Chabod christian counseling service /cccs/.

Chabod christian counseling service /cccs/. youth and family counseling counseling the youth on spiritual and psychological issues

 #በዚህ አመት    #ካውንስሊንግ እና  #ስልጠና አገልግሎት  #በቢሮ እና ከቢሮ ውጭ በተለያዩ  #ቤተክርስቲያናት  #የካምፒንግ ፕሮግራሞች ላይ አገልግሎት ሰጥተናል።  #ለመምህራኖችም የአሰ...
05/08/2024

#በዚህ አመት #ካውንስሊንግ እና #ስልጠና አገልግሎት #በቢሮ እና ከቢሮ ውጭ በተለያዩ #ቤተክርስቲያናት #የካምፒንግ ፕሮግራሞች ላይ አገልግሎት ሰጥተናል። #ለመምህራኖችም የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ተችሎአል።
ለመምህራን የስልጠና አዘገጃጀትን እና አቀራረብን አስመልክቶ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና የራሳቸውን ተማሪዎች እንዴት ማሰልጠን እንደሚችሉ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነበር።
ለተማሪዎች ደግሞ በብዙ እነርሱን በሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ጸሎት እና ምክክር ማከናወን ተችሎአል።

በዚህ ሁሉ በሁሉ ስፍራ ጸጋውን አብዝቶልን ብዙዎችን መድረስ ስለቻልን ጌታን ከልብ እናመሰግናለን።

 ምክር በችግር ውስጥ ስንገባ እና ግራ ስንጋባ ለመወሰን  ብቻ የምንፈልገው አገልግሎት አይደለም። ይልቁኑ ምክር  ዘርፈ ብዙ የሆኑ ጥቅሞችን የምናገኝበት በመሆኑ ሁልጊዜ ልንገለገልበት ይገባል...
03/01/2024



ምክር በችግር ውስጥ ስንገባ እና ግራ ስንጋባ ለመወሰን ብቻ የምንፈልገው አገልግሎት አይደለም። ይልቁኑ ምክር ዘርፈ ብዙ የሆኑ ጥቅሞችን የምናገኝበት በመሆኑ ሁልጊዜ ልንገለገልበት ይገባል።


👉 ምክር የሚያስፈልጋቸው ብዙ ኬዞች በሕይወታችን ስለሚገጥመን፤

👉 ምክር የቀና እና የተስተካከለ ሕይወት ለመምራት እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ።

👉 ከእግዚአብሔር፣ ከራሳችን ብሎም ከሰዎች ጋር ቅይማት ውስጥ እንድንገባ የሚገፋፉ ክስተቶች በሕይወታችን ስለሚገጥሙን፤

👉 ለአጠቃላይ ምክር ለመፍትሔ ፣ አቅጣጫን ለማየት በሕይወት እንቅስቃሴያችን ሁሉ በጣም አስፈላጊ የመሆኑ ጉዳይ ምንም ጥርጥር የሌለው ነገር ነው።

በተጨማሪም ምክር ምሪትን እና አካሄድን ለማወቅ፣ የተሻለ ስኬት ለማግኘት፣ ለባህሪ መሻሻል ለማምጣት፣ ብዙ አዙሪት ያለበት አሰልቺ የሆነን ሕይወት እንዳንመራ ፣ ከሌላው ውድቀት እንድንማር እና እኛም እራሳችን ደጋግመን እንዳንወድቅ፣ በግንኙነት ውስጥ ከሰው ጋር የላቀ ተግባቦትን ለማዳበር፣ በማንኛውም ሁኔታ የሚፈጠርን ግጭትን ለመፍታት በአጠቃላይ ጥሩ የሆነ ሕይወትን እና ግንኙነትን ለመገንባት ምክር እጅግ አስፈላጊ ነው።




  ክርስቲያናዊ  #ማማከርና  #ስልጠና አገልግሎት  #የ3 ኛ አመት  #የምስረታ በዓልና የምስጋና ፕሮግራም፤ እነሆ እለቱ  #ዛሬ ነው።   #እንድታመሰግኑ ሁላችሁንም  !!!❝የረዳኝን እግዚአ...
24/12/2023

ክርስቲያናዊ #ማማከርና #ስልጠና አገልግሎት #የ3 ኛ አመት #የምስረታ በዓልና የምስጋና ፕሮግራም፤ እነሆ እለቱ #ዛሬ ነው።

#እንድታመሰግኑ ሁላችሁንም !!!

❝የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ።❞ መዝሙር 13: 6
ቀን ፦ ታህሳስ 14 / 2016 ዓ.ም
ሰዓት፦ 8፤00 ከሰዓት
ቦታ ፦ መካነየሱስ ሴሚናሪየም ቻፕል/ አዲሱ ህንጻ አጠገብ


❝እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።❞  —ዘፍጥረት 1: 27
22/11/2023

❝እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።❞
—ዘፍጥረት 1: 27


04/11/2023


#የአሳፍ መዝሙር
ይህ ጸሎት የብዙ ቁጥር የሕብረት ዘማሪዎች መሪ የሆነው አሳፍ በመዝሙር የጸለየው ነው። 1 ዜና 16፥5
መዝሙር 73፥1 - 28
በአጠቃላይ አሳፍ ወደ መቅደሱ ከመግባቱ በፊትና በሁዋላ የጸለየው ጸሎት ብለን ለሁለት መክፈል እንችላለን።

ከመግባቱ በፊት/ ከሕልውናው ሩቅ ሆኖ /
- "ዘ ሶሊተሪ ሪፔር" በተሰኘ አጭር የግጥም ጽሑፍ ላይ አንድ ሰው በአጨዳ ውስጥ ያለችን ሴትን ዜማ ከሩቅ እየሰማ በጣም ደስ እያለው ይጉዋዛል። ቀስ እያለ..... ከድምጹ እየራቀ ....እየራቀ... ሲሄድ ድምጹ እየቀነሰ....እየቀነሰ ይሄድበታል፤ ድምጹ ለመጥፋት እየተቃረበበት ሲሄድ ውስጡ ይረበሻል ያዝናል።
የአሳፍም ሁኔታ እንዲሁ ነበር፦
የሃጢያተኞችን ሁለንተና ፦ አካሄዳቸው፣ አኩዋናቸው፣ የሕይወት ዘዬያቸውን .... እስከ ሞታቸው ድረስ ነበር የቃኛቸው።
አሳፍ ከሕልውናው ርቆ ሐጢያተኞችን ብቻ መከታተል ስራው ሲሆን፤ ያኔ በቃ ተስፋ ቆረጠ።

ሲገባ / በሕልውናው ውስጥ ሲሆን/
ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ሕልውና ውስጥ መቆየት አዋጭ እንደሆነ ሲገባው እንዲህ አለ፦
❝በአንተ ምክር መራኸኝ፤ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።❞ መዝሙር 73: 24
በመጨረሻም ጸሎቱንም በዚህ እውነት ደመደመ፦

❝ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።❞
—መዝሙር 73: 28

ዛሬም እንደ አሳፍ ሲሰማን፣ ቶሎ ወደ ጸጋው ዙፋን ቀርበን፣ በሕልውናው ውስጥ እንዲህ እያልን በመዝሙር መጸለይ እንችላለን፦
ሃዋርያው ዮሃንስ ግርማ
🎸አንዳንዴ እደክምና ካንተ ኃላ እቀራለው 🎸እርምጃዬም ሲዘገይ እርቄ እከተልሃለው፤
🎸ከጠረንህ እርቄ መኖር ለእኔ ሞት ያህል ነው፤
🎸እባክህ ሳበኝና ከደረትህ እጠጋለው።😭❤️.. ካንተ ኃላ እሮጣለው🏃‍♀🏃



04/11/2023


#የአሳፍ መዝሙር
ይህ ጸሎት የብዙ ቁጥር የሕብረት ዘማሪዎች መሪ የሆነው አሳፍ በመዝሙር የጸለየው ነው። 1 ዜና 16፥5
መዝሙር 73፥1 - 28
በአጠቃላይ አሳፍ ወደ መቅደሱ ከመግባቱ በፊትና በሁዋላ የጸለየው ጸሎት ብለን ለሁለት መክፈል እንችላለን።

ከመግባቱ በፊት/ ከሕልውናው ሩቅ ሆኖ /
- "ዘ ሶሊተሪ ሪፔር" በተሰኘ አጭር ታሪክ ውስጥ አንድ ሰው በአጨዳ ውስጥ ያለችን ሴትን ዜማ ከሩቅ እየሰማ በጣም ደስ እያለው ይጉዋዛል። ቀስ እያለ..... ከድምጹ እየራቀ ....እየራቀ... ሲሄድ ድምጹ እየቀነሰ....እየቀነሰ ይሄድበታል፤ ድምጹ ለመጥፋት እየተቃረበበት ሲሄድ ውስጡ ይረበሻል ያዝናል።
የአሳፍም ሁኔታ እንዲሁ ነበር፦
የሃጢያተኞችን ሁለንተና ፦ አካሄዳቸው፣ አኩዋናቸው፣ የሕይወት ዘዬያቸውን .... እስከ ሞታቸው ድረስ ነበር የቃኛቸው።
አሳፍ ከሕልውናው ርቆ ሐጢያተኞችን ብቻ መከታተል ስራው ሲሆን፤ ያኔ በቃ ተስፋ ቆረጠ።

ሲገባ / በሕልውናው ውስጥ ሲሆን/
ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ሕልውና ውስጥ መቆየት አዋጭ እንደሆነ ሲገባው እንዲህ አለ፦
❝በአንተ ምክር መራኸኝ፤ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።❞ መዝሙር 73: 24
በመጨረሻም ጸሎቱንም በዚህ እውነት ደመደመ፦

❝ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።❞
—መዝሙር 73: 28

ዛሬም እንደ አሳፍ ሲሰማን፣ ቶሎ ወደ ጸጋው ዙፋን ቀርበን፣ በሕልውናው ውስጥ እንዲህ እያልን በመዝሙር መጸለይ እንችላለን፦
ሃዋርያው ዮሃንስ ግርማ
🎸አንዳንዴ እደክምና ካንተ ኃላ እቀራለው 🎸እርምጃዬም ሲዘገይ እርቄ እከተልሃለው፤
🎸ከጠረንህ እርቄ መኖር ለእኔ ሞት ያህል ነው፤
🎸እባክህ ሳበኝና ከደረትህ እጠጋለው።😭❤️.. ካንተ ኃላ እሮጣለው🏃‍♀🏃



04/11/2023

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913080138

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Chabod christian counseling service /cccs/. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Chabod christian counseling service /cccs/.:

Share