Islamic History

Islamic History Spreading the Light through clarification

16/11/2022

1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋል። [ቡኻሪ፡ 1356]

ነገር ግን በክርስትና (በባይብል) ሙስሊምን መጠየቅ ሀጢያት ነው።
2ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
¹⁰ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤
¹¹ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።
(2ኛ ዮሐንስ 1:9–11)

2- የክርስቲያንን የግብዣ ጥሪ መቀበል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብዩን ﷺ አንድ የሁዲ ጠርቷቸው ሄደዋል። [አሕመድ፡ 13201]

3- ክርስቲያን የሆነ ሰው ቤተሰብ ቢሞትበት ለተዕዚያ ወይም ለማፅናናት መሄድ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለዚህ ድጋፍ መሆን ይችላሉ።

4- ለክርስቲያን ደሃ ሶደቃ መስጠት ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]

5- በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለክርስቲያን መልካም መዋል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [አልሙምተሒናህ፡ 8-9]

የእኛ እስልምና ይህ ነው።

2ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
¹⁰ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤
¹¹ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።

07/11/2022

እንግሊዛዊቷ አምበር ራሺድ እስልምናን ከተቀበለች በኃላ ለወላጅ እናት ቪኪ ኩክ ጥያቄ ቀረበላት

ልጅሽ እስልምናን መቀበሏ ስትሰሚ ምንድን ነበር የተሰማሽ?

" ስለ እስልምና ከሚዲያ ከምሰማው በቀር እውቀቱ የለኝም ፣
አምበር እጅጉን አስቸጋሪ ለእኔ የእናትነት ክብር የማትሰጠኝ ቁጡ ልጅ ነበረች
ከተለያዩ ወንዶች ጋር ስትዘል ውላ ሲላትም የምታድር

ጭፈራ ቤት አምሽታ ስክራ ሲነጋ ቤት የምትመጣ ፣ አንዳንዴ እራሷን ስታ ጓደኞቿ በር ላይ አድርሰዋት እኔ ደግፌ ነበር የማስገባት ፣
መስታወት ስር ተጥዳ ለምሽት እብደቷ በሜካፕ እራሷን ስትጋጊጥ ሰአታት የምታሳልፍ እና እርቃን በሚባል ሁኔታ ከቤት የምትወጣ ልጅ ነበረች
ሳዝንባት እና ሳለቅስላት ነበር የኖርኩት

እስልምና ከተቀበለች በኃላ
ለእኔ ያላት ክብር ቃላት አይገልፀውም ድምጿን ከፍ አድርጋ እንኳ አታወራኝም ፣ እጅጉን የተረጋጋች እና የሰከነች ሆናለች ፣
አልባሌ ቦታ ከሚወስዷት ጓደኞቿ እርቃ ከስራ ውጪ አብዛኛውን ጊዜዋን በፀሎት ፣ ቁርአን በማንበብ ከእኔ ጋር በመጫወት ነው የምታሳልፈው

እስልምና ልጄን መልሶልኛል ፣ ምኞቴን ሞልቶልኛል
በያዘችው እምነት እስከ መጨረሻ ትዘልቅልኝ ዘንድ ነው የምመኘው
እንዳልኩህ ስለ እስልምና አላውቅም ነገርግን ልጄን በባህሪ እንዲህ ያረቀልኝን እምነት ግን አከብራለሁ
Zeyd

06/11/2022

ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን

ወንድማችን አሊ መሐመድ (ቢራ) ወደ አኼራ ሄዷል

ከነበረበት ህይወት ወደ አላህ ተመልሶ መስጂዶችን በማስገንባት ላይ የነበረው ወንድማችን አሊ መሐመድ ባጋጠመው ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ወደ አኼራ አልፏል::

አላህ ምህረቱን ይለግሰው፣ ተውበቱን ይቀበለው፣ ማረፊያውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግለት

ለቤተሰቦቹም አላህ መፅናናቱን ይወፍቃቸው

بئر غرسThe Prophet ﷺ requested that the water in the well to be used to wash his body when he passes away. The Prophet ﷺ...
29/10/2022

بئر غرس

The Prophet ﷺ requested that the water in the well to be used to wash his body when he passes away. The Prophet ﷺ also drank from this well.

‎Credit:madeenahalmunawwara

ሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላን ማን ይተካቸው ይሆን???ሀገራችን በሞት ያጣቻቸው ሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላ የሀገራችን ትልቅ የኢልም ዋርካ ነበሩ:: ብቻቸውን ትልቅ የኢልም ተቋም ነበሩ:: የምድር ኮከ...
19/10/2022

ሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላን ማን ይተካቸው ይሆን???

ሀገራችን በሞት ያጣቻቸው ሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላ የሀገራችን ትልቅ የኢልም ዋርካ ነበሩ:: ብቻቸውን ትልቅ የኢልም ተቋም ነበሩ::

የምድር ኮከብ የሆኑት ኡለሞች በሞት እየረገፉ መሄዳቸው ቀጣዩ ትውልድ ላይ ትልቅ አደጋ መደቀኑን የሚያመላክት ነው::

እድሜያቸውን ሁሉ ለኢስላም የሰጡ፣ ጭንቀታቸው እና ልፋታቸው ሁሉ ለአኼራቸው የሆኑ አሊሞቻች ሲያልፉ አሻራቸው በትውልዱ ላይ የሚታይ ነው የሚሆነው::

የዛሬው የሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላ ስርዓተ ቀብር ላይ የተገኘው ህዝብ እሳቸው ምን ያህል ህዝቡ ልብ ውስጥ የነበሩ ፣ትልቅ አሻራ በህዝቡ ላይ አሳርፈው ያለፉ መሆናቸውን የሚያመላክት ነው::

ኡለሞች ሲያልፉ ብቻ ሳይሆን በህይወት እያሉም ማክበር የኡማው ባህሪ ሊሆን ይገባል::

እንቁ የሆኑ ኡለሞቻችንን በሞት እያጣን መገኘታችን እና እነዚህን ታላላቅ መሻይሆች ለመተካት ቀጣዩ ትውልድ ቆም ብሎ ካላሰበ ቀጣዩ ጊዜ አሳሳቢ ይሆናል::

ትውልዱ ከእውቀት እየራቀ በአለማዊ ህይወት እየተጠመደ ባለበት ወቅት የነብያት ወራሽ የሆኑት አሊሞችን በሞት ማጣት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እየሆነብን ነው::
ህይወታቸውን ለኡማው የሰጡ ኡለሞች ሲያልፉ እነሱን የሚተኩ ኡለሞች እየተመናመኑ መሄዳቸው እና ተተኪዎችን ለማፍራት የሚሰራ ጠንካራ አካል አለመኖሩ ትልቅ ፈተና ውስጥ መኖራችንን ያሳያል::

በተለይ ባለሃብቱ እና የንግዱ ማህበረሰብ እጅግ የተረሱትን የሀገራችን ኡለሞችን በህይወት እያሉ ማክበር እና መንከባከብ ተተኪ እንዲያፈሩም በደንብ ሊረዷቸው እና ሊያግዙ ይገባል:
የዱንያ ቆይታቸውን ሙሉ ኡማውን በመጥቀም፣ በማስተማር እና በማገልገል ያለፉ አሊሞች ምንኛ ታደሉ?? እነዚህንስ ማን ይሆን የሚተካቸው??

ሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላን አላህ በፊርዶስ ያሳርፋቸው

ጊዜ እንዲህ ነው!አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የሙስሊሙ ተቋም ይስተካከልልን የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም  ቱፋ በኡስታዝ አቡበክር አህመድ የክስ ...
16/10/2022

ጊዜ እንዲህ ነው!

አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የሙስሊሙ ተቋም ይስተካከልልን የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በኡስታዝ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ላይ ይሰቃዩ ነበሩ::

ዛሬ ቀኑ ተቀይሮ እሳቸው የታሰሩበት ተቋም መሪ ሆነው ከቀድሞ የአሳሪዎቻቸው ተምሳሌታዊ መሪ ጋር ተገናኝተው እንዲህ በክብር አናግሯቸዋል !

04/10/2022
Yesterday, October 2nd, Al-Quds (Jerusalem) was liberated from the Crusaders by Sultān Salaḥuddīn al-Ayyuūbi in the year...
03/10/2022

Yesterday, October 2nd, Al-Quds (Jerusalem) was liberated from the Crusaders by Sultān Salaḥuddīn al-Ayyuūbi in the year 1187.

After 88 years in which no Muslim was allowed to pray in al-Aqsa, the cries of 'Allāhu Akbar' rang through the city of Jerusalem.

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Islamic History posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Islamic History:

Share