Eyobe Moges

Eyobe Moges በዚህ ገፅ ውስጥ ስለተለያዩ ነገሮች እናወራለን በተለይ ግን ?

Laughter is the best medicine. Never lose your joy! 😂
13/08/2026

Laughter is the best medicine. Never lose your joy! 😂

11/08/2026

ታሪክ ብቻ አይሆንም፦

እስኪ ስሙኝ ማ እኔም ታሪክ ላውራ
አደመጥኩ የናንተን እኔም አንዴ ላውራ
ያኔ ድሮ በፊት ፅንፈኛ ሳይመጣ
የዘር ፖለቲካ ሳይሆንብን ጣጣ
እንደ ዛሬው ሳይሆን ሰው በሰው ሳይጨክን
ውሸት ሳይገንብን በእውነት አምሮብን
በጉራማይሌነት አንድነትን ፈጥረን
በመዋደድ መስመር እንዲያ ተከባብረን
አብዬ ጋሽዬ ታላቄ ታናሼ
እህትዬ እናቴ አንተው ወንድም ጋሼ
እንዲ ተጠራርተን በአንድ ተሰብስበን
ማእዱ ከመሀል እኛ ዙሪያ ከበን
እረ ለኔ በቃኝ ስጭው ለጋሽዬ
በይ እንጂ አንቺ ልጅ ጨምሪ ለትዬ
እረ ቆረስ አርገው ምነው ቆነጠርከው
ፉት በል ከጠላው አንሳ እንጂ ተጎንጨው
በይ እንቺ እማዬ ይችንማ ጉረሽ
አህቴ አለምዬ ሞት ይርሳኝ ረሳሁሽ
ይችን ጉረሽልኝ በይ በዝች ልካስሽ
አይ መዋደዳችን ፍቅር ውበታችን
ደስታ በቤታችን ሠላም ነው ቀያችን
ታዲያ በዚህ ሰሞን የነካንን እንጃ
ሴጣን መሀላችን ጦርነት አወጃ
ወቸው ጉድ
ፍቅራችን ተቀማ ሠላማችን ጠፋ
ደስታችን ደብዝዞ ሀዘናችን ሠፋ
ሳቃችን አለቀ ለቅሶችን በረታ
ወሬኛው በዛና ስራ እየፈታ
አጉል ዲስኩር ያዘ ሀገር የሚፈታ
ታዲያ ይህን ጊዜ
የሠራነው ሁሉ አልሰምር እያለን
የቀረበው ሁሉ ለኛ መች ጣፈጠን
ለካስ ሰላም ሲኖር ፍቅር ሲሰፍን ነው
ብልፅግና የሚሠምረው ሀገር የምትለማው
እናማ ከንግዲህ
ሞፈር ቀንበር እንጂ ወሬ ምን ያደርጋል
ህዝብ እያፈናቀለ ሀገርን ይፈታል

ገጣሚ Eyobe Moges

Follow MeEyobe Moges
19/07/2026

Follow Me

Eyobe Moges

Address

0977573186
Addis Ababa
ወንጌልለሁሉም

Telephone

+251977573186

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eyobe Moges posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Eyobe Moges:

Shortcuts

Share