25/08/2025
፦
1. መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መሪነት የተነገረ ቃል መሆኑን እናምናለን፤ ስለዚህ አስተማማኝ፥ ስህተት የሌለበት፥ ፍጹም ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
2. እግዚአብሔር እራሱን ለሰው ልጆች በሦስት አካላት፥ በአብ፣ በወልድ እና መንፈስ ቅዱስ እንደገለጠ እናምናለን።
3. ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ተወልዶ በሥጋ የመጣ መሆኑን እናምናለን።
4. ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ኃጢአት ምትክ ሆኖ በመስቀል ላይ መሞቱን እናምናለን።
5. ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በአካል መነሣቱን እናምናለን።
6. ኢየሱስ ክርስቶስ የሚታይ ሆኖ በእርግጥ ዳግመኛ እንደሚመለስ እናምናለን።
7. ያመኑ ለዘላለም እግዚአብሔር ባለበት የሚኖሩበት የእውን መንግሥተ ሰማይ እና የጠፉት ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር በቅጣት የሚለዩበት የእውን ገሃነም እንዳለ እናምናለን።
8. ደኅንነት በእርሱ ጸጋ ላይ ተመሥርቶ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ እንደሆነና ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ጌታ እና አዳኝ አድርገው እምነታቸውን በእርሱ ላይ ላደረጉ የተቸረ እንደሆነ እናምናለን።
ነሐሴ፦ 18/12/2017ዓ.ም
🙌መልካም ቀን!