ነገሮች ሁሉ የዘመኑ ፍፃሜ እያበሰሩ ነው

ነገሮች ሁሉ የዘመኑ ፍፃሜ እያበሰሩ ነው Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ነገሮች ሁሉ የዘመኑ ፍፃሜ እያበሰሩ ነው, Addis Ababa.

This religious website created for the purpose of learning each other about spiritual and religious related views sharing of important and relevant popular thoughts, posts by videos and audios.

13/02/2022
30/07/2021
18/11/2020
22/02/2020


በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
እጅግ ውብ የሆነው በ18 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተሠራ የሚነገርለት ከጨለቆት ሥላሴ የተሠረቀው ታላቅ ዘውድ ከ20 ዓመታት በኋላ በክብር ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።
ይህ እጅግ ያማረ ዘውድ ጫፉ በቤተ ክርስቲያን ጉልላት አምሳል የተሠራ ነው። ጉልላት በቤተ ክርስቲያን ትርጓሜ የሥላሴ የአንድነት ምሳሌ ነው። ከዘውዱ ጉልላት በላይ በ3 አቅጣጫ የተቀረጸ መስቀል ያለበት ሲሆን የመካከለኛው ዋናው መስቀል ላይ ጸወርተ መንበር አርባዕቱ እንስሳ ኪሩቤል እና ሱራፌል የሥሉስ ቅዱስን ዙፋን ተሸክመው በአንደኛው ገጽ ላይ ይታያሉ።
በዛው መስቀል ጀርባ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን ተሸክመው ተሥሏል። ይህም ሥጋን ቢዋሐድ ቅሉ በአንድነቱ ምንታዌ (ኹለትነት) በሦስነቱ ርባዔ (አራትነት) እንደሌለበት ማሳያ ነው።
በመሆኑም ይህን ዘውድ የሚቀዳጅ ከራሱ በላይ ይህንን ማድረጉ ከሁሉ በላይ የሆኑ ንጉሠ ነገሥት፣ አምላከ አማልክት ሥሉስ ቅዱስ መሆናቸውን ማመኑ፣ በወልደ እግዚአብሔር በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት መታመኑ ማሳያ ነው።
ክበብ ከሚመስለው ዓለም መካከለኛው ላይ ሌላ ከፍ ያለች ክበብ መካከል ላይ መኖሯ በዚያ ዘውድ ላይ መስቀል መቆሙ የሚያመለክተው በዳዊት መዝሙር ላይ “እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ።”
(መዝሙር 74፥12) እንዳለ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር መካከል በቀራንዮ ላይ ዓለምን ለማዳን በመስቀል መሰቀሉን አመልካች ነው።
በዚያ ክበብ ዙሪያ ሻሻቴ መርገፍ መኖሩ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ በማዕከለ ምድር በቀራንዮ በተሰቀለ ጊዜ ከእግረ መስቀሉ ሥር ተነጽፈው ያመሰገኑት መላእክትን ይወክላል "ወርኢኩ ኃይላተ ሰማያውያነ ድኑናነ ወድንጉጻነ በዐውደ መስቀሉ እኩት ወስቡሕ" እንዲል።
በዓለም ቅርጽ በአራት ማዕዘን ዙርያ አእማደ ምድር (የምድር ምሰሶዎች) የተባሉ በአራት የምድር አቅጣጫዎች ሁሉ ወንጌል ደርሷልና የወንጌላውያን አምሳል ዐምደ ወርቅ አለ።
በበታቹም የአበው ሐዋርያት ሥዕልና ስም በሚያምር ውብ በሆነ መልኩ በአራቱም አቅጣጫ ተሥሎና ተጽፎ ይገኛል ይህም ነቢዩ ዳዊት “ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።” (መዝሙር 19፥4) ብሎ በአራቱ የምድር መአዝናት ዙረው ወንጌልን መስበካቸውን ይወክላል።
ዙሪያውን በስንዴ ዘለላ በተለያዩ ሐረጋት አጊጦ የኢየሱስ ክርስቶስን ሐረገ ወይንነት ኅብስተ ሕይወትነት የሚመሰክረው ይህ ውብ ዘውድ በኔዘርላንድ ነዋሪ በሆኑት አቶ ሲራክ አስፋው ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ ከሚመለከታቸው በኔዘርላንድ ካሉ ኃላፊዎችና ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ጋር በመነጋገር የካቲት 12/ 2012 ዓ.ም. እንደተመለሰ The Associated Press ዛሬ በዘገባው ላይ ገልጾታል።
ከአስናቂ ዘውዱ ጋር እጅግ ውብ የሆነች ምስለ ፍቁር ወልዳ የእመቤታችን ሥዕል ዐብራ አለች። ይህም የቀደምት ኢትዮጵያውያንን የሃይማኖት ፍቅር፣ ድንቅ ጥበብን ያሳየ ሲሆን ወደ እናት ሀገሩ ይህ ክቡር ቅርስ መመለሱ በጣም አስደሳች ነው።
እጅግ በጣም አስደናቂ የኢትዮጵያ የወርቅ የዕንቁ ዘውዶች፣ መስቀሎች፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ምትክ የማይገኝላቸው በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የብራና መጻሕፍት፣ ጥቅሎች በየዓለማቱ ዛሬ ድረስ ያሉ ሲሆን በመቅደላ ጦርነት ጊዜ እንኳን ከመቅደላ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በ15 ዝሆኖች በ200 በቅሎዎች ተጭኖ ተዘርፎ የወጣው ቅርስ በጊዜው ወደ 35 ሚሊየን ፓውንድ እንግሊዝ ለንደን ላይ ለጨረታ እንደቀረበ የሚታወቅ ነው።
አሁንም በዚ አስደናቂ ዘውድ ላይ እንደተደረገው ሁሉ ይህን በጎ መልካም ሥራን አብነት አድርገው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ቅርሶቻችን መጻሕፍቶቻችን እንዲያስመልሱ ቢያደርጉ ታሪክ ሁልጊዜ ስማቸውን በወርቅ ቀለም ጽፎ ያስባቸዋል።
[ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ]

Address

Addis Ababa

Telephone

+251968318216

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ነገሮች ሁሉ የዘመኑ ፍፃሜ እያበሰሩ ነው posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share