17/03/2026
የእውነት እጅግ ሀዘን ተሰምቶኛል !!! ወድ ወንድማችን ወተት ክብሩ በድንገተኛ ሞት መነጠቃችን!!!
2ኛ መረጃው ሳናውቅ በመሆኑ 3ኛ ወንድማችንን ቆመን ባለማስቀበራችን
እጅግ በጣም የምንወደው ትሁቱ ወንድማችን ስራውና ግብሩ የተጣመረለት፥ እስከነ ስሙ ወተት የሆነ፥ ለታላቁም ለታናሹም ታዛዥ የነበረው ወተት ክብሩ ክፍሌ በማኀበረዜናማርቆስ ሀዋሳ ማዕከል ስራ አመራር ኮሚቴ ሆኖ ለረጅም ዓመታት በታማኝነት ሲያገለግል የነበረው አባታችን፥ መካሪያችን ዕድሜው ሳይገድበው በሌሊት ከእኛ ጋር ከገጠር እስከ አ/አ ከአ/አ እስከ ሐዋሳ በአገልግሎት ስናንከራትተው የነበረው ዝምተኛው አገልጋይ በተሽከርካሪ አደጋ ምክንያት በስጋ ሞት ተለይቶናል።ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን፣ ለቤተሰቦቹ፣ለጓደኞቹ ለወዳጅ ዘመዶቹና እና ለማኀበረዜናማርቆስ አገልጋዮች አምላከ ዜናማርቆስ መጽናናትን ያድልልን
የወንድሞቻችን የአገልጋዮቹ ሞት በቃችሁ ይበለን
ወንድሞቻችን አንረሳችሁም ዛሬም እንወዳችኋለን ።
ማዜማ ጽ/ቤት