳ አጥንቶቼ ከስጋዬ ጋር ተጣበቁ ፡፡

ቁጥ 9 . . . አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና መጠጤንም ከእንባ ጋር ቀላቅያለሁና . . . .

ምንም እንኳን ይህ ዘማሪ ቁጥ 10 ላይ የእግዚአብሔርን ቁጣ በመገንዘብ ቢናገርም ፤. . . ከቁጣህ እና ከመዓትህም የተነሳ አንስተኸኛልና ጥለኸኛልምና ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ያቀረበው ግላዊ የኃጢአት ኑዛዜ ግን የለም ፡፡ ይህም ምንም እነኳን እሱ በግሉ እግዚአብሔር የሰጠውን መሬት እና መልካም ትሩፋቶቹን ሁሉ ሊያጣ የማይገባው ታማኝ እስራኤላዊ ቢሆንም ፤ ስደቱ ግን እንደ አገር የሚገባቸው እነደሆነ የሚያሳይ ይመስላል፡፡

ታዲያ በሌሎች የህይወት ውሳኔ እና ምልልስ ሳቢያ የእምነት ሰው መከራ ውስጥ ሲገባ ምን ያደርጋል ? እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ያስባል ፡፡ የዚህ ዝማሬ ጸሃፊ የእግዚአብሄር ተስፋ ስጦታ የህይወት ተኃድሶ እንዳለው ያምናል ፡፡ ስለሆነም በመልካሙ ጊዜ በእግዚአብሔር ታምኖ እነደኖረ ሁሉ በአስከፊውም ክፉ ወቅት የእግዚአብሔርን ታማኝነት እያሰበ በልበ ሙሉነት በእምነት ይቆማል ( ቁጥ 12 እና 13 ፤ ሌዋ 26 ፡ 40-45 ) ፡፡

እኛም ብንሆን ፡- በዚህ ምድር ባለን የህይወት ዘመናችን ሙሉ ለሙሉ ራሳችንን እግዚአብሔርን ከማያምኑ እና ከማያከብሩ ሰዎች ነጥለን ማኖር አንችልም ፡፡ የኛ የህይወት ውሳኔ እና ምልልስ ሌሎችን የሌሎችም የሕይወት ውሳኔ እና ምልልስ እኛን ተጽእኖ ውስጥ ያስገባናል ፡፡ ስለሆነም በማይገባን የተለያዩ መከራዎች ስናልፍ በፈጠረን እና በሚያኖረን አምላክ ታምነን በልበ ሙሉነት ልንቆም ይገባል፡፡ አሜን ፡፡

ተጨማሪ ምንባቦች

መዝ 27

ምሳ 3፡25-26

ኤፌ 3፡11-12

1ጴጥ 4 ፡17 -18

---------------- // ----------------

22/09/2022

ለሕይወትህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፣ ራስህንና የሚሰሙህንም ታድናለህና።
1 ጢሞቴዎስ 4:16

ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።ምሳሌ 4:23
02/07/2022

ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።
ምሳሌ 4:23

29/06/2022

እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት፤ምሳሌ 23:23
27/06/2022

እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት፤
ምሳሌ 23:23

እግዚአብሔር ልጆቹ የሰይጣንን ጥቃቶች እንዲቋቋሙ እና እንዲያሸንፉ የሚያስታጥቃቸው ስድስቱ በጣም አስፈላጊዎቹ የመንፈሳዊ የጦር ትጥቆች እነዚህ ናቸው። ሰይጣን በክርስቲያኖች ላይ ያለው ኃይል ...
25/06/2022

እግዚአብሔር ልጆቹ የሰይጣንን ጥቃቶች እንዲቋቋሙ እና እንዲያሸንፉ የሚያስታጥቃቸው ስድስቱ በጣም አስፈላጊዎቹ የመንፈሳዊ የጦር ትጥቆች እነዚህ ናቸው።
ሰይጣን በክርስቲያኖች ላይ ያለው ኃይል ቀድሞ ተሰብሯል እናም ታላቁ ጦርነት በክርስቶስ ስቅለት እና ትንሳኤ ድል ተቀዳጅቷል፣ እሱም የኃጢአትንና የሞትን ኃይል ለዘላለም ድል አድርጓል።
ሆኖም፣ በምድር ላይ ባለው ህይወት፣ የፈተና ጦርነቶች በየጊዜው ይቀጥላሉ።
ለድል የጌታ ኃይል ፤

07/06/2022

እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፤
ኢዮ 40:4

ኢዮብ "ወራዳ ነኝ " ያለው ኃጢአተኝነቱን ተገንዝቦ ነው ። ምናልባት ስለ ራስህ ያለህ ግንዛቤ ኢዮብ ሥለ ራሡ ከተገነዘበው፣ ከተሰማው፣ ካመነበት የተለዬ ከሆነ እይታህ ልክ አይደለም ራስህን እያታለልክ ነው (1ዮሐ 1፡8) አሊያ ኃጢአትህን ተናዘህ ከእግዚአብሔር ጋር ተወዳጅተሐል ማለት ነው ። ኢዮብ ከሠዎች አንጻር ዕድቁ የተመሰከረለት አጠገቡ ካሉት ሠወች በላይ የተመሰገነ ሠው ነው፤ (ኢዮ 1፡1) ነገር ግን እንከን አልባ በሆነው በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት ማን ልክ ነኝ ማለት ይችላል? ( መዝ 143፡2) በርግጥ ይህ ነገር የገባው ኢዮብ ብቻ አይደለም አነ ዳዊት ፣ ኢሳያስ፣ ጳውሎስም ተመሳሳይ ነገር ብለዋል።

ጌታ ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷል (ሉቃ 19:10) እርሱ ኃጢአተኞችን እንጂ ፃድቃንን ልጠራ አልመጣሁም ብሏልና (ማቴ 9፡13) ኃጢአተኛ መሆንህን ካመንህ ጥሪውን ተቀበል ፤ አሁን የተወደደ የመዳን ሰዓት ነው (2 ቆሮ 6፡2) ። ማንም አድነኝ ለማለት እድል የማያገኝበት ሌሊት ይመጣል (ዮሐ 9፡4)። አሁን ግን ከኃጢአት ኃይልና ቅጣት የሚያድን የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧልና ( ቲቶ 2፡11) መንግስተ ሰማይም ቀርባለችና ንሥሐ ግባ ( ማቴ 3፡1)።
ታላቁን የመዳን ጥሪ ቸል አትበል !!!!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇2 ቆሮ 5፡ 20

መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።ዕብ 13፡16
04/06/2022

መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።
ዕብ 13፡16

Address

Addis Ababa

Opening Hours

09:00 - 17:00

Telephone

+251912614391

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mercy Reformed Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share