GMTC Ethiopia

GMTC Ethiopia Speak the truth, live for the glory of God, and serve those around you.

 #ባህል ማለት የአንድ ሕዝብ አጠቃላይ የሕይወት መንገድ፣ እምነት፣ እሴት፣ ሥነ-ሥርዓት፣ ቋንቋ፣ ጥበብና ታሪክ ድምር ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ሲሆን ማኅበረሰቡን የሚለይ መሠረ...
31/07/2026

#ባህል ማለት የአንድ ሕዝብ አጠቃላይ የሕይወት መንገድ፣ እምነት፣ እሴት፣ ሥነ-ሥርዓት፣ ቋንቋ፣ ጥበብና ታሪክ ድምር ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ሲሆን ማኅበረሰቡን የሚለይ መሠረታዊ ምንነት ነው።
#እኔ ግን የሚጠይቀው #ክርስቲያን በክርስቶስ አምኖ #የዳነ ሰው ሁሉ የጋራ ባህል የለውም ? ካለስ ምንድነው ? #ፃፉልኝ ቅዱሳን ።
photo credit: Donatello

23/07/2026

#የመጽሐፍ ቅዱስ 66 መጻሕፍት – አጭር ማብራሪያ
#ብሉይ ኪዳን (39)
#ዘፍጥረት – የፍጥረት፣ የሰው ውድቀት እና የአባቶች ታሪክ።
#ዘጸአት – እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብፅ ነፃ አወጣ፤ ሕጉንም ሰጠ።
#ዘሌዋውያን – የአምልኮ፣ የቅድስና እና የመሥዋዕት ሕጎች።
#ዘኍልቍ – በምድረ በዳ የእስራኤል ጉዞና ቆጠራ።
#ዘዳግም – ሙሴ ሕጉን እንደገና ለሕዝቡ ያስተምራል።
#ኢያሱ – የተስፋይቱን ምድር መውረስ።
#መሳፍንት – የእስራኤል ፈራጆች ታሪክ።
#ሩት – የታማኝነትና የቤዛነት ታሪክ።
#1 ሳሙኤል – ሳሙኤል፣ ሳኦል እና ዳዊት።
#2 ሳሙኤል – የንጉሥ ዳዊት አገዛዝ።
#1 ነገሥት – ሰሎሞንና የመንግሥቱ መከፈል።
#2 ነገሥት – የእስራኤልና የይሁዳ ውድቀት።
#1 ዜና መዋዕል – የዳዊት ዘመን ታሪክ።
#2 ዜና መዋዕል – የይሁዳ ነገሥታት ታሪክ።
#ዕዝራ – ከምርኮ መመለስና ቤተ መቅደስ መልሶ መገንባት።
#ነህምያ – የኢየሩሳሌምን ቅጥር መልሶ መገንባት።
#አስቴር – እግዚአብሔር ሕዝቡን ያድናል።
#ኢዮብ – በመከራ ውስጥ ያለ እምነት።
#መዝሙር – የምስጋና፣ የጸሎት እና የአምልኮ መዝሙሮች።
#ምሳሌ – የጥበብ ትምህርቶች።
#መክብብ – ያለ እግዚአብሔር ሕይወት ከንቱ ነው።
#መኃልየ መኃልይ – የፍቅር መዝሙር።
#ኢሳይያስ – ስለ መሲሑ የተሰጡ ትንቢቶች።
#ኤርምያስ – ወደ ንስሐ ጥሪ።
#ሰቆቃወ ኤርምያስ – በኢየሩሳሌም ውድቀት ላይ ልቅሶ።
#ሕዝቅኤል – የፍርድና የተስፋ ራእዮች።
#ዳንኤል – በምርኮ ውስጥ ያለ ታማኝነትና ትንቢት።
#ሆሴዕ – የእግዚአብሔር ታማኝ ፍቅር።
#ኢዮኤል – ወደ ንስሐ ጥሪ፤ የመንፈስ ቅዱስ ተስፋ።
#አሞጽ – ፍትሕን እና ጽድቅን ይጠራል።
#አብድዩ – በኤዶም ላይ ፍርድ።
#ዮናስ – የንስሐና የምሕረት ታሪክ።
#ሚክያስ – መሲሑ በቤተልሔም እንደሚወለድ ትንቢት።
#ናሆም – በነነዌ ላይ ፍርድ።
#ዕንባቆም – በእግዚአብሔር መታመን።
#ሶፎንያስ – የጌታ ቀንና ተስፋ።
#ሐጌ – ቤተ መቅደስን እንደገና መገንባት።
#ዘካርያስ – ስለ መሲሑ ብዙ ትንቢቶች።
#ሚልክያስ – ለጌታ ታማኝ መሆንን ያስተምራል።
#አዲስ ኪዳን (27)
#ማቴዎስ – ኢየሱስ የተስፋው መሲሕ ነው።
#ማርቆስ – ኢየሱስ ኃይለኛ አገልጋይ ነው።
#ሉቃስ – ኢየሱስ የዓለም አዳኝ ነው።
#ዮሐንስ – ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
#የሐዋርያት ሥራ – የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ።
#ሮሜ – በእምነት መጽደቅ።
#1 ቆሮንቶስ – የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና አንድነት።
#2 ቆሮንቶስ – በድካም ውስጥ የክርስቶስ ኃይል።
#ገላትያ – ድነት በጸጋ እንጂ በሕግ አይደለም።
#ኤፌሶን – በክርስቶስ ያለው አዲስ ሕይወት።
#ፊልጵስዩስ – በጌታ ደስታ።
#ቆላስይስ – የክርስቶስ በላይነት።
#1 ተሰሎንቄ – ለጌታ መምጣት መዘጋጀት።
#2 ተሰሎንቄ – ስለ ጌታ ዳግም ምጽአት።
#1 ጢሞቴዎስ – ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች መመሪያ።
#2 ጢሞቴዎስ – በእምነት ጸንቶ መቆም።
#ቲቶ – ጥሩ አመራርና መልካም ሥራ።
#ፊልሞና – ይቅርታና እርቅ።
#ዕብራውያን – ክርስቶስ ከሁሉ ይበልጣል።
#ያዕቆብ – እምነት በሥራ ይገለጣል።
#1 ጴጥሮስ – በመከራ ውስጥ ተስፋ።
#2 ጴጥሮስ – ከሐሰተኛ አስተማሪዎች ተጠንቀቁ።
#1 ዮሐንስ – በፍቅርና በእውነት መኖር።
#2 ዮሐንስ – በእውነት መጽናት።
#3 ዮሐንስ – እንግዳ መቀበልና ታማኝነት።
#ይሁዳ – ለእምነት መታገል።
#ራእይ – የክርስቶስ ድል፣ የመጨረሻ ፍርድ እና አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር።
Credit : Moges Mekonnen

የኢትዮጵያ ገንዘብ "ብር" ለምን ተባለ ?  1. ቀጥተኛ ትርጉም ከብረቱ ጋር"ብር" የሚለው ቃል መጀመሪያ ላይ የብር ብረትን (silver metal) ያመለክታል። በጥንት ዘመን ሳንቲሞች ከዚህ...
21/07/2026

የኢትዮጵያ ገንዘብ "ብር" ለምን ተባለ ?

1. ቀጥተኛ ትርጉም ከብረቱ ጋር
"ብር" የሚለው ቃል መጀመሪያ ላይ የብር ብረትን (silver metal) ያመለክታል። በጥንት ዘመን ሳንቲሞች ከዚህ ብረት ይሠሩ ስለነበር፣ ቃሉ ከብረቱ ስም ጋር ተያይዟል።

2. ታሪካዊ ዳራ (የሳንቲም ባህል)
በኢትዮጵያ ውስጥ ሳንቲሞች ከ100 ዓመታት በላይ ሲታወቁ ቆይተዋል። በተለይ በዘመነ ምኒልክ (19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ) የተፈጠሩት ሳንቲሞች ከብር ብረት የተሠሩ ነበሩ። ሕዝቡ እነዚህን ሳንቲሞች በብረቱ ስም "ብር" ብሎ መጥራት ጀመረ።

3. የመገበያያ ገንዘብ ምትክ
ከዚያ በፊት ጨው፣ ወርቅ፣ ወይም የባር ጨርቅ እንደ ገንዘብ ያገለግሉ ነበር። የብር ሳንቲሞች ሲመጡ፣ ዘላቂ፣ ሊቆጠር የሚችል እና ከፍተኛ እሴት ስለነበራቸው በፍጥነት ተቀባይነት አገኙ። ስለዚህ "ብር" የሚለው ቃል "ገንዘብ" ከሚለው ትርጉም ጋር ተያያዘ።

4. ዘመናዊ ምንዛሪ
በ1945 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ የአሁኑን ብር እንደ ኦፊሴላዊ ምንዛሪ አስተዋወቁ። ምንም እንኳን ሳንቲሞቹ ከብር ባይሠሩም (አሁን ከብረት ወይም ከወረቀት የተሠሩ ቢሆኑም)፣ ታሪካዊው ስም ተጠብቆ ቆይቷል።

5. ተመሳሳይ ምሳሌዎች
እንግሊዝኛ "pound" (ስተርሊንግ ሲልቨር ማለት ነበር)
ፈረንሳይኛ "argent" (ማለትም ብር)
ግሪክኛ "drachma" (ማለትም እፍኝ የብር)

እናመሰግናለን

ትንሽ ብሆን አሁን እንደተረዱት እንገምታለን
Follow, share, comment, like

 ✍️ ለውጥ በህይወታችሁ ከፈለጋችሁ የእግዚአብሔርን ቃል አንብቡ። አንድ ጊዜ ሳይሆን በየቀኑ፣ በጸሎት፣ በማሰላሰል። #ምሳሌ ፦✍️ አንድ ሰው ሌላውን ከጠላ በህግ "አትግደል" ተብሎ ይታገዳል...
16/07/2026


✍️ ለውጥ በህይወታችሁ ከፈለጋችሁ የእግዚአብሔርን ቃል አንብቡ። አንድ ጊዜ ሳይሆን በየቀኑ፣ በጸሎት፣ በማሰላሰል።

#ምሳሌ ፦
✍️ አንድ ሰው ሌላውን ከጠላ በህግ "አትግደል" ተብሎ ይታገዳል፣ ነገር ግን ልቡ በቁጣ ይሞላል። የእግዚአብሔር ቃል ግን "" ኢየሱስም አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ። ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?"
(የማቴዎስ ወንጌል 9:4) " ይላል — ይህም ሥሩን ይፈታል።
✍️ አንድ ሰው ሀብት ሲኖረው ህግ አይከለክለውም ነገር ግን እግዚአብሔር ቃሉ "ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፥ ገንዘብህንም የሚወስድ እንዲመልስ አትጠይቀው።"
(የሉቃስ ወንጌል 6:30)" ይለዋል — ይህ ደግሞ ልብን ያስተካክላል።

#በአለም ላይ ተጽዕኖ መፍጠር ትጀምራላችሁ።
✍️ ቃሉን በማንበብ የተለወጠ ሰው ቤተሰቡን ይለውጣል፣ ቤተሰብ ማህበረሰቡን፣ ማህበረሰብ ሀገሩን፣ ሀገርም አለምን ይቀይራል።
#ህግ ከላይ ወደ ታች ያስገድዳል፣ የእግዚአብሔር ቃል ግን ከታች ወደ ላይ—ከልብ ወደ ተግባር—ይሠራል።

#ማሳሰቢያ ፦ ህግ ባለመሳካቱ ሳይሆን ልብ ሳይለወጥ ስቀር ነው ለውጡ የማይታየው። ።


ቀን 09/11/2018 ዓ. ም.
ታርጫ

የተፈጠርኩት፣ የተወለድኩት፣ ያደኩት፣ የተማርኩት እና የሚኖረው ለእግዚአብሔር ክብር ለመኖር፣ የሰው ልጅን ጨምሮ ለፍጥረታት በረከት ለመሆን ነው።
15/07/2026

የተፈጠርኩት፣ የተወለድኩት፣ ያደኩት፣ የተማርኩት እና የሚኖረው ለእግዚአብሔር ክብር ለመኖር፣ የሰው ልጅን ጨምሮ ለፍጥረታት በረከት ለመሆን ነው።

 ?✍️ ትክክለኛውን አመለካከት ሊሰጠን የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።     ❤ በአሁኑ ጊዜ ለብዙ ነገሮች መለኪያና መነሻ የሚሆን እውነታ እየጠፋ ነው። ሰዎች ራሳቸውን የሚመዝኑት በ...
14/07/2026

?
✍️ ትክክለኛውን አመለካከት ሊሰጠን የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።

❤ በአሁኑ ጊዜ ለብዙ ነገሮች መለኪያና መነሻ የሚሆን እውነታ እየጠፋ ነው። ሰዎች ራሳቸውን የሚመዝኑት በሌሎች አስተያየት፣ በባህል፣ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ አዝማሚያ ነው—እነዚህ ግን እያንዳንዳቸው እንደ አየር የሚለዋወጡ ናቸው። ስለዚህ ሰው ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቃል ይመለስ።

መንግስት ብዙ አዋጅ ያፀድቃል፣ ህግ ያወጣል፣ መመሪያ ይሰጣል። ነገር ግን ለውጥ እምብዛም አይደለም።

#ለምሳሌ፦
👨‍✈️ የትራፊክ ህጎች ቢበዙም፣ ትርፍ የሚጭኑ ፣ ያለ ፍቃድ የሚያሽከረክሩ አሉ።

🕵️‍♂️የፍትህ ስርዓት ቢጠናከርም፣ ሙስና አሁንም አለ።
👨‍🏫 የሥነ ምግባር ትምህርት ቢሰጥም፣ ራስ ወዳድነት ፣ አድልዎ አልቀነሰም።

#ለምን?
✍️ ምክንያቱም ህጎች ውጫዊ ባህሪን መቆጣጠር ይችላሉ፣ ነገር ግን የልብ ለውጥ ማምጣት አይችሉም።

✍️ የሰውን ልጅ እይታ፣ አመለካከት፣ እና ተግባር ሊቀይር የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።

#እንዴት?
— በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል ሰው ራሱን እንደ አፍቃሪው ፍጡር እንጂ እንደ ዘፈቀደ አቶም አይቶ መኖር ይጀምራል።
— ቁጣን በይቅርታ፣ ፍርሃትን በእምነት፣ ተስፋ መቁረጥን በተስፋ ይተካል።
— ሰው መስዋዕት መሆን፣ መጋራት፣ ተግቶ መስራትን፣ ይቅር ማለት እና መውደድ የሚማረው ከቃሉ ነው።


✍️ የእግዚአብሔርን ቃል በቤታችሁ ማስቀመጥን አላልኩም፣ በእጅ ይዛችሁ ወደ ኃይማኖት ተቋም መሄድም አይደለም። እነዚህ ሁሉ መልካም ናቸው፣ ግን በራሳቸው በቂ አይደሉም።...................ይቀጥላል

ቀን 06/11/2018 ዓ. ም.
ታርጫ

  ✍️መሪነት ማለት በሁሉም ዘንድ ተወዳጅ መሆን ሳይሆን፣ ለሚከተሉት ታማኝ መሆን ነው። መሪ ጠላቶች ይኖሩታል፤ ምክንያቱም ውሳኔው ሁሉንም አያስደስትም። ነገር ግን የሚመራቸው ሰዎች ደህንነታ...
10/07/2026


✍️መሪነት ማለት በሁሉም ዘንድ ተወዳጅ መሆን ሳይሆን፣ ለሚከተሉት ታማኝ መሆን ነው። መሪ ጠላቶች ይኖሩታል፤ ምክንያቱም ውሳኔው ሁሉንም አያስደስትም። ነገር ግን የሚመራቸው ሰዎች ደህንነታቸው ከተጠበቀ፣ ራዕዩ ከተሳካ እና አሻራውን ካስቀመጠ ያ እውነተኛ ስኬት ነው።
#ስለዚህ
✍️ በሁሉም ሰው ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን ከመሞከር ይልቅ ለትውልድ ጠቃሚ ለመሆን ጥረት አድርግ።

✍️ ለውጥ ያደርጋል ለውጥ ደግሞ የቆዩ ጥቅመኞችን ይነካል
✍️ ቅድሚያ ይሰጣል አንዱን ለማስቀደም ሌላውን ወደኋላ ያደርጋል
✍️ እውነት ይናገራል እውነት ሁልጊዜ ጣፋጭ አይደለችም
✍️ ስልጣን ይጋራል ስልጣን የሚወዱ ሰዎች ይቃወሙታል።

!

03/11/2018
Tarcha

  ✍️ የሰው ልጅ ሁሉ የተማረ ይሁን ያልተማረ ለሌሎች ዕድገትና ለውጥ የሚጠቅም ሀሳብ አለው። ነገር ግን ከሚሰሙት እና ከሚቀበሉት ሰዎች መካከል ሀሳቡን አክብሮ አሰላስሎ እና ተረድቶ ምላሽ ...
05/07/2026


✍️ የሰው ልጅ ሁሉ የተማረ ይሁን ያልተማረ ለሌሎች ዕድገትና ለውጥ የሚጠቅም ሀሳብ አለው። ነገር ግን ከሚሰሙት እና ከሚቀበሉት ሰዎች መካከል ሀሳቡን አክብሮ አሰላስሎ እና ተረድቶ ምላሽ በመስጠት የሚያሳድግ እምብዛም አይታይም።
✍️ ብዙዎቻችን ሀሳቡን ብለን ከማሰላሰል፣ ከመረዳት፣ እና ምላሽ(Response) ከመስጠት ይልቅ በሚል አመለካከት ሀሳቡን መከላከል(Reaction) ላይ ትኩረት እናደርጋለን።
✍️ ይህ ደግሞ ወይም ሰዎች ካልሆነ #ማደግ፣ ከሚል ትንሽ አስተሳሰብ የሚመነጭ ትህትና የሌለበት አመለካከት ነው።
✍️ ከዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች ዕድሜያቸውን የሚጨርሱት የሌላውን ሀሳብና ራዕይ #በማጨናገፍ ላይ ስያተኩሩ ራሳቸው ይሄዳሉ።
✍️ ሰውን መጥላት ሀሳቡን ለማጨናገፍ ምክንያት ቢሆንም፣ ይህ የራሳችንን ጥቅም እንደሚያጎድል ታሪኮች ያሳያሉ። ሀሳቡን ከሰውዬው ለይተን ማየት ጥበብ ነው።
✍️ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ቆይተን ሳይሆን #ቀናነት ፣ #አመስጋኝነት ፣ #ትህትና ፣ እና #መተማመንን ያጎናፀፈ አመለካከት ባለቤቶች እንሁን።
ስለምትከታተሉን አመሰግናለሁ !
ቀን 28/10/2018 ዓ ም
ታርጫ
ማቴዎስ ሀደሮ
GMTC Ethiopia

 ✍️  እምነት ማለት በአእምሮ ብቻ መስማማት ሳይሆን፣ ለእግዚአብሔር ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ነው።  #መግቢያ፦ ዕብራውያን  11፥1“እምነት ተስፋ የምታደርገውን ነገር ማረጋገጫ፣ የማ...
04/07/2026


✍️ እምነት ማለት በአእምሮ ብቻ መስማማት ሳይሆን፣ ለእግዚአብሔር ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ ነው።

#መግቢያ፦ ዕብራውያን 11፥1“እምነት ተስፋ የምታደርገውን ነገር ማረጋገጫ፣ የማይታዩትንም ማስረጃ ናት።”
✍️ እምነት ስሜት ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ነው።

ሀ. እምነት መሠረቱ ቃል እንጂ ስሜት አይደለም

ሮሜ 10፥17 “እምነት ከመስማት፣ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ይመጣል።”

#ምሳሌ፦ ኢየሱስ በመርከብ ላይ ተኝቶ ሳለ ነፋሱ በጣም ጠነከረ (ማርቆስ 4፥38)። ደቀ መዛሙርት እያዩት ቢሆንም ፈሩ፤ ምክንያቱም እምነታቸው በስሜት (ፍርሃት) ላይ እንጂ በኢየሱስ ቃል ላይ አልነበረም። ኢየሱስ ነፋሱን በቃል ገሰጸው።

ለ. እምነት በጨለማ ውስጥ መመላለስ ነው

መዝሙር 119፥105 “ቃልህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው።”

#ምሳሌ፦ አብርሃም ወደ የማያውቀው ምድር ሲሄድ (ዘፍጥረት 12) የመንገዱን ካርታ አላየም፤ ግን የእግዚአብሔርን ቃል አየ።
✍️ እምነት ሁሉን ከማየት በፊት በተናገረው ላይ መቆም ነው።

ሐ. እምነት የሚያድገው በፈተና ነው

ያዕቆብ 1፥2-3 “የእምነታችሁ ፈተና ትዕግሥትን ያፈራል።”

#ምሳሌ፦ ኢዮብ ሀብቱን፣ ልጆቹን እና ጤናውን በአንድ ጊዜ አጣ። ሚስቱ “እግዚአብሔርን ስደብ” አለችው (ኢዮብ 2፥9)። ኢዮብ ግን “እርሱ ቢገድለኝ እንኳ ተስፋ አደርጋለሁ” (ኢዮብ 13፥15) አለ።
✍️ ይህ እምነት ሁኔታን ሳይሆን ማንነቱን ማመን እንደሆነ ያሳያል።
🙏 ለዛሬው እዚህ ላቆምና እውነት ስለ እምነት አስቡት የጠራችሁ ፣ የሚታምኑት ጌታ ምን አይነት ነው? ማንነቱን እወቁ!
ቀን 27/10/2018
ታርጫ
ማቴዎስ ሀደሮ
GMTC Ethiopia

 ሕይወትን ከሞገድ (wave) ጋር ማመሳሰል እና ከኤሌክትሪካል ምህንድስና ቃላት ጋር በማያያዝ ላቀርብላችሁ ነው። #1. የሕይወት ሞገድ (Life Wave) እንደ ኤሌክትሪካል ሲግናል ብንመለከ...
23/06/2026


ሕይወትን ከሞገድ (wave) ጋር ማመሳሰል እና ከኤሌክትሪካል ምህንድስና ቃላት ጋር በማያያዝ ላቀርብላችሁ ነው።
#1. የሕይወት ሞገድ (Life Wave) እንደ ኤሌክትሪካል ሲግናል ብንመለከተው፡-
a· Frequency (ድግግሞሽ) = በየቀኑ የሚያጋጥሙን ተግዳሮቶች ብዛት
b· Amplitude (ስፋት) = የደስታና የሀዘን መጠን
c· Peak (ከፍተኛ ነጥብ) = የህይወት መሪ ጊዜያት
d· Wave length (የሞገድ ርዝመት) = በተከታታይ ፈተናዎች መካከል ያለው ጊዜ
#2. የህይወት መንገድን ከ AC ወደ DC መቀየር ማለት፡-
a· ሕይወት በተፈጥሮው AC (ተለዋጭ ጅረት) ነው — አዎንታዊና አሉታዊ ጊዜያት ይለዋወጣሉ
b· DC (ቀጥተኛ ጅረት) ማድረግ ማለት ህይወትን በተረጋጋ፣ በተስተካከለ እና በቁጥጥር ስር ባለ መንገድ ማራመድ ነው።
c· RMS (Root Mean Square) እሴት ደግሞ የህይወትን አማካይ ውጤታማነት ያሳያል — ከፍተኛና ዝቅተኛ ጊዜያትን ሁሉ በማስተካከል የሚገኘው ዘላቂ እሴት።
#3.ለዚህ ህይወት የመፍትሔ ሃሳቦች ፡-
a· መጸለይ = የራስን ሞገድ ከአጽናፈ ሰማይ ሞገድ ጋር ማመሳሰል (frequency synchronization)
b· በርትቶ መስራት = ለማንኛውም የውጭ ጣልቃገብነትን (noise) መቋቋም የሚችል ጠንካራ ስርዓት መገንባት
c· የመግባባት ክህሎት(Smart Communication) = ከሰዎች ጋር impedance matching (የማጣጣም) በማድረግ የሲግናል ጥራትን ማሻሻል

#ማጠቃለያ፡- ህይወት AC ነው፣ ግባችን ግን ራሳችንን ወደ DC ማቅረብ ነው — ማለትም ሚዛናዊ፣ የተረጋጋ እና ውጤታማ መሆን። ይህ ግን የማያቋርጥ ጥረት፣ ማላመድ እና ትዕግስት ይጠይቃል። በእውነቱ ሕይወት የየራሱ የሆነ ልዩ ሞገድ አለው እና ማንም ሊደግመው አይችልም — የእርስዎን ሞገድ በመረዳት መጓዝ የራስዎ ልዩ ጥበብ ነው። መልካም ጉዞ!
ቀን 16/10/2018 ዓ.ም
ታርጫ
ማቴዎስ ሀደሮ
Founder of GMTC_Ethiopia

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GMTC Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share